ወደ እግዚአብሄር መቅረብ
አዳኛችን ፍቃዳችንን ከርሱ ፍቃድ ጋር እስክናስካሄድ ድረስ በእውነቱ እንድናፈቅረው ይፈልጋል።
በፍቅር “ፓፒ“ ብሎ የሚጠራኝ የስድስት አመቱ የልጅ ልጃችን ኦላይ ፥ ከመኪና ውስጥ የሆነ ነገር ማግኘት ነበረበት። ወደ መኪናው ሲቀርብ አባትየው ከቤት ሆኖ ኦላይ ሳያውቅ የመኪናውን በር በሪሞት ከፈተለት፥ እናም ከጨረሰ በሁአላም ቆለፈው። ኦላይም በፈካ ፈገግታ እየሮጠ ወደቤት ገባ።
በተሰቡ በሙሉ “ እንዴት አድርገህ በሩን ከፍተህ ዘጋህ? “ ብለው ጠየቁት። እሱም ፈገግ ብቻ አለ።
ልጃችን የሆነችው እናቱ “ ምናልባት ፓፒ እንደሚያደርገው አንተም አስማታዊ ሃይል አለህ “ አለችው።
ለሁለተኛ ጊዜ እንዲሁ ከተከሰተ ከደቂቃዎች በሁአላ፥ ስላዲሱ ግኝታዊ ችሎታው ለሚቀጥሉት ጥያቄዎች መልሱ “ የሚደንቅ ነው! እንደሚመስለኝ ፓፒ ያፈቅረኛል፥ ጓደኛዬም ነው እናም ይንከባከበኛል“ የሚል ነበር።
በታማኝ አፍሪካውያን ፥ በፓፓ ኒው ጊኒ፥ በአውስትራሊያ፥ በኒው ዚላንድ፥በፓሲፊክ ደሴቶች ላይ የሚገኙ ቅዱሳን ህይወት ውስጥ የሚከሰቱትን ታምራዊ ነገሮች በማወቅ በእውነቱ ተባርኬያለሁ። ከኦላይ ጋር እስማማለሁ። እንደሚመስለኝ እነዚህ ታማኝ ህዝቦች ስለ ሰማያዊ አባታችንና ስለአዳኛችን የሚሰማቸው ስሜት ኦላይ ለኔ እንደሚሰማው ሁሉ ነው። እግዚአብሄርን እንደ ቅርብ ጓደኛ ይወዱታል፥ እርሱም ይንከባከባቸዋል።
የቤተ ክርስቲያን አባላት መንፈሳዊ ምስክርን የመቀበል እና ጌታን ለመከተል ቅዱስ ቃል ኪዳን የመግባት መብት አላቸው እንዲሁም ብዙዎች ይቀበላሉ። ይህም ሆኖ ጥቂት ወደ እርሱ ይቀርባሉ፥ ሌሎች ግን አይቀርቡም። ታዲያ እኛ ከየትኛው ወገን ነን?
እግዚአብሄር የአለማችን ሁሉ ማእከል እና በርግጥም የትኩረት ነጥብ መሆን አለበት። እሱ አንዳንድ ጊዜ ከልባችን አስተሳሰብና አላማ የራቀ ነውን? (ሞዛያ 5፥13 ተመልከቱ)። እዚጋ የልባችን መሻት ብቻ ሳይሆን አላማችን ጠቃሚ እንደሆነ አስተውሉ። እንዴት ነው ባህሪያችንና ተግባራችን የልባችንን ቀናነት የሚያንፀባርቁት?
ልጃችን ቤን፥ በአስራ ስድስት አመቱ በካስማ ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ሲያደርግ ይህንን ጥያቄ ጠየቀ፥ “ አንድ ሰው የሆነ ነገር በየሳምንቱ ቃል ገብቶላችሁ ነገር ግን በፍፁም የማይተገብረው ከሆነ ምን ይሰማችሗል? “ ብሎ ጠየቀ። ቀጥሎም ሲናገር “ በቅዱስ ቁርባን ጊዜ የምንገባውን ቃል ኪዳን በትኩረት እንወስዳለን? ትእዛዛቱን ለመጠበቅ እና ሁልጊዜ እሱን ለማስታወስ ቃል እንገባለን? ብሎ ጠየቀ።
ጌታ እሱን የምናስታውስበትን መንገድ እና የሚደግፈንን ሃይል ይሰጠናል። አንዱም መንገድ ደግሞ ሁላችንም በምንጋራው መከራ ውስጥ ነው። (አልማ 32፥6) የገጠሙኝን ችግሮች ወደሗላ ስመለከት፥ ሁሉም በእድገቴ፥ በመረዳቴ፥ እናም ችግሮቹን በራሴ ህይወት እንድመለከት አድርገዋል ። እነዚህም ተሞክሮዎች ልቤንም በማጥራት ወደ ሰማያዊ አባቴ እና ወደ ልጁ አቅርበውኛል።
የሱ ምሪትና ምክር አስፈላጊ ናቸው። ታማኙን የያሬድ ወንድም ከነበሩት ሁለት ችግሮች መካከል ንፁህ አየር እንዴት በእምነት ወደተገነባችው ጀልባዋ ማስገባት አንደሚቻል አሳየው። (ኢተር 2፡20) ነገር ግን፥ ጌታ መብራት በጀልባዋ ውስጥ ያለመኖሩን ችግር ለጊዜው የተወ ብቻ ሳይሆን፥ መፍትሄን እንድንፈልግ የሚያነሳሱንን እንግልቶችና መከራዎች እንደሚፈቅድ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጧል። እሱ ነው ንፋሱን፥ ዝናቡን እና ጎርፉን የሚያዘው። (ኢተር 2፡23፥24)
ለምንድነው እነዚህን የሚፈቅደው? የአደጋዎችን ምንጭ ማስወገድ ሲችል ለምንድን ነው ካደጋዎች ተጠበቁ ብሎ የሚያስጠነቅቀን? ነብዪ ውልፈርድ ውድሩፍ እሳቸው ባለቤታቸው እና ህፃን ልጃቸው ተኝተውበት ስለነበሩበት ሰረገላ ጋሪ በመንፈስ ማስጠንቀቂያ የተቀበሉበትን ታሪክ ሲያወጉ፥ ከቅፅበት በሗላ እንዴት አውሎ ንፋስ ግዙፍ ዛፍ ከነስሩ ገንጥሎ ሰረገላው ቆሞ የነበረበት ቦታ ላይ እንደጣለው ተናገሩ (Teachings of Presidents of the Church: Wilford Woodruff [2004], 47 ተመልከቱ)።
በነዚህ ሁለት አጋጣሚዎች ፥ አደጋዎቹን ለማስወገድ ያየሩን ፀባይ ማስተካከል ይቻል ነበር። ነገር ግን ነጥቡ እዚህ ጋር ነው። ችግሮቹን በራሱ ከመፍታት ይልቅ፥ ለችግሮቻችን መፍትሄ በሱ ላይ እንድንታመን ይፈልጋል። ከዛን ፍቅሩ ያለማቋረጥ በሀይል፥በግልፅ፥ እና በግላችን ይሰማናል። ከርሱ ጋር እንጣበቃለን፥ እናም እሱን እንመስላለን። እሱን መምሰል ግባችን ነው፥ የሱም ክብር እና ስራም ነው። (መፅሀፈ ሙሴ 1፡39)
አንድ ወጣት ወንድ ልጅ በመኪና አሻንጉሊት ለመጫወት ከመኖሪያ ቤት ጀርባ ያለውን ቦታ ለማፅዳት እየሞከረ ነበር። ትልቅ አለት በመንገድ ላይ ሆኖ ተደነቀረበት። ልጁም ባለው ጥንካሬ ገፋ ጎተተ። ምንም ያህል ቢማክርም ድንጋዩ ንቅንቅ አልልም አለ።
አባትየው ለጊዜ ከተመለከተ በሗላ መቶ እንዲህ አለው። “ ይህንን የሚያክል ድንጋይ ለማንቀሳቀስ ሙሉ ጥንካሬክን መጠቀም አለብህ“
ልጁም መልሶ “ ሁሉንም ጥካሬዬን ተጠቀምኩኝ“ አለ።
አባትየውም “ የኔን እርዳታ እስካላግኘህ ድረስ ሁሉንም ጥንካሬህን አልተጠቀምክም“ ብሎ አስተካከለው።
ከዚያን ሁለቱም አጎንብሰው ድንጋዩን በቀላሉ አንቀሳቀሱት።
የፓፑአ ኒው ጊኒ የካስማ መሪ የሆኑት የጓደኛዬ አባት ቫይባ ሮም፥ ኣስፈለገ ጊዜ ወደ ሰማይ አባቱ መዞር እንደሚችል ተምረው ነበር። እሱና ባካባቢው ያሉ ገጠርተኞች የሚተዳደሩት በቆሎ በማብቀል ነው። አንድ ቀን ለመዝራት፥ የርሱ ድርሻ የሆነውን መሬት በእሳት መነጠረ። ሆኖም ግን ወቅቱ በጣም ሞቃት በመሆኑ ሁሉም እፅዋት ደረቅ ነበሩ። እሳቱም ነብዩ ቶማስ ሞንሰን ባለፈው በጉባኤ ላይ “ መታዘዝ በረከት ያመጣል“ ብለው የተናገሩት ነገር ሆነ ( “Obedience Brings Blessings,” Ensign orLiahona, May 2013, 89–90 ተመልከቱ)። ወደ ሳሮችና ወደ ቁጥቋጦ በመቀጣጠል መዝለቅ ጀመረ። የራሱ ልጅ በራሱ ቃል ሲገልፅ፥ “ ይሄ ትልቅ የእሳት ጭራቅ ነው አለ።“ ለገጠርተኞቹና ለእህላቸው ሰጋ። እነሱ ቢጎዱ ኖሮ ለገጠሩ ሸንጎ ይቀርብ ነበር። እሳቱን ማጥፋት ሲሳነው ጌታን አስታወሰ።
ጀመረ። በድንገት ትልቅ ጥቁር ደምና ሲፀል ከነበረበት አናት ላይ ሸፈነ፥ እናም በሃይል መዝነብ ጀመረ፥ ነገር ግን ዝናቡእሳት ባለበት ቦታ ላይ ብቻ ነበር። ቀና ብሎ ሲመለከት ከእሳቱ በስቲያ ዙሪያው በሙሉ ግልፅ የሆነ ሰማይ ነው። እግዚአብሄር እሱን ለመሰለ የተራ ሰው ፀሎት በመመለሱ ተደንቆ፥ ከንደገና ተንበርክኮ እንደ ህፃን ልጅ አለቀሰ። በጣፋጭ ስሜት ነበር አለ። ( አልማ 36፥3)
አዳኛችን በእውነቱ ፈቃዳችንን ከርሱ ጋር እስክናስተካክል ድረስ እንድንወደው ይፈልጋል። ከዛን ፍቅሩና ክብሩ ይገባናል። ከዛንም ደግሞ እንደወደደ ይባርከናል። ይህም የሄለማን ልጅ በሆነው ኔፊ ላይ ደርሷል ። ጌታ እሱን በማመኑ ምክንያት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በጠየቀው ነገር ሁሉ ይባርከው ነበር። (ሔላማን 10፤4_5)
“በፓይ ህይወት“ ውስጥ የተሰኘው በያን ማርትል የተፃፈው ልቦለዳዊ መፅሃፍ ጀግናው ስለክርስቶስ ያለውን ስሜት ሲያሰማ “ ከጭንቅላቴ እሱን ማውጣት አልችልም፥ መቼም አልችልም። ስለሱ ሳስብ ድፍን ሶስት ቀናት አሳለፍኩ። ባስጨንቀኝ ቁጥር ፥ አልረሳሁትም። ስለሱ በተማርኩ ቁጥር እሱን ለመተው አልፈለኩም።([2001], 57)
ስለአዳኛችን የሚሰማኝ ስሜት ተመሳሳይ ነው። ሁልጊዜ ቅርብ ነው፥ በተለይ በቅዱስ ቦታዎች እና ባስፈላጊ ጊዜ። አንዳንድ ጊዜ ባልጠበኩት ወቅት። ትከሻዬን በመንካት እንደሚወደኝ የሚነግረኝ ነው የሚመስለኝ። ፍፁም ባልሆነው መንገዴ ደግሞ ያንን ፍቅር ልቤን በመስጠት እመልሳለሁ። (ት እና ቃ 64፥22፤34 )
ከትቂት ወራት በፊት ኤልደር ሆላንድ የወንጌል አገልጋዮችን ወደ ስፍራቸው ሲመድብ አብሬ ተቀምጬ ነበር። ስንወጣ ጠበቀኝና አብረን እየተራመድን እያለ እጁን ትከሻዬ ላይ ጣል አደረገ። አውስትራሊያ ውስጥም እንዲሁ አድርጎ የተናገርኩትን አልኩት። አሱም መልሶ፥ “ይህም ስለምወድህ ነው አለ።“ እኔም ይህ እውነት እንደሆነ አወኩኝ።
ከጌታ ጋር አብረን የመራመድ እድሉን ብናገኝ፥ እጁ በትከሻችን ላይ ሆኖ ይሰማናል። በኤማሁስ መንገድ ላይ ያሉ ደቀ መዛሙርት እንዳሉት፥ “ ልባችን ይቃጠላል“። ( ሉቃስ 24፥32) የሱም መልእክት፥ “ ኑ እና እዩ“ ( የዩሃንስ ወንጌል 1፥39)። እጁ በትከሻችን ላይ ሆኖ እንዲህ ማለቱ የሚነካ ግብዣ ነው፥
በነዚህ የመጨረሻ ቁጥሮች ላይ እንዳንፀባረቀው ሁላችንም እንደ ኢኖስ ልበ ሙሉ እንሁን፥ የሚሞተው፥ የማይሞተውን ሲተካ፥ በዚያ ቀን እደሰታለሁ። እናም በርሱ ፊት እቆማለሁ። ፊቱንም በደስታ አያለሁ። እናም እርሱ እንዲህ ይለኛል፥ ወደ እኔ ና፥ ተባርከሃልና። በአባቴም ቤት የተዘጋጀልህ ቦታ አለ። “ ( ኢኖስ 1፤27)
ከልምድ ብዛትና የመንፈስ ቅዱስ ሃይል እንደመሰከረልኝ፥ እግዚአብሄር ህያው እንደሆነ ያለ ጥርጥር እመሰክራለሁ። ፍቅሩ ይሰማኛል። ፍቃዳችንን ከርሱ ጋር ለማዛመድ እና እሱን ለማፍቀር የሚያስፈልገውን ነገር እናድርግ። በእየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።