“ነሐሴ 23–29 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥ ‘የእርሱን ሙላት መቀበል’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) 2020 (እ.አ.አ)
“ነሐሴ 23–29 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ 2021 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 23–29 (እ.አ.አ)።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93
“የእርሱን ሙላት መቀበል”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93 “እውነት ነገሮች እንዳሉ፣ እንደነበሩ፣ እናም ወደፊት እንደሚሆኑት የሚታወቅበት እውቀት ነው” ሲል ያስተምራል (ቁጥር 24)። ይህንን ክፍል ስታጠኑ፣ እውነትን ፈልጉ እና የተማራችሁትን መዝግቡ። እውነትን ለመቀበል ምን ለማድረግ ፈቃደኛ ናችሁ? (ቁጥሮች 27–28 ይመልከቱ)።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ጆሴፍ ስሚዝ ፣ “መሰላል ላይ ስትወጡ፣ ወደ ላይ እስክትደርሱ ድረስ ከስሩ መጀመር እና ደረጃ በደረጃ መውጣት አለባችሁ፤ እና በወንጌል መሰረታዊ መርሆዎችም እንዲሁ ነው— ከመጀመሪያው ጀምሮ መጀመር እና ስለ ዘለአለማዊ ክብር እስክትማሩ ድረስ መቀጠል አለባችሁ” ሲል አስተምሯል (Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [2007 (እ.አ.አ)] 268)።
አንዳንድ ጊዜ ያ የዘለአለማዊ ክብር መሰላል ከሚገባው በላይ ከፍ ያለ መስሎ ሊታየን ይችላል፣ ግን እኛ የተወለድነው ወደ ላይኛው ጫፍ ለመውጣት ነው። ምንም ዓይነት ገደቦች በራሳችን ላይ ብናይም፣ የሰማይ አባት እና ልጁ በእኛ ውስጥ ታላቅነገርን ያያሉ፣ እንደ አምላክ ያለ ነገር። ልክ ኢየሱስ ክርስቶስ “በመጀመሪያ ከአብ ጋር እንደነበረ፣” ስለዚህ “ እናንተም እንዲሁ ነበራችሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥21፣ 23)። ልክ እርሱ “ሙላትን እስከሚቀበል ድረስ ከጸጋ ወደ ጸጋ” እንደ ቀጠለ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ “እናንተም በጸጋ ላይ ጸጋ ትቀበላላችሁ” (ቁጥሮች 13፣ 20)። ዳግም የተመለሰው ወንጌል ስለ እግዚአብሔር እውነተኛ ተፈጥሮ ያስተምረናል፣ እናም ስለራሳችን እና መሆን ስለምንችለው ያስተምረናል። ‘የክፉው’ ጥረት ቢኖርም (ቁጥር 39)—ምንም እንኳን የሚጎድላችሁ ነገር ቢሰማችሁም—“በጊዜው ሙላቱን [ለመቀበል]” (ቁጥር 19) የሚያስችል ብቃት ያላችሁ ቃል በቃል የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ።
ለግል ቅዱሳት መጻፍት ጥናት ሃሳቦች
እግዚአብሔር አብን እና ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እናመልካለን።
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93 ውስጥ ስላለው ራዕይ ጌታ ሲያብራራ፣ “እነዚህን አባባል የምሰጣችሁ እንዴት እንደምታመልኩ እንድትረዱ እና እንድታውቁ፣ እንዲሁም ምን እንደምታመልኩ እንድታውቁ፣ በስሜ ወደ አብ እንድትመጡ፣ እና በጊዜም ሙላትን ትቀበሉ ዘንድ ነው” (ቁጥር 19)። ይህንን ራዕይ ስታጠኑ፣ ስለምናመልካቸው አካላት፣ ስለ እግዚአብሔር አብ እና ስለ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ያገኛችሁትን እውነት ምልክት አድርጉባቸው። እነርሱ “እንዴት እንደሚመለኩ” በተመለከተ ምን እንማራለን? “ወደ አብ እንዴት መምጣት” እንዳለብንስ?
ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ፣ “ሰዎች የእግዚአብሔርን ባህርይ ካልተረዱ እራሳቸውን አይረዱም” ሲል አስተምሯል (ትምህርቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ፣ 40)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93ን በማጥናት ስለ አዳኝ ስትማሩ፣ ስለራሳችሁም ምን እንደምትማሩ ተመልከቱ። ለምሳሌ፣ በቁጥሮች 3፣ 12፣ 21 እና 26 ስለ እርሱ ምን ተማራችሁ? በቁጥሮች 20፣ 23 እና 28–29 ስለራሳችሁ ምን ተመሳሳይ እውነታዎችን አገኛችሁ? (በተጨማሪም 1 ዮሐንስ 3፥2፤ 3 ኔፊ 27፥27፤ ዲን ኤም. ዴቪስ “የአምልኮ በረከቶች፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 93–96 ይመልከቱ።)
የእግዚአብሔር ክብር ብርሀንና እውነት ነው።
በዚህ ራዕይ ውስጥ ክብር፣ ብርሃን እና እውነት ተደጋግመው እንደታዩ አስተውላችሁ ይሆናል። በተለይም ቁጥሮች 21–39 በምታጠኑበት ጊዜ፣ በተለይ ስለ ክብር፣ ብርሃን፣ እና እውነት የምትማሯቸውን እውነቶች ዝርዝር ጻፉ። እነዚህ እውነቶች የበለጠ ብርሃን እና እውነት እንድትፈልጉ እንዴት ያበረታቷችኋል? እነዚህ እውነቶች በዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ አሳድረዋል?
“ቤትህን በስርዓት አደራጅ።”
በቁጥር 40 አካባቢ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93 ከእግዚአብሔር ክብር እና መለኮታዊ ችሎታችን አስተምህሮቶች ወደ ልጆች አስተዳደግ እና ቤቶቻችንን በስርዓት ስለማደራጀት ትምህርት የተሻገረ ይመስላል። በቁጥሮች 1–39 ውስጥ ስለብርሃን፣ ስለ እውነት እና ክብር ያለው የጌታ ትምህርቶች እንዴት በቁጥሮች 40–50 ያለውን ምክር እንድትረዱ እና እንድትከተሉ ይረዳችኋል።
በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “በቤት ውስጥ የበለጠ ታጋሽ እና አሳቢ መሆን፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2009፣ (እ.አ.አ) 17–20 ይመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥2።ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወታችን ውስጥ “የእውነት ብርሃን” የሆነው እንዴት ነው? የእርሱ ብርሃን በአካባቢያችሁ ባሉ ሌሎች ሰዎች ውስጥ እንዴት አያችሁት?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥3–29።ቤተሰቦቻችሁ በ ክፍል 93 ውስጥ ስለ አዳኝ እና ስለራሳቸው ስለሚማሩት ነገር እንዲወያዩ ለማገዝ፣ የማዛመድ ጨዋታ መጫወት ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ በክፍል 93 ላይ ያሉትን ስለ አዳኛችን እውነቶችን የሚያስተምሩ ቁጥሮችን (ቁጥሮች 3፣ 12፣ 21፣ 26ን ይመልከቱ) በአንዱ፣ እና ስለራሳችን ተመሳሳይ ነገር የሚያስተምር ቁጥሮች (ቁጥሮች 20፣ 23፣ 28–29ን ይመልከቱ) በሌላ በካርድ ስብስብ ማዘጋጀት ትችላላችሁ። የቤተሰብ አባላት በየተራ ከእያንዳንዱ ስብስብ አንድ ካርድ በመውሰድ፣ ጥቅሶችን በማንበብ፣ እና የሚዛመዱ እውነቶችን ለማግኘት መሞከር ይችላሉ። እነዚህ እውነቶች ስለ አዳኝ እና ስለ ራሳችን በሚኖረን ስሜት ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ያሳድራሉ?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥12–13፣ 20።“ጸጋ በጸጋ” መቀበል እና “ከጸጋ ወደ ጸጋ” መቀጠል ምን ማለት ነው? (ቁጥሮች 12–13)። እነዚህ ቁጥሮች እንዴት ስለኛ ማደጊያ እና መማሪያ መንገዶች ምን ጥቆማዎችን ይሰጣሉ? ይህንን ማወቃችን ሌሎችን እና ራሳችንን በምንንከባከብበት ላይ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድራል?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥24።በዚህ ቁጥር ውስጥ የሚገኘውን የእውነትን ትርጉም አንብቡ፣ እና ከክፍል 93 እነርሱ ታላቅ ዋጋ እንዳለው የሚመለከቱትን እውነት እንዲያጋሩ የቤተሰብ አባላትን ጋብዙ። በዮሐንስ 14፥6፤ ያዕቆብ 4፥13፣ ወይም “አቤቱ በል፣ እውነት ምንድን ነው?” በሚለው አይነት የእውነት መዝሙር ውስጥ ስለእውነት ምን ሌላ ትርጓሜዎችን እናገኛለን? (መዝሙር፣ ቁጥር 272)።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥40።ምናልባትም ይህንን ጥቅስ ስታነቡ፣ ቤተሰቦቻችሁ በቤት ውስጥ ስለ መማር፣ “በብርሃን እንድራመድ አስተምረኝ” የሚለውን መዝሙር ልትዘምሩ ትችሉ ይሆናል (የልጆች መዝሙር መፅሐፍ 177)። ትናንሽ ልጆች ቃላቱን በመከተል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ሊያስደስታቸው ይችላል። የበለጠ “ብርሃን እና እውነት” ወደ ቤታችሁ ለመጋበዝ ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥41–50።በቤተሰብ በጋራ “በቤተሰብህ ውስጥ ትክክል” ላይሆን ስለሚችለው ነገር ተወያዩ። “[ቤታችንን] በስርዓት ለማደራጀት” ምን ማድረግ እንችላለን? (ቁጥሮች 43–44)።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርን በኑ፣ ተከተሉኝ—ለልጆች ይመልከቱ።
የሚመረጥ መዝሙር፥ “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 2–3።