ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ግንቦት 3–9 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46–48፥ “የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በፅኑ ፈልጉ”


“ግንቦት 3–9 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን 46– 48፥ ‘የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በፅኑ ፈልጉ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 3–9 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46–48፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
በኩሬ አጠገብ የተሰበሰቡ ሰዎች

የካምፕ ስብሰባ በወርዚንግተን ዊትሬጅ

ግንቦት 3–9 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46–48

“የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በፅኑ ፈልጉ”

ትምህርትና ቃል ኪዳኖችን 46-48ን ስታነቡ፣ የሚመጡላችሁን ግንዛቤዎች መዝግቡ። ከዚያም ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ. ስኮት እንደጠቆሙት፣ “ይበልጥ ላውቀው የሚገባኝ ነገር አለን?” ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ።(“መንፈሳዊ መመሪያን ለማግኘትኢንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2009 (እ.አ.አ)፣ 8)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ፓርሊ ፒ. ፕራት፣ ኦሊቨር ካውደሪ፣ ዚባ ፒተርሰን እና ፒተር ዊትመር ዳግማዊ ከከርትላንድ ወደ ሌላ የስራ መስክ ተዛወሩ፣ በዚያም ከመቶ የሚበልጡ ቅንአት ያላቸውን ነገር ግን ልምምድም ሆነ አቅጣጫ ያልነበራቸውን አዳዲስ አባላት ትተው ነበር። ምንም አይነት የመመሪያ መፅሀፎች አልነበሩም፣ የመሪዎች ስልጠና ስብሰባዎችም አልነበሩም፣ የአጠቃላይ ጉባኤ ስርጭትም አልነበረም—በእርግጥ የሚገኙ በጣም ብዙ የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂዎችም አልነበሩም። አብዛኛዎቹ እነዚህ አማኞች ዳግም ወደተመለሰው ወንጌል የተሳቡት በአስደናቂ የመንፈስ መገለጥ ቃልኪዳን ተስበው ነበር፤በተለይ ከአዲስ ኪዳን ጥናታቸው ያንን አውቀው የነበሩት( 1 ቆሮንቶስ 12፥1–11)ተመልከቱ። ወዲያውም፣ ያልተለመዱ፣ እንዲሁም ወደ መሬት መውደቅን ወይም እንደ እባብ መጥመልመልን አይነት የአምልኮ መገለጫዎች በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ውስጥ ገብተው ነበር። ብዙዎች የትኞቹ የአምልኮ መገለጫዎች የመንፈሱ እንደሆኑ እና የትኞቹ እንዳልሆኑ ለመገንዘብ አስቸጋሪ ሆኖ አግኝተውት ነበር። የነበረውን ግራ መጋባት ተመልክቶ ጆሴፍ ስሚዝ እርዳታ ለማግኘት ጸለየ። ሰዎች ብዙውን ጊዜ የመንፈስን ነገር በማይቀበሉበት ወይም ችላ በሚሉበት ጊዜ፣ ይህ የጌታ ምላሽ ዛሬም በእኩል ደረጃ ጠቃሚ ነው። ጌታ የመንፈስ መገለጦች እውነት፣ እንዲሁም “ለሚወዱ[ት] እና ትእዛዛ[ቱ]ን ለሚጠብቁ“ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥9) ከአፍቃሪ የሰማይ አባት የተሰጡ ስጦታዎች እንደሆኑ ገለጠ፣ ምን እንደሆኑም አብራራ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥1–6

በእውነት የሚፈልጉ ሁሉ በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማምለክ ይችላሉ።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ስብሰባዎች በአለም ካሉት ስብሰባዎች እጅግ በጣም ተቀባይ እና አነቃቂ መሆን ይኖርባቸዋል። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥1–6 ውስጥ በስብሰባዎቻችን ላይ ለመካፈል የሚመጡትን ስለመቀበል ጌታ እንዴት ይመክረናል? ጓደኞቻችሁ እና በአቅራቢያችሁ የሚገኙ ሰዎች በአጥቢያዎቻችሁ የአምልኮ አገልግሎቶች ላይ መልካም መስተንግዶ እንደተደረገላቸው ይሰማቸዋልን? የቤተክርስቲያን መሰብሰቢያ ቦታዎቻችሁ ሰዎች ተመለልሰው የሚመጡበት ቦታ እንዲሆኑ ምን እያደረጋችሁ ነው? በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ውስጥ መንፈስ ቅዱስን ለመከተል የምታደርጉት ጥረት ልምዳችሁን እንዴት እንደሚነካው አስቡ።

በተጨማሪም 3 ኔፊ18፥22–23ሞሮኒ 6፥5–9፤ “Welcome፣” ቪድዮ፣ ComeUntoChrist.orgበጥንቷ የኦሀዮ አዲስ አባላት መካከል የነበረ የሀይማኖት ጉጉት፣” ራእይ በአገባብ፣ 105–11 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥7–33

እግዚአብሔር ልጆቹን ለመባረክ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ሰጥቷል።

የመጀመሪያዎቹ ቅዱሳን በመንፈስ ስጦታዎች ያምኑ ነበር ነገር ግን በአላማቸው ላይ መመሪያ አስፈልጓቸው ነበር። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥7–33ን በመጠቀም ስለመንፈስ ስጦታዎች ስታጠኑ፣ “ለምን እንደተሰጧችሁ [ማ]ስታወሳችሁ“ (ቁጥር 8) ለምን እንደሚያስፈልግ አስቡ። እንዴት እነዚህ ጥቅሶች በሽማግሌ ሮበርት ዲ.ሄልስ ንግግር ላይ እንደሚተገበሩ አስቡ፥ “እነዚህ ስጦታዎች የተሰጡት ለክርስቶስ ታማኝ ለሆኑት ነው። የወንጌልን እውነታዎች ለማወቅ እና ለማስተማር ይረዱናል። ሌሎችን ለመባረክ ይረዱናል። ወደ ሰማያዊ አባታችን በምናደርገው ጉዞም ይመሩናል” (“የመንፈስ ስጦታዎች፣” ኢንዛይን፣ የካቲት 2002 (እ.አ.አ.) 16)። ስለመንፈስ መገለጥ ከእነዚህ ጥቅሶች ሌላ ምን ነገር ትማራላችሁ? እነዚህ እውነቶች “እንዳትታለሉ“ (ቁጥር 8) የሚረዷችሁ እንዴት ነው?

መንፈሳዊ ስጦታዎቻችሁ ምን እንደሆኑ፣ እና ከዚያም “ለእግዚአብሔር ልጆች ጥቅም“ እንዴት እንደምትጠቀሙበት አስቡ (ቁጥር 26)። የፓትርያርክ በረከቶችን ተቀብላችሁ ከሆነ ምናልባት የተሰጧችሁን ስጦታዎች ለይቶላችሁ ይሆናል።

በተጨማሪም ከወንጌል አርእስቶች “መንፈሳዊ ስጦታዎች፣” topics.ChurchofJesusChrist.org የሚለውን ተመልከት።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 47

ጌታ የእርሱ ቤተክርስቲያን ታሪኳን መዝግባ አንድትይዝ ይሻል።

የቤተክርስቲያኗን ታሪክ ለመጠበቅ ጆን ዊትመር የተጠራው ጥሪ በእግዚአብሔር ሕዝቦች መካከል የነበረውን የታሪክ መዝጋቢዎች ረጅም ባህል አስቀጥሏል (2 ኔፊ 29፥11–12ሙሴ 6፥5አብርሐም 1፥28፣ 31 ይመልከቱ)። በእርግጥም የቤተክርስቲያን ታሪክ አጥኚነት እና መዝጋቢነት የስራ ድርሻ አሁንም አለ። ታሪክን መመዝገብ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? ስለዚህ ስራ ለጆን ዊትመር የሰጠውን መመሪያ በበክፍል 47 ውስጥ ስታነቡ ይህንን አሰላስሉ። እንዲሁም ምን የግል ልምድ መመዝገብ እንደሚያስፈልጋችሁ አስቡ። ለምሳሌ፣ ጠብቃችሁ ለማስቀመጥ የምትፈልጉት ምን ነገር ጌታ አስተማራችሁ?

በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ ስታሰላስሉ፣ ከ2005 እሰከ 2012 (እ.አ.አ) ድረስ የቤተክርስቲያኗ የታሪክ አጥኝ እና መዝጋቢ በመሆን ያገለገሉትን የሰባዎቹ አባል ሽማግሌ ማርቲን ኬ. ጄንሰንን ሀሳብ ግምት ውስጥ አስገቡ።

“መዝገቦች የምንይዘው ለማስታወስ እንዲረዳን ነው። … እግዚአብሔር ለልጆቹ ያደረጋቸውን ታላላቅ ነገሮች እንዲያስታውሱ የቤተክርስቲያን አባላትን ለመርዳት እንፈልጋለን። … ካለፈው ታሪክ የሚገኝ ትምህርት ዛሬን መቋቋም እንድንችል እንዲሁም ለወደፊታችን ተስፋ ይሰጠናል።” (“ታሪካችሁ መመዝገብ ይኖርበታል፣” ኢንዛይን፣ ታህሳስ 2007 (እ.አ.አ)፣ 28፣ 33)።

በአሁኑ ሰአት በቤተክርስቲያኗ የታሪክ አጥኝ አመራር እየተሰራ ስላለው ስራ ይበልጥ ለመማር history.ChurchofJesusChrist.orgን ይጎብኙ።

ምስል
ጆን ዊትመር

ጆን ዊትመር የተጠራው የቤተክርስቲያኗን ታሪክ እንዲመዘግብ ነበር።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥2–6በቤተክርስቲያን ስብሰባዎቻችን ሌሎች መልካም አቀባበል እንደተደረገላቸው እንዲሰማቸው እንደ ቤተሰብ ምን ልናደርግ እንችላለን? (በተጨማሪም 3 ኔፊ18፥22–23 ይመልከቱ)። ከዚህ ዝርዝር ጋር ተያይዞ ያለው ሥዕል ወደዚህ ውይይት ሊጨመር ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥7–26እርስ በራሳችን ምን አይነት መንፈሳዊ ስጦታዎችን እናያለን? እነዚህ ስጦታዎች ቤተሰባችንን ሊባርኩ የሚችሉት እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 47ቤተሰባችሁ ሳምንታዊ የግል ታሪካቸውን እንዲመዘግቡ ማበረታታት የምትችሉት እንዴት ነው? ከግል ማስታወሻዎቻችሁ የተወሰነውን ልታጋሩ ትችላላችሁ ወይም ከዘር ሃረጋችሁ ውስጥ ስላንዱ ታሪክ ልታጋሩ ትችላላችሁ (FamilySearch.orgን ይመልከቱ)። አንዳንድ ቤተሰቦች እያንዳንዱ ማስታወሻቸው ውስጥ እንዲጽፉ በየሳምንቱ ጥቂት ደቂቃዎችን ይመድባሉ። “የልጅ ልጆቻችሁ እንዲያውቋቸው የምትፈልጓቸው በዚህ ሳምንት ምን ነገሮች ተከናውነዋል?” ወይም “በዚህ ሳምንት በህይወታችሁ ውስጥ የጌታን እጅ እንዴት አያችሁት?” የሚሉ የተወሰኑ በማስታወሻ የሚጻፍበት ጥያቄዎችን ማቅረብ ትችሉ ይሆናል። ትናንሽ ልጆች ልምዳቸውን የሚያንጸባርቁ ስዕሎችን መሳል ይችላሉ፣ ወይም ደግሞ ታሪካቸውን ሲናገሩ በቭድዮ ልትቀርጿቸው ትችላላችሁ። “መደበኛነት ታሪክ”ን በመመዝገቡ ምን በረከቶች ያስገኛል? (ቁጥር 1)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 48በኦሃዮ የሚገኙ ቅዱሳን መሬታቸውን ከምሥራቃዊ አሜሪካ ወደ ኦሃዮ ከሚዛወሩት ጋር እንዲጋሩ ታዝዘው ነበር። የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላት ምን ማጋራት እንችላለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር “Have I Done Any Good?” (መዝሙሮች፣ ቁጥር 223)።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ታሪኮችን እና ምሳሌዎችን ተጠቀሙ። አዳኝ የወንጌል መመሪያዎችን ለማስተማር ብዙ ጊዜ ታሪኮችን እና ምሳሌዎችን ተጠቅሟል። የወንጌልን መመሪያ ለቤተሰባችሁ ህያው ሊያደርጉ የሚችሉ ምሳሌዎችን እና ታሪኮችን ከራሳችሁ ህይወት አስቡ (በጌታ መንገድ ማስተማር፣ 22 ይመልከቱ)።

ምስል
ሰዎች በቤተክርስቲያን

የሰማይ አባት የሌሎችን ህይወት ለመባረክ ይችሉ ዘንድ ለልጆቹ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይሰጣል።

አትም