“ህዳር 8–14 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 129–132፥ ‘የትኛውንም በረከት ከእግዚአብሔር [የምናገኘው]፣ … ታዛዥ በመሆን ነው’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ህዳር 8–14 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 129–132፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)
ህዳር 8–14 (እ.አ.አ)
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 129–132
“የትኛውንም በረከት ከእግዚአብሔር [የምናገኘው]፣ … ታዛዥ በመሆን ነው”
ክፍሎች 129–132 ብዙ ውድ መመሪያዎችን ያስተምራሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ ጥቂቶቹ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ጎላ ብለው የተቀመጡ ናቸው። ምን ሌሎች እውነቶች ታገኛላችሁ?
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ብሪገም ያንግ ስለ ጆሴፍ ስሚዝ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለዋል፣ “እሱ የሰማይ ነገሮችን ወሰን ወዳለው ግንዛቤ ሊቀንሰው ይችላል” (በቤተክርስትያኗ ፕሬዘዳንቶች ትምህርቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ፣ 499–500)። ይህ አገላለጽ በተለይ በ1840ዎቹ አመታት (እ.አ.አ) ውስጥ በናቩ የነበሩትን የነቢዩ ትምህርቶች በተመለከተ እውነት ይመስላል፣ የተወሰኑትም በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 129–32 ውስጥ ተመዝግባዋል። አዳኝ ምን ይመስላል? “እርሱ እንደ እኛ ሰው ነው።” ሰማይ ምን ይመስላል? “በዚህ በመካከላችን የሚገኘው ማህበራዊ ግንኙነት … በዚያም እናገኘዋለን” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥1–2)፣ እናም በዚህ ዓለም ውስጥ በጣም የምንወዳቸው የቤተሰብ ግንኙነቶች፣ በተገቢው ስልጣን ከታተመ፣ በሚቀጥለው ዓለም “ሙሉ ሀይል ያለው ይሆናል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥19)። እንደነዚህ ያሉ እውነቶች ሰማይ በትንሽ ርቀት ላይ ያለ ያህል እንዲሰማን ያደርጉታል—የከበረ ግን ተደራሽ የሆነ ነው።
ነገር ግን በዚያን ጊዜ፣ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር፣ በጣም የማይመቹ ከመሆናቸው የተነሳ በቀላሉ የማይደረሱ የሚመስሉሉ ነገሮችን እንድናደርግ ሊጠይቀን ይችላል። ለብዙዎቹ የመጀመሪያ ቅዱሳን፣ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ከእንደዚህ ዓይነት ትእዛዝ ነበር። ተጨማሪ ሚስቶችን የማግባት ትእዛዝ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ለሚስቱ ኤማ እና ይህን ለተቀበሉት ለሁሉም ሰዎች ከባድ የእምነት ፈተና ነበር። በዚህ ፈተና ውስጥ ለማለፍ፣ በዳግም ስለተመለሰው ወንጌል ተገቢ ስሜቶችን ብቻ አልነበረም የፈለጉት፤ ከየትኛውም የግል ምኞቶች ወይም ፍላጎት በላይ እጅግ በጣም ጥልቅ የሆነ የእግዚአብሔር እምነት ያስፈልጋቸው ነበር። ይህ ትእዛዝ ዛሬ ቆሚ አይደለም፣ ነገር ግን የታመኑት የታማኝነት ምሳሌ አሁንም ይኖራል። “ታዛዥ በመሆን [የምናደርገውን] መስዋዕትነት” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥50) እንድናቀርብ ስንጠየቅ ይህ ምሳሌ ያበረታታናል።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ጆሴፍ ስሚዝ ስለ አምላኮች እና “መጪው ዓለም” እውነቶችን ገልጿል።
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍሎች 130–131 ውስጥ ያሉት ከሌሎች ክፍሎች ትንሽ ለየት ባለ መልኩ እንደሚነበቡ አስተውላችሁ ይሆናል። የዚህም ምክንያት ክፍሎች 130–131 ከጆሴፍ ስሚዝ ጸሐፊዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ዊልያም ክሌተን ነቢዩ ሲያስተምር የሰማቸውን ነገሮች በጻፈው በማስታወሻዎች ላይ የተመሠረቱ ናቸው። በዚህም ምክንያት፣ እነዚህ ክፍሎች ይበልጥ ተመሳሳይነት ያላቸው ከተገለፁ ራዕዮች ይልቅ የእውነት ስብስቦች ናቸው። ቢሆንም፣ ከእነዚህ ብዙ እውነቶች መካከል አንዳንድ ተመሳሳይ ጭብጦች አሉ። ለምሳሌ፣ስለ እግዚአብሔር ምን እማራለሁ? የሚሉ ጥያቄዎች በአዕምሮአችሁ በመያዝ ክፍሎች 130–131ን ማንበብ ትችላላችሁ። ከሟች ህይወት በኋላ ስላለው ሕይወት ምን እማራለሁ? ይህ እውቀት በሕይወቴ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?
በተጨማሪም “እሱ ሲናገር በመስማት ልባችን ተደሰተ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 277–80 ይመልከቱ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 131፥1–4፤ 132፥7፣ 13–25
የሰማይ አባት ቤተሰቦች ዘላለማዊ እንዲሆኑ አስችሏል።
በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል በዳግም ከተመለሱት በጣም የሚያፅናኑ እውነቶች አንዱ ጋብቻ እና የቤተሰብ ግንኙነቶች ለዘለአለም ሊቆዩ እንደሚችሉ ነው። በጆሴፍ ስሚዝ በኩል ጌታ እነዚህን ግንኙነቶች ዘለአለማዊ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑትን ስነስርዓቶች እና ሀይልን በዳግም መልሷል (ይመልከቱ፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥7፣ 18–19)። እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 131፥1–4፣ 132፥7፣ 13–15ን በምታነቡበት ጊዜ ስላላችሁ ወይም ለወደፊቱ እንዲኖራችሁ ተስፋ ስለምታደርጉት የቤተሰብ ግንኙነቶች አስቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እነዚህ ግንኙነቶች ባላችሁ አስተያየት ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ?
ይህም ቢሆን፣ አንዳንድ ጊዜ፣ የዘለአለማዊ ቤተሰቦች መሰረታዊ መርህ በጣም የሚያጽናና አይደለም—በተለይ አሁን ያለን የቤተሰብ ሁኔታችን ከሰለስቲያል የኑሮ ሁኔታ ጋር የማይስማማ ከሆነ፣ ጭንቀትን፣ እንዲሁም ሀዘንን እንኳን ያመጣም ይሆናል። ፕሬዘደንት ሄነሪ ቢ. አይሪንግ በቤተሰባቸው ውስጥ ስላለው ስለዚህ ጉዳይ ሲጨነቁ፣ የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ምልዓተ ጉባኤ አባል ከሆኑት ይህን ጥበብ ያዘለ ምክር ተቀበሉ፥ “እናንተ ለሰለስቲያል መንግስት ብቁ በመሆን ብቻ ኑሩ፣ እናም የቤተሰብ አደረጃጀታችሁ ከምትገምቱት በላይ አስደሳች ይሆናል” (“የጌታ መንፈስ የሚኖርበት ቤት፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 25)። በቤተሰባችሁ ሁኔታ ውስጥ ይህንን ምክር መከተል እንዴት ሊባርካችሁ ይችላል?
ደግሞም ክሪስቲን ኤም. ኦክስ፣ “ላላገቡ የቤተክርስቲያን አባላት” [የቤተክርስቲያኗ ለወጣቶች የተዘጋጀ የትምህርት ሥርዓት ጉባኤ፣ መስከረም 11 ቀን 2011 (እ.አ.አ)] broadcasts.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥1–2፣ 29–40
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው እሱ ሲያዝ ብቻ ነው።
ብሉይ ኪዳንን ያነበበ ማንም ሰው በርካታ ሚስቶችን ስላገቡት ስለ አብርሐም፣ ስለ ይስሐቅ፣ ስለ ያዕቆብ፣ ስለ ሙሴ እና ሌሎችም ይደነቁም ይሆናል። እነዚህ መልካም ሰዎች እያመነዘሩ ነበርን? ወይም እግዚአብሔር ድርጊታቸውን ፈቅዶ ነበርን? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥1–2፣ 29–40 ውስጥ መልሶችን ፈልጉ።
በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ያለው ጋብቻ የእግዚአብሔር የጋብቻ መስፈርት ነው (አስተዳደሪያዊ አዋጅ 1 የመግቢያ ክፍልን ይመልከቱ፤ በተጨማሪም ያዕቆብ 2፥27፣ 30ን ይመልከቱ)። ሆኖም፣ በታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር ልጆቹን ከአንድ በላይ ሚስት እንዲያገቡ ያዘዘበት ጊዜያት አሉ።
በዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያን የመጀመሪያዎቹ ዓመታትም ለየት ካሉት ጊዜያት አንዱ ነበሩ። ይህን ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ከአንድ በላይ ሚስቶችን አገቡ። በቀደሙት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መካከል ስለነበረው ከአንድ በላይ ሚስት የማግባት ልምምድ የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ፣ የሚቀጥሉትን ይመልከቱ፥ “ሜርሲ ቶምፕሰን እና ስለ ጋብቻ መገለጥ” (ራዕያት በአገባብ፣ 281–93)፤ ቅዱሳን፣ 1፥290–92፣ 432–35፣ 482–92፣ 502–4፤ “በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት” (የወንጌል ርዕሶች፣ topics.ChurchofJesusChrist.org)፤ “ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች ከአንድ በላይ ሚስት የማግባት ልምምድ ለምን አስፈላጊ ነበር?” (ቪዲዮ፣ ChurchofJesusChrist.org)።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥2፣ 18–19፤ 132፥13፣ 19።እነዚህን ጥቅሶች ቤተሰባችሁ ለዘለአለም የሚቀጥሉትን ነገሮች ቅድሚያ እንዲሰጥ ለማገዝ እንዴት ልትቀሙባቸው ትችላላችሁ? ምናልባት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥2፣ 18–19፤ 132፥19 መሰረት፣ ለምሳሌ እንደ ቤተሰብ ፎቶዎች ወይም ቅዱሳት መጻህፍት አይነት፣ ወደሚቀጥለው ህይወት ይዘነው ልንሄድ የምንችላቸውን የሚወክሉ ነገሮችን በሻንጣዎችን ወይም የጀርባ ቦርሳዎችን ለማሸግ ትችላላችሁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥13 ስለ ዓለም ነገሮች ምን ያስተምረናል? ይህ ዘላለማዊ ጠቀሜታ ባላቸው ነገሮች ላይ ስለማተኮር ወደ ውይይት ሊያመራ ይችላል።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥20፟–21።ስለ ምስጋና መዝሙር፣ ለምሳሌ “በረከትን ቁጠሩ” (መዝሙር፣ ቁጥር 241) መዘመር ትችላላችሁ፣ እና ቤተሰባችሁ የእግዚአብሔርን ህግጋት በማክበር የተቀበሏቸውን በረከቶች ዝርዝር ፃፉ። ምን በረከቶች እናገኛለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን? እነዚያን በረከቶች እንዴት ማግኘት እንችላለን?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 131፥1–4፤ 132፥15፣19።“ጋብቻ የተቀደሰ ነው” የሚለው ቪዲዮ (ChurchofJesusChrist.org) ቤተሰባችሁ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉትን እውነቶች እንዲወያዩ ሊረዳ ይችላል። ጌታ ስለ ትዳር ምን ይሰማዋል? ያገባንም ሆንንም ያላገባን፣ ዘለዓለማዊ ጋብቻ ለመያዝ እንዴት እንዘጋጃለን?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ “ቤተሰቦች ለዘላለም አብረው ሊሆኑ ይችላሉ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 188።