2010–2019 (እ.አ.አ)
የቃል ኪዳኖቻችሁን በረከቶች መቀበል
ኦክተውበር 2013


2:3

የቃል ኪዳኖቻችሁን በረከቶች መቀበል

ቃል ኪዳናችን በመጠበቅ እና በማደስ ሸክማችን ማቅለል እንችላለን እናም ያለማቋረጥ በመንፃት ብርታት ማግኘት እንችላለን።

እህቶች እንደገና ከናንተ ጋር በመሆነ ደስ ብሎኛል።

በቅርቡ ለጥምቀት ዝግጅት ላይ የነበረች ሴት ጋር ተገናኝቼ ነበር። በዝህ ልዩ የሆነ ሰንበት ዕለት በከባድ ጭቃ 3 ኪሎ ሜትር ተጉዛ ቤተክርስትያን ደረሰች። ወዲያው ወደ ሽንት ቤት በመሄድ ከጭቃ ልብስ ወደ ሰንበት ልብስ ቀየረች። ይህንንም በሴቶች ስብሰባ ተናገረች። በአዳኝ ሀጢያት ከፍያ እና ንሰሀ በመግባት በመታጠብ መንፃት ፍላጎቷ ልቤን ነካኝ። ከሰማይ አባታችን ጋር ቅዱስ ቃል ኪዳን ለመግባት በፍቃደንነት አሮጌ ህይወትን በመተዋ ተነካሁኝ። የመጠጥ ሱሰኝነትን በመተው ለመጠመቅ እቅዷን ስትናገር ከጓደኞቿ ተለየች። በአዳኝ ፍቅር ንፁህ ለመሆን ሀጥያት ለመተው ፍላጎት ነበራት። በዚያን ጠዋት በአካልም ሆነ በመንፈስ ንፁህ ለመሆን የነበራት ፍላጎት አነሳሳኝ።

ብዙዎቻችሁ በዝሁ ተመሳሳይ መስዋዕት በማድረግ የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት እንደተስማችሁ እና በጉጉት ንሰሀ በመጋባት ንፁህ እንሆናችሁ እናውቃለን። ምናልባትም ከማንኛውም ጊዜ የበለጠ የአዳኝ መለኮታዊ ፍቅር ንሰሀ ስንገባ የፍቅር ክንዱ እኛን ለመቀበል መዘርጋት በብዛት ይሰማናል።

ከጥቂት ሳምታት በፍት የቁርባን ፀሎት አዳምጬ ነበር፣ ቄሱ እያንዳንዱን ቃል በስሜት በማንበቡ ተነካሁኝ። በኃላም ለተሰብሳብዎቹ እና ለኔ ጥልቀት ያለው መንፈሳዊ ልምድ እንድናገኝ በማድረጉ ለማመስገን ለቄሱ ስልክ ደወልኩ። እሱ ቤት ስላልነበረ እናቱን አናገርኩ፣ ኦ ስለ ደወልሽ በጣም ደስ ይለዋል። የቁርባን ፀሎት ማድረግ ይህ የመጀመሪያ ጊዜው ነው እና ከአዳኝ ጋር የጥምቀት ቃል ኪዳን ለማደስ ስለ ቁርባን አስፈላጊነት አንድ ላይ ተዘጋጅተናል። የጥምቀት ቃል ኪዳን ልጇን በማስተማር የዎርድ አባሎች ይህ ሀይል እንድሰማችው በማድረጓ ይህን እናት እወዳለሁ።

ሌላ የማውቀው እናት ለብዙ ዓመት ከአራት ልጆቿ ጋር ብቻዋን ትቀመጥ ነበር። አንዳንዴ በቁርባን ጊዜ በአዳኝ ላይ ትኩረት ትሰጣለች፣ አሁን በየሳምንቱ ቅዳሜ ሳምንቱን በመከለስ ቃል ኪዳን በማሰብ ንሰሀ የሚትገባውን ታስባለች። ከዚያም አለች ከልጆቼ ጋር እሁድ ማኝኛውም ልምድ ብኖረኝም ቅርባን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። እናም ቃል ኪዳኔን በማደስ የሀጥያት ክፍያ ንፅህና ሀይል እንድሰማኝ ዝግጁ ነኝ።

ወድ እህቶች ለምንድነው አዳኝ የቁርባን ጠቃሚነት ላይ ብዙ ትኩረት ያደረገው? በየሳምቱ ቃል ኪዳንን ማደስ በህይዎታችን ላይ ምን ጥቅም ያመጣል? በብቃት በየሳምንቱ ቁርባን ስንቀበል የአዳኝ ሀይል ሙሉ በሙሉ እንደምያነፃን እናስትውሳለን? ፕሬዝዳንት ጃኬር እንዳሉት ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እና ሀጥያት ክፍያ ቃል ኪዳን ነው፣ በህይወታችን መጨረሻ ላይ ለሀጥያታችን ንሰሀ በመግባት እና በክርስቶስ ደም በመታጠብ መጋረጃውን መላፍ እንችላለን።1

እህቶቻችን እና ቤተሰባቸው ቃል ኪዳን በመግባት ስጠብቁ የኛ አመራራት ታላቅ ደስታ ይሰማቸዋል፣ ነገር ግን ቃል ኪዳን በመበጠስ የስቃይ ልምድ ላጋጠማችሁ በልባችን ህመም ይሰማናል። የኒፋይ ወንድም ነቢይ ያዕቆብ ለወንድሞቹ ስለ ቅዱሳን ሴቶች እና ለዘመኑ ልጆች እንድናገር በጌታ ታዘዘ። ቃሉ ለኛ ጊዜ እንደሆነ ቃል እገባለሁ። ጌታ ለኛ እንደምናገር ነው የተናገረው። ያዕቆብ ለባሎች እና አባቶች ስመሰክር በብዙ ሀሳብ ተሞልቶ ነበር።

እናም ደግሞ እናንተን በተመለከተ በሚስቶቻችሁ እናም በልጆቻችሁ ፊት፣ የብዙዎቹም ስሜት በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ለስላሳና ንፁህ፣ በቀላሉ ሊጎዳ የሚችል፣ ለእግዚአብሔርም አስደሳች ስለሆኑት በኃይል መናገር ስላለብኝ አዝናለሁ፤

በእነርሱም ፊት መጥፎ ምሳሌዎች በመሆናችሁ፤ እናም በልባቸው ጥልቅ ሀዘን በእናንተ ላይ ወደ እግዚአብሔር መጥተዋል። ብዙ ልቦች በሀዘን ቆሰሉ በጥልቅ ቁስልም ተበሱ።2

ቃል ኪዳን ለሚጠብቁ ሴቶች እና ልጆቹ እና ለዘመናችን ያዕቆብ ቃል ገብተዋል።

በሚያስተውል አዕምሮ ወደ እግዚአብሔር ተመልከቱ፣ እናም በታላቅ እምነትም ወደእርሱ ፀልዩ፣ እናም በመከራችሁ ያፅናናችኋል፣ እናም ምክንያታችሁን ይማፀናል፣

ምናልባት አዕምሮአችሁ ለዘለዓለም ጽኑ ይሆን ዘንድ ራሳችሁን አቅኑ፣ እናም አስደሳቹን የእግዚአብሔርን ቃል ተቀበሉ፣ እናም ፍቅሩንም ተቋደሱ።3

የልብ ህመማችን እና ፍላጎት ለሰማይ አባታችን በምንሰጥበት ጊዜ ያለውን የፀሎት ብርታትና ኃይል እናም ቃሉን በመመገብ የምንቀበለውን መልስ እና ኗሪ ስለሆነው ነቢያት ቃል እመስክራለሁ።

ሶስት ዓመት ወደምጠጋው በፕሮቮ ዩታ ታሪካዊ የሆነው ታበርናክል አደራሽ በእሳት ወደመ፤ ጥፋቱ በሁለቱም የአከባቢ ህዝቦች እና የቤተክርስትያን አባሎች በጣም አሳዛኝ ነበር። ብዙዎቹ ተገረሙ፣ ጌታ ለምን ይህ እንድሆን አደረገ? በውነትም እሳቱን በመከልከል ትፋቱን ማቆም ይችል ነበር።

ከአሥር ወራት በኃላ በጥቅምት ሁለትሺ አሥራ አንድ ዓ/ም ጉባኤ ላይ ፕሬዝዳንት ሞንስን የጠፋው ታበርናክል የጌታ ቤተመቅደስ እንደምሆን ብሎ ስናገር ትንፋሽን አስቆረጠ። ወዲያው ጌታ ሁሌ የሚያውቀውን ለማየት ችለናል። እሳቱ እንድነሳ አላደረገም፣ ነገር ግን እሳቱ ውስጣዊውን እንድያበላሽ አደረገ። ታበርናክሉ ቋሚ የሆነ ቅዱስ ቃል ኪዳን የሚደረግበት ቤተመቅደስ መሆኑን አየ፣ ይህም በመከራ ወቅት በታጋሽነት እና እምነት የሚመጣውን በረከቶች አስተምሮናል።4

ውድ እህቶች ጌታ በፈተና እንድንሞክር ያደርገናል፤ አንዳንዴም ከማንችለው በላይ እንድንፈተን ያደርገናል። በምንወዳቸው ህይወት እና በራሳችን ህይወት ላይ አይተናል። ለምን አፍቃሪ የሆነ የሰማይ አባት ይህ እንድሆን ያደርጋል ብለን እንገረማለን። ነገር ግን በአመድ ውስጥ አልተወንም፣ እጁን ዘርግቶ በመቆም በጉጉት ወደ እሱ እንድንመጣ ይጋብዘናል። መንፈሱ ለዘላለም እንድኖር ህይወታችን አስደናቅ በሆነ ቤተመቅደስ ይገነባል።

ትምህርታ ቃል ኪዳን 58፤3–4 ጌታ ይነግረናል፤

ከዚህ በኋላ ስለሚመጡት ነገሮች አምላካችሁ ያቀደውን፣ እናም ብዙ መከራን ተከትሎ የሚመጣውን ክብር፣ በእዚህ ጊዜ በተፈጥሮ አይኖቻችሁ ልታዩ አትችሉም።

ከብዙ መከራ በኋላ በረከቶች ይመጣሉና።ስለዚህ በብዙ ክብር አክሊልም የምትጭኑበት ቀን ይመጣል፤ ሰአቱ አልደረሰም፣ ነገር ግን እየቀረበ ነው።

እህቶች ጌታ ለሁላችንም ህይወት ዕቅድ እንዳለው እመሰክራለሁ። የሚደረገው ሁሉ ለሱ አስገራሚ አይደለም። ሁሉን አዋቂ እና ሁሉን የምወድ ነው። እኛን ለመርዳትና ለማፅናናት ይጓጓል እናም በሀጥያት ክፍያ በመመካት ቃል ኪዳናችን ስንጠብቅ ህመማችን ያቆማል። የችግርና መከራ ልምድ ወደ እሱ እንድንመጣ እንደምመራን አውቃለሁ። እናም ቃል ኪዳናችን በመያዝ ወደ እሱ በመመለስ አባት ያለውን ሁሉ መቀበል እንችላለልን።

ባለፈው አመት ችግር እንድቀለኝ የጌታ ፍቅር እና ግላዊ ራዕይ ፍልጌ ነበር። የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኔን የበለጠ ለመረዳት ፈልጌ ነበር። ለዝህ ልዩ ለሆነ ፀሎት በማድረግ ወደ ቤተመቅደስ በመሄድ የበረከቶቹን ቃል ማዳመጥ እንድችል መርቶኛል፣ ከልብ በማዳመጥ የእምነት ልምዴን ስሞክር ጌታ መሀሪ ስለሆነ ችግሮቼ እንድቀሉኝ አድርገዋል። መልስ ላላገኘው ፀሎቴ ታላቅ ሰላም እንዳገኝ ረድቶኛል። ጌታ ቃሉን እንደምጠብቅ የገባነውን ቃል ኪዳን በመጠበቅ በእምነት መለማመድ አለብን።5 ወድ እህቶች ወደ ቤተመቅደስ ኑ እና የሚገባችሁን በረከቶች ጠይቁ።

ሌላው በእርግጠኝነት እምነት እንድንይዝ የሚያደርገን መንካት እፍልጋለሁ። አንዳንድ ጊዜ እንደ ሴትነታችን ስለ ራሳችን አሳሳቢነት ላይ ዝንባሌ እናደርጋለን። በዝህ ወቅት ጌታ ስለ ራሴ እንደዚህ እንዳስብ ይፍልጋል ብለን በመንፈስ መጠየቅ አለብን። ወይም ስይጣን ልያሸንፈኝ ይሞክራል ብለን በጠየቅ ይኖ በመፈለግ ይህ አነሳሽ ከሰማይ አባት መሆኑን መተየቅ ይኖርብናል፣ ወይም ሰይጣን እራሴን ዝቅ እንዳደርግ ይሞክራል ብለን መጠየቅ አለብን። የሰማይ አባትችን መለኮት ፍፁም ፍቅር ወሰን እንድሌለው አስታውሱ።6 እሱ እኛን ለመገንባት ፍላጎት ያለው እንጂ የሚያዋርደን እንዳልሆነ አስታውሱ።

እንደ ቤተክርስትያን አባልነታችን አንዳንዴ በጌታ ተቀባይነት እንድኖረን ፍፁም የ LDS ቤተስብ መሆን እንዳለብን ስሜት ይሰማናል። አንዳንዴ በግዛቱ አነስተኛ የማይገጥም ስሜት ይሰማናል። ይህ ከተሰማን ከአላማው ጋር አይሄድም። ውድ እህቶች የተባለው ሁሉ ከተፈፀመ ለሰማይ አባት ፍቃድ ዋጋ ያለው እንዴት ቃል ኪዳናችን እንደጠበቅን እናም ምን ያህል የአዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌን ለመከተል መሞከራችን ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን እንደሆነ እመሰክራለሁ። በሀጥያት ክፍያው ምክንያት በየሳምንቱ በብቃት ቁርባን በመቀብል ንፁህ መሆን እንችላለን። ቃል ኪዳናችን በማደስ እና በማክበር ሽክማችን ልቀል ይችላል፤ እናም ባለሟቋረጥ በመንፃት ብርታት በማግኘት በመጨረሻው ህይወታችን ለዘላልለማዊ ህይወት ብቁ እንሆናለን። ይህን የሚመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።