“ሐምሌ 12–18 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን 77–80፥ ‘እመራችኋለሁ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ሐምሌ 12–18 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77-80፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 12–18 (እ.አ.አ)
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77-80
“እመራችኋለሁ”
ጌታ “[በጆሮው] የጥበብ ቃላትን [እንደሚናገርለት]” ለጆሴፍ ስሚዝ ነገረው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥2)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77–80ን ስታጠኑ ምን የጥበብ ቃላት ትቀበላላችሁ?
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በዳግም ከተመለሰች ከሁለት አመት ባነሰ ጊዜ ወደ 2000 በሚሆኑ አባላት እያደገጭ እና በፍጥነት እየተስፋፋች ነበር። በመጋቢት 1832 (እ.አ.አ) ጆሴፍ ስሚዝ “ስለቤተክርስቲያን ጉዳይ ለመወያየት” ከሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር ተገናኘ፥ ጉዳዮቹም ራዕዮችን የማሳተም አስፈላጊነት፣ የሚሰባሰቡበት መሬት ስለመግዛት እና ድሆችን ስለመንከባከብ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፣ የክፍል ርእስ ይመልከቱ)። ጌታ እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ጥረታቸውን “ወደፊት ለመግፋት“ (ቁጥር 4) የሚቀላቀሉ የትብብር ድርጅት ለመስራት ትንሽ ቁጥር ያላቸው የቤተክርስቲያን መሪዎችን ጠራ። ነገር ግን በእነዚህ አስተዳደራዊ ጉዳዮችም እንኳን፣ ጌታ በዘላለማዊ ጉዳዮች ላይ አተኩሯል። በመጨረሻም የማተሚያ ቤት ወይም የመጋዘን አላማ—በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ በሚገኙት ሁሉም ሌሎች ነገሮች አይነት—ልጆቹ “በሰለስቲያል አለም ውስጥ ቦታ” እና “የዘለአለም ባለጠግነት“ እንዲቀበሉ ለማዘጋጀት ነው (ቁጥሮች 7፣ 18)። እናም እነዚያን በረከቶች አሁን ለመገንዘብ ከባድ ቢሆኑም፣ በየዕለት ስራ መካከል “ተደሰቱ፣ እንደሚገባችሁ እመራችኋለሁ“ በማለት ያረጋግጥልናል (ቁጥር 18)።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
እግዚአብሔር ሚስጥሮቹን ሊያውቋቸው ለሚፈልጉት ይገልጻል።
ከመጀመሪያው ራዕይ አስራ ሁለት አመት በኋላ፣ በያዕቆብ 1፥5ላይ ያለው “እግዚአብሔርን ይጠይቅ“ የሚለው ግብዣ ጆሴፍ ስሚዝን ጥበብ በጎደለው ጊዜ ሁሉ መምራቱን ቀጥሏል። አርሱ እና ስድኒ ሪግደን በመንፈስ መሪነት በሚተረጉሙት መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እየሰሩ ሳሉ፣ ስለ መፅሐፈ ራዕይ ጥያቄዎች በነበራቸው ጊዜ ጆሴፍ ከእግዚአብሔር እውቀትን ጠየቀ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77ን ስታነቡ፣ በመፅሐፈ ራዕይ በተገቢ ምዕራፎች ውስጥ ያላችሁን ግንዛቤ ለመመዝገብ አስቡ።
በተጨማሪም፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠኑ የነቢዩን የጆሴፍን ምሳሌ እንዴት ልትከተሉ እንደምትችሉ አሰላስሉ። “ምንድን ነው መገንዘብ ያለብኝ“ ብላችሁ የሰማይ አባታችሁን ልትጠይቁት ትችላላችሁ።
የትብብር ድርጅቱ ምን ነበር?
የትብብር ድርጅቱ በኦሃዮ እና በሚዙሪ ውስጥ የቤተክርስቲያኗን የህትመት እና የንግድ ጉዳዮች ለማስተዳደረር የተቋቋመ ነበር። ይህም በማደግ ላይ ያለችውን ቤተክርስቲያን ስጋዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ሀብቶቻቸውን ያዋሃዱትን ጆሴፍ ስሚዝን፣ ኒዊል ኬ. ውትኒን እና ሌሎችን የቤተክርስቲያን መሪዎች ያካትታል። እንደ መጥፎ እድል ሆኖ፣ የትብብር ድርጅቱ እዳ ውስጥ ገባ እናም እዳው ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑም በ1834 (እ.አ.አ) ፈረሰ።
“ኒዊል ኬ. ውትኒ እና የትብብር ድርጅት፣” ራዕይ በአገባብ፣ 142–47፤ “የትብብር ድርጅት፣” የቤተክርስቲያን ታሪክ ርዕሶች ChurchofJesusChrist.org/study/church–history።
የቤተክርስቲያንን “ምክንያት ወደፊት ለመግፋት” መርዳት እችላለሁ።
ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች ጎተራውን እና ማተሚያ ቤቱን ማስደደር “ራሳችሁ የተቀበላችሁትን ምክንያት ወደፊት ለመግፋት” ይረዳል ብሎ ነገራቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥4)። በሀሳባችሁ የቤተክርስቲያኗ “ምክንያት“ ምንድን ነው? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥1–7ን ስታነቡ ይህንን አሰላስሉ። ምናልባት ስለእነዚህ ጥቅሶች ማሰብ የቤተክርስቲያን ጥሪያችሁን በምታሟሉበት ወይም ቤተሰባችሁን በምታገለግሉበት መንገድ ተጽዕኖ ሊያደርግ ይችላል። አገልግሎታችሁ የጌታን “ምክንያት ወደፊት የሚገፋው“ እንዴት ነው? ይህስ “በሰለስቲያል አለም ውስጥ ቦታ ለማግኘት” እንዴት እያዘጋጃችሁ ነው? (ቁጥር 7)።
ጌታ ይመራኛል።
ምን አልባት “ገና ያልተረዳችሁት” ወይም “መሸከም ያልቻላችሁ“ አንድ ነገር እንደ ትንሽ ልጅ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ አድርጎ ያውቃልን? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥17–18)። “እንድትደሰቱ“ (ቁጥር 18) የሚረዳችሁን ምክር በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ፈልጉ። ጌታ ተከታዮቹን አንዳንድ ጊዜ “ትንሽ ልጆች“ ብሎ የሚጠራው ለምን ይመስላችኋል? (ቁጥር 17)። ጌታ እንዴት “እየመራችሁ“ እንደሆነ (ቁጥር 18) ልታሰላስሉ ትችላላችሁ።
ከማገለግልበት ቦታ ይልቅ እግዚአብሔርን ለማገልገል የተሰጠኝ ጥሪ ይበልጥ ትርጉም ያለው ነው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 80ን አስመልክቶ ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዳስተማሩት፣ “ምናልባትም አዳኝ በዚህ ራእይ ውስጥ እያስተማረን ያለው ትምህርት አንዱ፣ በተወሰነ ቦታ ላይ ተመድቦ ማገልገል አስፈላጊ እና ጠቃሚ ቢሆንም ነገር ግን የአገልግሎት ጥሪውን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው” (“ለስራው መጠራት፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 68)። የወቅቱን ወይንም ያለፈውን የቤተክርስቲያን ጥሪያችሁን አስቡ። የሽማግሌ ቤድናር ቃላት እውነት እንደሆኑ እንድትማሩ ምን ልምዶች ረድተዋችኋል? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 79–80 ውስጥ አንድ አዲስ ጥሪ የተቀበለን ሰው ሊረዳ የሚችል ምን ተጨማሪ ትምህርት ታገኛላችሁ?
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77፥2።ይህንን ጥቅስ ካነበባችሁ በኋላ፣ የቤተሰብ አባላት የሚወዷቸውን በእግዚአብሔር የተፈጠሩ “እንስሳትን፣ በምድር የሚንቀሳቀሱት እና የሰማይ አእዋፋት“ ሊስሉ ይችላሉ። ከዚህ ጥቅስ ስለእግዚአብሔር ፍጥረት ምን እንማራለን? (በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥16–20 ይመልከቱ)። እንደ የሰማይ አባቴ ይወደኛል ያሉ ስለ እግዚአብሔር ፍጥረት የሚያሰኙ መዝሙሮችን ልትዘምሩ ትችላላችሁ (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 228–29)፣ እናም ከዚህ መዘርዝር ጋር ያለውን ስዕል ልታሳዩ ትችላላችሁ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77፥14።ይህ ጥቅስ እስራኤልን የመሰብሰብ ሚስዮናዊ ስራውን የሚወክለውን መጽሃፍ እንደበላ ይገልጻል። የመብላቱ ምልክት እስራኤልን ለመሰብሰብ ወይም ጌታ እንድናደርግ የሚፈልገውን ሌሎች ነገሮች ለማድረግ የምንጫወተውን ሚና እንዴት ማየት እንዳለብን ምን ይጠቁማል? መብላትን የሚጠቀሙ፣ መንፈሳዊ እውነትን ለማስተማር ጥቅም ላይ የዋለባቸው አንዳንድ ቅዱስ ጽሁፎች እነሆ፥ ዮሀንስ 6፥48–51፤ 2 ኔፊ 32፥3፤ ሞሮኒ 4። ምናልባት በዚህ ውይይት ወቅት ቤተሰባችሁ የሚወደውን ምግብ ለመስራት እና አብራችሁ ለመብላት ትችላላችሁ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥17–19።የቤተሰብ አባላት ከእግዚአብሔር የተሰጡ አመስጋኝ የሆኑባቸውን በረከቶች ስዕሎች ሊስሉ ይችላሉ። ለእነዚህ በረከቶች ያለንን አመስጋኝነት ለመግለጽ ምን እያደረግን ነን? “ሁሉንም ነገሮች በምስጋና ተቀበሉ” (ቁጥር 19) የሚለውን ምክር ቤተሰባችሁ እንዴት እየተከተለ እንደሆነም ልትወያዩ ትችላላችሁ። ጌታ እንዲህ ለሚያደርጉ ምን ቃል ገብቷል?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 79፥1።በቤተክርስቲያን ጥሪ ስትሾሙ ወይም ስትለዩ ስለተቀበላችሁት “ሃይል” ምስክርነታችሁን አጋሩ። ስታገለግሉ ጌታ በምን ልዩ ስጦታዎች እና መነሳሳት ባረካችሁ?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ ”በረከቶቻችሁን ቁጠሩ፣“ መዝሙሮች፣ ቁጥር 241።