2010–2019 (እ.አ.አ)
እውነተኛ እረኛ
ኦክተውበር 2013


17:34

እውነተኛ እረኛ

የቤት ለቤት ማስተማር ብዙ ጸሎቶችን መልስ ይሰጣል እናም በሰዎች ህይወቶች የሚመጡትን ለውጦች እንድናይ ይፈቅድልናል።

በዚህ ምሽትበሶልት ሌክ ሲቲ የጉባኤ አዳራሽ እና ቅርብም ይሁን ሩቅ በሆኑት ቦታዎች የእግዚአብሔር ክህነት ያላቸው ሰዎች ተሰብስበዋል። በእውነተም እናንተ “ልዑል ካህናት”፣ እንዲሁም ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው “ምርጥ ትውልድ” ናችሁ።1 ከእናንተ ጋር ለመነጋገር በመቻሌ ክብር ይሰማኛል።

በልጅነቴ፣ በየበጋው ከቤተሰቤ ጋር ከሶልት ሌክ ከተማ በምስራቅ በኩል ወደሚገኘው ወደ ፕሮቮ ሸለቆ ለሽርሽር እሄድ ነበር። እና ወንዶቹ አሳ ወደምናጥምድበት ወይም ወደምንዋኝበት ለመደርሽ እንቸኩላለን፣ እናም መኪናው በትንሽ ፍጥነት እንዲሄድ ለማድረግ እንችላለን። በእነዚያ ቀናት አባቴ የሚነዳው መኪና የ1928 መኪና ነበር። ፍጥነቱ ከ56 ኪሎ ሜትር በሰዓት በላይ የሚሄድ ከሆነ፣ እናቴ “ቀስ በል! ቀስ በል!” ትለዋለች። እኔም፣ “ቶሎ በል፣ ፍጠን” እለዋለሁ።

መንጋዎች ጉዞአችንን እስከሚያቁርጡብን ድረስ ወደ ፕሮቮ ሸለቁ እስከሚደርስ ድረስ አባቴም 56 ኪሎ ሜትር በሰዓት ይጓዛል። ብዙ መቶ የሚሆኑ የበግ መንጋዎች፣ እረኛ የማይጠብቃቸው እየመሰሉ ግን የሚጮሁ ውሻዎች እየመሯቸው፣ በፊታችን ሲሄዱ እንመለከታለን። ከኋላቸውም በሩቁ በፈረስ ላይ የተቀመጠውን እረኛ እናያለን። አንዳንዴም በፈረሱ ላይ ተቀምጡ ያንቀላፋል፣ ምክንያቱም ፈረሱ መንገዱን ያውቀዋል እናም ውሻዎቹ ስራውን ያከናውናሉና።

በሚዩኒክ፣ ጀርመን ውስጥ ካየሁት ጋር ይህን አስተያያለሁ። ያም በእሁድ ጠዋት ነበር፣ እናም እኛው ወደ ሚስዮን ጉባኤ እየሄድን ነበር። ከሚስዮን ፕሬዘደንቱ መኪና ወደውጪ ስመለከት፣ በእጁ በትር የያዘ እረኛ በጎቹን ሲመራ ተመለከትኩኝ። ይትም በሚሄድበት ይከተሉት ነበር። ወደ ግራ ከሄደ እነርሱም ወደ ግራ ይከተሉታል። ወደ ቀኝ ከሄደ፣ እነርሱም ወደዚያ ይከተሉታል። እኔም በጎቹን የሚመራውን እውነተኛ እረኛ ከበጎቹ በኋላ ከሚከተለው ጋር አነጻጸርኩኝ።

ኢየሱስ እንዳለው፣ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ የራሴን በጎች ያውቁኛል።”2 እውነተኛ እረኛ ምን መሆ እንደሚገባው ፍጹም ምሳሌ ሰጥቶናል።

ወድሞች፣ እንደ እግዚአብሔር ካህናት እኛም የእረኝነት ሀላፊነት አለን። የጌታ ጥበብ እኛ እንደ ቤተክርስቲያኗ ቤተሰቦች እረኞች የምንሆንበት፣ የምናገለግልበት፣ እና ለእነርሱ የምንመሰክርበት መመሪያዎች ሰጥቶናል። ይህም የቤት ለቤት ማስተማር ተብሎ ይጠራል፣ እናም በዚህ ምሽት ላነጋግራችሁ የምፈልገው ስለዚህ ነው።

የእያንዳንዱ ዎርዶች ኤጲስ ቆጶሶች በየወሩ የአባላትን ቤት የሚጎበኙ የቤት ለቤት አስተማሪዎች እንዲሆኑ የክህነት ባለስልጣንን ይመድባሉ። እነርሱም ሁለት በሁለት ይሄዳሉ። የሚቻል ሲሆንም፣ ካህን ወይም አስተማሪ የሆነ የአሮናዊ ክህነት አባል ከጎልማሳው ከመልከ ጼዴቅ ክህነት አባል ጋር ይሄዳሉ። ሀላፊነት ወዳላቸው ሰዎች ቤት ሲሄዱም፣ የአሮናው የክህነት ባለስልጣኖች በሚቀርበም ትምህርት መሳተፋቸው ተገቢ ነው። እንደዚህ አይነት ምድብ እነዚህን ወጣት ሰዎች ለሚስዮን እናም ለህይወት ሙሉ የክህነት አገልግሎች እንዲዘጋጁ ይረዳቸዋል።

የቤት ለቤት ማስተማሪያ ፕሮግራምበክህነት ለተቀቡት ይህን ሀላፊነት የሚሰጥ፣ ለዚህ ቀን ራዕይ መልስ ነው፣ “...ማስተማር፣ ማብራራት፣ አጥብቆ መምከር፣ እናም ማጥመቅ፣... የእያንዳንዱን አባል ቤትን መጎብኘት፣ እናም በሚስጥር እና በድምፅ እንዲጸልዩ እና የቤተሰብ ሀላፊነታቸውን እንዲያከናውኑ በጥብቅ ማበረታት...ቤተክርስቲያኗን ዘወትር መጠበቅ፣ እና እነርሱን መርዳትና ማጠንከር ነው፤እናም ምንም ጥፋት በቤተክርስቲያኗ እንዳይኖር፣ እንዲሁም አባላቶቿ እርስ በራሳቸው እንዳይከፋፉ፣ እንዳይዋሹ፣ እንዳይተማሙ፣ ወይም ለክፉ እንዳይነጋገሩ መጠበቅ ነው።”3

ፕሬዘደንት ዴቪድ ኦ. መኬይ እደገሰጹት፣ “በቤት ለቤት ማስተማር የአባታችንን ልጆች ለመንከባከብና ለማነሳሳት፣ ለመምከርና ለማነሳሳት ባስቸኳይ መደረግ ያለበትና የሚሸልም እድል ነው።...ይህም መለኮታዊ አገልግሎት፣ መለኮታዊ ጥሪ ነው። መንፈስን ለእያንዳንዱ ቤት እና ልብ መውሰዱም የእኛ የቤት ለቤት አስተማሪዎች ሀላፊነት ነው። ስራን መውደድ እናም የምንችለውን ያህል ማድረግ መለካት የማይቻል ሰላም፣ ደስታ፣ እና እርካታ ለእግዚአብሔር ልጆች በክብር ለሚያስተምሩት ያመጣል።”4

ከመፅሐፈ ሞርሞን እንደምናነበርው፣ አልማ “የእነርሱን ካህናትንና መምህራኖቻቸውን ሾመ፤ እናም ማንም ትክክለኛ ሰው ካልሆነ በቀር አልተሾመም ነበር።

“ስለዚህ ህዝባቸውን ጠበቁ፣ እናም ከፅድቅነት ጋር የተገናኙ ነገሮችን መገቧቸው።”5

የቤት ለቤት አስተማሪነት ሀላፊነታችንን በማሟላት፣ በስኬት ለማስተማር እና የሚያስፈልገውን እርዳታ ለመስጠት እንድንችል፣ የምናስተምራቸውን የእያንዳንዱን ቤተሰቦች ፈተናዎች ለመማርና ለመረዳት ከቻልን ጥበበኞች ነን።

በቤት ለቤት ማስተማሪያ ጉብኝት ከሚኬድበት በፊት ቀጠቆ ካለ ውጤታማ ለመሆን ይችላል። ይህን በምሳሌ ለማሳየት፣ ከጥቂት አመቶች በፊት የነበረኝን አጋጣሚ ልንገራችሁ። በዚያ ጊዜ የሚስዮን መዳቢ ቡድን አባል የነበሩት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል፣ ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ እና ሮማስ ኤስ. ሞንሰን ነበሩ። አንድ ምሽት ወንድም እና እህት ሒንክሊ የቡድኑን አባላት እና ባለቤቶቻቸውን ለእራት ጋበዧቸው። መልካም የነበረውን ምግብ በልተን ስንጨርስ በሩ ተንኳኳ። ፕሬዘደንት ሒንክሊ በሩን ከፈቱ እና ከቤት ለቤት አስተማሪያቸው አንዱ በራቸው ላይ ቆሞ ተመለከቱ። የቤት ለቤት አስተማሪውም “ለመምጣት ቀጠሮ እንደሌለኝ አውቃለሁ፣ እናም ጓደኛዬ ከእኔ ጋር አይደለም፣ ነገር ግን በዚህ ምሽት እንድመጣ ስሜት ተሰምቶኝ ነበር። የምትጋብዟቸው እንዳሎት አላወቅኩም ነበር” አለ።

ፕሬዘደንት ሒንክሊም እንዲገባ፣ እንዲቀመጥ፣ እና ሶስት ሀዋሪያትንና ባለቤቶቻቸውን የአባልነት ሀላፊነቶቻቸውን እንዲያስተምር ጠየቁት።፡ፍርሀት ቢኖረውም፣ የቤት ለቤት አስተማሪውም የሚችለውን ያህል አደረገ። ፕሬዘደንት ሒንክሊም በመምጣቱ አመሰገኑት፣ ከዚያም በፍጥነት ወደቤቱ ሄደ።

ሌላ የቤት ለቤት ማስተማርን መደረግ የማይገባበትን አንድ ተጨማሪ ምሳሌ ልጥቀስ። የቀዳሚ አመራር አማካሪ የነበሩት ፕሬዘደንት ማሪያን ጂ ሮምኒ አንድ ቀን ወደ ቤታቸው በብርድ ቀን መጥቶ ስለነበር የቤት ለቤት አስተማሪ ይናገሩ ነበር። እንዲቀመጥና መልእክቱን እንዲያቀርብ በሚጋበዝበት ጊዜ ኮፍያውን በእጁ ይዞ ፈርቶ ነበር። ሳይቀመጥም “ወንድም ሮምኒ፣ ውጪ ብር ነው፣ እናም መኪናዬ እንዳይቆምም ኢንጅኑን እንዲንቀሳቀስ እያደረግሁኝ ነው። የመጣሁት ለኤጲስ ቆጶስ ጉብኝቴን አከናውኛለሁ ለማለት ነው”6 አለ።

ፕሬዘደንት ኤዝራ ታፍት ቤንሰን የወንድም ሮምኒን አጋጣሚ በክህነት ስብሰባ ጀተናገሩበት በኋላ፣ “ወንድሞች፣ ከዚህ በተሻለ፣ በጣም በተሻለ ለማድረግ እንችላለን”7 ብለው ነበር።7 እኔም ከእርሳቸው ጋር የምስማማ ነኝ።

የቤት ለቤት አስተማሪነት በየወሩ መከናወን ያለበት ጉብኝት ብቻ አይደለም። የማስተማር፣ የማነሳሳት፣ እናም ተሳታፊ ያልሆኑትን የምንጎበኝ ከሆነም ወደ ተሳታፊነት የምንመልስበት እና በመጨረቻው የእግዚአብሔርን ወንድ እና ሴት ልጆች ወደዘለአለማዊነት ከፍ የምናደርግበት ሀላፊነት ነው።

በጥረታችን ለመርዳት፣ የቤት ለቤት አስተማሪዎች የሚጠቅም አንድ ጥበባዊ ምክር እካፈላለሁ። ይህም እንዲህ ካሉት ከአብርሀም ሊንከን ያሉት ነው፣ “ሰው ወደ እናንተ ምክንያት እንዲመጣ ከፈለጋችሁ፣ መጀመሪያ እናንተ የእርሱ ልባዊ ጓደኛ እደሆናችሁ አሳምኑት።” ፕሬዘደንት ኤዝራ ታፍት ቤንሰን እንደገፋፉንም፣ “ከሁሉም በላይ፣ ለምታስተምሯቸው ቤተሰቦች እና ግለሰቦች፣ እውነተኛ ጓደኞች ሁኑ።”8 “ከሁሉም በላይ፣ ለምታስተምሯቸው ግለሰቦችና ቤተሰቦች ጓደኞች ሁኑ። ጉደኛ የሀላፊነት ጉብኝት በየወሩ ያደርጋል።፡ጓደኛ ሰዎችን መርዳት እንጂ ታዋቂነትን ከማግኘት አያስብበትም። ጓደኛ ያስባል። ጓደኛ ፍቅርን ያሳያል።፡እናም ጓደኛ እርዳታ ያቀርባል።”9

የቤት ለቤት ማስተማር ብዙ ጸሎቶችን መልስ ይሰጣል እናም በሰዎች ህይወቶች የሚመጡትን ለውጦች እንድናይ ይፈቅድልናል።

የዚህ ምሳሌም በኢኮኖሚ ችግር ጊዜ ለስራ ወደ ዩታ የመጣው ዲክ ሀመር ነው። በዚህም እያለ፣ የኋለኛ ቀን ቅዱሳን ሴት ጋር ተገናኝቶ ተጋቡ። በኔንት ጆርጅ፣ ዩታም ተዋቂ የሆነ የቡና ቤት ሰራ።

ለሀመር ቤተሰብ የቤት ለቤት አስተማሪ እንዲሆን የተመደበውም የእኔ ጓደኛ ዊለርድ ሚልን ነበር። ዲክ ሃመርን ስለማውቀም፣ ወደ ሴንት ጆርጅ በምሄድበት ጊዜ ጓደኛዬን ወንድም ሚልንን “ጓደኛችን ዲክ ሀመር እንዲት ነው?” ብዬ እጠይቃለሁ።

በአብዛኛውም ጊዜ እርሱም “በቀስታ ቢሆንም ወደፊት እየገፋ ነው” ብሎ ይመልስልኛል።

ዊለርድ ሚልን እና ጓደኛው የሀመርን ቤት ሲጎበኡ፣ እንደምንም የወንጌል መልእክትን ያቀርባሉ እናም ከዲክ እና ቤተሰቡ ጋርም ምስክርነታቸውን ይካፈላሉ።

አመታት አለፉ፣ እናም አንድ ቀን ዊለርድ እኔን መልካም ዜና ለመንገር ደወለልኝ። “ወንድም ሞንሰን፣ ዲክ ሀመር ተለወጠና ሊጠመቅ ነው። 90 አመቱ ነው፣ እናም በህይወታችን በሙሉ ጓደኞች ነበርን። ውሳኔው ልቤን ያሞቀዋል። የእርሱ የቤት ለቤት አስተማሪ ለብዙ አመታት ነበርኩኝ” አለኝ። ይህን መላክም ዜና ሲነግረኝ ድምጹ በእንባ እየተሰባበረ ነበር።

ወንድም ሀመር በእርግጥም ተጠመቀ እናም ከአንድ አመት በኋላ ወደ ሴንት ጆርጅ ቤተመቅደስ ገብቶ በመንፈስ ስጦታታ በመተሳሰር ስርዓቶችተሳተፈ።

ዊለርድንም “ለብዙ አመታት የቤት ለቤት አስተማሪው ስለሆንክ ተስፋ ቆርጠህ ነበር ብዬ ጠየቅሁት።

እንዲህም መለሰ “አልነበርኩን፣ ይህም ለጥረቴ ብቁ ነው። ለሀመር ቤተሰብ የመጣውን ደስታ ስመለከት፣ ወንጌሉ ወደ ህይወታቸው ስላመጣው በረከቶች እና በአንድ መንገድ ለመርዳት ለነበረኝ እድል ልቤ በምስጋና ይሞላል። እኔ ደስተኛ ሰው ነኝ።”

ወንድሞች፣ በአመት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑትን እና በደንብ የሚሳተፉትን የተለያዩ ሰዎችን ለመጎብኘትና ለማስተማር እድል አላችሁ። በጥሪአችሁ በልብ የምናገለግን ከሆንን፣ ህይወቶችን ለመባረክ ብዙ እድሎች ይኖሩናል። ከቤተክርስቲያን እራሳቸውን ያራቁትን መጎብኘት የሚመለሱበትን በሮች የሚከፍት ቁልፍ ለመሆንም ይችላል።

በዚህ ሀሳብም፣ ሀላፊነት ያለንባቸውንም እንርዳ እናም በቃሉ እንዲመገቡ ዘንድ ወደ ጌታ ጠረጴዛ እንዲመጡ እናም የመንፈሱን ጓደኝነት እንዲደሰቱ፣ እናም “ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ... እንጂ እንግዶች...”10 እንዲሆኑሀላፊነት አለን።

ማንኛችሁም የምትጎበኛቸውን በሚመለከት ችላ የምትሉ ካላችሁ፣ የቤት ለቤት አስተማሪነት ሀላፊነታችሁ ለማሟላት ለመወሰን ከአሁን በላይ የሚሻል ጊዜ የለም። ለእናንተ በሀላፊነት የተሰጣችሁንም ለመርዳት የምትችሉትን ያህል ጥረት ለማድረግ ወስኑ። አንዳንዴ የቤት ለቤት አስተማሪነት ጓደኛችሁ አብሯችሁ እንዲመጣ ተጨማሪ መገፋፋት የሚያስፈልግበት ጊዜ አለ፣ ነገር ግን ያለማቋረጥ ከጣራችሁ፣ ስኬታማ ትሆናላችሁ።

ወንድሞች፣ በቤት ለቤት ማስተማር ያለን ጥረት የሚቀጥል ነው። ጌታችን እና መምህራችን “ብቁ ነው” እስከሚል ድረስ ይህ ስራ አይፈጸምም። ብርሀን ይሚገባላቸው ህይወቶች አሉ። መነካት የሚገባቸው ልቦች አሉ። የሚድኑም ነፍሳት አሉ። እኛም እንድንንከባከብ በአደራ የተሰጡንን ነፍሳት የማብራት፣ የመንካት፣ እና የማዳን ቅዱስ እድል አለን። ይህንንም በታማኝነት እና በደስታ በተሞላ ልብ ማከናወን ይገባናል።

ምን አይነት የቤት ለቤት አስተማሪዎችመሆን እንዳለብን በሚያሳይ አንድ ምሳሌ እጨርሳለሁ። ህይወቱ ሁሉንም የሚያደበዝዝ አንድ የቤት ለቤት አስተማሪ አለ። እርሱም ህይወትና ሞትን፣ ሀላፊነትና እጣፈንታን አስተማረ። እንዲገለገል ሳይሆን ለማገልገል፣ ለመቀበል ሳይሆን ለመስጠት፣ህይወቱን ለማዳን ሳይሆን ለሌሎች መስዋዕት ለማድረግ ይኖር ነበር። ከዙመት በላይ የሆነን ፍቅር ገልጿል፣ ከሀብት በላይ የሆነውን ድሀነትንም ገልጿል። እርሱ ያስተማረው እንደ ጸሀፊዎቹ ሳይሆን በስልጣን ነው ተብሎበታል።”11 ህግጋቱ የድንጋይ ላይ የተቀረጹ ሳይሆን በሰው ልብ ላይ የተቀረጹ ናቸው።

የምናገረውም ታላቅ መምህር ስለነበረው ስለኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የሰው ዘር አዳኝና ቤዛ ነው። የቅዱስ መፅሐፍም ስለእርሱ “መልካም በማድረግ ሄደ”12 ብሎ ነበር። እንደ እርሱ አይነት የማይወቅድ መሪና ምሳሌ እያለን፣ በቤት ለቤት በምናስተምርበት ለመለኮታዊ እርዳታው ብቁ ለመሆን እንችላለን። ህይወቶች ይባረካሉ። ልቦች ይፅናናሉ። ነፍሳት ይድናሉ። እውነተኛ እረኞችም እንሆናለን። ይህም ይሆን ዘንድ የምጸልየው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።