ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ሰኔ 21–27(እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67–70፥ “… ከአለም ሁሉ ሀብቶች በላይ ታላቅ ዋጋ”


“ሰኔ 21–27 (እ.አ.አ)። ትምህትና ቃል ኪዳኖች 67–70፥ ‘… ከአለም ሁሉ ሀብቶች በላይ ታላቅ ዋጋ እንዳላቸው’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 21–27 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67–70፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

revelation manuscript book in display case

ሰኔ 21–27 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67–70

“… ከአለም ሁሉ ሀብቶች በላይ ታላቅ ዋጋ እንዳላቸው”

ምንም እንኳን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ያሉት ራዕዮች ለተለዩ ሰዎች እና ለተወሰኑ ሁኔታዎች የተሰጡ ቢሆኑም፣ “ለሁሉም ጠቃሚዎች ናቸው” (“የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ስለትምህርት እና ቃል ኪዳኖች የተሰጠ ምስክርነት፣” introduction to the Doctrine and Covenants [የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ማስተዋወቂያ])። ስታጠኑ ለእናንተ የሚጠቅሙ እውነቶችን እና መርሆችን ፈልጉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ከ1828 እስከ 1831 (እ.አ.አ) ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለግለሰብ መለኮታዊ ምክርን፣ ቤተክርስቲያንን የማስተዳደር መመሪያን እና ስለኋለኛው ቀናት አነቃቂ መገለጦችን ጨምሮ ብዙ ራዕዮችን ተቀብሏል። ነገር ግን ብዙዎቹ ቅዱሳን አላነበቧቸውም ነበር። ራዕዮቹ ገና አልታተሙም ነበር፣ እናም የነበሩት ጥቂት ቅጂዎች አባላት የሚቀባበሏቸው እና ሚስዮናውያን ይዘዋቸው የሚዞሩት በወረቀት ላይ በእጅ የተጻፉ ነበሩ።

ከዚያም በህዳር 1831 (እ.አ.አ)፣ ጆሴፍ ራእዮችን ስለማሳተም ለመወያት የቤተክርስቲያን መሪዎች የምክር ስብሰባ አደራጀ። የጌታን ፈቃድ ከጠየቀ በኋላ፣ እነዚህ መሪዎች የትእዛዛት መፅሐፍን ለማሳተም አቀዱ—ለአሁኑ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መፅሐፍ መንገድ መንገድ አዘጋጅ ነበር። ወዲያው እያንዳንዱ ሰው በነቢዩ አማካኝነት የተገለጸውን የእግዚአብሔር ቃል ራሳቸው ለማንበብ ቻሉ “የአዳኛችን መንግስት ሚስጥር ቁልፎች እንደገና ለሰው በአደራ እንደተሰጡም ለማሳየት” ግልጽ ማስረጃ ሆነ። በእነዚህ እና በሌሎች ብዙ ምክንያቶች፣ ቅዱሳን እነዚህ ራዕዮች “ከአለም ሁሉ ሃብቶች በላይ ታላቅ ዋጋ እንዳላቸው” ያስባሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች የክፍል መግቢያ)።

ቅዱሳን፣ 1፥140–43ን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67፥1–968፥3–6

እግዚአብሔር ከአገልጋዮቹ ጋር ይሆናል ፤ እንዲሁም በስሙ ከሚናገሩት ቃላት ጋር።

በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት የተገለጸውን ራዕይ ማሳተም ቀላል ይመስል ነበር ነገር ግን አንዳንድ የመጀመሪያዎቹ የቤተክርስቲያን መሪዎች ጥሩ ሃሳብ እንደሆነ እርግጠኞች አልነበሩም። አንደኛው አሳሳቢ ነገር የነበረው ጆሴፍ ራዕዮቹን ለመጻፍ ከተጠቀመበት ፍጹም ያልሆነ ቋንቋ ጋር ግንኙነት አለው። በ ክፍል 67 ውስጥ ያለው ራዕይ የመጣው ለዚያ ስጋት ምላሽ ነበር። ከ ቁጥር 1–9 ስለነቢያት እና ስለራዕዮች ምን ትማራላችሁ? ከ 68፥3–6 ምን ተጨማሪ ግንዛቤ ታገኛላችሁ?

መጽሃፈ ትእዛዛት ከመታተሙ በፊት ብዙ የቤተክርስቲያን መሪዎች በመጽሃፉ ውስጥ ያሉት ራዕዮች ትክክል እንደሆኑ የሚገልጽ የጽሁፍ ምስክርነት ላይ ፈርመዋል። የምስክርነቱን ቅጂ ለማየትምስክርነት ህዳር 2 1831(እ.አ.አ) አካባቢየራዕይ መጽሃፍ 1፣121 josephsmithpapers.org ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥1–8

ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጣ መነሳሳት የእግዚአብሔርን ፍላጎት ያንጸባርቃል።

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉት ቃላት የተሰጡት ኦርሰን ሃይድ እና ሌሎች “በህያው እግዚአብሔር መንፈስ ዘላለማዊውን ወንጌል ከህዝብ ወደ ህዝብ እንዲሁም ከአገር አገር ለማወጅ”(ቁጥር 1) በተጠሩበት ጊዜ ነበር። በቁጥር 4 ውስጥ ያለው መልእክት ወንጌልን ለመስበክ ለተላከ ሰው እንዴት ሊረዳው ይችላል? እነዚህ ቃላት ለእናንተ የሚሆኑት እንዴት ነው? “በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት” ቁጥር 3 አንድ ነገር እንድትናገሩ ወይም እንድታደርጉ የተገፋፋችሁበትን ጊዜ አስቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የመንፈስ መመሪያን እንድትከተሉ ማስተማመኛ የሚሰጣችሁ ምን ነገር ታገኛላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25–28

ወላጆች ልጆቻቸውን ለማስተማር ሃላፊነት አለባቸው።

የመጀመሪያ ክፍል አጠቃላይ ፕሬዚዳንት የሆኑት እህት ጆይ ዲ. ጆንስ እንዳስተማሩት፣ “ልጆች ኃጢያትን የሚጠሉ እንዲሆኑ ለመርዳት ቁልፍ የሆነው ነገር ቢኖር፣ ገና በለጋነታቸው የወንጌልን መሰረታው አስተምህሮቶች እና መርሆዎች ከቅዱሳት መጻህፍት፣ ከእምነት አንቀጾች፣ ከለወጣቶች ጥንካሬ መፅሔት፣ ከመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮች፣ ከመዝሙሮች፣ እና ከራሳችን የግል ምስክርነቶች ውስጥ ልጆችን ወደ አዳኝ በሚመሩ ነገሮች በፍቅር እንዲማሩ በማስታጠቅ ነው (“ሀጥያትን የሚቃወም ትውልድ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2017(እ.አ.አ.)፣ 88።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25–28 መሰረት፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ሊያስተምሩ የሚገባቸው እህት ጆንስ የጠቀሷቸው “የወንጌል መሰረታዊ … መርሆዎች“ ምንድን ናቸው? ይህ ጠቃሚ ሃላፊነት ለወላጆች የተሰጠው ለምንድን ነው? እነዚህን ትምህርቶች ለልጁ ወይም ለልጇ ለማስተማር ብቁ እንደሆነ/ነች ለማይሰማው/ት ወላጅ ምን ትላላችሁ?

በተጨማሪም ታድ አር. ካሊስተር፣ “ወላጆች፥ የልጆቻቸው ዋነኞቹ የወንጌል አስተማሪዎች፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2014 (እ.አ.አ)፣ 32–34 ይመልከቱ።

ቤተሰቦች ሲያጠኑ

ቤት ልጆች ወንጌልን የሚማሩበት አመቺ ስፍራ ነው።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67፥10–14ምቀኝነት፣ ፍርሃት፣ እና ኩራት እንዴት ወደጌታ እንዳንቀርብ ያደርጉናል? “የተፈጥሮ ሰው“ በጌታ ፊት ለመገኘት ለምን አይችልም? (ቁጥር 12፤ ደግሞም ሞዛያ 3፥19 ይመልከቱ)። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “ፍጹም [እስክንሆን] ድረስ በትዕግስት [እንድንጸና]” (ቁጥር13) ሊያነሳሱ የሚችሉ ምን ታገኛላችሁ? ።

እንደቤተሰብ “ስለዚህም በመጨረሻ ፍፁም ሁኑ” ያለ ረዕስ ያለውን የሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድን መልዕክት ልትከልሱ ትችላላችሁ (ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር. 2017 (እ.አ.አ)፣ 40–42)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥3–4የጌታ አገልጋዮች ቃላት “የጌታ ፈቃድ” ፣“የእግዚአብሔር አእምሮ፣” እና “ለደህንነት የእግዚአብሔር ሃይልም” (ቁጥር 4) እንደሆኑ የቤተሰብ አባላት እምነታቸውን ያጠናከሩላቸውን ልምድ ሊያጋሩ ይችላሉ። ወይንም ቤተሰባችሁን ላጋጠመው አስቸጋሪ ሁኔታን የሚነካ የቅርብ የአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶችን ሊፈልጉ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25–35እነዚህ ጥቅሶች “ለጽዮን ኗሪዎች” (ቁጥር 26) ጠቃሚ መልዕክቶችን ይዘዋል። እነዚህን ጥቅሶች ካነበብን በኋላ ምን እንድናሻሽል እንነሳሳለን? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉ አንዳንድ መርሆዎችን የሚያሳዩ ስዕሎችን ማዘጋጀት እና በቤታችሁ መደበቅ አስደሳች ሊሆን ይችላል። ከዚያም፣ በቀጣዮቹ ቀናት አንድ ሰው አንድ ስዕል ሲያገኝ ያንን አጋጣሚ ስለዚያ መርህ ለማስተማር ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ። ቤት ልጆች እነዚህን ነገሮች ለመማር የተሻለ ስፍራ የሆነው ለምንድን ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 69፥1–2ኦሊቨር ካውድሪ ቤተክርስቲያኗን በዚያ ለመገንባት ለመርዳት የሚውል ገንዘብ እና የሚታተሙትን የነቢዩን ራዕዮች ቅጅዎች ይዞ ወደ ሚዙሪ ተልኮ ነበር። በቁጥር 1 ውስጥ ጌታ ስለ ኦሊቨር ጉዞ ምን አይነት ምክር ሰጥቷል? “እውነተኛ እና ታማኝ” ከሚሆኑ ሰዎች ጋር መሆን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ቁጥር 1)። ጓደኞች ጥሩ ወይም መጥፎ ውሳኔ እንድናደርግ መቼ ተጽዕኖ አድርገውብናል? በሌሎች ላይ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 70፥1–4ጌታ ለተወሰኑ ሽማግሌዎች የራዕዮቹን ህትመት ስራ በበላይነት የመቆጣጠር ሃላፊነት ሰጠ። ምንም እንኳን ያ የተለየ ሃላፊነት ባይጣልብንም፣ በምን መንገድ ነው የ“ራዕዮቹ እና ትዕዛዛት ጠባቂ“ ልንባል የምንችለው? (ቁጥር 3)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ቤት በምድር ላይ ያለ ገነት ሊሆን ይችላል፣” መዝሙር፣ ቁጥር 298።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ቅዱሳት መጻህፍትን ከሕይወታችን ጋር ማመሳሰል። የቅዱሳት መጻህፍትን ክፍል ካነበባችሁ በኋላ፣ የቤተሰቡ አባላት በህይወታቸው እንዲተገብሩት ጋብዟቸው። ለምሳሌ፣ ተመሳሳይ የወንጌል መርሆችን የሚመለከቱ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ተመሳሳይ ሁኔታዎችን እንዲያስቡ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ።

የግራንዲን የማተሚያ ቤት

የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መንገድ አዘጋጅ የነበረው የትእዛዛት መፅሐፍ በእንደዚህ ያለ ማተሚያ ላይ ነበር የታተመው።