በመፅናት ቀጥሉ
ወደ ሰማይ አባታችን የሚመራን የብረት በትር በፅናት እንድንይዝ ያድርገን።
አባቴ ቤተሰቦቹ አባቱ፣ እናቱ አራት ልጆቻቼው ቤተክርስትያን ለቀው የሄዱበትን ጊዜ እንድያውም ሰዓቱን ያስታውሳል። ብዙዎቹ በዚህ ህይወት እንደገና አልተመለሱም። እሱም የ13 ዓመት ዕድሜ ዲያቆን ነበር፣በዚያን ጊዜ በተሰቦች የሰንበት ትምህርት የሚካፈሉት ጠዋት ነበር። የቁርባን ስብሰባ ከሰዓት በኃላ ነበር። በቆንጆ ፀደይ ቀን ከእሁድ ጠዋት ስብከት አገልግሎት ከተመለሱ በኃላ እና ከቤተሰብ አንድ ላይ ምሳ እየበሉ እናቱ ወደ አባቱ በመዞር ደህና ውድ ከሰዓት በኃላ ለቁርባን ስብሰብ መሄድ አለብን ወይስ ቤተሰብ መኪና ለመንዳት ወደ ገጠር እንውሰድ በማለት አባቱን ጠየቀች።
ለአባቴ የቁርባን ስብሰባ አስተያየት በፍፁም ተከስቶ አያውቅም። ሶስቱ ወጣት ልጆቹ ቁጭ ብለው ትኩረት ይሰጡ ነበር። ያን ሰንበት ከሰዓት በኃላ ወደ ገጠር ለሽርሽር መኪና መንዳት ለቤተሰብ የሚያስደት ተሳትፎ ነበር። ነገር ግን ይህ ትንሽ ውሳኔ የአድስ አቅጣጫ መጀመሪያ ሆነ፣ ይህም በመጨረሻ ቤተስቡን ከቤተክርትያን ድህንነት፣ ጥበቃ እና በረከቶች በማራቅ ወደ ሌላ አቅጣጫ ልመራቸው ችለዋል።
ምንልባትም በኛ ጊዜ ሌላ መንገድ ለምረጥ ለሚገፋፉ ትምህርት ይሆን ዘንድ በመፅሀፈ ሞርሞን ነቢይ ሊሀይ ርእይ ለቤተሰቦቹ አካፍሎ ነበር። ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎችን አየሁ፣ እኔ ወደ ቆምኩበት ዛፍ ለመድረስ አብዛኞቹ ወደፊት ይገፉ ነበር።
“እናም እንዲህ ሆነ ወደዛፉ በሚያመራው መንገድ ወደፊት ተጓዙ።
“እናም እንዲህ ሆነ የጨለማ ጭጋግ ተነሳ፣ አዎን በመንገዱ ጉዞ የጀመሩት መንገዳቸውን እስኪስቱና ተንከራተው እስኪጠፉ ድረስ እጅግ ታላቅ የጨለማ ጭጋግ ተነሳ።”1
ከዚያም ሊሀይ ሁለተኛው ቡድን ወደ ፍት ስገፉ አያቸው፣ እናም እንዲህ ሆነ ሌሎች ደግሞ ወደፊት ሲገፉ አየሁ፣ እናም እነርሱም ወደፊት መጡና የብረት በትሩን ጫፍ ያዙ፣ የብረቱን በትር ተጠግተው በጨለማው ጭጋግ ውስጥ ወደፊት መጥተው የዛፉን ፍሬ እስኪካፈሉ ድረስ ወደፊት ገፉ። በሚያሳዝን ሁኔታ ከዛፉ ፍሬ ከተካፈሉ በኋላ ያፈሩ በመምሰል ተመለከቱ። በዝህም ምክንያት ትልቅና ሰፊ ህንፃን ተመለከትኩ፣ እናም ወደፍሬው መጥተው በተካፈሉት ላይ እጃቸውን እየጠቆሙ እና እየተሳለቁባቸው ነበር። ከዚያም እንኝህ ሰዎች “ወደተከለከለውም መንገድ ገቡና ጠፉ።” 2እስከ መጬረሻ ለመዛለቅ አልቻሉም ወይም ፍቃደኞች አልነበሩም።
የሆነ ሆኖ ሶስተኛው ቡድን ወደ ህይወት ዛፍ መድረስ ብቻ ሳይሆን በኃላም አልጠፉም። “ለዝህም ቅዱስ መፅሀፍ እንዳለው እነሆ ሌሎችም ብዙዎች የብረት በትሩን ጫፍ ይዘው ወደፊት ሲገፉ አየ፣ እና ወደፊት መጥተው የዛፉን ፍሬ እስኪካፈሉና እስኪወድቁ ድረስ መንገዳቸውን ወደፊት በመቀጠል ያለማቋረጥም የብረቱን በር ፀንተው ያዙ።”3 ለዚህ ቡድን ህዝቦች የብረት በትር የሚወክለው ድህንነት እና ጥበቃን ነው። እንኝህ ሰዎች ያለማቋረጥ ቀላል የሆነውን የእሁድ ከስዓት በኃላ ወደ ገጠር ሽርሽር እንኳ ያለማድረግ በፅናት ለመያዝ ችለዋል።
ስለ እነኝህ ሰዎች ቡድን ሽማግሌ ዴቭድ ኤ ቤድናር ይህን አስተምረዋል፣ “የዚህ ሀረግ ዋና ቁልፍ ያለማቋረጥ የብረቱን በትር ፀንተው መያዛቸው ነው። ምናልባትም የሶስተኛው ቡድን ሰዎች ያለማቋረጥ የክርስቶስ ቃልን በማንበብ ጥናት አድርገዋል። ከእነዚህ ቡድን ጋር ነው እናንተና እኔ መሆን የሚንፈልገው።”4
እኛ የእግዚአብሄር ቤተክርስትያን አባል የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል እና ለእግዚአብሄር ትእዛዝ ታዛዥ ለመሆን ቃል ኪዳን ገብተናል። በጥምቀት ጊዜ ለአዳኝ መስካሪ ሆነን 5 ለመቆም እና ደካሞችን እና የተቸገሩትን 6ለመርዳት ቃል ገብተናል። የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ለመጠበቅና የተፈለገውን ንሰሀ ለመግባት ሀዋሪያው ጳውሎስ አስተምረዋል፣ “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል።” 7
በየሳምንቱ የቁርባን ሥርአቶችን ውሀና ዳቦ በመቋደስ ቃል ኪዳናችን እናድሳለን። ይህ ቀላል የሆነ ሥራ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል እንደገና እራሳችን ቃል ያስገባናል። እግዚአብሄርም በተመላሽ መንፈሱ እንድመራን እና እንደምጠብቀን ቃል ገብቶልናል።
ወንጌሌን ስብኩ ከምለው መፅሀፍ ምስዮናችን ምስክርነት እና ራዕይ የሚመጣው የሰንበት ስብሰባን በመካፈል እንደሆነ ያስተምራሉ። “የቤተክርስትያን አገልግሎት በመካፈል እና አንድ ላይ በመስበክ እርስ በርስ ብርታት እንሰጣጣለን። ከጓደኞቻችን እና በተሰባችን ጋር በሚናደርገው ማህበር እድሳት እናገኛለን። መፅሀፍ ቅዱስ በምናጠናበት እና ዳግመኛ የተመሰረተውን ወንጌል የበለጠ በመማር እምነታችን ብርታት ያገኛል።”8
ለምን እሁድ ሶስት የተለያየ ስብሰባ አስፈለገ ብሎ አንድ ሰው ልጠይቅ ይሆናል። እነንህን ሶስቱን ስብሰባዎች በዝርዝር እንመልከት።
-
የቁርባን ስብሰባ ለቁርባን ስርዓት እንድንሳተፍ ያደርጋል። ቃል ኪዳናችን በማዳስ ብዛት ያለው መንፈስ እንድንቀበል ያደርጋል። እናም ተጨማሪ በረከቶችን በመቀበል በመንፈስ ቅዱስ ንፃት እናገኛለን።
-
የሰንበት ትምህርት “የእግዚአብሄር ግዛት ትምህርትን እርስ በርስ በማስተማር”9 “ሁላችንም በመሻሻል እንድንደሰት ያደርገናል።”10 ዳግመኛ የተመሰረተውን የወንጌል ህግጋት በመረዳት ታላቅ ሀይል እና የግል ስላም ልመጣ ይችላል።
-
የክህነት ሥልጣን ስብሰባ ወንዶች እና ወጣት ወንዶች “የሥራ ድርሻቸውን በትክክል የሚማሩበት”11 “በደንብ የሚሰለጥኑበት”12 ወቅት ነው። የሴቶች መረዳጃ ምህበር ስብሰባ ለቤተክርስትያናት ሴቶች እምነታቸውን እንድጨምሩ በማድረግ “ለቤተሰብ ብርታት በመስጠት ችግርተኞችን የሚረዱበት ዕድል ይፈጥራል።”13
እንደዚሁም ወጣት ሲቶቻችን እና ልጆች አስፈላጊ ለሆነ ሀላፍነት የሚያዘጋጃቸው የወንጌል ትምህርት ክፍል የሆነ የራሳቸው ስብሰባ አላቸው። በዚህ ልዩ በሆነው እያንዳንዱ ስብሰባ ህግጋትን በመማር እና መንፈስን በመስማት እርስ በርስ አገልግሎት እንሰጣለን። በርቀት፣በመጓጓዣ ወይም በጤንነት ምክንያት ምናልባት ለየት ቢሆንም ሁሉንም የሰንበት ስብሰባችን ተካፋይ መሆን አለብን። በሶስቱም የሰንበት ስብሰባ ስብከት ተካፋይ ከመሆን ታላቅ የሆነ የሰላም በረከቶች እንድምመጡ ቃል እገባለሁ።
ቤተሰባችን ሁሉንም የሰንበት ስብሰባ ላይ ሁል ጊዜ ተካፋይ ለመሆን ወስነዋል። ይህ እምነታችን እና ወንጌልን በጥልቀት እንድንረዳ የሚያደርግ መሆኑን አውቀናል። የቤተክርስትያን ስብሰባችን መካፈል ውሳኔ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ተረድተናል። በተለይም ከበተክርስትያን ተመልሰን ሰንበትን ለማክበር መቀጠል ደስ ያሰኛል። በእረፍት ጊዜ እና ጉዞ ላይ እያለንም ሁሉንም ስብሰባችን እንካፈላለን። በቅርቡ አንድ ሴት ልጃችን እንደፃፈችው በጉዞ ላይ ባለች ከተማ ለቤተክርስትያን ተካፋይ ሆናለች፣ አዎ አባት ሶስቱንም የሰንበት ስብሰባ ተካፍያለሁ አለች። ለዝህ ቅዱስ ምርጫ እንደተባረከች እናውቃለን።
ሁላችንም ሰንበትን እንዴት ማክበር እንዳለብን ብዙ ምርጫዎች አለን። ለቤተክርስትያን ስብሰባ ሁል ጊዜ አንዳንድ ጥሩ የሆኑ ተሳትፎዎችን አስተዋፅኦ የምናደርግ ልሆን ይችላል። ይህም ዲያብሎስ “ነፍሳችን በማታለል ወደ ጥፋት የሚመራን አንዱ መንገድ ነው።”14 ጥሩ ተሳትፎን በተሻለ ይተካል።15
በመቀጠል የብረት በትርን መያዝ ማለት ሁሉንም የሰንበት ስብሰባ የቁርባን፣ የሰንበት ትምህርት እና የክህነት ወይም የሴቶች መረዳጃ ስብሰባዎች ተካፍይ መሆን ማለት ነው። ልጆቻችን የራሳቸውን የልጆች ክፍለ ጊዜ፣ የወጣት ወንዶች እና ወጣት ሴቶች ስብሰባን ይካፈላሉ። የትኛውን ስብሰባ መካፈል እንዳለብ በፍፁም መምረጥ የለብንም። የእግዚአብሄር ቃል በመቀጠል ለሰንበት ስብሰባዎችን ሁሉ ተካፍይ መሆን አለብን።
በፅናት የብረት በትርን መያዝ ማለት ሁሉንም የእግዚአብሄር ትእዛዝን መጠበቅ ነው፣በየቀኑ የግል እና የቤተስብ ፀሎት ማድረግ እና በየቀኑ ቅዱስ መፅሀፍን ማጥናት ማለት ነው።
በመቀጠል መያዝ ማለት በመፅሀፈ ሞርሞን ውስጥ እንደተገለፀው የክርስቶስ ህግጋት አካል መሆኑን ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ልምድ በማድረግ ለሀጢያታችን ንሰሀ በመግባት እና ልባችን በመለወጥ ወደ ጥምቀት ውሀ እንከተለዋለን፣ ከዚያም የመንፈስ ቅዱስ ማረጋገጭ እንቀበላለን፣ ይህም እንደ መሪ እኛን በማገልገል ፅናት ያደርግልናል። ኔፍ እንዳስተማረው፡ የክርስቶስን ቃል ብትመገቡ፣ እናም እስከመጨረሻው ብትፀኑ፣ እነሆ የዘለዓለም ህይወት ይኖራችኋል ይላል።16
ወንድሞቼ እና እህቶቼ እኛ የቃል ኪዳን ሰዎች ነን። በፍቃደንነት ቃል ኪዳን በማድረግ እንጠብቃለን። እናም ቃል የተገባውን በረከቶች “አባት ያለውን ሁሉ እንቀበላለን።”17 ቃል ኪዳናችን በመጠበቅ የብረት በትርን መያዝ በመቀጠል የአለማትን ፍተናዎች ለመቋቋም ብርታት እናገኛለን። “በጣም ዕንቁ እና ከሁሉም በላይ የሚንመኘው”18 ወደ ፍሬያማው ዛፍ እስከምንደርስ የዚህን ምድራዊ ህይወት ፈተና ውስጥ ማለፍ እንችላለን።
አባቴ ጥሩ ሴት አግብቶ ወደ ቤትክርስትያን እንድመለስ ብርታት ስለሰጠችው እና ወደ ደህና መንገድ ተመልሰው እድገት በማሳየቱ እድለኛ ነው። የእነሱ ታማኝነት ህይወት ሁሉንም ልጆቻቸውን እና የሚቀጥለውን ትውልድ የልጅ ልጃቸውን ባርከዋል።
ልክ ቀላል የሆነ ውሳኔ ተካፍይ መሆን ወይም ለሰንበት ስብሰባ ስብከት ተካፍይ አለመሆን በአያቶቼ ቤተሰብ ህይወት ላይ አስፍላጊ ልዩነት አምጥተዋል። በየቀኑ የሚናደርገው ውሳኔዎች በህይወታችን ላይ አስፈላጊ የሆነ ተፅእኖ ልያመጣ ይችላል። ትንሽ ውሳኔ የሆነው ለምሳሌ የቁርባን ስብሰባ ላይ ተሳታፍ አለመሆን ዘላለማዊ ጉዳት ላይ ልያደርስ ይችላል።
ትጋት እንድኖረን እንምረጥ እናም በአንድነት ተሰብስበን ቃል ኪዳን በመጠበቅ የሚመጡትን ታላቅ በረከቶች እና ጥበቃዎች እንድናገኝ ያድርገን። ወደ ሰማይ አባታችን የሚመራን የብረት በትሪን መያዝ መቀጠላችን ያድርገን ዘንድ ፀሎቴ በተቀደሰው ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።