ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ግንቦት 17–23 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 51–57፥ “ታማኝ፣ ሐቀኛ፣ እና ብልህ መጋቢ”


“ግንቦት 17–23 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 51–57፥ ‘ታማኝ፣ ሐቀኛ፣ እና ብልህ መጋቢ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦችና ለቤተሰቦች፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 17–23 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 51–57፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ገበሬ ከበሬ ጋር

በማረሻ የታረሰ የመጀመርያ ረድፍ፣ በጄምስ ቴይለር ሀርውድ

ግንቦት 17–23 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 51–57

“ታማኝ፣ ሐቀኛ፣ እና ብልህ መጋቢ“

ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት የጌታን ድምጽ እንድትለዩ ይረዳችኋል፣ ቅዱሳት መጻህፍት በመንፈሱ አማካኝነት ከእርሱ የተሰጡ ናቸውና (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥34–36 ይመልከቱ)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በ1830 (እ.አ.አ) አመታት ለነበሩት የቤተክርስቲያኗ አባላት፣ ቅዱሳኑን መሰብሰብ እና የፅዮንን ከተማ መገንባት፣ ከብዙ ተግባራዊ ምላሽ ሊሰጥባቸው ከሚገቡ ነገሮች ጋር መንፈሳዊም ስጋዊም ስራ ነበር፥ አንዱ ቅዱሳን ሊሰፍሩ የሚችሉበት መሬት መግዛት እና ማከፋፈል ያስፈልገው ነበር። አንዱ መጻህፍትን እና ሌሎች ህትመቶችን ማሳተም ያስፈልገው ነበር። አንዱ ደግሞ በፅዮን ለሚገኙ ቁሳቁስ ለማቅረብ የመጋዘን ስራን ማካሄድ ያስፈልገው ነበር። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 51–57 ውስጥ በተመዘገቡት ራዕዮች፣ እነዚህን ስራዎች የሚሰሩ ሰዎችን ጌታ መድቧል እንዲሁም መመሪያ ሰጥቷል፥ እናም ኢንዲፔንደንስ፣ ምዙሪን እንደ ፅዮን “መካከለኛ ቦታ“ ለይቷት ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 57፥3)።

ነገር ግን መሬትን የመግዛት፣ የህትመት እና የሱቅን ስራ የማካሄድ ችሎታዎች ለፅዮን ግንባታ ስጋዊ ስራ ጠቃሚነት ቢኖራቸውም፣ እነዚህ ራእዮች በተጨማሪም ቅዱሳን የፅዮን ህዝቦች ተብለው ለመጠራት በመንፈሳዊ ብቁ እንዲሆኑ ጌታ እንደሚፈልጋቸው ያስተምራሉ። እያንዳንዳችን “ታማኝ፣ ሐቀኛ እና ብልህ መጋቢ፣“ የተዋረደ መንፈስ ያለን፣ በተሾምንበት ስልጣን “[ጸንተን የምንቆም]” እንድንሆን ይጠራናል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 51፥1952፥1554፥2 ይመልከቱ)። ከስጋዊ ክህሎቶቻችን ምን አይነት ቢሆንም፣ ይህንን ለማድረግ ከቻልን፣ ጌታ ፅዮን ለመገንባት እኛን ሊጠቀም ይችላል እናም “ከተማውን በጊዜው [ያፈጥነዋል]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 52፥43)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 51

ጌታ ታማኝ፣ ሐቀኛ እና ብልህ መጋቢ እንድሆን ይሻል።

በ1831 (እ.አ.አ) የቤተክርስቲያኗ አባል ብትሆኑ ኖሮ፣ በኢጲስ ቆጶሱ በኩል ንብረታችሁን ለቤተክርስቲያን በማስረከብ የቅድስና ህግጋትን እንድትኖሩ ትጋበዙ ነበር። ከዚያም አብዛኛውን ጊዜ ከሰጣችሁት በላይ ያህል ለእናንተ ይመልስላችኋል። ነገር ግን ከዚህ በኋላ ያም ንብረታችሁን ብቻ አልነበረም—ይህም የእናንተን መጋቢነትም ነበር።

ዛሬ የአሰራር ቅደም ተከተሎቹ የተለዩ ናቸው፣ ነገር ግን የማጋራት መርሆቹ እና መጋቢነት ዛሬም ለጌታ ስራ ወሳኝ ናቸው። የሽማግሌ ክውንተን ኤል. ኩክ ያሏቸውን እነዚህን ቃላት አስቡ፥ “ብዙዎች በእግዚአብሔር ተጠያቂነት የለብንም እና ለራሳችን እና ለሌሎች የግል ሃላፊነት የለብንም ብለው በሚያምኑበት በአደገኛ ጊዜ ውስጥ ነው የምንኖረው። በአለም ብዙዎች ትኩረታቸው በግል እርካታ ላይ ነው … [እናም] የወንድማቸው ጠባቂዎች መሆናቸውን አያምኑም። ነገር ግን በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ እነዚህ መጋቢነቶች የተቀደሱ ሃላፊነቶች እንደሆኑ እናምናለን።” (“መጋቢ የተቀደሰ ሀላፊነት፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2009 (እ.አ.አ.)፣ 91)።

ክፍል 51ን ስታነቡ፣ ጌታ ለእናንተ በአደራ ምን እንደሰጣችሁ አስቡበት። በቁጥር 19 ውስጥ የሰፈረው “መጋቢ“ የሚለው ቃል እና በቁጥር 5 ውስጥ ያለው“በቅድስና … [መስጠት]” የሚሉት ቃላት ምን ማለት ናቸው፣ እናም እግዚአብሔር ከእናንተ ስለሚጠብቀው ነገሮች ምን ያመለክታሉ? በክፍል 51 እና በሽማግሌ ኩክ ቃላት ውስጥ መጋቢ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚያስተምር ምን መርሆች ታገኛላችሁ? (በተለይም ቁጥሮች 9፣ 15–20 ይመልከቱ)።

በተጨማሪም ማቴዎስ 25፥14–30፤ “የቅድስና ህግጋት“ ቪዲዮን ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 52፥14–19

እግዚአብሔር መታለልን የማስወገጃ ንድፎች ሰጥቷል።

ብዙ ሰዎች የመንፈስ መገለጫዎች አለን ይሉ ስለነበረ፣ የመጀመሪያዎቹ ቅዱሳን እንታለላለን ብለው ተሰግተው ነበር። ማን “በእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው” (ቁጥር 15) እንደሆነ በምን ያውቁ ነበር? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 52፥14–19 ጌታ ጠቃሚ ንድፎችን ሰጥቷል። በአለም ውስጥ ያሉ ሃሰተኛ መልእክቶችን ለመለየት እነዚህን ንድፎች እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል ትችላላችሁ? “በምናገርበት ጊዜ፣ መንፈሴ የተዋረደ ነው?” እና የተመሳሰሉ ጥያቄዎችን በመጻፍ ከእነዚህ ጥቅሶች ሃረጎችን በመጠቀም ራሳችሁን ለመገምገም ይህንን ንድፍ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 54

በሌሎች ሰዎች ምርጫ በምጎዳበት ጊዜ ወደጌታ ለመመልከት እችላለሁ።

ወደ ኦሃዮ የመሰባሰብ አካል በመሆን፣ በኑዌል ናይት የተመራ የቅዱሳን ቡድን በኮልስቪል፣ ኒው ዮርክ ደርሰው መኖሪያ ስፍራ ይፈልጉ ነበር። ሊመን ኮፕሊ በከርትላንድ አካባብ ትልቅ እርሻ ነበረው፣ እናም ቅዱሳን በመሬቱ ላይ እንዲሰፍሩ ለመፍቀድ ተስማማ። ነገር ግን እዚያ መስፈር በጀመሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ኮፕሊ በእምነቱ መጠራጠር ጀመረ፣ ቃል ኪዳኑን አፈረሰ እናም ቅዱሳን ከይዞታው ላይ አባረራቸው (ቅዱሳን፣1፥125–28)።

ክፍል 54 ውስጥ እንደተመዘገበው፣ ቅዱሳን ስላሉበት ሁኔታ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጌታ ለኑወል ናይት ነገረው። ሌሎች ሰዎች ቃል የገቡትን መስበራቸው ይም መጥፎ ምርጫዎቻቸው ተጽእኖ ሲያሳድርባችሁ ሊረዷችሁ የሚችሉ ምን ነገሮች በዚህ ራእይ ውስጥ ታገኛላችሁ?

ምስል
አረንጓዴ ሜዳ

ሊመን ኮፕሊ ለቤተክርስቲያኗ ቃል ገብቶት የነበረው በኦሃዮ የሚገኘው የእርሻ ቦታ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 56፥14–20

በልባቸው ንጹህ የሆኑ የተባረኩ ናቸው።

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጌታ ለሃብታሙም ለድሃውም ተናግሯል፤ ለእነዚህ ሁለቱም ቡድኖች የሰጠውን ምክር ማነጸጸር የሚያስገርም ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለእናንተን የሚናገር የሚመስሉት የትኛዎቹ ናቸው? በሃብት ላይ ትኩረትን ማድረግ ነፍሳችሁን ”የሚያዝለው” እንዴት ነው? (ቁጥር 16)። ቁሳዊ ነገሮችን በተመለከተ “በልብ ንጹህ” መሆን (verse 18) ለእናንተ ምን ትርጉም አለው?

በተጨማሪም ያዕቆብ 2፥17–21ን ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 51፥9ቤተሰቡን የሚያስደስት ጨዋታ ልትጫወቱ ትችላላችሁ ከዚያም አንድ ሰው አጭበርብሮ ቢሆን ኖሮ እንዴት ጨዋታው ሌላ መልክ ሊይዝ ይችል እንደነበረ ተነጋገሩ። አንዱ ከሌላው ጋር “በቅንነት መስራት” ጠቃሚ ሊሆን የሚችለው ለምንድን ነው? ሐቀኝነት “አንድ” እንድንሆን እንዴት ይረዳናል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 52፥14–19በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተገለጸውን ንድፍ ስትወያዩ፣ ቤተሰባችሁ ልብስን ለመስፋት ወይም የእጅ ጥበብ ለመስራት የምትጠቀሟቸውን ሌሎች ንድፎች ማየት ሊያስደስታቸው ይችላል። ጌታ መታለንን ለማስወገድ የሰጠውውን ንድፍ በመወያየት፣ ንድፍን በመጠቀም አንድ ነገር አብራችሁ ልትሰሩ ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 53፥1እንደ ስድኒ ጊልበርት “ጥሪያችሁን በተመለከተ” ጌታን ስለምትጠየቃችሁበት ጊዜ ከቤተሰባችሁ አጋጣሚያችሁን ለማካፈል አስቡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 54፥257፥6–7እግዚአብሔር እንድንሰራው በጠየቀን ነገር ላይ ”[ጸንተን መቆም]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 54፥2) ማለት ምን ማለት ነው? የቤተሰበብ አባላት እንዲቆሙ እና እግዚአብሔር እንዲሰሩ ያዘዛቸውን አንድ ነገር እንዲጠሩ ልትጋብዙ ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 55ጌታ የዊልያም ፌልፕስን የጸሐፊነት እና የአታሚነት ችሎታዎች እንዴት ነበር የተጠቀመው? (ለምሳሌ፣ በመዝሙር መፅሀፍ ውስጥ ይጻፋቸውን መዝሙሮች ዝርዝር ለመመልከት የደራሲ መረጃ ጠቃሚን ይመልከቱ)። ምናልባት የቤተሰብ አባላት አንዳቸው በሌላው ውስጥ ስለሚመለከቱት ተሰጥኦ እና ችሎታ መነጋገር ይችሉ ይሆናል ። ችሎታዎቻችን እንዴት ለእግዚአብሔር ሥራ አስተዋጽኦ ማበርከት ይችላሉ?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “‘ትንሹ ወንዝ ስጡ ሲል ተናግራል፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 236።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የጥናት ማስታወሻ ደብተርን መዝግቡ። በምታጠኑበት ጊዜ የሚመጡላችሁን ሃሳቦች፣ ጥያቄዎች ወይም ግንዛቤዎች ለመመዝገብ ማስታወሻ ደብተር ጠቃሚ ሆኖ ልታገኙት ትችላላችሁ።

ምስል
አባላት ለኤድዋርድ ፓርትሪጅ ቁሳቁስን ሲሰጡ

ኤጲስ ቆጶስ ፓርትሪጅ የተቀደሱ ስጦታዎችን ሲቀበል በአልቢን ቬሴልካ

አትም