ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 30–መስከረም 5 (እ.አ.አ)። ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 94–97፥ “ለፅዮን ደህንነት”


“ነሐሴ 30–መስከረም 5 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94–97፥ ‘ለፅዮን ደህንነት፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 30–መስከረም 5 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94–97” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
የከርትላንድ ቤተመቅደስ

ከርትላንድ ቤተመቅደስ በአል ራውንድስ

ነሐሴ 30–መስከረም 5 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94–97

“ለፅዮን ደህንነት”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94–97ን በምታጠኑበት ጊዜ ምን መርሆዎች እና ትምህርቶች ለእናንተ ጎልተው ታዩአችሁ? ያሳደረባችሁን ስሜት መመዝገባችሁን እርግጠኛ ሁኑ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ጌታ ማደሪያውን እንዲሠራ ሙሴን ባዘዘው ጊዜ፣ እርሱም “በተራራው እንደ ተገለጠለት ምሳሌ ሁሉን እንዲያደርግ ለሙሴ ነግሮት ነበር” (ዕብራዊያን 8፥5፤ ደግሞም ዘፀአት 25፥8–9 ይመልከቱ)። የማደሪያው ድንኳንም የእስራኤል ምድረበዳ ሰፈር ማዕከል ሊሆን ነበር (ዘኁልቁ 2፥1–2)። በኋላም፣ ሰለሞን እና ህዝቡ እርሱ በገለጠው ንድፍ መሰረት ቤተመቅደስ እንዲሠሩ እግዚአብሔር አዘዛቸው (ይመልከቱ፥ 1 ዜና መዋዕል 28፥12፣ 19)።

ጌታ የወንጌሉን ሙላት ዳግም ሲመልስም፣ በተገለጠው ንድፍ መሠረት ቤተመቅደሶችን እንዲገነባ ጆሴፍ ስሚዝን አዘዘው። ጌታም “በአለም በሚሰሩበት ሳይሆንም፣ ቤት ይሰራ” በማለት አወጀ። “በማሳያችሁ ስርዓት ይሰራ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥13–14፤ እንዲሁም 97፥10ን ይመልከቱ)። እንደ ምድረበዳው ማደሪያው ድንኳን፣ ቤተመቅደሱ በከርትላንድ ውስጥ ማዕከላዊ ገፅታ ሆኖ እንዲያገለግል ታስቦ ነበር (ይመልከቱ፥ ትምህርት እና ቃልኪዳን 94፥1)።

ዛሬ የጌታ ቤቶች በዓለም ዙሪያ ይገኛሉ። ምንም እንኳን በከተሞቻችን መሃል ባይሆኑም፣ በሕይወታችን ውስጥ ማዕከላዊ መሆን ይችላሉ። እያንዳንዱ ቤተመቅደስ በመልክ የሚለያይ ቢሆንም፣ በውስጣቸው ተመሳሳይ መለኮታዊ ንድፎችን እንማራለን—እኛን ወደ እግዚአብሔር ፊት የሚመልስ ሰማያዊ እቅድ። የተቀደሱ፣ ዘላለማዊ ስርዓቶች ህይወታችንን እንድንገነባ እና ቤተሰቦቻችንን “አለም በሚሰሩት ሳይሆን” እግዚአብሔር በሚያሳየን ንድፍ ለማጠናከር ይረዳናል።

ቅዱሳን፣ 1፥169–70፤ “ለአምላካችን የሚሆን ቤት፣” ራዕይ በአገባብ፣ 165–73 ይመልከቱ፥።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 9497፥15–17

በዕለት ተዕለት ሕይወቴ ጌታ ከእኔ ጋር ሊሆን ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94 እና97 ውስጥ ያሉት መመሪያዎች የተሰጡት በአንድ ቀን ነው—በነሀሴ 2፣ 1833 (እ.አ.አ)። ክፍል 97 በከፊል በጃክሰን ካውንቲ፣ ሚዙሪ ስለ ታቀደው ቤተመቅደስ ያወራል፤ ክፍል 94 ደግሞ ስለከርትላንድ፣ ኦሃዮ አስተዳደራዊ ህንፃዎች ይናገራል። ስለ እነዚህ የተለያዩ ህንጻዎች ጌታ በሚለው ውስጥ አንዳንድ ተመሳሳይነቶችን አስተውላችሁ ይሆናል (ይመልከቱ፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94፥2–1297፥10–17)። እነዚህን መመሪያዎች በምታሰላስሉበት ጊዜ፣ በቤተክርስቲያን ህንፃዎች ውስጥ እና በዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ ውስጥ​​የጌታን ክብር እና መገኘት ብዙ ጊዜ ለመለማመድ ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቡበት።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95

ጌታ የሚወዳቸውን ይቀጣል።

ከጥር 1833 (እ.አ.አ) አምስት ወራት ካለፉ በኋላ፣ ጌታ ለከርትላንድ ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲሠሩ እና ትልቅ ስብሰባ እንዲያካሂዱ አዘዛቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥117–19 ይመልከቱ)። በክፍል 95 ውስጥ የተመዘገበው ራዕይ በሰኔ 1833 (እ.አ.አ) ሲቀበሉ፣ ያንን ትእዛዝ ገና ተግባራዊ አላደረጉትም ነበር። በዚህ ራዕይ ውስጥ ጌታ ቅዱሳንን ከገሰጸበት መንገድ ምን ትማራላችሁ? ገና እርምጃ ያልወሰዳችሁባቸው ትእዛዛት ወይም የምክር ቃላት አሉ? ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል?

በተጨማሪም ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻለሁ እና እቀጣለሁ፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 97–100 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥8፣ 11–1797፥10–17

በቤተመቅደስ ውስጥ እግዚአብሔር ህዝቡን ይባርካል።

በከርትላንድ የጌታን ቤት ባለመገንባታቸው ከተገሰጹ በኋላ፣ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች የስንዴ እርሻ ላይ የሚገነቡበትን ስፍራ መረጡ። የነቢዩ ወንድም ኃይረም ስሚዝ ወዲያውኑ ረጅም ማጭድ ለማግኘት እና እርሻውን ማጽዳት ለመጀመር ሮጠ። “የጌታን ቤት ለመገንባት በዝግጅት ላይ ነን፣ እና እኔ በሥራው የመጀመሪያ ለመሆን ቆርጫለሁ” አለ (በየቤተክርስትያኗ ፕሬዘዳንቶች ትምህርቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ [2007 (እ.አ.አ)] 271፣ 273)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥8፣ 11–1797፥10–17ን ስታነቡ የኃይረምን ጉጉት አሰላስሉ። የቤተመቅደስን በረከቶች ለመቀበል በእናንተ ውስጥ ተመሳሳይ ውሳኔን የሚያነቃቃ ምን ግፊት አገኛችሁ?

ምስል
ኃይረም ስሚዝ ረጅሙን ማጭድ ይዞ

ኃይረም ስሚዝ እርሻን ሲያጸዳ በጆሴፍ ብሪኪ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥18–28

ፅዮን “ልበ ንጹህ” ናት።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳስተማረው፣ “የፅዮንን ግንባታ እንደ ታላቅ አላማችን ልንይዘው ይገባል” (ትምህርቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ፣ 186)። በ1830 (እ.አ.አ) ለነበሩት ለቅዱሳን፣ ፅዮን ቃል በቃል “የአምላካችን ከተማ” ነበረች (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥19)። ነገር ግን በ ክፍል 97ውስጥ በተመዘገበው ራዕይ ውስጥ ጌታ ያንን እይታ አሰፋ። ፅዮን በተጨማሪ “ንፁህ ልብ” ያለውን ሕዝብ ትገልጻለች (ቁጥር 21)። እናንተም በ ቁጥር 18–28፣ “ፅዮን” የሚለውን ቃል ስታነቡ ስለዚህ ትርጉም አስቡ። ለእናንተ በልብ ንጹህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ቤተመቅደስ “የፅዮንን መዳን” ለማከናወን የሚረዳው እንዴት ነው? (ቁጥር 12)።

በተጨማሪም ሙሴ 7፥18፣ የወንጌል ርዕሶች፣ “ጽዮን፣” topics.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክቶች

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥8የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን መጠበቅ እና ማክበር “ከላይ መንፈሳዊ ስጦታ” ወደ ህይወታችን ያመጣትእንዴት ነው? ምናልባት የቤተሰብ አባላት ስለ ቤተመቅደስ ምን እንደሚሰማቸው ሊያካፍሉ ወይም በቤተመቅደስ አምልኮ ጊዜ “ከበላይ መንፈሳዊ ስጦታ” የተባረኩበትን አጋጣሚ ሊያካፍሉ ይችላሉ።

ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት በዝግጅት ላይ ያሉ ሰዎችን ለመርዳት፣ በtemples.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ የሚገኙትን ቪዲዮዎች፣ ፎቶግራፎች፣ እና መመሪያዎች መከለስ ትችላላችሁ። ልጆች ስለ ቤተመቅደስ እንዲማሩ ለመርዳት፣ ”ወደ ቤተመቅደስ የሚወስደው መንገድን” መጠቀም ትችላላችሁ (በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቤተመቅደሶች [የኢንዛይን ወይም ሊያሆና ልዩ እትም፣ ጥቅምት 2010 (እ.አ.አ)]፣ 72–75)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥1–11ከእነዚህ ጥቅሶች ስለመገሰጽ ምን እንማራለን? ስለጌታ ምን እንማራለን? እነዚህ እይታዎች ተግሳጽን በምንቀበልበት ወይም ሌሎችን በምንገስጽበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩትእንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥8በዚህ ጥቅስ መሠረት፣ በጌታ “ተቀባይነት ማግኘት” የምንችለው እንዴት ነው? ይህ በዓለም ተቀባይነት ከማግኘት ጋር የሚለየው እንዴት ነው? “[ቃል ኪዳናችንን] በመሥዋዕት … ለመከተል” ሲባል ምን ማለት ነው? ይህንን ያደረግነው እንዴት ነው ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥10–21ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ ብሎ አስተምሯል፥ “ቅዱሳን የሚሰበሰቡበት ቦታ ሁሉ ጽዮን ይባላል፣ ይህም እያንዳንዱ ጻድቅ ወንድ [ወይም ሴት] ሁሉ ለልጁ [ወይም ለልጇ] የሚገነባው [የምትገነባው] የደህንነት ቦታ ነው” (ትምህርቶች፣ ጆሴፍ ስሚዝ፣ 186)። ፅዮንን በቤታችን እንዴት መገንባት እንችላለን? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥10–21 ውስጥ ምን መሠረታዊ ሥርዓቶችን እናገኛለን? እንደ ቤተሰብ፣ በዚህ ሳምንት የሚተኮርበት መሰረታዊ መመሪያ ምረጡ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፥ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 95።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ። በምትማሯቸው መሰረታዊ መርሆች እና ትምህርቶች ያላችሁን ልምምዶች መዝግቡ። እነዚህ ልምዶች የወደፊት ትውልዶችን የሚባርኩ የግል ታሪክ አካል ሊሆኑ ይችላሉ።

ምስል
የከርትላንድ ቤተመቅደስ ግንባታ

የከርትላንድ ቤተመቅደስን መገንባት፣ በዋልተር ሬን

አትም