2010–2019 (እ.አ.አ)
በእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን ማስተማር
ኦክተውበር 2013


10:44

በእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን ማስተማር

መንገዱ ከባት አይደለም። እያንዳንዱ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በጌታ መንገድ እንዲያስተምሩ መንገድ አዘጋጅቷል።

በቤተክርስቲያኗ በሙሉ ለሚያስተምሯት ለመመዘን ከማይቻል በላይ ምስጋና አለን። እናፈቅራችኋለን እናም በእናንተ እንመካለን። ከዚህም አስፈላጊ በሆነ ሁኔታ፣ ጌታ እንደሚያፈቅራችሁ እናውቃለን።

ስኬታማ የወንጌል አስተማሪ ለመሆን፣ በእግዚአብሔር ሀይልና ስልጣን ለማስተማር ልዩ ሚስጥር አለ። ሚስጥር የምልበት ምክንያት የአስተማሪ ስኬታማነት የሚመካበት መሰረታዊ መርሆ የሚረዱት በ1820 ዓ/ም በ ጸደይ ቀኗ ጠዋት ላይ ምን እንደደረሰ ምስክርነት ያላቸው ሰዎች ስለሆነ ነው።

ለ14 አመት ትሁት ልጅ ጸሎት መልስ ለመስጠት ሰማያት ተከፈቱ። ዘለአለማዊው አብ እግዚአብሔር እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በነቢዩጆሴፍ ስሚዝ ታዩ እናም አነጋገሩት።ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የሁሉም ነገሮች በዳግም መመለስ ተጀመረ፣ እናም የራዕይ መሰረታዊ መርሆችም ለዘላለም በዘመናችን ተመሰረቱ። ለአለም ጆሴፍ የሰጠ መልእክት በሁለት ቃላት በአጭር ሊጠቃለል ይችላል፥ “እግዚአብሔር ይናገራል።” በጥንት ተናግሯል፣ ለጆሴፍ ተናግሯል፣ እናም ለእናንተም ይናገራል እናም ስታስተምሩ መመሪያ ይሰጣችኋል።ይህም በአለም ከሚገኙ ከሌሎች አስተማሪዎች የሚለያችሁ ነው። ይህም የማትወድቁበት ምክንያት ነው።

በትንቢት መንፈስ እና በራዕይ ተጠርታችኋል እናም በክህነት ስልጣን ተለይታችኋል። ይም ምን ማለት ነው?

መጀምሪያ፣ ይህም እናንተ በጌታ ለመልእክት የተላካችሁ ናችሁ ማለት ነው። እናንተ የእርሱ ወኪል ናችሁ፣ እናም እርሱን ለመወከል እናም በእርሱ ምትክ ለመስራት ስልጣን የተሰጣችሁ ናችሁ። እንደ እርሱ ወኪል፣ ለእርሱ እርዳታ መብት አላችሁ። እራሳችሁንም፣ “ዛሬ ክፍሌን የሚያስተምር ቢሆን፣ ጌታ ምን ይላል፣ እናም እንዴትስ ይለዋል?” ብላችሁ ጠይቁ።

ይህም ሀላፊነት አንዳንዶች ብቁነት እንዳይሰማቸው እና እንዲፈሩም ያደርጋቸዋል። መንገዱ ከባት አይደለም። እያንዳንዱ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በጌታ መንገድ እንዲያስተምሩ መንገድ አዘጋጅቷል።

ሁለተኛ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንድትሰብኩ ተጠርታችኋል። የራሳችንን ሀሳቦች ወይም ፍልስፍናን አናስተምርም። ወንጌል “የሚያድን የእግዚአብሔር ሀይል ነው፣”1 እናም ለመዳን የምንችለው በወንጌል በኩል ብቻ ነው።

ስታስተምሩ መንፈስ ከእናንተ ጋር እንዲሆን የሚደረግበት ዋና መንገድ ቢኖር፣ ከቅዱስ መጻህፍት፣ ከአሁን ዘመን ሐዋሪያትና ነቢያት፣ እና መንፈስ ቅዱስ ያስተማራችሁን በማስተማር ነው።

ስለዚህ የት ለመጀመር እንችላለን?

የመጀመሪያው ሀላፊነታን መንፈስ ቅዱስ የእኛ መሪና ጓደኛ እንዲሆን መኖር ነው። ሀይረ ስሚዝ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሥራ ለመሳተፍ ሲፈልግ፣ ጌታ እንዲህ አለ፣ “እነሆ፣ አዎን፣ ሁሉ ሀይልህ፣ አዕምሮህ እናም ብርታትህ፣ ትእዛዛቴን መጠበቅ ይህ የአንተ ስራ ነው።”2 ይህም የመጀመሪያ ቦታ ነው። ለሀይረም ጌታ የሰጠው ምክር ጌታ በየዘመኑ የሰጠው አንድ አይነት ምክር ነው።

ዛሬ ለአስተማሪዎች በመናገር፣ የቀዳሚ አመራር እንዳሉት፣ “ከአገልግሎታችሁ በጣም አስፈላጊ የሆነው በየቀኑ በመንፈስ፣ እንዲሁም በጸሎት፣ ቅዱሳት መጻህፍትን በማንበብ፣ እና ትእዛዛትን በማክበር መዘጋጀታችሁ ነው። ከዚህ እብፊት ከምታደርጉት በላይ በታላቅ አላማ በወንጌል እንድትኖሩም እናበራታታችኋለን።”3

የአስተማሪ አገልግሎት አስፈላጊ ሀላፊነት ትምህርትን በደንብ ማዘጋጀት ወይም የተለያዩ የማስተማር ዘዴዎችን መወቅ ነው እንዳላሉ ተመልከቱ። ለእያንዳንዱ ትምህርቶች በትጋት መዘጋጀት እና ተማሪዎቻችሁ የነጻ ምርጫቸውን እንዲጠቀሙበትና ወንጌል በልባቸው እንዲገባ ለመፍቀድ መጣር አለባችሁ፣ ነገር ግን የአገልግሎታቹ የመጀመሪያና አስፈላጊ ክፍል ቢኖር የግል፣ የመንፈስ ዝግጅታችሁ ነው። ይህም ምክር ስትከተሉ ቀዳሚ አመራርም “መንፈስ ቅዱስ ምን እንደምታደርጉ ይረዳችኋል። ምስክራችሁ ያድጋል፣ የተቀየራችሁበትም ዝልቅ ይሆናል፣ እናም የህይወት ፈተናዎችን ለመቋቋምም ትጠናከራላችሁ”4 ብለው ቃል ገብተዋል።

ምን ታላቅ በረከቶች አስተማሪ ለመፈለግ ይችላል?

በመቀጥልም፣ ጌታ ቃሉን ለማወጅ ከመፈለጋችን በፊት ይህን ለማግኘት መፈለግ አለብን ብሎ አዝዟል።5 ቅዱሳት መጻህፍትን በትጋት በመፈተሽ፣ የክርስቶስን ቃላት በመመገብ፣ እና እነዚህን ቃላት በልባችሁ እንደ ሀብት በመያዝ ጥንካራ እውቀት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች መሆን አለባችሁ። ከዚያም የጌታን እርዳታ ስትጠይቁ፣ በመንፈሱና በቃሉ ይባርካችኋል። ሰዎችን ለማሳመን የእግዚአብሔር ሀይል ይኖራችኋል።

ጳውሎስ ወንጌል በሁለት መንገዶች እንደሚመጡ ነግሮናል፣ በቃል እና በሀይል።6 የወንጌል ቃላት የተጻፉት በቅዱሳት መጻህፍት ነው፣ እናም ቃልን ለማግኘት የምንችለው በትጋት በመፈተሽ ነው። ህይወታቸው መልካም ሆኖ መንፈስ ቅዱስ ጓደኛቸው ወደሆነላቸው እና የሚቀበሉትን መነሳሻዎች ወደሚከተሉትን ህይወት ነው የወንጌል ሀይል የሚመጣው። አንዳንዶች ትኩረታቸውን ቃላትን በማግኘት ላይ ብቻ ይጥላሉ እናም መረጃዎችን በመስጠት ባለሙያ ይሆናሉ። ሌሎች መዘጋጃቸውን ችላ ይላሉ እናም በክፍል ጊዜ እንደምንም ብለው እንዲጨርሱ እንዲረዳቸው ተስፋ በጌታ ላይ ይጥላሉ። መንፈስ ቅዱሳት ያላጠኑትን መጻህፍትን እና መሰረታዊ መርሆችን እንዲያስታውሱ እንዲረዳቸው ይጠብቃሉ። ወንጌልም በውጠኢታማነት ለማስተማር፣ የወንጌል ቃል እና ሀይል በህይወታችሁ ሊኖራችሁ ያስፈልጋችኋል።

ስለሞዛያ ልጆችን እና በእግዚአብሄር ሀይል እና ስልጣን እንዴት እንዳስተማሩ ሲገልጽ አልማ እነዚህን መሰረታዊ መርሆች ተደርቶ ነበር።

“ትክክለኛ ማስተዋል የነበራቸው፣ የእግዚአብሔርን ቃል ያውቁ ዘንድ ቅዱሳን መጻሕፍትን በትጋት የሚያጠኑ ሰዎች ነበሩ።

“ነገር ግን ይህ ብቻም አይደለም፤ እራሳቸውን በብዙ ጸሎትና ፆም አተጉ፤ ስለዚህ የትንቢት መንፈስ ነበራቸው።”7

ከጥቂት አመት በፊት፣ ሽማግሌ ሆላንድ አዲስ የሚስዮን ፕሬዘደንቶች እንዴት ሚስዮኦች የተሻሉ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ለመርዳት እንደሚችሉ አስተማሩ። ያሏቸው ለሁሉም አስተማሪዎች ይጠቅማሉ።፡ሽማግሌ ሆላድ ያሉትን እጠቅሳለሁ ግን ስለሚስዮኖችናፈታሾች የሚናገሩትን በአስተማሪዎችናበተማሪዎች ተክቻለሁ።፥ “አስተማሪዎች መንፈስን ለማድመጥ ካላቸው ተከታይ የሚሆነው ለተማሪዎቻቸው ያላቸው ሀላፊነት ነው።...በመንፈስ ጆሮዎች ከሰማን...፣ [ተማሪዎቻችን] ለመስማት የሚፈልጉት የትኛው ትምህርት እንደሆነ ይነግሩናል!”

ሽማግሌ ሆላንድም ቀጥለው፥ “አስተማሪዎች በተማሪዎቻቸው እንደ ግለሰብ ከማትኮር በላይ የተመቸ፣ የተደጋገመ ትምህርት ማስተማር ላት ትኩረት አላቸው፡”8

እራሳችንን እና የምናስተምረውን ከችሎታችን ያህል ካዘጋጀን በኋላ፣ ለመተው ፈቃደኞች መሆን አለብን። የምንችለውን ያህል አዘጋጅተናል እናም መንፈስ ቅዱስ እኛንና ክፍላችንን እንዲመራን ጸልየናል። ጸጥተኞቹ መነሳሻዎች ሲመጡ፣ የመደብናቸውን የትምህርት አላማዎች እና ማስታወሻዎች ትተን መንፈስ እንድንሆእድ በሚያደርገል ለመሄድ ብርቱነት ያስፈልገናል።፡ይህን ስናደርግ፣ የምናቀርበው ትምህርት የእኛ ትምህርት አይደለም፣ ነገር ግን ይህም የአዳኝ ትምህርት ይሆናል።

ከዚህ በፊት ከነበራችሁ በላይ በሆነ ታላቅ አላማ በወንጌሉ ለመኖር ስትወስኑ እና ቅዱሳን መጻህፍትን ስትፈትሹ፣ በልባችሁ እንደሀብት ስትይዙ፣ እነዚህን ቃላይ ለጥንት ነቢያትና ሐዋሪያት የገለጸው ያም መንፈስ ቅዱስ ስለእውነትነታቸው ይመሰክርላችኋል። በዚህም መሰረት፣ መንፈስ ቅዱስ እነዚህን እንደ አዲስ ይገልጽላችኋል።፡ይህም ሲሆን፣ የምታነቧቸው ቃላይ የኔፊ ወይም የጳውሎስ ወይም የአልማ ሳይሆን የእናተ ቃላት ይሆናል።፡ከዚያም ስታስተምሩ፣ መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ሊያስተምራችሁ እና ሁሉንም ነገሮች እንድታስታውሱ ያደርጋል። በእርግጥም፣ “የምትናገሩት በዚያች ሰዓት፣ አዎን፣ በዚያች ጊዜም፣ ምን እንደምትናገሩ ይሰጣችኋል።”9 ይህም ሲሆን፣ ለማለት ያላሰባችሁትን ስትሉ እራሳችሁን ትሰማላችሁ። ከዚያም፣ ስታስተምሩ የምትሉት ላይ ትኩረት ካደረጋችሁ፣ ከምትሉት አዲስ ነገር ትማራላችሁ። ፕሬዘደንት ማሪዮን ጂ. ሮምኒ እንዳሉት፣ “በመንፈስ ቅዱስ በመነሳሳት ስናገር አውቅበታለሁ ምክያቱም ከተናገርኩት አንድ አዲስ ነገር እማራለሁና።”10

በመጨረሻም፣ አስተማሪዎች፣ በመፅሐፍ ውስጥ ያለውን ወይም የሌሎችን ሀሳቦች በመድገም ሳይሆን ስለሚያስተምረው ወይም ስለምታስተምረው ነገሮች እንደ ምስክር መሆንም አለባቸው። ስለምታስተምሩት መሰረታዊ መርሆች እውነተኛነት ምስክርስችሁን መካፈል ያስፈልጋችኋል።፡ስትጸልዩ፣ ስትፈትሹ፣ እና ከዚህ በፊት ከነበረው ባላይ በወንጌል ለመኖር ስትወስኑ ምስክሮች ትሆናላችሁ።

ቅዱሳት መጻህፍትን ህይወታችንን እና የምናስተምረውን ስናዘጋጅ በጌታ መንፈስ እና በቃሉ፣ ሰዎችን ለማሳመን በእግዚአብሔር ሀይል እንደምትባረኩ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።