ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ግንቦት 31–ሰኔ 6 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60–62፥ “ሁሉም ስጋ በእጄ ነው”


“ግንቦት 31–ሰኔ 6 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60– 62፥ ‘ሁሉም ስጋ በእጄ ነው’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 31–ሰኔ 6 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60–62፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
የምዙሪ ወንዝ

ሰፋሪዎች እሳት የሚያቃጥሉበት ቦታ፣ በብራያን ማርክ ቴይለር

ግንቦት 31–ሰኔ 6 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60–62

“ሁሉም ስጋ በእጄ ነው“

ፕሬዚዳንት ኤዝራ ቴፍት ቤንሰን እንዳስተማሩት ቅዱሳት መጻህፍትን ስናጠና “ምስክርነት ይጨምራል። ቁርጠኝነት ይጠነክራል። ቤተሰቦች ይታንጻሉ። የግል ራዕይም ይመጣል።” (“የቃል ሀይል፣” ኢንዛይን፣ ግንቦት 1986 (እ.አ.አ)፣ 81)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በሰኔ 1881 ጆሴፍ ስሚዝ ከቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች ጋር በከርትላንድ በጉባኤ ተሰበሰቡ። በዚያም ጌታ አንዳንድ ሽማግሌዎችን በጥንድ አደራጀ፣ ከዚያም ወደ ጃክሰን ካውንቲ ሚዙሪ “በየመንገዱ እንዲያስተምሩ “ አዝዞ ላካቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 52፥10)። ብዙዎቹ ሽማግሌዎች በታታሪነት እንደታዘዙት አደረጉ፣ ነገር ግን ሌሎች አላደረጉም። ስለዚህ ወደ ከርትላንድ የመልስ ጉዞ የማድረጊያው ቀን ሲመጣ፣ ጌታ እንዲህ አለ፣ “በአንዳንዶች [ሽማግሌዎች] አልተደሰትኩም፣ አንደበቶቻቸውን አልከፈቱምና፣ ነገር ግን ሰውን በመፍራት የሰጠኋቸውን ችሎታ ደብቀዋል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥2)። ብዙዎቻችን ለእነዚህ ሽማግሌዎች አዘኔታ ይሰማናል—እኛም ደግሞ አፋችንን ለመክፈት እና ወንጌልን ለማካፈል የማመንታት ስሜት ሊሰማንም ይችላል። ምናልባት እኛም “በሰዎች ፍርሃት” ተወረን ይሆናል። ምናልባት ብቁነታችንን እና ችሎታችንን ተጠራጥረን ይሆናል። ምክንያታችን ምንም ይሁን ምን፣ ጌታ “የሰውን ድክመት [እና እንዴት እንደሚረዳን ያውቃል]” (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 62፥1)። ለመጀመሪያ ሚስዮናውያን በተሰጠው በዚህ ራዕይ ውስጥ ወንጌልን ለማካፈል ያሉብንን ፍርሃቶች ወይም የሚያጋጥሙን ሌሎች ፍርሃቶች ለመቋቋም ሊረዱን የሚችሉ ማረጋገጫዎች ተዘርዝረው ይገኛሉ፥ “እኔ ጌታ ከላይ በሰማያት … እገዛለሁ።” “ቅዱሳን አደርጋችሁ ዘንድ ይቻለኛል።” “ሁሉም ስጋ በእጄ ነው።” እናም “ሀህጻናት ሆይ፣ ተደሰቱ፤ በመካከላችሁ ነኝና።” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥4 ፣761፥6፣ 36።)

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6062

ጌታ ወንጌልን ለማካፈል አፌን ስከፍት ይደሰታል።

ወንጌልን ከሌላ ሰው ጋር ለማካፈል እንችል የነበረበት አጋጣሚ ሁላችንም አግኝተን፣ ነገር ግን በሆነ ምክንያት፣ ያላደረግንበት አጋጣሚ ሁላችንም አለን። ጌታ ”አፋቸውን መክፈት” ላልቻሉ ለመጀመሪያዎቹ ሚስዮናውያን የተናገራቸውን ቃላት ስታነቡ፣ የራሳችሁን ወንጌልን የማካፈል አጋጣሚዎች አስቡ። የወንጌል ምስክርነታችን “የተፈጥሮ ስጦታ“ ወይም ከእግዚአብሔር የተሰጠ ሃብት የሚሆንልን እንዴት ነው? አንዳንድ ጊዜ በምን አይነት መንገዶች “ችሎታ[ችንን] እንደብቃለን”? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥2፤ እንዲሁም ማቴዎስ 25፥14–30 ይመልከቱ)።

ጌታ ለእነዚህ የመጀመሪያ ሚስዮናውያን ማረሚያ ሰጣቸው፣ ነገር ግን ደግሞ ሊያነቃቃቸውም ሞከረ። በክፍል 60 እና 62 ውስጥ ከእርሱ ምን አበረታች መልእክቶች ታገኛላችሁ? እነዚህ መልእክቶች ወንጌልን ለማካፈል በራስ መተማመናችሁን የሚገነቡት እንዴት ነው? በመጪዎቹ ጊዜያት፣ አፋችሁን ለመክፈት እና እግዚአብሔር በአደራ የሰጣችሁን ሃላፊነት የምትካፈሉበትን አጋጣሚዎች ፈልጉ።

ትምህርተ እና ቃል ኪዳኖች 33፥8–10103፥9–10፤ ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “የሚስዮናውያን ስራ ፥ በልብህ ውስጥ ያለውን ማካፈል፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 15–18 ይመልከቱ።

ምስል
ሚስዮናውያን በአውቶቡስ

እግዚአብሔር ወንጌልን ለሌሎች እንዳካፍል ይፈልጋል?”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 61፥5–6፣ 14–18።

ውሃዎች ሁሉ በጌታ ተረግመዋልን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 61 ውስጥ ያሉት የጌታ ማስጠንቀቂያዎች፣ በከፊል ህዝቦቹ በዚያን ወቅት በአደገኝነቱ በሚታወቀው በምዙሪ ወንዝ ላይ ወደ ጽዮን በሚጓዙበት ወቅት ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉት አደጋዎች የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎች ነበሩ። ይህ ማስጠንቀቂያ በውሃ ላይ ከመጓዝ መታቀብ እንዳለብን ማለት እንደሆነ ተደርጎ መተርጎም የለበትም። ጌታ በውሃ ላይ ያለውን ሃይል ጨምሮ ”በሁሉም ሃይል” አለው (ቁጥር 1)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 61–62

እግዚአብሔር ሃያል ነው እናም ሊጠብቀኝ ይችላል።

ወደ ከርትላንድ እየተመለሱ እያሉ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች በሚዙሪ ወንዝ ላይ ለህይወት የሚያሰጋ አደጋ አጋጥሟቸው ነበር። (ቅዱሳን፣ 1፥133–34)። ጌታ ይህንን አጋጣሚ አገልጋዮቹን ለማስጠንቀቅ እና ለማስተማር ተጠቀመበት። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 61 ውስጥ እናንተም ከአሰቸጋሪ ጊዜ ጋር ስትጋፈጡ እምነታችሁን በጌታ ላይ እንድታደርጉ የሚያበረታታ ምን ነገር ታገኛላችሁ? ለምሳሌ፣ እግዚአብሔር “ከዘለአለም እስከ ዘለአለም“ መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ቁጥር 1)።

ተመሳሳይ ሃሳቦችም በክፍል 62 ውስጥ አሉ። ጌታ ስለራሱ እና በዚህ ራእይ ውስጥ ስላለው ሃይሉ ምን ያስተምራችኋል?

ጌታ መንፈሳዊ ወይም አካላዊ መከራን እንድትቋቋሙ በረዳችሁ ጊዜ ያጋጠሟችሁን እምነት የሚገነቡ ልምዶች አሰላስሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 62

ጌታ “ለእኔ ትክክል የሚመሰሉኝን“ ውሳኔዎች እንዳደርግ ይፈልጋል።

አንዳንድ ጊዜ ጌታ የተለየ መመሪያ ይሰጠናል፣ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን እኛ እንድንወስንባቸው ይተውልናል። ይህ መርህ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 62 ውስጥ በምሳሌ ሲሰጡ ትዩታላችሁ? (ደግሞም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥561፥22 ይመልከቱ)። ይህንን መርህ በህይወታችሁ እንዴት ነው ያያችሁት? ከእግዚአብሔር የተለየ መመሪያ ሳይሰጠን አንዳንድ ውሳኔዎችን ማድረጋችን ለምን ለእኛ ጥሩ ይሆናል?

ደግሞም ኤተር 2፥18–25ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥27–28 ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥2–3አንዳንድ የመጀመሪያ ሚስዮናውያን ወንጌልን ለማካፈል ማመንታት የነበራቸው ለምን ነበር? አንዳንድ ጊዜ ለምን እናመነታታለን? የቤተሰብ አባላት በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ወንጌልን እንዴት ማካፈል እንደሚችሉ የሚያሳይ ትዕይንት መጫወት አስቡበት።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 61፥36–39በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “ደስተኛ ለመሆን“ ምን ምክንያቶች እናያለን? (በተጨማሪም ዮሀንስ 16፥33 ይመልከቱ)። ምናልባት ቤተሰባችሁ ደስታ ሊያመጡላቸው የሚችሉ ነገሮችን ሊጽፉ ወይም ስእል ሊስሉ እና “በደስታ ማሰሮ“ ውስጥ ሊያጠራቅሙ ይችላሉ። (የአዳኙን ምስል እና ለእኛ ያለውን ፍቅር አስታዋሾች ማካተታችሁን እርግጠኛ ሁኑ።) ሳምንቱን በሙሉ ቤተሰቡ ደስተኛ ለመሆን ምክንያት የሚሆን አስታዋሽ ሲፈልጉ ከማሰሮ ውስጥ አንድ ነገር መምረጥ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 61፥36አዳኝ “[በመካከላችን]“ እንደሆነ ቤተሰባችሁ እንዲያስታውስ እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? የእርሱን ምስል በቤታችሁ በዋናነት የት እንደምታደርጉ አብራችሁ ልትወስኑ ትችላላችሁ። አዳኝን በእለት ተዕለት ህይወታችን እንዴት ልንጋብዘው እንችላለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 62፥3ምናልባት ይህንን ጥቅስ ካነበባችሁ በኋላ የቤተሰብ ምስክርነት ስብሰባ ሊኖራችሁ ይችላል። ምስክርነት ምን እንደሆነ ለማብራራት፣ ከሮናልድ ኤም. ራዝባንድ መልእክት። “ንፁሕ ምስክርነት” ውስጥ ጥቂት ልታካፍሉ ትችላላችሁ(ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር. 2004 (እ.አ.አ)፣ 40–43)። ምስክርነታችንን መመዝገብ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 62፥5፣ 8ለምንድን ነው ጌታ ለእያንዳንዱ የህይወታችን ሁኔታ ትእዛዛት ያልሰጠው? በቁጥር 8 መሰረት፣ እንዴት ነው ውሳኔዎችን ማድረግ ያለብን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ምስክርነት፣” መዝሙር፣ ቁጥር 137።

የግል ጥናትን ማሻሻል

መንፈስ ጥናታችሁን ይመራላሁ ዘንድ ፍቀዱ። መንፈስ ቅዱስ ይምራችሁ ዘንድ ፍቀዱ። ምንም እንኳን ሹክሹክታው እናንተ ከለመዳችሁት የተለየ ርዕስ ወይም በተለየ መንገድ እንድታነቡ ወይም እንድታጠኑ ቢጠይቅም፣ በየእለት መማር ወዳለባችሁ ነገሮች በሚመራችሁ ጊዜ ለሹክሹክታው ንቁ።

ምስል
ኢየሱስ ጠቦትን ተሸክሞ

መልካም እረኛ፣በ ዴል ፓርሰን

አትም