ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 16–22 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89–92፥ “ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ”


“ነሐሴ 16–22 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89–92፥ ‘ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦችና ለቤተሰቦች፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 16–22 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89–92፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ወንድ እና ሴት ምግብ እያበሰሉ

ነሐሴ 16–22 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89-92

“ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ”

በጸሎት መንፈስ ትምህርትና ቃል ኪዳኖችን 89–92ን አንብቡ፣ እና የምትቀበሉትን መንፈሳዊ ስሜቶች መዝግቡ። ስታጠኑ ለእናንተ እንዴት “መንፈስ እውነትን [እንደሚገልጥ]” ንቁዎች ሁኑ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 91፥4)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በነቢያት ትምህርት ቤት ውስጥ የእስራኤል ሽማግሌዎችን የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ስለመገንባት አስተማረ። መንፈሳዊ እውነቶችን ተወያዩ፣ አብረው ጸለዩ፣ ጾሙ እንዲሁም ወንጌልን ለመስበክ ተዘጋጁ። ነገር ግን ስለሁኔታው ዛሬ ለእኛ እንግዳ የሚመስል አንድ ነገር ነበር፣ እና ለኤማ ስሚዝም እንዲሁ ትክክል አልመሰላትም ነበረ። በስብሰባው ወቅት ወንዶቹ ትምባሆ ያጨሱ እና ያኝኩ ነበር፣ ይህም በወቅቱ እንግዳ ነገር አልነበረም፣ ነገር ግን የእንጨት ወለሉን አጥቁሮት ነበር እና መጥፎ ሽታ አየሩን በክሎት ነበር። ኤማ ስጋቷን ለጆሴፍ ነገረችው፣ ጆሴፍም ጌታን ጠየቀ። ውጤቱም ከማጨስ እና ከትንባሆ መበለዝ በላይ የሚሄድ ራዕይ ነበር። ለቅዱሳን፣ እንዲሁም ከዚያ አልፎ ለሚመጣው ትውልድ፣ “ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ” —የአካላዊ ጤንነት፣ “ጥበብ፣” እና “ታላቅ የእውቀት ሃብቶች” ተስፋ ሰጠ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥3፣ 19)።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥166–68 ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89

የጥበብ ቃል “ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ” ነው።

በነቢያት ትምህርት ቤት የነበሩ ሽማግሌዎች በመጀመሪያ ጆሴፍ ስሚዝ የጥበብ ቃልን ሲያነብ ሲሰሙት፣ ወዲያውኑ “ሲጋራቸውን እና ጥፍጥፍ የሚታኘክ ትንባሆ አሽቀንጥረው ጣሉ“ (ቅዱሳን፣ 1፥168)። በዚያን ጊዜ፣ የጥበብ ቃል ከትእዛዝነት ይልቅ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ይታሰብ ነበር፤ ነገር ግን ለመታዘዝ ያላቸውን ፍላጎት ለማሳየት ፈልገው ነበር። ምናልባት የጥበብ ቃል አንዳትጠቀሙ የሚከለክላችሁን ነገሮች ቀድሞውኑ ከህይወታችሁ “አሽቀንጥራችሁ” ጥላችሁ ይሆናል፣ ነገር ግን ከዚህ ራዕይ ውስጥ ሌላ ምን ነገር ልትማሩ ትችላላችሁ? እነዚህን ሃሳቦች ከግምት ውስጥ አስገቡ፥

  • ምናልባት ቀድሞ እስካሁን አይታችኋቸው ያልነበሩ—ወይም ብዙ ያላሰባችሁባቸው—ሃረጎችን ፈልጉ። ከእነርሱ ምን ትማራላችሁ?

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89 ብዙ ተስፋዎችን ያካትታል (ቁጥሮች 18–21ን ይመልከቱ)። እነዚህ ተስፋዎች ምን ትርጉም ያላቸው ይመስላችኋል?

  • ይህ ራዕይ ስለጌታ ምን ያስተምራችኋል?

  • “በሚያድሙ ሰዎች ልብ ውስጥ…ተንኮል እና አላማዎች” ምን የሚሆን ምሳሌዎች አይታችኋል? (ቁጥር 4)።

  • ራዕዩ እንዲያው ዝም ብሎ አድርጉ አታድርጉ ያልሆነ፣ “ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ” (ቁጥር 3)፣ እንዲሁም ውሳኔ አሰጣጥን የሚመሩ ፅኑ እውነቶች እንደሆነ አድርጋችሁ አስቡት። ውሳኔዎቻችሁን የሚመሩ ምን መርሆችን ታገኛላችሁ?

የዚህ ዘመን ነቢያትም በጥበብ ቃል ውስጥ ከተጠቀሱት ሌላ ስለአደገኛ ንጥረ ነገሮች እና ባህርዮች አስጠንቅቀዋል (“አካላዊ እና መንፈሳዊ ደህንነት፣” For the Strength of Youth [ለወጣቶች ጥንካሬ]፣ 25–27 ይመልከቱ)። አእምሯችሁን እና ሰውነታችሁን በተሻለ ሁኔታ ለመንከባከብ ምን እንድታደርጉ ነው የተነሳሳችሁት?

በተጨማሪም ዳንኤል 11 ቆሮንቶስ 6፥19–20፣ የወንጌል አርዕስቶች፣ “የጥበብ ቃል፣” topics.ChurchofJesusChrist.org፤ “የጥበብ ቃል፣” ራዕይ በአገባብ፣ 183–91፤ addictionrecovery.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ምስል
ወንዶች ልጆች በባህር ዳርቻ ሲሮጡ

የጥበብ ቃል ሰውነታችንን እንድንንከባከብ ያስተምረናል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥1–17

ቀዳሚ አመራር “የእግዚአብሔርን መንግስትን ቁልፍ“ በምድር ላይ ይዘዋል።

ክፍል 90 ውስጥ ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ለስድኒ ሪግደን እና ለፍሬድሪክ ጂ.ዊሊያምስ አሁን የቀዳሚ አመራር አባላት ብለን ስለምንጠራቸው “[አገልግሎት እና አመራር]” መመሪያ ሰጥቷል (ቁጥር 12)። ከቁጥሮች 1–17 ውስጥ ስለመጀመሪያ አመራር ምን ትማራላችሁ? ከቅርብ ጊዜ የመጀመሪያ አመራር መልዕክቶችን ከልሱ። ቃላታቸው “ተነግረው የማያውቁ የመንግስትን ሚስጥራትን” የሚገልጡት እንዴት ነው? (ቁጥር 14)። “የዚህን ቤተክርስቲያን እና መንግስት ጉዳዮች በስርአት የሚያደራጁት” እንዴት ነው? (ቁጥር 16)።

በተጨማሪም ሄንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “የጽኑ እምነት ሃይል፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 58–60።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥24

”ሁሉም ነገሮች [ለእኔ] በጎነት አብረው ይሰራሉ።”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥24 ውስጥ ስለጌታ ቃል ኪዳን ምስክርነት የሚሰጡ የነበሯችሁን ማንኛውንም ልምዶች አሰላስሉባቸው። ልምዶቻችሁን መመዝገብ እንዲሁም ከቤተሰብ ወይም ከሚወዱት ጋር መጋራትን አስቡ—ምናልባት ማረጋገጫ ወይም ማበረታቻ ለሚፈልግ አንድ ሰውም። አሁንም የምትጠብቋቸው በረከቶች ካሉ፣ በታማኝነታችሁ ለመዝለቅ ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቡበት።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥28–31

ቪዬና ጃኪ ማን ነበረች?

ቪዬና ጃክ በሰኔ 10 ቀን 1787 (እ.አ.አ) በማሳቹሴት ውስጥ ተወለደች። የእምነት ሴት እና ጥሩ የገንዘብ ምንጭ ባለቤት የሆነችው ቪዬና፣ ሚስዮናውያንን ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በ1831 (እ.አ.አ) ተገናኘች። መልዕክታቸው እውነት መሆኑን መንፈሳዊ ምስክርነት ከተቀበለች በኋላ፣ ነቢዩን ለማግኘት ከርትላንድ ኦሃዮ ተጓዘች፣ በዚያም ተጠመቀች።

ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90 ውስጥ ለእርሷ የሰጠውን ምክር ቪዬና ታዘዘች። ቀደም ሲል በከርትላንድ ውስጥ ያደረገችውን መዋጮ ጨምሮ፣ ለጌታ የሰጠችው የተቀደሰ ስጦታ መሪዎች የከርትላንድ ቤተመቅደስ የሚገነባበትን መሬት ለመግዛት በሚሞክሩበት ጊዜ መጣ። ቪዬና በህይወቷ ሙሉ “ታማኝ እና ስራ ፈት … ያልነበረች” ስትሆንም፣ በመጨረሻም በ96 አመቷ ባረፈችበት በሶልት ሌክ ሸለቆ ውስጥ ”በሰላም ልትሰፍር” (ቁጥር 31) ችላ ነበር።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89የቤተሰብ አባላቶቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89 የተጠቀሱትን ምግቦች እና ሌሎች ነገሮች መሳል ወይም ማግኘት ሊያስደስታቸው ይችላል። ከዚያም የቤተሰብ ጨዋታ ልትጫወቱ ትችላላችሁ—የቤተሰብ አባላት ተራ በተራ ስዕሎችን በዘፈቀደ በመውሰድ፣ ልንጠቀምባቸው የማይገባንን ነገሮች በቆሻሻ መጣያው ውስጥ ለማድረግ እና የምንጠቀምባቸውን ነገሮች ጠረጴዛ ላይ ለማስቀመጥ ይችላሉ። በቁጥሮች 18– 21 ውስጥ ያሉት ተስፋዎች እንዴት በህይወታችን ውስጥ ተፈጸመዋል ?

አካላዊ እና ስሜታዊ ጤንነት”ን በFor the Strength of Youth [ለወጣቶች ጥንካሬ] (25–27) ውስጥ ማንበብ ጤናችንን መንከባከብ ስለምንችልባቸው ስለሌሎች መንገዶች ውይይት ሊያነሳሳ ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥5”የእግዚአብሔርን ቃላት [ራዕዮችን እና ነቢያትን] ” እንዴት እንደምትቀበሉ ተነጋገሩ። እነዚህ ለእኛ “እንደ ቀላል ነገር” እንዳልሆኑ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 91ስለአፖክርፋ (ቁጥሮች 1–2) በተመለከተ ጌታ የሰጠው ምክር ዛሬ ቤተሰባችሁ ለሚያጋጥማቸው የመተላለፊያ ዘዴዎች ጋረ እንዴት እንደሚገናኙ ልትወያዩ ትችላላችሁ (በተጨማሪም አፖክርፋ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ)። “በመንፈስ መረዳትን ባገኛችሁበት” (ቁጥር 5) ጊዜ ትክክል የሆነውን እና ስህተት የሆነውን ለማስተዋል የረዳችሁን የግል ልምዶቻችሁንም ልታካፍሉ ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 92፥2የቤተክርስቲያኗ ”ተሳታፊ አባል” መሆን ምን ማለት ነው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ጌታ ቤተመቅደስን ሰጠኝ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 153።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የተለያዩ መንገዶችን ተጠቀሙ። በቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ቤተሰባችሁን ለማሳተፍ የተለያዩ መንገዶችን ፈልጉ። ለምሳሌ የቤተሰብ አባላት ከአንድ ጥቅስ ጋር የተያያዘ መዝሙር ወይም የልጆች መዝሙሮች ሊዘምሩ፣ ስላነበቡት ነገር ስዕል ሊስሉ ወይም አንድን ጥቅስ በራሳቸው ቃላት በአጭሩ ሊያጠቃልሉ ይችላሉ።

ምስል
አትክልት እና ፍራፍሬ

“ትእዛዛትን በማክበር፣ እነዚህን ነገሮች የሚጠብቁ እና ለማድረግ የሚያስታውሱ ቅዱሳን ሁሉ፣ ለስጋቸው ፈውስ እና ለአጥንታቸው መጠገን ይቀበላሉ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥18)፡፡

አትም