ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 9–15 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥ “የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ”


“ነሐሴ 9–15 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች –124፥ ‘የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 9–15 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች የለው ክፍል

ነሐሴ 9–15 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88

“የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ”

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “ቤታችሁን ወደ ወንጌል መማሪያ ማዕከልነት ለመቀየር ስትጥሩ፣ … የጠላት ተጽዕኖ በእናንተ ህይወት እና በእናንተ ቤት እንደሚቀንስ ቃል እገባላችኋለሁ” ብለዋል (“አርአያነት ያለው የኋለኛው ቀን–ቅዱሳን መሆን፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ.)፣ 113)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

አልፎ አልፎ ጌታ ለነቢያቱ መገለጥን በማብዛት ማለቂያ የሌለውን “ሞገሱ እና ክብሩ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥47) ትንሽ ፍንጭ ይሰጠናል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88ም እንዲህ ያለ ራዕይ ነው—ስለ ብርሃን እና ክብር እና መንግስታት የሚናገር በንጽጽር ምድራዊ ፍላጎቶቻችንን አነስተኛ መስለው እንዲታዩ ሊያደርጉ የሚችል ነው። ምንም እንኳን ጌታ የሚያስተምረንን ሁሉ መረዳት ባንችልም በዘላለማዊነት ውስጥ አሁን ከምንገነዘበው በላይ እጅግ ብዙ የሚበልጥ ነገር እንዳለ ቢያንስ ሊሰማን ይችላል። በእርግጥ ጌታ እነዚህን ታላላቅ ምስጢሮች እኛን ለማስፈራራት ወይም ትንሽ እንደሆንን እንዲሰማን ለማድረግ አልተናገረም። በእርግጥ እንዲህ የሚል ተስፋ ሰጥቷል፣ “እግዚአብሔርን የምትረዱበት ቀን ይመጣል” (ቁጥር 49፤ የሰያፍ ቅርጸት ተጨምሯል)። ጌታ ምናልባት ከፍ ያለ ውጤትን ጠብቆ ነው የከርትላንድ ቅዱሳን የነቢያትን ትምህርት ቤት እንዲመሰርቱ ያሳሰበው። “ራሳችሁን አደራጁ” ብሏል። “አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ አዘጋጁ፤ … እንዲሁም … የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ” (ቁጥር 119)። ከማንኛውም ቦታ ሁሉ በላይ በእግዚአብሔር ቅዱስ ቤት ውስጥ—እንዲሁም በቤታችን ውስጥ—እይታችንን ከሟች አለም ባሻገር ከፍ ያደርጋል፣ “ፊቱን ለእኛ ይገልጣል፣” እንዲሁም “በሰለስቲያል መንግስት ህግ እንድንጸና” ያዘጋጀናል (ቁጥር 68፡22)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88

ኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋን እና ሰላምን ይሰጠናል።

ጦርነት “በሁሉም ህዝብ ላይ እንደሚፈስ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87፥2) ካስጠነቀቀ ከቀናት በኋላ፣ ጆሴፍ ስሚዝ “‘የወይራ ቅጠል’ …ከገነት ዛፍ የተቀጠፈች ለእኛ የተሰጠ የጌታ የሰላም መልእክት” ሲል የጠራውን ራዕይ ጌታ ሰጠው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፣ የክፍል መግቢያ)። ይህ ራዕይ ባህላዊ የሰላም ምልክት እንደሆነው የወይራ ቅጠል የሆነው እንዴት ነው? (በተጨማሪውም ዘፍጥረት 8፥11 ይመልከቱ)። በዚህ ክፍል ውስጥ የትኞቹ እውነቶች በክርስቶስ ተስፋ እና ሰላም እንዲሰማችሁ ይረዷችኋል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6–67

ብርሃን እና ህግ ከኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል።

ብርሃን እና ህግ የሚሉት ቃላት በክፍል 88 ውስጥ ብዙ ጊዜ ተደጋግመዋል። እነዚህ ቃላት በሌሎች ቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን እና የእርሱን ወንጌል ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውለዋል (ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ 60፥19ዮሀንስ 1፥1–93 ኔፊ 15፥9 ይመልከቱ)። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6–67 ውስጥ እነዚህን ቃላት የምታገኙባቸውን ቁጥሮች ምልክት አድርጉ ወይም ጻፉ። እነዚህ ጥቅሶች ይበልጥ በታማኝነት ብርሃን ለመቀበል እና “የክርስቶስን ህግ” (ቁጥር 21) ለመኖር በህይወታችሁ ውስጥ ለውጦች ለማድረግ ሊያነሳሳችሁ ይችላል።

በተጨማሪም የሼረን ዩባንክን፣ “በጨለማው የሚያበራው ብርሀን፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 73–45ን ይመልከቱ።

ምስል
ቤተሰቦች ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነቡ

ቅዱሳት መጻህፍት የክርስቶስን ህግ ይይዛሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥62–126

አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ አዘጋጁ።

በአንዳንድ መንገዶች እኛ የምንኖረው ጌታ “ሁሉም ነገሮች በሁከት ውስጥ ይሆናሉ፤ እና በእርግጥም የሰዎች ልብ በፍርሃት ይደክማል” ብሎ በገለጸበት በወቅት ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥91)። ቁጥሮች 62–126ን ስታነቡ፣ የጌታ ምክር እንዴት ለአዳኝ ዳግም ምጽዓት ለመዘጋጀት እንደሚረዳችሁ አስቡበት። የሚቀጥሉት የምታስቡባቸው አንዳንድ ጥያቄዎች ናቸው፥

ቁጥሮች 62–76በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ስታሰላስሉ፣ ወደ እግዚአብሔር “ለመቅረብ” ምን ለማድረግ ተነሳሳችሁ? (ቁጥር 63)። “ራሳችሁን ቀድሱ” የሚለው የጌታ ትዕዛዝ ለእናንተ ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል አስቡ (ቁጥር 68)።

ቁጥሮች 77–80፣ 118–26የአስተምህሮ እና ስጋዊ ጉዳዮች “የሆኑትን ፈጽማችሁ እንድትማሩ አሰፈላጊ” የሆነው ለምንድን ነው? (ቁጥር 78)። “ትምህርትን ፈልጉ” የሚለውን ምክር እንዴት እየተከተላችሁ ነው? (ቁጥር 118)። “በጥናትና ደግሞም በእምነት“ መማር ምን ማለት ይመስላችኋል?

ቁጥሮች 81–116በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ከአዳኝ ዳግም ምፅዓት ጋር የተያያዙ ትንቢቶችን መመዝገብን አስቡ። ጌታ ስለእነዚህ ነገሮች ምን እንድታውቁ የሚፈልግ ይመስላችኋል?

ቁጥሮች 117–26ቤተመቅደስን በአዕምሮአችሁ ይዛችሁ እነዚህን ጥቅሶች ማንበብን አስቡ፤ በእዚህ ውስጥ ወደጌታ ቤት ለመግባት እንድትዘጋጁ ሊረዳችሁ የሚችል ምን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ዲ.ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “ለጌታ መመለስ መዘጋጀት፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ.)፣ 81–84፤ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “በእምነት መማርን እሹ፣” ኢንዛይን፣ መስከረም 2007 (እ.አ.አ.)፣ 61–68፤ ቅዱሳን፣ 1፥164–66፤ “ትምህርት ቤት እና ስጦታ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 174–82 ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥14–33፣ 95–101ስለትንሳኤ ከእነዚህ ጥቅሶች ምን እንማራለን? እነዚህ እውነቶች በምናደርጋቸው ምርጫዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩት እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥33የቤተሰብ አባላት ስለተሰጣቸው ስጦታዎች፣ በደስታ የተቀበሉትንም ያልቀበሉትንም፣ እንዲናገሩ በመጠየቅ በእነዚሀ ጥቅሶች ላይ ውይይት ማድረግ ልትጀምሩ ትችላላችሁ። ስለተሰጠን የሰለስቲያል መንግስት ስጦታ ደስተኛ እንደሆንን ለጌታ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? “በስጦታ ሰጪው” መደሰት የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥63፣ 68.እነዚህ ቁጥሮች በውስጣቸው ያሉትን መልዕክቶች ለልጆቻችሁ ለማስተማር ሊያነሳሷችሁ የሚችሉ የፈጠራ መንገዶችን እንድታስቡ አንዳንድ የድርጊት ቃላት ይዘዋል። ለምሳሌ “ወደእኔ ቅረቡ እና እኔም ወደእናንተ እቀርባለሁ” (ቁጥር 63 ሰያፍ ቅርጸት ተጨምሯል)በሚለው ሃረግ ላይ ለመወያየት ድብብቆሽ ልትጫወቱ ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥81እንደ ቤተሰብም፣ በመድኃኒቶች ላይ እንዳሉ የማስጠንቀቂያ ጽሁፎች ወይም ለሾፌሮች እንደተዘጋጁ የትራፊክ ምልክቶች አይነት በቤታችሁ ውስጥ እና በቤታችሁ ዙሪያ ያሉ አንዳንድ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ለዩ። እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች እንዴት ይረዱናል? ሰማያዊ አባት “ጎረቤቶቻችንን ስለምን እንድናስጠነቅቅ” ይፈልጋል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥119ቤታችሁን በቁጥር119 ውስጥ እንዳለው ገለፃ እንዲያደርጉ ቤተሰባችሁ ለማነሳሳት እንደዚህ ያለ ነገር ሞክሩ፥ ከእነዚህ ጥቅሶች ወስዳችሁ በቁርጥራጭ ወረቀቶች ላይ ሀረጎችን ጻፉ፣ ከዚያም የቤተመቅደስን ስዕል ለመሸፈን ተጠቀሙባቸው። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥119ን አብራችሁ አንብቡ፣ ከዚያም በጥቅሶች ውስጥ ያለውን ተጓዳኝ ሐረግ ሲሰሙ የቤተሰብ አባሎች እያንዳንዱን ቁርጥራጭ ወረቀት ያንሱት ። ቤታችንን የእግዚአብሔር ቤት ለማድረግ ምን ማድረግ እንችላለን? (ቁጥር 119)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “Nearer, My God, to Thee፣” መዝሙር፣ ቁጥር 100።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ልጆች የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲገልጹ ፍቀዱ። ልጆቻችሁ ከአንድ የወንጌል መርሆ ተነስተው አንድ ነገር እንዲፈጥሩ ስትጋብዟቸው፣ መርሆውን በተሻለ ሁኔታ እንዲገነዘቡ ብቻ አይደለም የሚረዳቸው፣ ነገር ግን ስለተማሩት ነገር ተጨባጭ አስታዋሽም ነው የምትሰጧቸው (Teaching in the Savior’s Way፣ 25 ይመልከቱ)።

ምስል
ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርት ጋር

ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን ይሰጠናል። ሰላምን እተውላችኋለሁ፣ በዋልተር ሬን

አትም