ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 26–ነሐሴ 1 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥ “የአምላክ አይነት ሀይል”


“ሐምሌ 26–ነሐሴ 1 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥ ‘የአምላክ አይነት ሀይል’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) 2020 (እ.አ.አ)

“ሐምሌ 26–ነሐሴ 1 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ 2021 (እ.አ.አ)

ጆሰፍ ስሚዝ የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ሲቀበል

ዳግም መመለስ፣ በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

ሐምሌ 26–ነሐሴ 1 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84

“የአምላክ አይነት ሀይል”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84ን ስታነቡ፣ “ከእግዚአብሔር አንደበት ከሚመጣው እያንዳንዱ ቃልም ለመኖር“ ምክሩን አስቡበት” (ቁጥር 44)። በዚህ ራዕይ ቃል የምትኖሩት እንዴት ነው?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በ1829 (እ.አ.አ) የክህነት ስልጣን ከተመለሰ ጊዜ ጀምሮ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በዚያ ቅዱስ ሃይል እየተባረኩ ነበር። ልክ አሁን እኛ እንደምናደርገው፣ እነርሱም በክህነት ስልጣን ተጠምቀው፣ ተረጋግጠው እና እንዲያገለግሉ ተጠርተው ነበር። ነገር ግን የክህነትን ሀይል ማግኘት ይህን ሙሉ በሙሉ ከመረዳት ጋር አንድ አይደለም፣ እናም እግዚአብሔር ቅዱሳን እንዲገነዘቡ ይፈልግ የነበረው ብዙ ነበር—በተለይ እየመጡ ስለነበሩት የቤተመቅደስ ዳግም መመለስ ስርአቶች። አሁን ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84 የሆነው ስለክህነት የተሰጠው የ1832 (እ.አ.አ) ራዕይ፣ ስለክህነት እውነተኛ ምንነት የቅዱሳንን እይታ አስፋፋው። እና ዛሬም ለእኛ ተመሳሳይ ነገር ሊያደርግልን ይችላል። “የእግዚአብሔርን የእውቀት ቁልፎች“ ስለሚይዘው “የአምላክ አይነት ሃይል“ እንዲገለጥ ስለሚያደርገው እና “የእግዚአብሔርን ፊት፣ እንዲሁም አብን፣ ለመመልከት እና ለመኖር“ ስለሚያዘጋጀን ስለ መለኮታዊው ኃይል ብዙ የምንማራቸው ነገሮች አሉ (ቁጥር 19–22)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥1–5፣ 17–28።

የእግዚአብሔር የክህነት ሀይል እና በረከቶች አለኝ።

ክህነት ስለሚለው ቃል ስታስቡ ወደአዕምሮአችሁ የሚመጣው ምንድን ነው? ስለክህነት እና በዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ ላይ ስላለው ተጽዕኖ ምን ያህል ጊዜ ታስባላችሁ? በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ ካሰላሰላችሁ በኋላ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥1–5፣ 17–28ን አጥኑ፣ እናም ጌታ ስለክህነት ስልጣን ምን እንድታውቁ እንደሚፈልግ አስቡ። እነዚህን ጥቅሶች በመጠቀም ለአንድ ሰው ስለክህነት እና ስለዓላማዎቹ ለማብራራት እንዴት ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ?

ስለተሳተፋችሁበት የክህነት ስርዓቶችም ማሰላሰል ትችላላችሁ። “የአምላክ አይነት ሀይል” (ቁጥር 20) እንዴት ሲገለጥባቸው አይታችኋል? ኃይሉን የበለጠ በሕይወታችሁ ውስጥ እንድትቀበሉ ጌታ ምን እንድታደርጉ እንደሚፈልግ አስቡ።

በተጨማሪም ኤም. ራስል ባላርድ “ወንዶች እና ሴቶች እና የክህነት ሃይል፣” ኢንዛይን፣ መስከረም 2014 (እ.አ.አ)፣ 28–33፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “ክህነት፣” topics.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥31–42

ጌታንና አገልጋዮቹን ከተቀበልኩ አብ ያለውን ሁሉ እቀበላለሁ።

ሽማግሌ ፖል ቢ.ፓይፐር እንዳስተማሩት፥ “በክህነት ቃለ መሃላ እና ቃል ኪዳን ጌታ ውስጥ [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥31–42]፣ ማግኘት እና መቀበል የሚሉትን ግሶች መጠቀሙ ትኩረትን የሚስብ ነው። ሹመት የሚለውን ቃል አልተጠቀመም። በቤተመቅደስ ውስጥ ነው ወንዶች እና ሴቶች —አብረው—ሁለቱንም የአሮናዊ እና የመልከጸዴቅ የክህነት በረከቶችን እና ሀይልን የሚያገኙት እና የሚቀበሉት (“ ስለሟችነት የተገለጡ እውነታዎች፣” ኢንዛይን፣ ጥር 2016 (እ.አ.አ)፣ 21)።

ትምህርትና ቃል ኪዳኖችን 84፥31–42ን ስታጠኑ፣ “ማግኘት“ እና “መቀበል“ የሚሉትን ቃላት ፈልጉ። በዚህ አውድ ውስጥ ምን ማለት ሊሆኑ እንደሚችሉ አሰላስሉ። ጌታን እና አገልጋዮቹን እንዴት “[እየተቀበላችሁ]” ናችሁ?

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እግዚአብሔር “ሊሰብራቸው [ከማይችላቸው]“ የክህነት መሃላ እና ቃል ኪዳን ጋር የተያያዙ ተስፋዎችን ልታስተውሉ ትችላላችሁ (ቁጥር 40)። አብን፣ አገልጋዮቹን እና የክህነት ስልጣኑን ለመቀበል ይበልጥ ታማኝ ለመሆን የሚያነሳሳችሁ ምን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ ቃል ኪዳን፣” “መሃላ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥43–58

ቃሉን ስሰማ እና መንፈሱን ሳዳምጥ ወደ ክርስቶስ እመጣለሁ።

ቅዱሳት መጻህፍትን እና የነቢያትን ቃላት አዘውትሮ ማንበብ ልንሰራቸው ካቀድናቸው መንፈሳዊ ስራዎች ውስጥ እየጨረስን ከዝርዝሮች ውስጥ ከምንሰርዛቸው በላይ ነው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥43–58 ውስጥ ያለማቋረጥ የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት ለምን እንደሚያስፈልግ እንድትገነዘቡ የሚረዳችሁ ምን እውነት ታገኛላችሁ? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በብርሃን እና በጨለማ መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ፤ “ለዘላለም ህይወት ቃላትም በትጋት [ማዳመጥ]” ብርሃንን፣ እውነትን እና “የኢየሱስ ክርስቶስ [መንፈስን]” ወደ ህይወታችሁ እንዴት አምጥቷል? (ቁጥሮች 43፣ 45)።

በተጨማሪም 2 ኔፊ 32፥3፤ “መፅሐፈ ሞርሞን—የእምነታችን የመሰረት አለት፣” Teachings of Presidents of the Church: Ezra Taft Benson [የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚደንቶች ትምህርቶች፥ እዝራ ታፍት ቤንሰን] [2014 (እ.አ.አ)]፣ 125–35 ይመልከቱ።

አንዲት ሴት ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠና

ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት የመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ እንዲሰማኝ ይረዳኛል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥62–91

በእርሱ አገልግሎት ላይ ስሆን ጌታ ከእኔ ጋር ይሆናል።

እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ፣ ጌታ ሐዋርያቱን እና ሚስዮናውያንን እንደሚደግፋቸው የተናገረባቸውን መንገዶች መለየት ትችላላችሁ። እነዚህ ቃል ኪዳኖች እናንተ እንድትሰሩ ከተጠየቃችሁት ሥራ ጋር እንዴት ይገናኛሉ? ለምሳሌ በቁጥር 88 ውስጥ ያሉት ተስፋዎች በህይወታችሁ ውስጥ እንዴት ተፈፅመዋል?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥6–18ሙሴ የክህነት ሥልጣኑን እንዴት እንደ ተቀበለ ካነበባችሁ በኋላ፣ በቤተሰባችሁ ውስጥ ያለ አንድ የክህነት ተሸካሚ ወይም አገልጋይ ወንድም በክህነት ሀላፊነት የመሾም ልምዱን ሊያካፍል ይችላል። ከተቻለ ስለክህነት ስልጣኑ መስመር ሊያካፍል እና ሊያስረዳ መወያየት ይችላል። በዛሬው ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ የክህነት ስልጣንን መስመር አስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣን ድረስ መፈለጋችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? የክህነት ስልጣን መስመር ለመጠየቅ ወደ lineofauthority@ChurchofJesusChrist.org ኢሜል ይላኩ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥20–21እንደ ጥምቀት ወይም ቅዱስ ቁርባን ባሉ ስርዓቶች ላይ ቤተሰባችሁ “የአምላክ አይነት ሀይል” ሲንጸባረቅ መቼ ተመለክተዋል? ምናልባት እነዚህ ስነስርዓቶች እንዴት የእግዚአብሔርን ኃይል በህይወታችን ውስጥ እንደሚያመጡ ለመነጋገር ትችላላችሁ። የአንድ ቤተመቅደስ ስዕል ልታሳዩ እና በቤተመቅደሱ የሚከናወኑ ስርአቶች እንደ አዳኙ እንድንሆን ተጨማሪ ሀይል የሚሰጡን እንዴት እንደሆነ ለመወያየትም ትችላላችሁ። የክህነት ስልጣን በዳግም ተመልሷል እንደሚል ስለ ክህነት የሚያወሱ መዝሙሮችን ልትዘምሩ ትችላላችሁ (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 89)፣ ከዚያም መዝሙሩ ስለክህነት ምን እንደሚያስተምር መወያየት ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥43–44ምግብ ወይም አንድ መዝናኛ በህብረት ልታዘጋጁ እንዲሁም እያንዳንዱን ግብአት ከቁጥር 44 ቃል ወይም ሃረግ ወስዳችሁ መሰየም ትችላላችሁ። እያንዳንዱን ግብአት ማካተት ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? በእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ቃል መኖር ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥98–102ከእነዚህ ጥቅሶች “ከአዲሱ መዝሙር” (ቁጥር 98) ውስጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንማራለን? በዚህ መዝሙር ውስጥ የተገለጹት ሁኔታዎች እንዲመጡ ለመርዳት በእኛ ዘመን ምን ልናደርግ እንችላለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥106–10“በእያንዳንዱ አባል” ስጦታዎች እና ጥረቶች ቤተሰባችን እንዴት ነው “አብረው [የሚታነጹት]”? (ቁጥር 110)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ክህነት ስልጣን በዳግም ተመልሷል፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 89፤ ደግሞም “የቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትን ለማሻሻል የሚረዱ ሃሳቦች” ይመልከቱ።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

በተግባር እንዲውሉ የተደረጉ የግብዣ ጥሪዎችን ክትትል ያድርጉ። ቤተሰባችሁ በሚማሩት ነገር ላይ ተግባራዊ እርምጃ እንዲወስዱ ስትጋብዟቸው፣ ወንጌል የሚነጋገሩት ነገር ብቻ ሳይሆን የሚኖሩት ነገር መሆኑን ታሳያላችሁ። ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84 ጥናታችሁ በመነሳት በምን ላይ ተግባራዊ እርምጃ እንዲወስዱ ለመጋበዝ ትችላላችሁ?

የሮም ጣልያን ቤተመቅደስ

የሮም ጣልያን ቤተመቅደስ