እንደገና እስከምንገናኝ
ወደ እርስ በራስ ተጨማሪ ደግነት እናሳይ፣ እናም ሁልጊዜም የጌታን ስራ በማከናወን እንገኝ።
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ይህን አስደናቂውን የቤተክርስቲያኗን አጠቃላይ ጉባኤ ስንፈጽም ልቤ ሙሉ ነው። በዚህ ስብሰባ በተካፈሉት ንግግሮችና ምስክሮች በኩል በመንፈስ ተመግበናል።
በዚህ በጉባኤ አዳራሽ በሰላም እና በደህንነት በመገናኘታችን ተባርከናል። በክፍለ አህጎሮች እና በባህር ተሻግሮ የሚተላለፍ አስደናቂ ግንኙነት ነበረን። ከብዙዎቻችሁ በአካል የተለየን ብንሆንም፣ መንፈሳችሁ ይሰማናል።
በዚህ ጉባኤ ከሀላፊነት ለተለቀቁት ወንድሞች፣ ለብዙ አመት የልብ አገልግሎታችሁ ከፍተኛ ምስጋኔዬን በቤተክርስቲያኗ በሙሉ ወኪል ላቅርብላችሁ። በጌታ ስራ በድርሻችሁ ባደረጋችሁት የተባረኩት በቁጥር ለመቆጠር የማይችሉ ናቸው።
ለታበርናክል ዘማሪዎች እና በዚህ ጉባኤ ለተሳተፉት ዘማሪዎች ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ሙዚቃዎቹ አስደናቂ ነበሩ እማ፣ በእያንዳንዱ ስብሰባ ለተሰምሙን መንፈስ ምክንያትም ነበሩ።
ለእኔ እና ለቤተክርስቲያኗ ለአጠቃላይ ባለስልጣኖች እና ሀላፊዎች ላቀረባችሁት ጸሎትም አመሰግናችኋለሁ። በእናንተም እንጠናከራለን።
የሰማይ በረከቶች ከእናንተ ጋር ይሁኑ። ቤታችሁ በፍቅርና በትህትና እናም በጌታ መንፈስ ይሞላ። የወንጌል ምስክራችሁን ሁልጊዜም መግቡ፣ እነዚህ አጥፊው ሲያጠቃችሁ መከላከያ ይሆንላችኋልና።
ጉባኤው አሁን ተፈጽሟል። ወደ ቤቶቻችን ስንመለስ፣ በደህና እንመለስ። በዚህ የተሰማን መንፈስ፣ በየቀኑ የምናደርጋቸውን ስናከናውን ከእኛ ጋር ይቆይ። ወደ እርስ በራስ ተጨማሪ ደግነት እናሳይ፣ እናም ሁልጊዜም የጌታን ስራ በማከናወን እንገኝ።
ወንድሞቼና እህቶቼ፣ እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ቃል የገባላችሁ ሰላም አሁንም ይሁን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይሁን። እንደገና በስድስት ወር ጊዜ እስከምንገናኝ ድረስ ደህና ሁኑልኝ። በአዳኛችን፣ እንዲሁም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።