ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 2–8 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85–87፥ “በተቀደሱ ስፍራዎች ቁሙ”


“ነሐሴ 2–8 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85–87፥ ‘በተቀደሱ ስፍራዎች ቁሙ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦችና ለቤተሰቦች፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 2–8 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85–87፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ቤተሰብ ወደ ቤተመቅደስ ሲሄድ

ነሐሴ 2–8 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85–87

“በተቀደሱ ስፍራዎች ቁሙ”

መንፈስ በክፍል 85–87 ውስጥ ያሉ በዚህ ውሰጥ ጎላ ያልተደረጉትን መርሆች እንድታጠኑ ሊመራችሁ ይችላል። እርሱ ያነሳሳችሁን ተከተሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ብዙውን ጊዜ የገና ቀን እንደ “ሰላም በምድር” እና “ለሰውም በጎ ፈቃድ” ያሉ መልእክቶችን የማሰላሰያ ጊዜ ነው (ሉቃስ 2፥14 ይመልከቱ)። በታህሳስ 25 ቀን 1832 (እ.አ.አ.) ግን የጆሴፍ ስሚዝ አእምሮ በጦርነት ስጋት ውስጥ ነበር። ደቡብ ካሮላይና ለአሜሪካን መንግስት አልታዘዝም አልች እናም ለጦርነት እየተዘጋጀች ነበር። ጌታም ለጆሴፍ ይህ ነገር ገና ጅማሬው ብቻ እንደሆነ ገለጠለት፥ “ጦርነት“ ሲል ተናገረ፣ “በሁሉም ህዝብ ላይ [ይፈሳል]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87፥2)። ይህ ትንቢት በጣም በቅርቡ የሚፈጸም መሰለ።

ግን በዚያን ጊዜ አልተፈጸመም። በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ደቡብ ካሮላይና እና የአሜሪካ መንግስት ስምምነት ላይ ደረሱ፣ እናም ጦርነቱ ቀረ። ነገር ግን ራዕይ ሁልጊዜ በተጠበቀው ጊዜ ወይም በጠበቅነው መንገድ አይከናወንም። ወደ 30 ከሚጠጉ ዓመታት በኋላ ጆሴፍ ስሚዝ ሰማዕት ከሆነ እና ቅዱሳን ወደ ምዕራብ ከተንቀሳቀሱ ከረዥም ጊዜ በኋላ፣ ደቡብ ካሮላይና አመፀች ከዚያም የእርስ በእርስ ጦርነት ተከተለ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ የነበረው ጦርነት “ምድር … [እንድታዝን]“ ምክያት ሆኗል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87፥6)። ትንቢቱ በመጨረሻ መፈጸሙ ቢፈጸምም፣ የዚህ ራዕይ ዋጋ ጥፋቱ መቼ እንደሚመጣ በመናገር አነስ ያለ ጠቀሜታ ሲኖረው፣ ሲፈጸም ምን ማድረግ እንዳለብን ለማስተማር ግን ያለው ዋጋ የበለጠ ነው። በ1831፣ በ1861 እና በ2021 (እ.አ.አ) ምክሩ ያው ነው፥ “በተቀደሱ ስፍራዎች ቁሙ፣ እናም አትነቃነቁ“ (ቁጥር 8)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥1–2

“ታሪክን መጠበቅ“ መልካም ነው።

ቁጥር 1 የተገለጸው “ታሪክ” በፅዮን “ውርስን በህግ የሚቀበሉትን” ሰዎች ስም ይዘረዝራል (ተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 72፥24–26 ይመልከቱ)። ነገር ግን ይህ ታሪክ ከአስተዳደራዊ ክንውንነትም በላይ ነበር—ይህም የቅዱሳንን “አኗኗራቸውን፣ እምነታቸውን፣ እና ስራቸውን” የሚመዘግብ ጠቃሚ መዝገብም ነበር (ቁጥር 2)።

የግል ታሪካችሁን ወይም የማስታወሻ ደብተር እየያዛችሁ ናችሁን? ለወደፊቱ ትውልድ በረከት ሊሆን የሚችል ስለአኗኗሯችሁ፣ እምነታችሁ፣ እና ስራችሁ ምን ትመዘግባላችሁ? ይህ ታሪክ እንዴት ለእናንተ በረከት ሊሆን ይችላል?

ደግሞም “ማስታወሻ ደብተሮች፥ ‘ከወርቅ በላይ ይበልጥ ውድ የሆነ,’” Teachings of Presidents of the Church: Wilford Woodruf [የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፥ ውልፈርድ ውድረፍ [2011 (እ.አ.አ.)]፣ 125–33፤ “ልቦችን መመለስ” (ቪዲዮ፣ ChurchofJesusChrist.org) ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥6

መንፈስ በ“አነስተኛ ለስላሳ ድምጽ” ይናገራል።

ጆሴፍ ስሚዝ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥6 ውስጥ መንፈስን ለመግለጽ የተጠቀማቸውን ቃላቶች አሰላስሉ። የመንፈስ ድምጽ “አነስተኛ” እና “ለስላሳ” የሚሆነው በምን መንገድ ነው? ይህም በህይወታችሁ “ሰንጥቆ የሚገባው” አንዳንድ ነገሮች ምን ናቸው ?

መንፈስ እንዴት እንደሚያነጋግራችሁ ስታስቡ፣ በጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጡትን እነዚህን መገለጫዎች አስቡባቸው፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥22–248፥2–39፥7–911፥12–13128፥1። ባነበባችሁት መሰረት፣ የመንፈስን ድምጽ ለመስማት ምን የተሻለ ነገር ማድረግ እንደሚያስፈልጋችሁ ይሰማችኋል?

በተጨማሪም1 ነገስት 19፥11–12ሔለማን 5፥30 ይመልከቱ።

ምስል
አንዲት ሴት ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠና

ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት የመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ እንዲሰማን ይረዳናል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86

በመጨረሻው ቀን ጻድቃን ይሰበሰባሉ ።

ማቴዎስ 13፥24–3037–43 ውስጥ ከሰጠው ጥቂት የተለየ አጽንዖት ጋር፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86፥1–7 የጌታን የስንዴ እና የእንክርዳድ ምሳሌ ማብራሪያን ይይዛል። ሁለቱን ስታነጻጽሩ ምን አይነት ልዩነቶች ታያላችሁ? ይህ ምሳሌ—ከእነዚህ ልዩነቶች ጋር—ለምን “በመጨረሻ ቀናት፣ እንዲሁም አሁንም” መደገም እንደሚገባው አስቡ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86፥4)። ከዚህ ምሳሌ እና ከኋለኛው ቀን ትርጉሙ ምን መማር ትችላላችሁ?

ቁጥሮች 8–11 ውስጥ እንደተመዘገበው፣ ከዚያ ጌታ ስለክህነት፣ ዳግም መመለስ፣ እና ስለ ህዝቡ መዳን ተናገረ። በእነዚህ ጥቅሶች እና በስንዴ እና እንክርዱ ምሳሌ ምን ግንኙነት ትመለከታላችሁ? “[ለጌታ ህዝቦች እንደ] አዳኝ” ለመሆን የምትችሉት እንዴት ነው? (ቁጥር 11)።

በተጨማሪም ከወንጌል አርዕስቶች፣ “ክህደት፣” “የክህነት ዳግም መመለስ፣” topics.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87

“በተቀደሱ ስፍራዎች“ ሰላም ይገኛል።

“ከደም መፋሰስ… [እና] ረሃብ እንዲሁም ቸነፈር እና የመሬት መንቀጥቀጥ” ከሆኑት አካላዊ አደጋዎች በተጨማሪ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87፥6)፣ በዚህ ራዕይ ውስጥ ያለው ምክር በዚህ በመጨረሻው ቀን ሁላችንን ለሚያጋጥሙን መንፈሳዊ አደጋዎችም ሊሰራ ይችላል። ሰላም እና ጥበቃ የምታገኙባቸው “የተቀደሱ ስፍራዎች” (ቁጥር 8) ምንድን ናቸው? አንድን ቦታ ቅዱስ የሚያደርገው ምንድን ነው? ምናልባት ከአካላዊ ስፍራዎች በተጨማሪ ሰላምን ሊያመጡ የሚችሉ የተቀደሱ ጊዜዎች፣ የተቀደሱ ተግባራት ወይም የተቀደሱ ሃሳቦች አሉ። ከእነዚህ ቦታዎች “አለመነቃነቅ” ማለት ምን ማለት ነው?

በተጨማሪም ሄንሪ ቢ.አይሪንግ፣ “የጌታ መንፈስ የሚያድርበት ቤት፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 22–25፤ ቅዱሳን፣ 1፥163–64፤ “ሰላም እና ጦርነት፣”ራዕያት በአገባብ፣158–64 ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥6ቤተሰባችሁ የመንፈስን አነስተኛ እና ለስላሳ ድምጽ እንዲለይ ለማስተማር የምትችሉት እንዴት ነው? ምናልባት አንድ ሰው በሚረብሽ ድምጽ መሃል ጠቃሚ መመሪያን ያንሾካሹክበት አንድ ጨዋታ ልትጫወቱ ትችላላችሁ። መንፈስ ቅዱስን ከመስማት ምን ሊያግደን ይችላል። ምናልባት የቤተሰብ አባላት የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ለመስማት ምን እንደሚያደርጉ ሊያካፍሉ ይችሉ ይሆናል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86ስዕሎችን መሳል እና መመልከት ቤተሰባችሁ የስንዴ እና የእንክርድን ምሳሌን እንዲገነዘቡ ሊረዳ ይችላል። በማቴዎስ 13፥24–30 ውስጥ በተገለጹት ነገሮች ምስሎች ለመጀመር ልትፈልጉ ትችላላችሁ። ከዚያም ቤተሰባችሁ ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86፥1–7 ውስጥ ከወጡ ማብራሪያዎች የስዕሎቹን ስያሜ ሊለጥፉባቸው ይችላሉ። እንደ ስንዴው የሆንነው እንዴት ነው? ስንዴውን እንደሚሰበስብ መላዕክት እንዴት ልንሆን እንችላለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87፥8ቤታችሁን እንዴት የተቀደሰ ቦታ ማድረግ እንደሚቻል ውይይት ለመጀመር፣ የቤተሰብ አባላት አዳኝን ለሚወድ አንድ ሰው ቤት እንዲያነጹለት ልትጋብዙ ትችላላችሁ። በዓለም ውስጥ ባለው መንፈሳዊ አደጋ ውስጥ ቤታችሁን ሰላም የሰፈነበት ቦታ ለማድረግ “እንዴት እንደገና ማነጽ” እንደሚቻል ይህም ሀሳቦችን ያስከትላል ። እንደ “ፍቅር በቤት፣” “ቤት በምድር ላይ ያለ ገነት ሊሆን ይችላል፣” (መዝሙሮች፣ ቁጥሮች 294፣ 298)፣ ወይም “ፍቅር ባለበት” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 138–39) ያሉ መዝሙሮች ሃሳብ ሊሰጧችሁ ይችላሉ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ፍቅር ባለበት፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 138–39።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የፈጠራ ችሎታችሁን ተጠቀሙ። ከቅዱሳት መጻህፍት ቤተሰባችሁን ስታስተምሩ፣ በዚህ መዘርዝር ውስጥ በተጠቆሙት ጥያቄዎች እና የመልመጃ ሀሳቦች እራሳችሁን አትገድቡ። እነዚህ ሀሳቦች የራሳችሁን የፈጠራ ችሎታ እንዲያፈነጥቁ ፍቀዱ። ቤተሰባችሁ ስለሚደሰቱበት ነገር እና በቅዱሳት መጻሕፍት እና በህይወታቸው መካከል ግንኙነቶችን ለማግኘት ምን ሊረዳቸው እንደሚችል አስቡ።

ምስል
የስንዴ ማሳ

ጌታ የስንዴውን እና የእንክርዳዱን ምሳሌ በመጨረሻው ቀን ህዝቡ እንዴት እንደሚሰበሰብ ለማስረዳት ተጠቀመ።

አትም