ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ሰኔ 28–ሐምሌ 4 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71–75፥ “በእናንተ ላይ እንዳትበለጽጉ የሚከላከል መሳሪያ አይከናወንም”


“ሰኔ 28–ሐምሌ 4 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71–75፥ ‘በእናንተ ላይ እንዳትበለጽጉ የሚከላከል መሳሪያ አይከናወንም’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 28–ሐምሌ 4 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71–75፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ከጠቦት ጋር

ለእረኛው ልብ ውድ በሳይመን ዲዊ።

ሰኔ 28–ሐምሌ 4 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71–75

“በእናንተ ላይ እንዳትበለጽጉ የሚከላከል መሳሪያ አይከናወንም።“

ሽማግሌ ክውንተን ኤል. ኩክ እንዳስተማሩት፣ “የመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ አብዛኛውን ጊዜ በግለሰብ የቅዱስ መጻህፍት ጥናት እና በቤት በሚደረግ ጸሎት ይከሰታል” (“ወደሰማይ አባት እና ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥልቅ እና ዘለቄታዊነት ያለው መለወጥ ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 10)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ከልጅነቱ ጀምሮ የእግዚአብሔርን ስራ ለመስራት ሲሞክር፣ ጆሴፍ ስሚዝ ተቺዎች፣ እንዲሁም ጠላቶች ገጥመውታል። ነገር ግን በ1831 (እ.አ.አ) እዝራ ቡዝ ቤተክርስቲያኗን በይፋ ማውገዝ ሲጀምር በተለየይ አሳዛኝ ሳይሆንለት አይቀርም ነበር፣ ምክንያቱም በዚህ ጊዜ ተቺው የቀድሞ አማኝ ስለነበረ። እዝራ ጆሴፍ ስሚዝ አንድን ሴት ለመፈወስ የእግዚአብሔርን ሃይል ሲጠቀም አይቶ ነበር። በመጀመሪያው የሚዙሪ የጽዮን መሬት በሚመለከቱበት ጊዜ፣ ከጆሴፍ ጋር እንዲሄድ ተጋብዞ ነበር። ነገር ግን ከዚያን ጊዜ በኋል እምነቱን አጥቶ ነበር፣ እናም የነቢዩን ክብር ለመንካት በሚያደርገው ጥረት በአንድ የኦሃዮ ጋዜጣ ላይ ተከታታይ ደብዳቤዎችን አሳተመ። እናም ጥረቶቹ እየተሳኩ መጡ፥ “በአካባቢው በቤተክርስቲያኗ ላይ የጥላቻ ስሜት አድጎ ነበር” (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 71 የክፍል መግቢያ)። በእንደዚያ አይነት ሁኔታ ላይ አማኞች ምን ማድረግ አለባቸው? ለሁሉም ሁኔታዎች የሚሆን አንድ መልስ ባይኖርም፣ አብዛኛውን ጊዜ—በ1831 (እ.አ.አ) ጨምሮም—የጌታ መልስ በክፍልም “ወንጌልን በማወጅ” (ቁጥር 1) እውነትን መከላከል እና ሃሰትን ማስተካከል ነበር። አዎን፣ የጌታ ስራ ሁል ጊዜ ተቺዎች ይኖረዋል፣ ነገር ግን በመጨረሻ “[በዚህ ላይ የተሰራ መሳሪያ አይበለፅግም]” (ቁጥር 9)።

እዝራ ቡዝ እና አይዛክ ሞርሊ፣” ራዕይ በአገባብ፣ 134 ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71

ጌታ የስራውን ተቺዎች በራሱ ጊዜ ዝም ያሰኛቸዋል።

ሰዎች ቤተክርስቲያንን ወይም መሪዎችን ሲተቹ ወይም ሲያላግጡ ስንሰማ ልንጨነቅ አንችላለን፣ በተለይም የምናውቃቸው እና የምንወዳቸው ሰዎች በዛ ትችት ተጽዕኖ ይደርስባቸዋል ብለን ስንፈራ። በ1831 (እ.አ.አ) በኦሃዮ ተመሳሳይ ነገር ሲፈጠር (የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71 ክፍል ርዕስ ይመልከቱ)፣ ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን የነበረው መልዕክት የእምነት እንጂ የፍርሃት አልነበረም። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71ን ስታጠኑ፣ በጌታ እና በስራው እምነታችሁን የሚገነባ ምን ነገር ታገኛላችሁ? ጌታ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ላሉ አገልጋዮቹ ከሰጠው መመሪያ ምን ያስደንቃችኋል?

ሮበርት ዲ. ሔልስ፣ “የክርስቲያን ብርታት፥ የደ ቀመዛሙርትነት ዋጋ ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2008 (እ.አ.አ.)፣ 72–75፤ ጆርግ ክሌቢንጋት፣ “Defending the Faith [እምነትን መከላከል]፣” ኤንዛይን፣ መስከረም 2017 (እ.አ.አ.)፣ 49–53።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 72

ኤጲስ ቆጶሳት የጌታ መንግስት መንፈሳዊ እና ስጋዊ ጉዳዮች ጠባቂ ናቸው።

ኑዌል ኬ.ውትኒ እንደ ቤተክርስቲያኗ ሁለተኛ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ሲጠራ የነበሩበት ሃላፊቶች ከአሁኖቹ ኤጲስ ቆጶሳት ሃላፊነቶት ትንሽ ለየት ይላሉ። ለምሳሌ፣ ኤጲስ ቆጶስ ዊትኒ የይዞታን ቅዱስ ስጦታ እና በሚዙሪ፣ በጽዮን መሬት ላይ ለመስፈር የሚሰጥን ፈቃድ ይቆጣጠር ነበር። ነገር ግን ስለጥሪው እና ሃላፊነቶቹ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 72 ውስጥ ስታነቡ፣ ዛሬ ከሚያገለግሉት ኤጲስ ቆጶሳት ጋር አንዳንድ ተያያዥነቶችን ለማስተዋል ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ በምን መንገዶች ለኤጲስ ቆጶሳችሁ “[የመጋቢነታችሁን] መግለጫ” ታቀርባላችሁ? (ቁጥር 5)። በምን መንገዶች ነው ኤጲስ ቆጶሳችሁ “የጌታን ጎተራ [የሚጠብቀው]” እና የአጥቢያው አባላትን የተቀደሰ መዋጮ የሚያስተዳድረው? ( ቁጥሮች 10፣ 11 ይመልከቱ). ኤጲስ ቆጶስ እንዴት ረድቷችሁ ያውቃል?

በተጨማሪም ከወንጌል አርዕስቶች፣ “ኤጲስ ቆጶስ ፣” topics.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

በምግብ የተሞሉ በርሜሎች እና ጆንያዎች።

ኑዌል ኬ.ውትኒ የኤጲስ ቆጶሱን ጎተራ አስተዳድሯል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 73

ወንጌልን ለማካፈል አጋጣሚዎችን መፈለግ እችላለሁ።

ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን እዝራ ቡዝ ያደረገውን አፍራሽ ነገር ለማስተካከል ካደረጉት አጠር ያለ የሚስዮናዊ ስብከት ከተመለሱ በኋላ ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71 ይመልከቱ)፣ ጌታ መፅሐፍ ቅዱስን ወደ መተርጎሙ ስራ እንዲመለሱ ነገራቸው (የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም” ይመልከቱ)። ነገር ግን በተጨማሪ ወንጌልን እንዲሰብኩም ፈልጎ ነበር። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 73 ስታነቡ፣ ወንጌልን መስበክ ከሌሎች ሃላፊነቶቻችሁ ጋር እንዴት ቀጣይነት ያለው፣ “በተቻለው መጠን” (ቁጥር 4)—ወይም እውነተኛ—የህይወታችሁ አካል ልታደርጉት እንደምትችሉ አስቡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 75፥1–12

ጌታ ወንጌልን በታማኝነት የሚያውጁትን ይባርካል።

ወንጌልን ለመስበክ “ወደ አለም ሁሉ ሂዱ“ ለሚለው ትዕዛዝ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥8) ምላሽ ለመስጠት ብዙ ታማኝ ሽማግሌዎች ጌታ እንዴት ትእዛዙን እንዲፈጽሙ እንደሚፈልግ ተጨማሪ መረጃ ፈለጉ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 75፥1–12 ውስጥ ወንጌልን እንዴት በብቃት ለመስበክ እንደሚቻል እንድትረዱ የሚያግዛችሁ ምን ቃላት እና ሃረጎች ታገኛላችሁ? ለታማኝ ሚስዮናውያን ጌታ ምን አይነት በረከቶችን ቃል ይገባል? እነዚህ መመሪያዎች እና በረከቶች ወንጌልን ስታካፍሉ እንዴት ለእናንተ እንደሚሰሩ አስቡ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71ሌሎች ቤተክርስቲያኗን እና መሪዎቿን ሲተቹ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሲድኒ ሪግደን እንዲያደርጉ የተጠየቁት ምን ነገሮች ነበሩ? ሰዎች የእግዚአብሔርን ራዕዮች እንዲቀበሉ “መንገዱን የምናዘጋጀው” እንዴት ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71፥4

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 72፥2ኤጲስ ቆጶሳት ቤተሰባችንን የባረኩልን እንዴት ነው? ኤጲስ ቆጶሳችን ምን እንድናደርግ ጠይቀውናል፣ እናም እንዴት ልንደግፋቸው እንችላለን? ምናልባት እንደ ቤተሰብ ኤጲስ ቆጶሳችሁ ለሰጡት አገልግሎት የሚያመሰገን ካርድ ለማዘጋጀት ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 73፥3–4ቤተሰባችሁ ስለጆሴፍ ስሚዝ የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም ከመማር ለመጠቀም ይችላሉን? (የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም”) በጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ተከልሰው የነበሩ ጥቂት ምንባቦችን ልትፈትሹ እና ጌታ በነቢዩ አማካኝነት በገለጻቸው እውነቶች ላይ ልትወያዩ ትችላላችሁ። ለጥቂት ምሳሌዎች፣ በጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ውስጥ ዘፍጥረት 14፥25–40 እና ዘፍጥረት 50፥24–38ን በመፅሐፍ ቅዱስ ተጨማሪ ክፍሎች ውስጥ፤ በየማቴዎስ 4፥1–11 እና ሉቃስ 2፥46 ውስጥ ያሉ የተለያዩ የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ የግርጌ ማስታወሻ c ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 74፥7ይህ ጥቅስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለትንንሽ ልጆች ምን ያስተምረናል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 75፥3–5፣ 13፣ 16በ“ስራ ፈትነት“ እና “በአቅም ሁሉ በመስራት“ መካከል ያለውን ልዩነት በመናገር ጌታ እንዴት እንድናገለግለው እንደሚፈልግ ቤተሰባችሁ እንዲገነዘብ መርዳት ትችላላችሁ። ምናልባት አንድ የቤት ስራ ልትመርጡና እነዚህን ስራዎች በለዘብተኝነት ከዚያም በሙሉ አቅማቸው በመስራት እንዲያሳዩ ቤተሰባችሁን ልትጋብዙ ትችላላችሁ። አዳኝን በሙሉ አቅማችን እንዴት ልናገለግለው እንችላለን? እንደ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 1፥1–5፣ 13፣ 16 ገለጻ መሰረት፣ ጌታ ለታማኝ አገልጋዮቹ ምን ቃል ገብቷል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “Let Us All Press On [ሁላችንም ወደፊት እንግፋ]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 243።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የሚያነቃቁ ቃላትን እና ሃረጎችን ፈልጉ። እያነበባችሁ እያላችሁ መንፈስ አንዳንድ ቃላትን እና ሃረጎችን ወደ ትኩረታችሁ ሊያመጣ ይችላል። ከትምህርትና ቃል ኪዳኖች 71–75 ውስጥ ያስደነቃችሁን ቃላቶችን እና ሃረጎችን ለመመዝገብ አስቡበት።

ወጣት ወንድ ከክህነት መሪ ጋር

ወጣት ወንድ ከክህነት መሪ ጋር የሚያሳይ ስዕል በዲ. ኬት ላርሰን