ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ግንቦት 24–30 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58–59፥ “መልካም ስራን በጉጉት ማከናወን“


“ግንቦት 24–30 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58–59፥ ‘መልካም ስራን በጉጉት ማከናወን፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 24–30 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58–59፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢንድፔንደንስ፣ ሚዙሪ ጎዳና

ንዲፔንደንስ፣ ሚዙሪ፣ በአል ራውንድስ

ግንቦት 24–30 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58–59

“መልካም ስራን በጉጉት ማከናወን“

ፕሬዚደንት ዳልን ኤች. ኦክስ እንዳስተማሩት፣ “ቅዱሳት መጻህፍት ሁሉንም የግል ጥያቄዎቻችንን ለመፍታት ይረዱናል ምክንያቱም እነርሱን በማንበብ መንፈስ ቅዱስን እንጋብዛለን እናም ለመነሳሳት ራሳችንን ብቁ እናደርጋለን፣ እርሱም ወደ እውነት ሁሉ ይመሩናል” (በዴቪድ ኤ. ኤድዋርድ “መልሶቼ እዚያ ውስጥ አሉን?” ውስጥ ኒው ኤራ፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 42)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች በመጀመሪያ የፅዮንን ከተማ ቦታ፣ ኢንድፔንደንስ፣ ሚዙሪን፣ ሲመለከቱ እንደጠበቁት ሆኖ አላገኙትም። አንዳንዶች የበለጸጉ ታታሪ ማህበረሰብና ጠንካራ የቅዱሳን ቡድን እንደሚያገኙ አስበው ነበር። ከዚያ ይልቅ በብዛት ሰዎች ያልነበሩበት፣ የለመዱትን ስልጣኔ ያጡ እና ከቅዱሳን ይልቅ አስቸጋሪ የድንበር ሰፋሪዎች የሰፈረሩበት ቦታ ነበር ያገኙት። ጌታ ወደ ፅዮን እንዲመጡ ብቻ አልነበረም የጠየቃቸው—እርሱ ይህችን እንዲገነቧት ፈልጓቸው ነበር።

ግምቶቻችን ከእውነታው ጋር በማይገናኙ ጊዜ፣ ጌታችን በ1881 (እ.አ.አ) ለቅዱሳን የነገራቸውን ማስታወስ እንችላለን፥ “ከዚህ በኋላ … አምላካችሁ ያቀደው እናም ብዙ መከራን ተከትሎ የሚመጣውን ክብር በዚህ ጊዜ በተፈጥሮ አይኖቻችሁ ልታዩ አትችሉም“ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥3)። አዎን፣ ህይወት በፈተና እንዲሁም በክፋት የተሞላ ነች፣ ነገር ግን “ብዙ ጽድቅንም መስራት [እንችላለን]፤ ሀይል [በእኛ] ውስጥ ነውና” (ቁጦርች 27–28)።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥127–33ን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥1–5፣ 26–33፣ 4459፥23

በረከቶች የሚመጡት በእግዚአብሔር ሰአት እና በእኛ ትጋት ነው።

ቅዱሳን በብዙ ፈተናዎች በጸኑበት በጃክሰን ካውንቲ፣ ሚዙሪ ውስጥ የፅዮንን መሰረት ጣሉ። በሕይወት እያሉ ይህ አካባቢ ሁሉም ቅዱሳን ሊሰበሰቡበት ወደሚችሉበት ስፍራ ያድጋል ብለው ተስፋ አድርገው ነበር። ነገር ግን፣ ቅዱሳኑ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከጃክሰን ካውንቲ ተሰድደውው ወጡ፣ እንዲሁም ጌታ ህዝቦቹ “የፅዮን ቤዛነት ለትንሽ ዘመን ይጠብቁ” ብሎ ገልጧል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 105፥9)።

የሚከተሉትን ምንባቦች ስታጠኑ፣ ለተወሰነ ጊዜ በረከቶች ሊዘገዩ የሚችሉባቸውን ምክንያቶች ፈልጉ። ከዚህ በታች ያሉት ጥያቄዎች እንድታሰላስሉ ሊረዷችሁ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥1–559፥23 በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ የትኞቹ መልእክቶች ናቸው መከራን የበለጠ በትዕግሥት የመቋቋም ችሎታችሁን የሚያጠናክሩት? ከፈተናዎች በኋላ ምን በረከቶችን ተቀብላችኋል? አንዳንድ በረከቶች ከመከራ በኋላ ብቻ የሚመጡት ለምን ይመስላችኋል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥26–33 “መልካም ስራን በጉጉት የሚያከናውኑ” መሆን የአምላክ ቃል ኪዳኖች እንዲፈጸሙ በማድረግ ረገድ ምን ሚና ይጫወታል? ታዛዥነታችሁ ምን ሚና ይጫወታል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥44 “በእምነት ጸሎት“ እና ጌታ ለእኛ ባለው ፈቃድ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፣ የክፍል መግቢያ

ፖሊ ናይት ማን ነበረች?

ፖሊ ናይት እና ባለቤቷ ጆሴፍ ናይት ቀዳማዊ ከጆሴፍ ስሚዝ ነቢያዊ ጥሪ አማኞች ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ነበሩ። ፖሊ እና ጆሴፍ በመፅሐፈ ሞርሞን የመተርጎም ስራ ላይ ለነቢዩ ወሳኝ ድጋፍ ሰጥተዋል። የናይት ቤተሰብ ኦሃዮ ውስጥ ከቅዱሳኑ ጋር ለመሰብሰብ ኮልቪል፣ ኒው ዮርክን ለቀቁ እና በኋላም ወደ ጃክሰን ካውንቲ፣ ሚዙሪ እንዲሄዱ ታዘዙ። በሚጓዙበት ጊዜ የፖሊ ጤንነት ማሽቆልቆል ጀመረ፣ ነገር ግን ከመሞቷ በፊት ፅዮንን ለማየት ቆርጣ ነበር። ስትሞትም ሚዙሪ ውስጥ የነበረችው ለጥቂት ቀናት ብቻ ነበር (ቅዱሳን፣ 1፥127–28132–33 ይመልከቱ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59 የመጣው እርሷ ያረፈች እለት ነበር፣ እናም ቁጥሮች 1 እና 2 በተለይ ስለ እርሷ የሚያወሩ ይመስላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥9–19

ሰንበትን ማክበር ስጋዊ እና መንፈሳዊ በረከቶችን ያስገኛል።

ጌታ በፅዮን ውስጥ ለሚገኙት ቅዱሳን “ጥቂት ባልሆኑ ትእዛዛት“ ለመባረክ ቃል ከገባ በኋላ፣ ለአንድ ትእዛዝ ለየት ያለ ትኩረት ሰጠ፥ የእርሱን “የተቀደሰ ቀን” የማክበር ትእዛዝ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥4 ፣9)። ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 59፥9–19ን ስታነቡ፣ ቅዱሳን ፅዮንን እየገነቡ ሳሉ ሰንበትን ማክበር ለእነርሱ ለምን እጅግ አሰፈላጊ እንደሆነ አሰላስሉ።

እንደነዚህም ያሉ ጥያቄዎችንም ልታስቡባቸው ትችላላችሁ፥ የሰንበትን ቀን ጌታ እንደሚፈልገው እጠቀማለሁን? የሰንበትን ቀን መቀደስ ራሴን “ከአለም ነገሮች ራስን ንጹህ እና ነውር የሌለበት ለማድረግ“ እንዴት ይረዳኛል? (ቁጥር 9)። “ለልዑል አምልኮን ለመስጠት“ ምን ማድረግ እችላለሁ? (ቁጥር 10)።

ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ፣ የሰንበትን ቀን ሙሉ በሙሉ ለመጠበቅ ምን ለማድረግ ትነሳሳላችሁ? ዘፍጥረት 2፥2–3ዘጸአት 20፥8–1131፥13፣ 16ኦሪት ዘዳግም 5፥12–15ኢሳይያስ 58፥13–14ማርቆስ 2፥27ዮሃንስ 20፥1–19የሃዋርያት ስራ 20፥7

እንዲሁም ሰንበትን ከሚመለከቱ በsabbath.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ የሚገኙትን ብዙ ቪዲዮዎች ወይም ሌሎች የጥናት ምንጮች ልትጠቀሙ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ይመልከቱ፥ ራስል ኤም. ኔልሰን፣“ቅዱስ ቁርባን ደስታ ነው፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣129–32፤ የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “ሰንበት”።

ምስል
ዳቦ እና የቅዱስ ቁርባን ጽዋዎች

ከቅዱስ ቁርባን መካፈል የሰንበትን ቀን ቅዱስ የማድረግ አንድ አካል ነው።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥26–29ምናልባትም የቤተሰብ አባላት “በጉጉት የሚያከናውኗቸውን“ የተወሰኑ ነገሮችን ዝርዝር ማዘጋጀት ይችሉ ይሆናል። ሁሉም “መልካም ስራዎች“ ናቸውን? ጌታ ለምንድነው “ብዙ ነገሮችን [በራሳችን] ምርጫ እንድናደርግ“ የሚፈልገን? በዚህ ሳምንት “ብዙ ጽድቅን ለመስራት” ምን ማድረግ እንደሚችሉ እንዲያስቡ እያንዳንዱን የቤተሰብ አባል ጠይቁ። በኋላም ስላደረጉት ነገር ሀተታ መስጠት ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42–43የቤተሰብ አባላት እነዚህን ጥቅሶች ሲያነቡ ምን ይሰማቸዋል? እነዚህ ጥቅሶች ንስሐ መግባት የሚያስፈልገውን ሰው እንዴት ሊረዱት ይችላሉ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥3–19በ“ትእዛዛት … አክሊል [ይቀበላሉ]“ ማለት ምን ሊሆን ይችላል? (ቁጥር 4)። በቁጥሮች 5–19 ውስጥ ያሉትን ትዕዛዛት ስታነቡ፣ በእያንዳንዱ ትዕዛዛት በመታዘዝ ያገኛቸኋቸውን በረከቶች ተወያዩባቸው።

እንዲሁም “ደስታ” “ፍስሃ“ “የሚሉት ቃላት የሰንበትን ቀን አክብሩ የሚለውን ትዕዛዝ ለመግለጽ እንዴት እንደሚያመለክቱ ማስተዋል ትችላላችሁ። የሰንበትን ቀን እንዴት ይበልጥ አስደሳች ለማድረግ ትችላላችሁ? ምናልባት የሰንበትን ቀን ለመቀደስ ማድረግ የምትችሏቸውን ነገሮች በሚያመለክቱ ካርዶች ቤተሰባችሁ የግጥሚያ ጨዋታ ለማዘጋጀት ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥18–21በሁሉም ነገሮች ውስጥ “የእርሱ እጅ እንዳለበት … ለመመስከር” ምን ማድረግ እንችላለን? ቁጥር 21)። “…አይንና ልብን የሚያስደሰቱ “ነገሮችን ለማስተዋል በእግር ለመሄድ ወይም ስዕሎችን ለመመልከት አስቡ (ቁጥር 18)። የምታገኟቸውን ነገሮች ፎቶ ማንሳት ወይም መሳል ትችላላችሁ፣ ከዚያም ለእነዚህ ነገሮች ያላችሁን አመስጋኝነት እንዴት ማሳየት እንደምትችሉ መወያይርት ትችላላችሁ። በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን እጅ እንዴት አይተናል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ትክክለኛውን ምረጥ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 239።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ቅዱሳት መጻህፍትን ማጋራት። የቤተሰብ አባላት በግል ጥናታቸው ያገኟቸውን ለእነሱ ትርጉም የሰጧቸውን የቅዱስ መጻህፍት ምንባቦች እንዲያካፍሉ ጊዜ ስጧቸው።

ምስል
ሴት ልጅ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ስትጸልይ

ስእል በማርቲ ሜጀር

አትም