“ሐምሌ 19–25 (እ.አ.አ)። ትምህትና ቃል ኪዳኖች 81–83፥ ‘ብዙ ለተሰጠው ከእርሱ ብዙ ይጠበቅበታል’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ሐምሌ 19–25 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81–83፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 19–25 (እ.አ.አ)
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81–83
“ብዙ ለተሰጠው ከእርሱ ብዙ ይጠበቅበታል”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81–83ን ስታጠኑ፣ በቤተሰባችሁ፣ በጓደኞቻችሁ እና በሌሎች መካከል መልካም እንድታደርጉ የሚረዷችሁን መርሆች መዝግቡ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
በመጋቢት 1832 (እ.አ.አ)፣ ጌታ ጄሲ ጋውዝን በከፍተኛ ክህነት አመራር ውስጥ (አሁን ቀዳሚ አመራር ይባላል) የጆሴፍ ስሚዝ አማካሪ እንዲሆን ጠራው። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81 ለወንድም ጋውዝ ስለ አዲሱ ጥሪ እና በታማኝነት በማገልገል ስለሚገኙ በረከቶች የሚያስተምር መገለጥ ነው። ጄሲ ጋውዝ ግን በታማኝነት አላገለገለም። ስለዚህ ፍሬድሪክ ጂ. ዊልያምስ እርሱን ለመተካት ተጠራ፣ እናም በራዕዩ ውስጥ የወንድም ጋውዝ ስም በወንድም ዊሊያምስ ስም ተተካ።
ይህ ትንሽ ዝርዝር ሊመስል ይችላል፣ ነገር ግን ትርጉም ያለው እውነታን ያመላክታል፥ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች የየሚገኙ አብዛኛዎቹ ራዕዮች ስለ ተለዩ ሰዎች የሚናገሩ ናቸው፣ ነገር ግን ሁል ጊዜ እነዚህን ስለራሳችን እንዴት እንደሚያመለክቱ ለማወቅ መንገዶችን ልንፈልግ እንችላለን (1 ኔፊ 19፥23)። ጌታ “የሰለሉትን ጉልበቶች አጠንክር” ሲል ለፍሬድሪክ ጂ. ዊሊያምስ የሰጠው ምክር ሃሳባችንን ወደምናበረታታቸው ሰዎች ሊመልስ ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥5)። ጌታ የቤተክርስቲያኗን ስጋዊ ፍላጎቶች ለማሟላት “በዚህ ቃልኪዳን ራሳችሁን እንድታስተሳስረሩ“ ሲል ለተባበረው ድርጅት አባላት የሰጠው ምክር ሃሳባችንን ወደራሳችን ቃል ኪዳኖች ይመልሳል። ጌታም “እኔ የምለውን ስታደርጉ በቃሌ እታሰራለሁ” በማለት የገባልን ቃል ኪንዳን እኛ ታዛዥ በምንሆንበት ስለሰጠው የተስፋ ቃል እንድናስታውስ ያደርገናል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥10፣ 15)። ያ መሆን እንዳለበት ነው፣ ምክንያቱም ጌታ ደግሞ እንዳወጀው፣ “ስለዚህ፣ ለአንዱ የምናገረው ለሁሉም የተናገርሁት ነው” (ቁጥር 5)።
“ኑውል ኬ.ዊትኒ እና የተባበረው ድርጅት፣” “ጄሲ ጋውዝ፥ የነብዩ አማካሪ፣” ራዕይ በአገባብ፣ 142–47፣ 155–57።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ጌታ እንዳደርግ የሚፈልግብኝን ነገር በማድረግ ታማኝ ልሆን እችላለሁ።
በህይወታችሁ ያሉ አስፈላጊ ሃላፊነቶችን እንዴት እንደምትወጡ አንዳንድ ጊዜ ታስባላችሁን? እንደ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካሪነቱ፣ ፍሬድሪክ ጂ.ዊልያምስ በእርግጠኝነት ብዙ ሃላፊነቶች ነበሩበት። በክፍል 81 ውስጥ እንዴት እንደሚፈጽማቸው ጌታ ምክር ሰጥቶታል። በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ በጌታ ለእናንተ የተሰጡ ሃላፊነቶችን እንድትወጡ የሚረዳችሁ ምን ነገር ታገኛላችሁ?
ቁጥር 5ን ለማሰላሰል እንዲረዷችሁ እነሆ አንዳንድ ጥያቄዎች፥
-
ሰው “ደካማ” ሊሆን የሚችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ምን ናቸው? ደካማ የሆኑትን “መርዳት“ ማለት ምን ማለት ነው?
-
የሰው እጆች በምሳሌያዊ ሁኔታ “የዛሉት“ የሚሆኑት በምን መነሻ ሊሆን ይችላል። እነዚያን እጆች እንዴት “ለማቅናት” እንችላለን?
-
“የሰለሉትን ጉልበቶች” የሚለው ሃረግ ምን ማለት ሊሆን ይችላል? እነዚያን የሰለሉ ጉልበቶች “ልናጠናክር” የምንችለው እንዴት ነው?
ምናልባት ይህንን ጥቅስ ማጥናት “ደግፉ፣” ”ቀና” ልታደርጉ፣ ወይም “ልታጠነክሩት” የምትችሉት አንድ ሰው ወደ አእምሯችሁ አምጥቷል። ያንን ሰው ለማገልገል ምን ታደርጋላችሁ?
ጌታ ንስሃ እንድገባ እና ኃጢያቴን እንድተው ይጋብዘኛል።
ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 82፥1–7ን ስታነቡ፣ የተማራችኋቸውን ሁለት ነገሮች በዝርዝር ለመጻፍ አስቡ፥ ስለኃጢያት ማስጠንቀቂያ እና ስለይቅርታ እውነቶች። እነዚህ እውነቶች የጠላትን ፈተናዎች እንድትቋቋሙ እንዴት ይረዷችኋል?
ትዕዛዛቶች ለእኔ መዳን እና ጥበቃ ናቸው።
እናንተ ወይም ሌላ የምታውቁት ሰው ጌታ ለምን በጣም ብዙ ትእዛዛትን እንደሰጠ አስቦ የሚያውቅ ከሆነ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥8–10 ሊረዳ ይችላል። የጌታን ትእዛዛት ለምን መከተል እንደመረጣችሁ ለሌላ ሰው ለማስረዳት በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉ ምን ሃሳቦች ይረዳችኋል? የእርሱ ትእዛዛት ህይወታችሁን እንዴት እንደለወጡ ልታስገቡበትም ትችላላችሁ። ቁጥር 10ን ስታነቡ ስለ ጌታ ምን ትማራላችሁ?
በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥20፤ ካሮል ኤም. ሰቴቨንስ፣ “ከወደዳችሁኝ ትእዛዛቴን ጠብቁ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 118–20 ይመልከቱ።
“ባልቴቶች እና የሙት ልጆችም … ይረዳሉ።”
በሚያዝያ 1832 (እ.አ.አ)፣ በጌታ እንደታዘው ጆሴፍ ስሚዝ በሚዙሪ የተሰባሰቡትን ቅዱሳን ለመጎብኘት በ1287 ኪሎ ሜትር ተጓዘ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥9ን ይመልከቱ)። በጎበኛቸው አንድ ማህበረሰብ ውስጥ ህጻናቶቻቸውን በብቻቸው የሚያሳድጉ መበለቶችን ያካተተ ነበር። ከእነዚያም ውስጥ ነቢዩ በግል የሚያውቃቸው ፊቤ ፔክ እና አና ሮጀርስ ነበሩ። የ1830 (እ.አ.አ) የሚዙሪ የክልል ህግ ለባልቴቶች በሞቱ ባሎቻቸው ንብረት ላይ የተወሰነ መብት ይሰጥ ነበር። ከክፍል 83 ውስጥ ጌታ ስለ መበለቶች እና አሳዳጊ ስላጡ ልጆች ምን ስሜት እንዳለው ምን ትማራላችሁ? በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለ ከእናንተ ፍቅር እና ክብካቤ ሊጠቀም የሚችል ሰው ታውቃላችሁን?
በተጨማሪም ኢሳይያስ 1፥17፤ ያዕቆብ 1፥27 ይመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥3።ከወረቀት የተሰሩ ልቦችን ለቤተሰብ አባላት ልትሰጡ እና ስለአንድ ሊጸልዩበት ስለሚፈልጉት ነገር እንዲስሉ ወይም እንዲጽፉ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። “ሁልጊዜም ድምጽን አውጥቶ እንዲሁም በልብ” መጸለይ ምን ማለት እንደሆነ ተነጋገሩበት።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥5በዚህ ጥቅስ ውስጥ ያሉትን መርሆች ለመማር ምናልባት የቤተሰብ አባላት “ደካማ” ሆነው የተሰማቸውን ጊዜ እና አንድ ሰው የረዳቸውን ወይም ያጠናከራቸውን ጊዜ ምሳሌዎች ሊያጋሩ ይችላሉ። እንደ “Works of God” ወይም “The Miracle of the Roof” ያሉ ሌሎችን ስለማገልገል የሚያወሱ ቪዲዮዎችን ልትመለከቱ ትችላላችሁ (ChurchofJesusChrist.org)። ቤተሰባችሁን እንዴት በየወቅቱ አንዳቸው ላንዳቸው ማገልገል እንደሚችሉ ተወያዩ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥8–10።ምናልባት አንድ ቀላል ጨዋታ ቤተሰባችሁን ስለእግዚአብሔር ህግጋት አመስጋኝ እንዲሆን ሊረዳው ይችላል። አንድ የቤተሰብ አባል አይኑን የታሰረ የቤተሰብ አባል ቀላል ምግብ እንዲሰራ ወይም እንቅፋታማ መንገድ ማለፍ እንዲችል ለመርዳት መመሪያ ሊሰጥ ይችላል አስደሳች እና ፈጠራ የታከለበት ነገር አስቡ። ከዚያም የእግዚአብሔር ህግጋት በጨዋታው ውስጥ እንዳየናቸው መመሪያዎች እንደሆኑ ተወያዩ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥18–19።እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል “ተሰጥኦውን/ዋን ለማሻሻል” እና “ሌሎች ተሰጥኦዎችን ለማግኘት” ምን ሊያደርግ/ልታደርግ ይችላል/ትችላለች? የቤተሰብ ተሰጥኦ ትርኢት ማቅረብ አስደሳች ሊሆን ይችላል። በቀላሉ ለእይታ ሊቀርቡ የማይችሉ ተሰጥኦዎችን (እንደ መንፈሳዊ ስጦታዎች) ለማካተት መንገዶችን አስቡ (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 46፥11–26ን ይመልከቱ)። ተሰጥኦዋችንን እንዴት ልንጠቀም እንዲሁም ያሉንን ነገረሮች ከቤተሰቦቻችን እና ከጎረቤቶቻችን ጋር እንዴት ልንጋራ እንችላለን። ተሰጥኦዋችንን “አይንን ወደ እግዚአብሔር ክብር በማድረግ” መጠቀም ምን ማለት ነው?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ “ምን መልካሙን አድርጌአለሁ?” መዝሙሮች፣” 223፤ በተጨማሪም “የቤተሰባችሁን የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ለማሻሻል ሀሳቦች” ይመልከቱ።