ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ግንቦት 10–16 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49–50፥ “ከእግዚአብሔር የሆነው ብርሀን ነው”


“ግንቦት 10–16 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49– 50፥ ‘ከእግዚአብሔር የሆነው ብርሀን ነው፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 10–16 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49–50፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ኩሬ በንጋት

ግንቦት 10–16 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49–50

“ከእግዚአብሔር የሆነው ብርሀን ነው”

“ብርሀንን ተቀብሎ በእግዚአብሔር የሚቀጥል፣ ተጨማሪ ብርሀንን ይቀበላል፤ እናም ብርሀኑም ፍጹም እስከሆነው ቀን ድረስም እየጨመረ ይበራል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥24)። በእግዚአብሔር በመቀጠል እንዴት ብርሃን እየተቀበላችሁ እንዳላችሁ አሰላስሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

አዳኝ የእኛ “መልካም እረኛ” ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥44)። እርሱም አንዳንድ ጊዜ በግ ዘወር ሊል እንደሚችል እና ምድረበዳውም ብዙ አደጋዎች እንዳሉት ያውቃል። ስለዚህ “አለምን የሚያታልሉ፣ በምድር ውስጥ የሚሄዱ፣ ብዙ የሀሰት መናፍስት የሆኑ መናፍስት” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥2 ከመሳሰሉት አደጋዎችም እንድንርቅ በመርዳት፣ በፍቅር ወደ ትምህርቱ ደህንነት ይመራናል። አብዛኛውን ጊዜ እሱን መከተል ማለት የተሳሳቱ ሃሳቦችን እና ልማዶችን መተው ማለት ነው። ይህም በኦሃዮ ለሚኖሩት ዳግም የተመለሰውን ወንጌል ለተቀበሉ ነገር ግን አሁንም ትክክል ያልሆኑ እምነቶችን ለያዙ ሊመን ኮፕሊ እና ለሌሎች እውነት ነበር። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49 ውስጥ ጌታ እንደ ጋብቻ እና የአዳኝ ዳግም ምፃት በመሳሰሉ ርእሶች ያሉ የሊመንን የቀድሞ እምነቶች የሚያስተካክሉ እውነቶችን አወጀ። የኦሃዮ አዳዲስ አባላት “የማይገባቸውን መናፍስት ሲቀበሉ፣” የመንፈስን እውነተኛ መገለጫዎች እንዴት ማስተዋል እንደሚችሉ ጌታ አስተማራቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50–15)። መልካሙ እረኛ ታጋሽ ነበረ፤ የመጀመሪያዎቹ ቅዱሳን፣ ልክ እንደኛም፣ “በጸጋ እና በእውነት እውቀትም ማደግ” ያለባቸው “ህጻናት“ እንደነበሩ ያውቅ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥40)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49፥5–23

የወንጌል እውነቶች የተሳሳቱ ትምህርቶችን እንዳውቅ ሊረዱኝ ይችላሉ።

በቤተክርስቲያኗ ከመቀላቀሉ በፊት ሊመን ኮፕሊ በተለምዶ ሼከርስ [የተወዛዋዦቹ] ተብለው የሚጠሩ የዩናይትድ ሶሳይቲ ኦፍ ብሊቨርስ እን ክራይስትስ ሰክንድ አፒሪንግ [በክርስቶስ ዳግም ምፅዓት የሚያምኑ የአንድነት ህብረተሰብ] ሀይማኖት ስብስብ አባል ነበር(“ሊመን ኮፕሊ እና ሼከሮቹ ”፣ ራዕያት በአገባብ፣ 117–21) ይመልከቱ። ከሊመን ጋር ከተነጋገረ በኋላ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ከጌታ ስለሼከርስ አስተምህሮቶች ማብራሪያ ፈለገ፣ እናም ጌታ በክፍል 49 ውስጥ ባለው ራእይ መልስ ሰጠ።

ጥቂቶቹን የሼከሮች እምነቶች በክፍል 49 መግቢያ ውስጥ ተጠቅሰው ልታገኟቸው ትችላላችሁ። እነዚያን እምነቶች ያረሙትን በቁጥሮች 5–23 ውስጥ ያሉት እውነቶች ላይ ምልክት ማድረግን ወይም ማስታወሻ መያዝን አስቡ። በዛሬው አለም ውስጥ ስላሉ ሌሎች ሃሰተኛ ትምህርቶች ወይም ልማዶች አስቡ። የትኞቹ የወንጌል እውነታዎች ከእነሱ እንድትጠበቁ ሊረዷችሁ ይችላሉ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49፥15–17

በወንዶች እና ሴቶች መካከል ያለው ጋብቻ ለእግዚአብሔር እቅድ አስፈላጊ ነው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49፥15–17 ውስጥ ስለ ጋብቻ ምን እውነት ትማራላችሁ? በወንድ እና በሴት መካከል የሚደረግ ጋብቻ ለሰማያዊ አባት እቅድ አስፈላጊ ለምን እንደሆነ ይሰማችኋል? ሽማግሌ ዴቭድ ኤ. በድናር ሁለት ምክንያቶችን ሰጥተዋል፥ “ምክንያት 1፥ የወንድ እና የሴት መንፈሶች አንደኛው ሌላውን ያሟላዋል እናም እንከን አልባ ያደርገዋል፤ እናም ስለዚህ ወንዶች እና ሴቶች ወደ ከፍታ አብረው እንዲያድጉ ነው የታሰቡት። … ምክንያት 2፥ በመለኮታዊ ንድፍ፣ ወንድ እና ሴት ልጆችን ወደዚህ አለም ለማምጣት እና ለማሳደግ እና ለመንከባከብ አመቺ ሁኔታን ለማቅረብ አስፈላጊ ናቸው (“ጋብቻ ለእርሱ ዘላለማዊ እቅድ አስፈላጊ ነው፣” ኢንዛይን፣ ሰኔ 2006 (እ.አ.አ.)፣ 83–84)።

በተጨማሪም ዘፍጥረት 2፥20–241 ቆሮንቶስ 11፥11፤ “ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ.)፣ 145 ይመልከቱ።

ምስል
ጥንዶች ከቤተመቅደስ ውጪ

በወንድ እና በሴት መካከል የሚደረግ ጋብቻ በእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50

የጌታ ትምህርቶች ከሰይጣን ማታለል ሊጠብቁኝ ይችላሉ።

በኦሃዮ የነበሩ አዳዲስ አባላት በቅዱሳት መጻህፍት ቃል የተገቡትን መንፈሳዊ መገለጫዎች ለመቀበል ጓጉተው ነበር፣ ነገር ግን ሰይጣንም ሊያታልላቸው ጓጉቶ ነበር። አንድ ሰው ሲጮህ ወይም ነፍሱን ሲስት፣ ያ ነገር የመንፈስ ውጤት ነውን? ብለው አሰቡ።

እነዚህን አዳዲስ አባላት እውነተኛ የመንፈስ ቅዱስ መገለጫዎችን እንዲያውቁ እና ከሰይጣን የማስመሰል መታለል እንዲርቁ እንድትረዱ ተጠይቃችሁ እንደነበር አይነት በአዕምሮዋችሁ ተመልከቱ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50 ውስጥ ልታጋሩት የምትችሉት ምን መርህ ታገኛላችሁ? (በተለይም ቁጥሮች 22–25፣ 29–34፣ 40–46 ይመልከቱ)።

በተጨማሪም 2 ጢሞቴዎስ 3፥13–17 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥13–24

አስተማሪዎች እና ተማሪዎች በጋራ በመንፈሱ ይታነጻሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥13–24ን ልታጠኑ የምትችሉበት አንደኛው መንገድ የአስተማሪ እና የተማሪ ምስልን መሳል፣ እና ከእያንዳንዱ ስእል አጠገብም ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለወንጌል መማርና ማስተማር የሚያስተምሯችሁን ቃላት እና ሃረጋትን በዝርዝር በመጻፍ ሊሆን ይችላል። በመማርና በማስተማር ሂደት ላይ የመንፈሱን አስፈላጊነት ያስተማራችሁ ልምምድ የነበራችሁ ጊዜ ነበርን? እንደ ወንጌል ተማሪ እና አስተማሪ ጥረታችሁን ለማሻሻል ምን ልታደርጉ እንደምትችሉ አስቡ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49፥2“ሙሉ እውነትን ሳይሆን ከፊሉን ብቻ ለማወቅ መሻት” ምን ማለት ነው። ምናልባት በከፊል የተሸፈነ ስእል ልታሳዩ እና የቤተሰብ አባላት ምን እንደሆነ እንዲገምቱ ማድረግ ትችላላችሁ። ከፊሉን እውነት ብቻ ስንቀበል ምን ይሆናል? (2 ኔፊ 28፥29 ይመልከቱ)። የወንጌል ሙላት እንዴት ለእኛ በረከት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49፥26–28“እነሆ፣ ከፊታችሁ እሄዳለሁ እናም እከተላችኋለሁ፤ እና በመካከላችሁ እሆናለሁ” በሚለው የጌታ ቃል ኪዳን እንዴት ተባርከናል? የቤተሰብ አባላት ጌታ “በፊታቸው ሲሄድ ወይም በመካከላቸው እንደነበረ” በተሰማቸው ጊዜ የነበራቸውን ልምድ ሊያካፍሉ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥23–25ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥23–25ን ለማንበብ በጨለማ ክፍል ውስጥ ልትሰባሰቡ እና ቀስ በቀስ ሻማዎችን በመለኮስ ወይም አምፑሎችን አንድ በአንድ በማብራት ብርሃኑን ለመጨመር ትችላላችሁ። እነዚህን ጥቅሶች ጠዋት ጸሀይ ስትወጣ እያያችሁም ልታነቡ ትችላላችሁ። የወንጌል ብርሃናችን ማደጉን እንዲቀጥል ምን ማድረግ እንችላለን? የቤተሰብ አባላት በሳምንቱ ውስጥ ስለወንጌል አንድ አዲስ ነገር ሲማሩ፣ ማስታወሻ በመጻፍ እና ከአምፑል ወይም ከሌላ በቤቱ ካለ ብርሃን ሰጪ ነገር ጋር በማያያዝ ከቤተሰበቡ ጋር እንዲያጋሩት አበረታቷቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥40–46ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥40–46ን ካነበባችሁ በኋላ፣ ከዚህ ማውጫ ጋር ያለውን የጌታን ምስል ልታሳዩ እናም እንደዚህ የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ለመጠየቅ ትችላላችሁ፥ አዳኝ በጎችን እንደሚወድ እንዴት ለማወቅ ችላችኋል? አዳኝ እንደ እረኛ የሆነልን እንዴት ነው? ከቅዱሳት መጻህፍት የትኞቹ ሃረጎች አዳኝ እረኛ እኛ በጎቹ የመሆናችንን ሃሳብ ያንጸባርቃሉ?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “አብሩ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 144።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ከነገሮች ጋር በቀላሉ የምትላመዱ ሁኑ። አመቺው የማስተማር ጊዜ፣ በተለይ በቤት ውስጥ፣ የሚገኘው ብዙውን ጊዜ ባልታሰበበት እና ባልተጠበቀበት ሁኔታ ነው፥ የቤተሰብ የመመገቢያ ጊዜ ከአምላክ ቃል ስለመመገብ ውይይትን ሊያነሳሳ ይችላል፣ እንዲሁም ዶፍ ዝናብ ስለ ህይወት ውሃ ለመመስከር እድል ሊሰጥ ይችላል። በመንፈሳዊ ዝግጁ ከሆናችሁ ጌታ “በዚያች ጊዜም፣ ምን እንደምትናገሩ” ሊሰጣችሁ ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 100፥6)።

ምስል
ኢየሱስ ከጠቦት ጋር

ጨዋ እረኛ፣ በኪም ዮንግሱንግ

አትም