“ሚያዝያ 26–ግንቦት 2 (እ.አ.አ)። ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 45፥ ‘ቃል የገባሁላችሁ…[ይፈጸማሉ]’” ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ሚያዝያ 26–ግንቦት 2 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ 2021 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 26–ግንቦት 2 (እ.አ.አ)
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45
“ቃል የገባሁላችሁ…[ይፈጸማሉ]”
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳተማሩት፥ “ወደ አዕምሮአችሁ የሚመጡትን ሀሳቦች ፃፉ። ስሜቶቻችሁን መዝግቡ እና እንድታደርጉ በተነሳሳችሁት እርምጃዎች ተከታሉ” (ራዕይ ለቤተክርስትያኗ፣ ራዕይ ለህይወታችን፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 95)።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
የምንኖረው አደገኛ በሆኑ ጊዜያት ውስጥ ነው፣ እናም ያ የሚያስጨንቅ ነገር ሊሆን ይችላል ። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶች እንኳን እርሱ በዘመናችን ስለሚከሰቱት ጥፋቶች ትንቢት ሲናገር ሲሰሙት “ተረበሹ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥34)። በከርትላንድ ኦሃዮ የነበሩት የመጀመሪያዎቹ ቅዱሳንም ይኖሩበት በነበረው አደገኛ ጊዜ ተረብሸው ነበር። ሌሎች ነገሮችን ጨምሮ፣ “የሀሰት ዘገባዎችና ረብ የለሽ ታሪኮች” የወንጌልን መልእክት እያሰናከሉ ነበር (የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች የክፍል 45 መግቢያ )። በእዚያ ጊዜም ይህን አሁን፣ የጌታ ምላሽ “አትጨነቁ” ነው (ቁጥር 35 )። እርግጥ ነው ክፋት አለ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ሥራውን እያፋጠነ እንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃም አለ። እርግጥ ነው ከዳግም ምፅዓት ቀድመው የሚከሰቱ የተተነበዩ አደጋዎች አሉ፣ እናም እኛ እነርሱን ማወቅ ይገብናል። ነገር ግን እነዚህ የአደጋ ማስጠንቀቂያዎች ብቻ አይደሉም ፣ የእግዚአብሔር ተስፋዎች ሊፈጽሙ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶችም ናቸው ። ምናልባት ከእነዚህን ምልክቶች ብዙዎቹን በዝርዝር የሚገልጸው ራዕይ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፣ “ለቅዱሳን ደስታ” እንዲሆን የተቀበሉት ለዚህ ምክንያት ነው (የክፍል መግቢያ)።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ፊት አማላጃችን ነው።
በእግዚአብሔር ፊት ብቃት እንደሌላችሁ ወይም ብቁ እንዳልሆናችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃልን? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥1–5 ውስጥ ማበረታቻን ልታገኙ ትችላላችሁ። እንደ “አማላጅ” እና “መማጸን” ያሉት ቃላት ለእናንተ ምን ይጠቁማሉ? አዳኝ ለእናንተ እንዴት አማላጃችሁ ነው ወይም እንዴት ለእናንተ ምክንያት ያማፅናል? ክርስቶስ አማላጃችሁ መሆኑን ማወቃችሁ ለእናንተ ምን ማለት ነው?
የሚከተሉት የፕሬዘዳንት ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ ቃላት እነዚህን ቁጥሮች እንድታሰላስሉ ሊረዷችሁ ይችላሉ፥ “በአገልግሎቱ አማካይነት የእኛ አስታራቂ በመሆን በመማጸን እና እኛን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ በብርቱ በመስራት ኢየሱስ አማላጃችን ነው።” (የጉባኤ ሀተታ፣ ጥቅምት 1953 (እ.አ.አ.)፣ 58).
በተጨማሪም 2 ኔፊ 2፥8–9፤ ሞዛያ 15፥7–9፤ ሞሮኒ 7፥27–28፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥5፤ 62፥1 ይመልከቱ።
ወንጌል የአገሮች መስፈርት ነው ።
በጥንት ጊዜ መስፈርት ጦርነት ሲኬድ የሚያዝ ባንዲራ ወይም ሰንደቅ ዓላማ ነበር። ወታደሮችን ያነሳሳና አንድ ያደርጋቸው እንዲሁም የት መሰብሰብ እንዳለባቸውና እና ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲያውቁ ይረዳቸው ነበር። መስፈርት በተጨማሪም ሌሎች ነገሮች የሚለኩበት ማነጻጸሪያ ምሳሌ ወይም ደንብ ነው። ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 45፥9–10ን ስታነቡ፣ የወንጌል ቃል ኪዳኖች ለእናንተ እንዴት መስፈርት እንደሆኑላችሁ አሰላስሉ። እነዚህ ቃልኪዳኖች ባይኖሯችሁ ኖሮ ህይወታችሁ በምን መልኩ የተለየ ሊሆን ይችል ነበር?
በተጨማሪም ኢሳይያስ 5፥26፤ 11፥10–12፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥5–6ን ይመልከቱ።
የጌታ ቃል ኪዳኖች ይፈጸማሉ።
ጦርነት፣ ጥፋት፣ እና ባድማነት ከአዳኙ ዳግም ምጽዓት ቀድመው ይመጣሉ። ነገርግን “አትጨነቁ”፣ ብሏል ጌታ፣ “ምክንያቱም እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሊሆኑ ግድ ስለሚሆን፣ ቃል የገባሁላችሁ ነገሮች ሁሉ እንደሚፈጸሙ ታውቃላችሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥35)።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥11–75ን ስታነቡ ይሆናሉ ተብለው ቀድመው በተተነበዩት አስጨናቂ በሆኑት ክስተቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በጌታ በተሰጡት በረከቶችም ላይ በማተኮር አሰላስሉ (ለምሳሌ በቁጥሮች 54–59 ውስጥ ባለው ስለአዳኝ የሺህ አመት ግዛት)። ዝርዝሮችን በመፍጠር ወይም ጥቅሶችን በመለጠፍ ወይም ምልክት በማድረግ ይህንን ማድረግ ትችላላችሁ። ስለመጨረሻው ቀን “[ላለመጨነቅ]” የሚረዳችሁ ምን አገኛችሁ?
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥31–32፣ 56–57።
“በተቀደሱ ስፍራዎች ላይ ይቆማሉ፣” እናም አይነቃነቁም።
አዳኝ እና ነቢያቱ የዳግም ምጽዓቱን ምልክቶች እኛን የሚያስተምሩበት አንደኛው ምክንያት እንድንዘጋጅ ለመርዳት ነው ። ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥31–32 ስለ ጌታ ዳግም ምፅዓት ምን ትማራላችሁ? በማቴዎስ 25፥1–13 ውስጥ የሚገኘውን የአሥሩን ደናግል ምሳሌ መከለሱ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። በዚህ ምሳሌ ውስጥ ያለውን ዘይት አዳኝ ከእውነት እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አነጻጽሮታል (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 45፥57ን ይመልከቱ)። ምሳሌውን በዚህ መንገድ ስታነቡ ምን ግንዛቤዎች አገኛችሁ?
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥11–15፣ 66–71
ፅዮን ለእግዚአብሔር ቅዱሳን የደህንነት ስፍራ ናት ።
በጆሴፍ ስሚዝ ዘመን የነበሩ ቅዱሳን፣ ልክ በመፅሐፈ ሞርሞን (ኤተር 13፥2–9ን ይመልከቱ) እና በጆሴፍ ስሚዝ በመንፈስ አነሳሸነት በተከለሰው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ (ሙሴ 7፥62–64ን ይመልከቱ) እንደተገለጸው አይነት አዲሲቷን ኢየሩሳሌምን፣ እንዲሁም ፅዮንን፣ ለመገንባት ጓጉተው ነበር። ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥11–15፣ 66–71 ስለ ፅዮን፣ እንዲሁም ሰለሁለቱ የጥንቷ የሔኖክ ዘመን ከተማ እና የኋለኛው ቀን ከተማ ምን ትማራላችሁ?
ፅዮንን የማቋቋም ትእዛዝ በዛሬው ጊዜ የሚያመለክተው በምንኖርበት ቦታ የእግዚአብሔርን መንግሥት፣ እንዲሁም የእግዚያብሔር ልጆች ወደ እርሱ “ዘላለማዊ ቃል ኪዳን“ (ቁጥር 9) በደህንነት የሚሰበሰቡበትን ቦታ መመስረትን ነው። ባላችሁበት ቦታ ፅዮንን በመገንባት ለማገዝ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
በተጨማሪም ከወንጌል ርእስቶች፣ “ጽዮን፣” topics.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥3–5።አማላጅ ለእኛ ምን ሊያደርግልን ይችላል? “The Mediator [አስታራቂው]” የተሰኘውን ቪዲዮ ለመመልከት (ChurchofJesusChrist.org) እና አዳኝ ለምን አማላጃችን ተብሎ እንደተጠራ ለመወያየት ትችላላችሁ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥9–10።ቤተሰባችሁ ለወንጌል ያላችሁን ቁርጠኝነት የሚወክል “መስፈርት” ወይም ባንዲራ ቢኖራችሁ፣ ይህ ምን ይመስል ነበር? የቤተሰብ ባንዲራ በአንድነት መስራት ከዚያም ሌሎች የወንጌል መስፈርትን እንዲከተሉ እንዴት መርዳት እንደምትችሉ መወያየት አስደሳች ሊሆን ይችላል።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥32።“የተቀደሱ ስፍራዎቻችን“ ምንድን ናቸው። “አለመነቃነቅ“ ምን ማለት ነው? ቤታችንን እንዴት አድርገን የተቀደሰ ስፍራ ማድረግ እንችላለን?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥39–44።የጌታን ዳግም ምፅዓት መጠበቅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲገነዘቡ የቤተሰብ አባሎችን እንዴት ለመርዳት ትችላላችሁ? አንድ ይከሰታል ብላችሁ የምትጠብቁትን ሁኔታ ልታስቡ እና ከዚያም ያንን ክስተት “የምትጠብቁበትን“ መንገድ ለማጋራት ትችላላችሁ። ወይም አንድን ነገር አብራችሁ ለመጋገር እናም ለመብላት ዝግጁ እንደሆነ የሚያሳይ ምልክቶችን መጠበቅ ትችላላችሁ። የአዳኝን ዳግም ምፅዓት ለመጠበቅ ምን እያረግን ነን?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥55።1 ኔፊ 22፥26ን እና ራዕይ 20፥1–3ን ማንበብ ሰይጣን በሺህ ዘመን ግዛት እንዴት “እንደሚታሰር“ ቤተሰባችሁ እንዲገነዘብ ይረዳል። በህይወታችን ሰይጣንን እንዴት ማሰር እንችላለን።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ “በድጋሚ ሲመጣ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 82–83፤ በተጨማሪም “የቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትን ለማሻሻል የሚረዱ ሃሳቦችን” ይመልከቱ።