ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ሰኔ 7–13 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥ “ከላይ የሚመጣው እርሱ ቅዱስ [ነው]”


“ሰኔ 7–13 (እ.አ.አ)። ትምህትና ቃል ኪዳኖች 63፥ ‘ከላይ የሚመጣው እርሱ ቅዱስ [ነው]’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 7–13 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
የሚዙሪ ሜዳ

ስፕሪንግ ሂል፣ ዴቪስ ካውንቲ፣ ሚዙሪ፣በጋርት ሮቢንሰን ኦቦርን

ሰኔ 7–13 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63

“ከላይ የሚመጣው እርሱ ቅዱስ [ነው]”

”መንፈሱን የምትቀበሉት በጸሎት በኩል ነው” ብሏል ጌታ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥64)። መንፈስ ጥናታችሁን ይመራላችሁ ዘንድ መጸለይን አስቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የፅዮን ከተማ መመስረቻ ስፍራ ተመርጦ ነበር። የቤተክርስቲያን መሪዎች ቦታውን ጎብኝተው እና ለቅዱሳን መሰብሰቢያነት እንዲሆን ቀድሰውት ነበር። በጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ መሰረት፣ “የፅዮን ምድርን በሚመለከት የጊዜው አሳሳቢ ጉዳይ [ነበር]” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63 የክፍል መግቢያ። ነገር ግን በፅዮን የሚታየው እይታ የተደባለቀ ነበር። ብዙ ቅዱሳን በምዙሪ መሰባሰብ ለመጀመር ጓጉተው ነበር። በሌላ በኩል፣ እንደ እዝራ ቡዝ ያሉ ሰዎች በፅዮን መሬት ተናደው ነበር እናም ሀሳባቸውን አሳውቀው ነበር። በእርግጥም፣ ጆሴፍ ከሚዙሪ ወደ ከርትላንድ ሲመለስ፣ እርሱ ባልነበረበት ሰአት ጠብ እና ክህደት ወደ ቤተክርስቲኗ ሰርገው ገብተው አገኛቸው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63 ውስጥ ያለው ራዕይ የመጣው በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ነበር። እዚህ ላይ ጌታ መሬት ስለመግዛት እና ቅዱሳኑን ወደ ሚዙሪ ስለማዛወር ተናገረ። ነገር ግን በእነዚህ ተግባራዊ ጉዳዮች ውስጥ “እኔ ጌታ ድምጼን አሰማለሁ፣ እና ይህም ይከበራል” (ቁጥር 5) የሚል ወቅታቂ ማስታወሻም ነበር። ድምጹ፣ ፍላጎቱ፣ ትእዛዙ—ሁሉም “[የመጡት] ከላይ ነው”—በጥርጣሬ ወይም በችላ መታየት የለባቸውም። “ቅዱስ [ነው]፣ እናም በጥንቃቄ … መነገር [አለበት]” (ቁጥር 64)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥1-6፣ 32-37

የጌታ ቁጣ በኃጢያተኞች እና በአመጸኞች ላይ ተቀጣጠለ።

ይህ ራዕይ በመጣ ጊዜ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ከብዙ ፊታቸውን ካዞሩበት የቤተክርስቲያኗ አባላት ሃይለኛ ትችት ገጥሞት ነበር (“Ezra Booth and Isaac Morley [እዝራ ቡዝ እና አይሳክ ሞርሊ]፣“ ራዕያት በአገባብ፣ 130–36 ይመልከቱ)። በትምህርትና ቃል ኪዳኖች 1፥1–6፣ 32–37 ውስጥ ጌታ ኃጢአተኞችን እና አመጸኞችን በተመለከተ ምን ማስጠንቀቂያ ሰጠ? እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች የእግዚአብሔር ፍቅር ማረጋገጫዎች የሆኑት እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥7–12

ምልክቶች የሚመጡት በእምነት እና በእግዚአብሔር ፍላጎት ነው።

ምልክቶች እና ተአምራት ብቻቸውን ዘላቂ እምነትን አያመጡም። በ1830 (እ.አ.አ) አመታት ውስጥ መጀመሪያ የሜተዲስት ሰባኪ የነበረው እዝራ ቡዝ ጆሴፍ ስሚዝ የቡዝ ጓደኛ የሆነውን የኤልሳ ጆንሰንን እጅ በተአምር ሲፈውስ ካየ በኋላ ለመጠመቅ ወሰነ።

ሆኖም በጥቂት ወራት ውስጥ ቡዝ እምነቱን አጣ እና ነቢዩን ተቺ ሆነ። አይቶ የነበረውን ተአምር ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥7–12ን ስታነቡ ይህንን አሰላስሉ። አንዳንድ ሰዎች ምልክቶችን “ለሰዎች ጥቅም እና [ለእግዚአብሔር ክብር]” (ቁጥር 12) ሌሎች ደግም “ለእርግማን …” (ቁጥር 11) ለምን እንደሚቀበሉ ማሰብ ትችላችሁ። ባነበባችሁት መሰረት፣ ጌታ ምልክቶችን በተመለከተ እንዴት ማሰብ እንዳለባችሁ እና ምን አይነት ስሜት እንዲሰማችሁ የሚፈልግ ይመስላችኋል።

በተጨማሪምየማቴዎስ 16፥1–4ዮሃንስ 12፥37ሞርሞን 9፥10–21ኤተር 12፥12, 18ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥13–23

ንጽህና ማለት ሃሳቦቼን እና ድርጊቶቼን ንጹህ ማድረግ ማለት ነው።

ብዙ ሰዎች ዝሙት ስህተት እንደሆነ ይቀበላሉ። ነገር ግን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥13–19 ውስጥም የዝሙት ሃሳቦችም ከባድ መንፈሳዊ ውጤቶች እንዳሏቸው አዳኝ ግልጽ አድርጓል። “የዝሙት ሃሳብ ከባድ ኃጢያት የሆነው ለምንድን ነው”? በማለት ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ ጠይቀዋል። “በነፍሶቻችን ላይ ካለው ሙሉ ለሙሉ መንፈስ ሰባሪ ውጤቱ በተጨማሪ፣ በዚህ ሟች ህይወታችን አግዚአብሔር የሰጠንን ታላቅ እና የተቀደሰ ግንኙነት የሚያረክስ በመሆኑ ምክንያት ኃጢያት እንደሆነ አስባለሁ—ወንድና ሴት አንዳቸው ላንዳቸው ያላቸው ፍቅር እና ጥንዶች ልጆችን ወደ ቤተሰብ ለማምጣት ያላቸው ፍላጎት ዘላለማዊ እንዲሆን የታሰበ ነው” (“ለነፍሴ ጠላት ከእንግዲህ ቦታ የለም፣”ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት (እ.አ.አ) 2010፣ 44)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥13–19 ውስጥ ንጽህና በጎደላቸው ሃሳቦች እና ድርጊቶች ንስሃ በማይገቡ ሰዎች ላይ ስለሚመጡት ውጤቶች ጌታ ምን ጠቅሷል? አዳኝ በቁጥሮች 20 እና 23 ውስጥ ታማኝ ለሆኑት ቃል የገባቸውን በረከቶች ልብ በሉ። የንጽህና ህግን በማክበር ምን አይነት በረከቶች ወደ ህይወታችሁ ገብተዋል? አዳኝ ወደ ንጽህና እንድትመጡ ወይም ንጹህ እንደሆናችሁ እንድትቀጥሉ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥45፣ ሊንዳ ኤስ. ሪቭስ “ቃል ለተገቡልን በረከቶች ብቁ መሆን፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 9–11 ይመልከቱ።

ምስል
ወንድ እና ሴት በቤተመቅደስ አጠገብ

ሃሳቦቻችንን እና ድርጊቶቻችንን ንጹህ አድርገን ስንጠብቅ እንባረካለን።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥24–46

ጌታ የቅዱሳንን መንፈሳዊ እና ስጋዊ ጉዳዮች ይመራል።

ጌታ ፅዮን የት እንደምትገነባ ካመለከተ በኋላ፣ በኦሃዮ የነበሩት ቅዱሳን መቼ መዛወር እንዳለባቸው እና መሬቱን ለመግዛት ገንዘብ ከየት እንደሚያገኙ አሁንም መመረሪያ አስፈልጓቸው ነበር። ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 63፥24–46ን ስታነቡ፣ ፅዮንን በተመለከተ ጌታ ምን አይነት መንፈሳዊ እና ስጋዊ መመሪያ እንደሰጠ ፈትሹ። ጌታ ምን አይነት መንፈሳዊ እና ስጋዊ መመሪያ እየሰጣችሁ ነው?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥7–12የኤልሳ ጆንሰንን መፈወስ በሚመለከትም የእዝራ ቡዝ ቤተክርስቲያንን የመተው ታሪክ ስለ ተአምራት ውይይት ሊያነሳሳ ይችላል (“ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች” በሚለው ርዕስ ስር እና ከዚህ መዘርዝር ጋር ካለው የጥበብ ስራ ውስጥ ዝርዝሩንም ይመልከቱ)። ከቤተሰባችሁ ወይም ከቤተሰባችሁን ታሪክ ውስጥ ከሚገኙት ተሞክሮ በተጨማሪ፣ የቤተሰብ አባሎቻችሁ እምነታቸውን ስላጠናከሩላቸው ተአምራት ሊናገሩ ይችላሉ። እነዚህን ተአምራት ለመቀበል የሚያስፈልገውን እምነት እንዴት በተግባር አዋሉት። ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 63፥7–12 በእምነት እና በተአምራት መካከል ስላለው ግንኘነት ምን ያስተምራል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥13–19ወሲባዊ ምስል እና ቪዲዮዎችን ጨምሮ ከማይጠቅሙ ተጽዕኖዎች ራሳችንን መከላከል የምንችለው እንዴት ነው? ለቤተሰብ የሚሆኑ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን በAddressingPornography.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ ታገኛላችሁ። የንጽህናን ህግ መኖር የሚያስገኘው በረከት ምንድን ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥23“[የመንግስት] ሚስጥራት“ ወይም የወንጌል እውነቶች እንዴት እንደ “ህያው ውኃ ምንጭ“ እንደሆኑ ይገነዘቡ ዘንድ ቤተሰባችሁን እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ? ለምሳሌ፣ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ ምንጭ ወይም ወንዝ ልትሄዱ (ወይንም ቪዲዮውን ወይም ፎቶውን ልታሳዩ) ትችላላችሁ። የወንጌል እውነት እንደ ውሃ የሆነው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥58ክፍል 63 ውስጥ ምን ማስጠንቀቂያዎችን እናገኛለን? ዛሬ ከቤተክርስቲያን መሪዎቻችን እየሰማናቸው ያሉ አንዳንድ ማስጠንቀቂያዎች ምን ምን ናቸው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥58–64ውድ የሆነ የቤተሰብን ሀብት ለቤተሰባችሁ አሳዩ። እንደዚህ ውድ ካልሆኑት አብልጠን እንዴት ነው ይህንን ነገር በተለየ ሁኔታ የምንይዘው? ለተቀደሱ ነገሮችን ጥልቅ አክብሮት ለመስጠት ምን ማድረግ እንደምንችል ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 63፥58–64 ምን ያስተምረናል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “አምልኮት ፍቅር ነው፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 31።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የምትማሩትን ኑሩበት። “ወንጌሉን ከመገንዘብ የሚመጣው ደስታ ሲሰማችሁ የተማራችሁትን ነገር በተግባር ለማዋል ትፈልጋላችሁ። ከተገነዘባችሁት ነገር ጋር በመስማማት ለመኖር ጣሩ። ይህንን ማድረግ እምነታችሁን፣ እውቀታችሁን እና ምስክርነታችሁን ያጠነክርላችኋል (ወንጌሌን ስበኩ፣ 19)።

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ የሴትን እጅ ይዞ

የኤልሳ ጆንሰን ትከሻ መፈወስ፣ በሳም ላውሎር

አትም