የምንደሰትበት ብዙ ምክንያቶች አሉን
ሌሎችን በትንሽ እና በቀላል መንገድ ስታፈቅሩ፣ ስትጠብቁ፣ እና ስታገለግሉ፣ በደህንነት ስራ ላይ እየተሳተፋችሁ ናችሁ።”
የባለቤቴ አባት በሞቱበት ጊዜ፣ ቤተሰቦቻችን ተሰበሰቡ እና ለለቅሶ የመጡትን ሰላም አሉ። በምሽቱ በሙሉ ቤተሰብን እና ጓደኞችን ስጎበኝ፣ የአስር አምት እድሜ ያለው የልጅ ልጃችን ፖርተር ከአያቱ አጠገብ እንደሚገኝ ተመለከትኩኝ። አንዳንዴ በአጠገቧ በመቆም ይጠብቃታል። አንድ ጊዜም እጇን ይዞ እየነካካት፣ እያቀፋት፣ እናበአጠገቧ ሲገኝም ተመለከትኩኝ።
ከዚያ አጋጣሚ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ያየሁትን ከአዕምሮዬ ላወጣው አልቻልኩም። ለፖርተር ደብዳቤ ጽፌ ምን እንዳየሁ እንድነግረው ተገፋፋሁ። ያየሁትን እና የተሰማኝን ለመግለጽ ኢሜል ጻፍኩለት። ፖርተር በጥምቀት የገባውን ቃል ኪዳን እንዲያስታውስ በሞዛያ 18 ውስጥ ያሉትን የአልማን ቃላት ጠቀስኩኝ፥
“እናም አሁን፣ እናንተ ወደ እግዚአብሔር በረት ለመምጣትና፣ ህዝቡ ትባሉ ዘንድ፣ እንዲሁም አንዳችሁ የአንዳችሁን ሸክም ቀላል እንዲሆኑ ዘንድ ለመሸከም ፈቃደኞች በመሆን እንደፈለጋችሁ፤
“አዎን፣ እናም ከሚያዝኑት ጋር ለማዘን፤ መፅናናትን ለሚፈልጉም ካፅናናችኋቸው፤ እናም በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገርና፣ በምትኖሩበት ቦታዎች ሁሉ፣ እስከሞት ድረስ፣ የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን ትቆሙ ዘንድና፣ በጌታ ትድኑ ዘንድ፣ እናም ዘለዓለማዊ ህይወትም ይኖራችሁ ዘንድና የፊተኛውን ትንሳኤ ከሚያገኙት ጋርም ለመቆጠር ፈቃደኞች ከሆናችሁ ---
“ይህ የልባችሁ ፍላጎት ከሆነ፣ እርሱን እንደምታገለግሉ እናም ትዕዛዛቱን እንደምትጠብቁ፣ እርሱም በእናንተ ላይ መንፈሱን በብዛት ያፈስባችሁ ዘንድ በፊቱ እንደምስክርነት ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት በጌታ ስም ለመጠመቅ የሚያስቸግራችሁ ምንድን ነው?”1
አልማ እንዳስተማረው ለመጠመቅ የሚፈልጉ በህይወታቸው በሙሉ ሌሎችን በማገልገል ጌታን ለማገልገል ፈቃደኛ መሆን እንዳለባቸው ለፖርተርም ገለጽኩለት። እንዲህ አልኩኝ፥ “እንደገባህ አላውቅም፣ ግን ለአያትህ ያደረግከው፣ ለእርሷ ፍቅርህንና ሀሳብህን ያሳየህበት፣ ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅበት ነው። በየቀኑ ቃል ኪዳናችንን የምንጠብቀው ደግ በመሆን፣ ፍቅርን በማሳየት፣ እርስ በራስ በመንከባከብ ነው። የቃል ኪዳን ጠባቂ በመሆንህ በአንተ ኩራት ይሰማኛል! በጥምቀትህ የገባኸውን ቃል ኪዳን ስታከብር፣ በክህነት ለመሾም የተዘጋጀህ ትሆናለህ። ይህ ተጨማሪ ቃል ኪዳን ሌሎችን ለመባረክና ለማገልገል ተጨማሪ እድል ይሰጥሀል እናም በቤተመቅደስ ለምትገባው ቃል ኪዳኖችን ያዘጋጅሀል። ለእኔ መልካም ምሳሌ በመሆንህ አምሰግንሀለሁ። ቃል ኪዳን ጠባቂ መሆን ምን አይነት እንደሆነ ስላሳየኸኝ አመሰግንሀለሁ!”
ፖርተርም እንዲህ መለሰ፥ “አያቴ ሆይ፣ ለመለክትሆ አመሰግናለሁ። አያቴን ሳቅፋቸው፣ ቃል ኪዳኖችን እያከበርኩኝ እንዳለሁ አላወቅኩም ነበር፣ ነገር ግን በልቤ ሙቀት ተሰማኝ እናም መልካም ስሜትም ሰጠኝ። በልቤ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ እንደነበርም አውቃለሁ።”
ቃል ኪዳን ማክበርን “መንፈሱ ሁልጊዜም ከእኛ ጋር እንዲገኝ”2 ከሚለው ጋር እንዳስተያያዘ ሳውቅ እኔም በልቤ ሙቀት ተሰማኝ። ይህም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን በመቀበል የሚገኝ የተስፋ ቃል ነው።
እህቶች፣ በአለም አቀፍ ስጎበኛችሁ፣ ብዙዎቻችን እንደ ፖርተር እንደሆናችሁ ተመልክቻለሁ። በጸጥታ በጥምቀት ውሀውስጥ እና በቤተመቅደስ ውስጥ የገባችሁንት ቃል ኪዳን እያከበራችሁ እንደሆናችሁ ሳታውቁ፣ እንደ እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፣ ከሚያዝኑ ጋር ታዝናላችሁ፣ መፅናናት የሚያስፈልጋቸውን ታፅናናላችሁ። ሌሎችን በትንሽ እና በቀላል መንገድ ስታፈቅሩ፣ ስትጠብቁ፣ እና ስታገለግሉ፣ “የሰውን ህያውነትና ዘለአለማዊ ህይወትን ማምጣት”3 በሆነው በእግዚአብሔር ስራ፣ በደህንነት ስራ ላይ እየተሳተፋችሁ ናችሁ።”3
እንደ “ጌታ መንግስት ሴት ልጆች፣”4 ቃል ኪዳኖች ገብተናል። ኔፊ “ወደ ዘለዓለማዊው ህይወት በሚመራው በዚህ በቀጭኑና ጠባቡ ጎዳና”5 በሚለው እየተጓዝን ነን። ሁላችንም በጎዳናው ላይ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ነን ያለነው። ነገር ግን እርስ በራስ “ፍጹም የሆነ የተስፋ ብርሃን፣ እናም የእግዚአብሔርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር እየኖራችሁ በክርስቶስ ባላችሁ ፅኑነት”6 ለመቀጠል ለመርዳት አብረን መስራት እንችላለን።
ጂን እንደ ወጣት ሴቶች አማካሪ ታገለግል ነበር። ከጥቂት ወራት በፊት ወደ ማላን ተራራ ጫፍ ስለሚኼድበት በዎርዱ ስለሚደረገው የወጣቶች መሳተፊያ አወቀች።በቅርብ ወደዚያ ጫፍ ለመድረስ አላማ ስለነበራት በጣም ተደስታ ነበር።
ወደ ጉዞም መጀመሪያ ላይ ስትደርስ ጓደኛዋ አሽሊ ወደ እርሷ መጣች። የጄኒን እጅ ይዛ “ከአንቺ ጋር እሄዳለሁ” አለቻት።፡አሽሊ በዚያ ጊዜ 16 አመቷ ነበር እናም በፍጥነት ወደ ተራራው ላይ ለመውጣት የሚያስቸግራት የሰውነት ችግር ነበራት። ስለዚህ እርሷ እና ጄኒ የእግዚአብሔር ፍጥረቶች የሆኑትን የተራራ ጫፍ ድንጋዮችን፣ በአካባቢያቸው ያሉትን አበባዎች፣ ከአንድ አበባ ወደሌላ አበባ የሚበሩትም ንቦችን በማየት በቀስታ ሄዱ። ጄኒም በኋላ እንዲህ አለች፣ “ወደ ተራራው ጫፍ ለመድረስ የነበርኝን አላማ ለመርሳት ብዙ ጊዜም አልፈጀብኝም፣ ምክንያቱም ሌላ አይነት ጀብዱ፣ በመንገድ ላይ የሚገኙ ወብቶችንየማጠቆም ጀብዱ ሆነ። ብዙዎቹንም ወደ ማላን ተራራ ጫፍ ለመድረስ ባለኝ አላማ የምሄድበት ቢሆን ኖሮ አላያቸውም ነበር።”
ጄኒ እና አሽሊ ከቡድናቸው በጣም ኋለኛ ሆነው ጉዞአቸውን ሲቀጥሉ፣ ከእነርሱ ጋር አብራ ለመሄድ የወሰነች ለኢአል የዎርዱ ወጣት ሴት ኤማ መጣች። ዝዘፈኖችን አስተማረቻቸው እናም ተጨማሪ ድጋፍ እና መበረታቻ ሰጠች። ጄኒም እንዲህ አስታወሰች፣ “ለማረፍ ተቀመጥን፣ ዘፈንን፣ ተነጋገርን፣ እናም ሳቅን። አሽሊንና ኤማን ይህን አብረን ካላደረግን ለማወቅ እችል ከነበረው በላይ ለዋወቅ ቻልኩኝ። ይህ ምሽት ስለተራራው አልነበረው፣ ይህም ከዚህ እላይ ስለሆነ ነገር ነበር። ይህም እርምጃ በእርምጃ እርስ በራስ በጎዳናው ስለመረዳዳት ነበር።”
ጄኒ፣ አሽሊ፣ እና ኤማ አብረው ሲጓዙና ሲዘምሩ እናም ሲስቁ፣ “ቃል ኪዳናችንነሁን እየጠበቅን ነን” ብለው አያስቡም ነበር። ነገር ግን ቃል ኪዳናቸውን እየጠበቁ ነበሩ። በፍቅር፣ በርህራሄ፣ በአሳቢነት። ለእርስ በራስ አገልግሎት ሰጡ፣ እናም እርስ በራስ ሲበረታቱ፣ ሲደጋገፉ፣ እና ሲያገለግሉ እምነታቸውን አጠነካከሩ።
ሽማግሌ ራስል ኤም ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “የቃል ኪዳን ልጆች እንደሆንን ስናውቅ፣ ማን እንደሆንን እና እግዚአብሔር ምን እንደሚጠብቅብን እናውቃለን። ህጉ በልባችን የተጻፈ ነው።”7
ማሪና ኪዩዜና ማን እንደሆነች እና እግዚአብሔር ምን እንደሚጠብቅባት የምታውቅ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሴት ልጅ ነች። በኦምስክ፣ ራሽያ ውስጥ ወደ ቤቷ ስትጋብዘኝ፣ እርሷን ለማገልገል በእዚያ እገን እንደነበር አስብ ነበር፣ ነገር ግን ከእርሷ ለመማር እዚያ እንደነበርኩኝ ወዲያው አወቅኩን። ወደ ቤተርክርስቲያኗ የተቀየረችው ማሪና በሉቃስ 22 ውስጥ ባለው መመሪያ ትኖር ነበር፥ “አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና።”8እንዲህ ባሉት በህያው ነቢያችን ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰንም እምነት ነበራት፥
“አባላትና ሚስዮኖች አብረው የሚሰሩበት፣ ነጌታ የወይን አትክልት ውስጥ ነፍሳትን ወደ እርሱ ለማምጣት የሚያገለግሉበት ጊዜ አሁን ነው።...
“በእምነት ስንሰራ ጌታ ቤተክርስቲያኑን በምንኖርበት ዎርዶችና ቅርንጫፎች እንዴት ለማጠናከር ያሳየናል። እርሱም ከእኛ ጋር ይሆናል እናም በሚስዮን አገልግሎታችንም ይሳተፋል።
“ከቤተሰቦቻችሁ፣ ከጓደኞቻችሁም ከጎረቤቶቻችሁ፣ እና ከምታውቋቸው መካከል የትኞቹን ወደ ቤታችሁ ከሚስዮኖች ጋር እንዲገናኙና በዳግም የተመለሰውን መልእክት እንዲሰሙ በጸሎት ስታስቡበት እምነታችሁን እንድትጠቀሙበት እለምናችኋለሁ።”9
ማሪና እንድትጎበኝ የተጠየቀችውን እህቶች በመጠበቅና በማገልገል እናም ደግሞ ከዚህ ጥሪ በላይ በማድረግ ይህን ምክር ተከትላለች። በብዛት የማይሳተፉ እና በዳግም የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን ያልሰሙ ብዙ ጓደኞች አሏት። በየቀኑ እምነቷን በመጠቀም እና እርዳታዋን ማን እንደሚፈልግ ለማወቅ ትጸልያለች፣ ከዚያም በተሰጣት መነሳሻም ላይ ትሰራለች። ስልክ ትደውላለች፣ ፍቅሯን ትገልጻለች፣ እናም ጓደኞቿን “እንፈልጋችኋለን” ትላቸዋለች። በየሳምንቱ የቤተሰብ የቤት ለቤት ምሽት ታደርጋለች እናም ጎረቤቶችን፣ አባላትን፣ እና ሚስዮኖችን እንዲመጡ ትጋብዛለች---እናም ትመግባቸዋለች። ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመጡ ትጋብዛቸዋለች፣ ትጠብቃቸዋለች፣ እና ሲመጡም አብራቸው ትቀመጣለች።
ማሪና ሽማግሌ ጀፍሪ አር ሆላንድ እንድናስታውስ ያደረጉትን ተረድታለች፥ “ለሌሎች እና ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባለን ፍቅር … የሚያስከፋ አይደለም።”10 ስሜታችን ተጎድቷል የሚሉትን ሰዎች ስም በዝርዝር ትጠብቃለች፣ እናም እነርሱንም ማገልገል ትቀጥላለች።፡እንደምትወዳቸው ስለሚያውቁ፣ “ስሜታችሁ አይጎዳ፣ ይህ የሚያስቅ ነ!” ስትላቸውም ትችላለች።
ማሪያ ቃል ኪዳን የምትጠብቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙር ናት። በቤቷ ክህነት ያለው ባይኖርም፣ በጉዳናው ወደፊት በምትገፋበት፣ እስከመጨረሻ በምትጸናበት እና በጉዞዋም ሌሎች በደህንነት ስራ እንዲሳተፉ በምትረዳበት ሁኔታ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኗን ስታሟላ የእግዚአብሔር ሀይል በየቀኑ ይሰማታል።
እነዚህን አጋጣሚዎች ሳገርባቸው፣ በደህንነት ስራ እራሳችሁን ተመለከታችሁን? በመንገድ ለመመለስ ማበረታቻ ስለሚያስፈልጋት ወይም በጎዳናው ለመቆየት ትንሽ እርዳታ ስለሚያስፈልጋት ሌላ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ ለማስብ ጊዜ ውሰዱ። የሰማይ አባታችሁን ስለእርሷ ጠይቁ። እርሷ የእርሱ ሴት ልጅ ነች። በስም ያውቃታል። እናንተንም ያውቃል፣ እናም ምን እንደሚያስፈልጋት ይነግራችኋል። ትዕግስተኛ ሁኑ፣ ለእርሷም ለመጸለይ ቀጥሉ፣ እናም በምትቀበሉትም መነሳሻ ስሩ። በእነዚህ መነሳሻዎች ስትሰሩ፣ በመንፈስ የምታቀርቡት በጌታ ተቀባይ እንደሆነ ያረጋግጥላችኋል።
እህት እላይዛ አር. ስኖው እህቶች እርስ በራስ ለማጠነካከር የሚያደርጉትን ጥረት በምስጋና አሳውቀዋል። ምንም እንኳን ቤተክርስቲያኗ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለመርዳት በበጎ ድርገት የሰጡትን ሁሉ በመዝገብ የማትጠብቀው ቢሆንም፣ ጌታ የማዳን ስራዎቻቸውን ፍጹም የሆነ መዝገብ ይጠብቃል።
ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ ይህ ማህበር የተደራጀው ነፍሳትን ለማዳን ነው ብለዋል። “የጠፉትን መልሰን ለማምጣን፣ በወንጌል ላይ ልባቸው ቀዝቃዛ የሆኑትን ለማሞቅ ምን እያደረግን ነን? ስለእምነታችሁ፣ ስለደግነታችሁ. ስለመልካም ስራችሁ፣ እና ስለቃላቶቻችሁ የሚጠበቅ ሌላ መፅሐፍ አለ። ሌላ መዝገብም አለ። ምንም የጠፋ የለም።”11
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ስለምንደሰትበት ታላቅ ምክንያት አሞን ተናግሮ ነበር። እንዲህም አለ፥ “እናም አሁን፣ [እግዚአብሔር] ምን ዓይነት ታላቅ በረከት በእኛ ላይ አድርጓል? ብዬ እጠይቃችኋለሁ፣ ይህንን ለመናገርስ ትችላላችሁን?”
በደስታውም፣ አሞን ለመልስ አልጠበቀም። እንዲህም አለ፥ “እነሆ፣ እኔ እመልስላችኋለሁ፤... ይህንን ታላቅ ስራም ለመፈፀም በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ መሆናችን፣ ይህ በእኛ ላይ የወረደው በረከት ነው።” 12
እኛ በእግዚአብሔር መንግስት የምንገኝ የቃል ኪዳን ሴት ልጆች ነን፣ እናም በእጁ መሳሪያዎች የመሆን እድል አለን። በትንሽ እና ቀላል መንገዶች፣ በመጠበቅ፣ በማጠናከር፣ እና እርስ በራስ በማስተማር በደህንነት ስራ በየቀኑ ስንሳተፍ፣ ከአሞን ጋር እንዲህ ለማወጀ እንችላለን፥
“እነሆ፣ ደስታዬ ሙሉ ነው፣ አዎን፣ ልቤ በደስታ ይሞላል፣ እናም በአምላኬ ሐሴት አደርጋለሁ።
አዎን፣ እኔ ምንም እንዳልሆንኩ አውቃለሁ፤ ጉልበቴን በተመለከተ ደካማ ነኝ፤ ስለዚህ በራሴ አልኮራም፣ ነገር ግን በአምላኬ እኮራለሁ፣ ምክንያቱም በእርሱ ኃይል ሁሉንም ነገር ማድረግ እችላለሁና”13
ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።