ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
መስከረም 6–12 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98–101፥ “ዕረፉ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ”


“መስከረም 6–12 (እ.አ.አ) ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98–101፥ ‘ዕረፉ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“መስከረም 6–12 (እ.አ.አ) ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98–101፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ቅዱሳን ከአመጸኞች ለማምለጥ ሲሮጡ

ሲ.ሲ.ኤ. ክሪስቸንሰን [1831–1912 (እ.አ.አ)]፣ ቅዱሳን ከጃክሰን ካውንቲ ሚዙሪ ተባረሩ፣ በ1878 (እ.አ.አ) አካባቢ፣ tempera on muslin,196.2 × 287.02 ሴንቲ ሜትር።. ብሪንግሀም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የሥነጥበብ ሙዚየም፣ የ ሲ. ሲ. ኤ. ክሪስቸንሰን የልጅ ልጆች ስጦታ፣ 1970 (እ.አ.አ)

መስከረም 6–12 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98–101

“ዕረፉ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ”

እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98–101ን ስታነቡ፣ ለሚመጡባችሁ ሀሳቦች እና ግንዛቤዎች ትኩረት ስጡ። በእነሱ ላይ እርምጃ መውሰዳችሁ እግዚአብሔር ልትሆኑ የሚፈልገውን ሰው መሆን እንድትችሉ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በ1830ዎቹ (እ.አ.አ) ለነበሩት ቅዱሳን፣ ኢንዲፐንደንስ፣ ሚዙሪ፣ ቃል በቃል የተስፋ ቃል ምድር ነበር። ይህም የፅዮን “አማካዩ ቦታ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 57፥ 3ን ይመልከቱ)፣ ለመገንባት ታላቅ መስዋእትነትን የከፈሉበት በምድር የእግዚአብሔር ከተማ ነበር። ለእነርሱ፣ የቅዱሳን በዚያ መሰብሰብ ወደ ዳግም ምፅአቱ የሚመራ አስደሳች እና ታላቅ ቅድመ–ሁኔታ ነበር። በአካባቢው ያሉ ጎረቤቶቻቸው ግን ነገሮችን በተለየ መንገድ አይተውታል። እግዚአብሔር ምድሪቱን ለቅዱሳን ሰጣቸው በሚለው ተናደዱ፣ እና ከማያውቁት ሃይማኖት ወደ አካባቢው በፍጥነት ብዙ ሰዎች በመምጣታቸው የተነሳ በሚኖረው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ውጤቶች ምቾት አልነበራቸውም። ብዙም ሳይቆይ አሳሳቢ ጉዳዮች ወደ ማስፈራሪያዎች ተለወጡ፣ ማስፈራሪያዎችም ወደ ስደት እና አመፅ ተለወጡ። በሐምሌ 1833 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያኗ ማተሚያ ቤት ወደመ፣ ከዚያም በህዳር ቅዱሳን በጃክሰን ካውንቲ፣ ሚዙሪ ውስጥ ያሉትንው ቤቶቻቸውን ለመተው ተገደዋል።

ጆሴፍ ስሚዝ ከ800 ማይል በላይ ርቀት በነበረው በከርትላንድ ውስጥ ነበር ፣ እናም ይህ ዜና እሱ ጋር ለመድረስ ሳምንታትን ወስዶ ነበር። ነገር ግን ጌታ ምን እየሆነ እንዳለ ያውቅ ነበር፣ እናም ቅዱሳንን የሚያጽናኑ የሰላም እና የማበረታቻ መሰረታዊ መርሆዎችን፣ እንዲሁም ስደት በሚያጋጥመን ጊዜ፣​የጽድቅ ፍላጎታችን ሳይፈጸም በሚቀሩበት ጊዜ፣ ወይም የዕለት ተዕለት መከራችን ውሎ አድሮ በሆነ መንገድ “ለመልካም ነገር አብረው እንደሚሠሩ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥3) ማስታወሻ በሚያስፈልገን ጊዜ የሚረዱ መርሆችን ለነቢዩ ገልጦለታል።

ቅዱሳን፣ 1፥171–93፤ “የጌታን ቃል መጠበቅ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 196–201 ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥1–3፣ 11–14101፥1–16

ፈተናዎቼ ለእኔ ጥቅም አብረው ሊሠሩ ይችላሉ።

በሕይወታችን ውስጥ አንዳንድ መከራዎች የሚከሰቱት በራሳችን ምርጫዎች ምክንያት ነው። ሌሎቹ ደግሞ የሚከሰቱት በሌሎች ምርጫዎች ነው። እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ማንም ተጠያቂ አይሆንም—መጥፎ ነገሮች ዝምብለው ያጋጥማሉና። ምክንያቱ ምንም ቢሆን፣ መከራ መለኮታዊ ዓላማዎችን ለመፈፀም ሊረዳ ይችላል። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥1–3፣ 11–14 እና 101፥1–16 ውስጥ ጌታ ስለቅዱሳን ችግር የተናገረውን ስታነቡ፣ በፈተናዎቻችሁ ውስጥ ምን ሊረዳችሁ የሚችል ነገር አገኛችሁ? እነዚህ ጥቅሶች የሚያጋጥሟችሁን ፈተናዎች በምትመለከቱበት መንገድ ላይ እንዴት ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ? ፈተናዎቻችሁ ለእናንተ ጥቅም እንዴት አብረው እንደሠሩ እና በህይወታችሁ ውስጥ የእግዚአብሔርን ዓላማዎች እንዴት እንዳሟሉ አሰላስሉ።

በተጨማሪም 2 ኔፊ 2፥2ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥24

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥23–48 ይመልከቱ።

ጌታ በእሱ መንገድ ሰላምን እንድፈልግ ይፈልጋል።

ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 98፥23–48 ውስጥ ያለው ሁሉም ነገር ከሌሎች ጋር ባላችሁ የግል ግንኙነቶች ላይ ተፈፃሚ ባይሆኑም፣ በሌሎች ስትበደሉ ሊመሯችሁ የሚችሉ ምን መሠረታዊ ሥርዓቶችን አግኝታችኋል? ቅዱሳኑ በሚዙሪ ውስጥ ያለውን ግጭት እንዲፈቱ ጌታ እንዴት እንደፈለገ የሚገልጹ ቃላትን ወይም ሀረጎችን ምልክት ማድረጉ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

በተጨማሪም ጄፍሪ አር ሆላንድ፣ “የማስታረቅ አገልግሎት፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 77–79 ይመልከቱ።

ኢየሱስ ክርስቶስ

ማብራሪያ ከክርስቶስ እና ሀብታም ወጣት ገዢ በሄንሪክ ሆፍማን

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 100

ጌታ እርሱን የሚያገለግሉትን ይንከባከባል።

ጆሴፍ በሚዙሪ ስለደረሰው ስደት ከተረዳ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ፣ አንድ አዲስ በቅርብ የተቀየረ ሰው ለልጆቹ ወንጌልን ለማካፈል ወደ ካናዳ አብሮት እንዲሄድ ጠየቀው። በተለይም በቤተሰቡ እና በቤተክርስቲያኗ ላይ በነበረው ስደት እና ማስፈራሪያ ምክንያት ቤተሰቡን ትቶ ለመሄድ ቢጨነቅም፣ ጆሴፍ ተስማማ። ወደ ካናዳ ሲጓዙ፣ ጆሴፍ እና ባልደረባው ሲድኒ ሪግደን መጽናናትን ለማግኘት ጸለዩ፣ እና ጌታ ለእነርሱ የሰጠው መልስም ክፍል 100 ነበር። በጌታ ምላሽ ውስጥ አረጋጋጭ እና ረጂ የሚሆንላችውን ምን አግኝታችኋል?

ምናልባት ለቤተክርስቲያኗ ኃላፊነቶች እና ለቤተሰባችሁ አሳቢነት ሚዛን እንድትጠብቁ የሚያስፈልጓችሁ ተሞክሮዎች አጋጥመዋችሁ ይሆናል። በክፍል 100 ውስጥ ያሉት የጌታ ቃላት እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት ሊረዷችሁ ይችላሉ?

በተጨማሪም “ወደ ካናዳ ተልእኮ፣” ራዕያት በአገባብ 202–7ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥43–65

የእግዚአብሔር ምክር መከተል ደህና እንድሆን ይረዳኛል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥43–62 ውስጥ ያለው የምሳሌ ተረት ጌታ ቅዱሳንን ከፅዮን እንዲባረሩ ለምን እንደፈቀደ ለማብራራት የተሰጠ ነበር። እነዚህን ጥቅሶች በምታነቡበት ጊዜ፣​በምሳሌው ውስጥ በሚገኙት አገልጋዮች እና በእናንተ መካከል ተመሳሳይነትን ታያላችሁ? እራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ፥ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እጠራጠራለሁን? እምነት ወይም ቁርጠኝነት አለመኖር “ጠላት” በሕይወቴ ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድር እንዴት ሊፈቅድ ይችላል? “በትክክል እና በተገቢ መንገድ ወደ [ደህንነቴ] ለመመራት እንደምፈልግ” እግዚአብሔርን እንዴት ማሳየት እችላለሁ? (ቁጥሮች 63–65 ይመልከቱ)።

የቤተሰብ ጥናት ምልክቶች

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥16፣ 39–40ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በቤተሰባችን ውስጥ የበለጠ ሰላም እንዲኖር ምን ሊረዳን ይችላል? ለምሳሌ “እውነት በአስተሳሰባችን ላይ ይንፀባርቃል” (መዝሙር ቁጥር 273) የሚሉ ስለ ሰላም ወይም ይቅር ባይነት የሚያወሩ መዝሙሮችን መዘመር ትችላላችሁ። ትናንሽ ልጆች እርስ በእርስ ይቅር ስለመባባል መተወን ሊወዱት ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 99ጆን ሙርዶክ ቤቱን ለቅቆ ሲወጣ “ዘላለማዊውን ወንጌል ለማወጅ” (ቁጥር 1)፣ ሚዙሪ ውስጥ ካለ አስቸጋሪ የአንድ አመት ሚሽን ገና መመለሱ (“የጆን መርዶክ ወደ ሚዙሪ የሄደበት የሚስዮን አገልግሎትን ተመልከቱ፣” ራዕይ በአገባብ 87–89)። በክፍል 99 ውስጥ ለወንድም መርዶክ ጠቃሚና አበረታች ሊሆን የሚችል ምን አግኝተናል? በዚህ ራዕይ ውስጥ ጌታ ለእኛ ምን መልእክት አለው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 100፥16101፥3–5፣ 18እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ፣ አንጥረኞች የብረትን ግድፈት ለማስወገድ በታላቅ ሙቀት እንደሚያቀልጡት እና ከዚያም ቅርጽ እስኪይዝ ድረስ ደጋግመው እንደሚቀጠቅጡትት መወያየት ትችላላችሁ። (“የአጣሪው እሳት” የሚለውን ቪዲዮን በChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ)። እንዲሁም እንደ ውሃ ወይም ጨው ያሉ ሌሎች ነገሮች እንዴት እንደሚጣሩ አብራችሁ መማር ትችላላችሁ። ምናልባት እንደ ቤተሰብ አንድ ነገርን ማጣራት ወይም ማፅዳት ትችሉ ይሆናል። ንጹህ መሆን የምንፈልገው ለምንድን ነው? የሚደርሱብን ፈተናዎች “ንጹሕ ሕዝብ” እንድንሆን እንደሚረዱን እነዚህ ምሳሌዎች እንዴት ያስተምሩናል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥22–36እነዚህ ጥቅሶች ስደት ያጋጠሟቸውን ቅዱሳን እንዴት ረድተዋቸው ሊሆን ይችላል? በአሁኑ ጊዜ ስላለው የዓለም ሁኔታ ፍርሃት የሚሰማቸውን ሰዎች እንዴት መርዳት ይችላሉ?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ውድ አባቴ፣ እርዳኝ፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 99።

የግል ጥናትን ማሻሻል

መርሆዎችን መፈለግ። ሽማግሌ ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ. ስኮት እንዳስተማሩት፣ “መንፈሳዊ ዕውቀት ስትፈልጉ፣ መሰረታዊ መርሆችንም ፈልጉ። … በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ተግባራዊ ለመሆን የታሸጉ መርሆዎች የእውነት ክምችት ናቸው” [“መንፈሳዊ ዕውቀትን ማግኘት፣” ኤንዛይን ህዳር 1993 (እ.አ.አ)፣ 86]።

አመጸኞች ቅዱሳንን ሲያሳድዱ

ምዙሪ እየተቃጠለ፣ በግሌን ኤስ. ሆፕኪንሰን