ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 19–25 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41–44፥ “ቤተክርስቲያኔን የሚያስተዳድር ህግ”


“ሚያዝያ 19–25 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን 41–44፥ ‘ቤተክርስቲያኔን የሚያስተዳድር ህግ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ሚያዝያ 19–25 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41–44፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ

ሚያዝያ 19–25 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41–44

“ቤተክርስቲያኔን የሚያስተዳድር ህግ”

ጌታ ቃል እንደገባው፣ “ብትጠይቁ … በራዕይ ላይ ራዕይን፣ በእውቀት ላይ እውቀትን ትቀበላላችሁ” (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥61)። የሚያስፈልጋችሁ ራዕይ ለመቀበል ምን ጥያቄዎች መጠየቅ ትችላላችሁ?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በ1830 እና 1831 (እ.አ.አ) የነበረው ፈጣን የቤተክርስትያኗ እድገት—በተለይም ወደ ከርትላንድ፣ ኦሃዮ በፍጥነት ይመጡ የነበሩት አዳዲስ አማኞች—ለቅዱሳን አስደሳች እና አበረታታች ነበሩ። ነገር ግን ደግሞ አንዳንድ ፈተናዎችንም አምጥተዋል። በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ አማኞችን ስብስብ፣ በተለይም ደግሞ ከራሳቸው ጋር ከቀደምት እምነታቸው ይዘውት የመጡ ልምዶችና አስተምህሮዎች ያላቸው ሲሆኑ፣ ህብረት እንዲኖራቸው ለማድረግ እንዴት ትችላላችሁ? ለምሳሌ ጆሴፍ ስሚዝ በየካቲት 1831 (እ.አ.አ) በከርትላንድ ሲደርስ፣ አባላቶቹ በቅን ልቦና በአዲስ ኪዳን ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ያደርጉት እንደነበረው አይነት የጋራ ሃብትን ማፍራት ጀምረው አገኛቸው (የሐዋርያት ስራ 4፥32–37 ይመልከቱ)። ጌታ በዚህ እና በሌሎች ርዕሶች በሚመለከት አንዳንድ አስፈላጊ እርማትን እና ማብራሪያዎችን “ቤተክርስቲያኔን የሚያስተዳድር ህግ” (ቁጥር 59) በማለት የጠራውን ራዕይ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42 ውስጥ ሰጠ። በዚህ ራእይ ውስጥም፣ ሁሌም ተጨማሪ ልንማረው የሚገባ ነገር እንዳለ የሚያብራሩ ግልጽ የሆኑ ቃል ኪዳኖችን በመስጠት፣ የጌታን ቤተክርስቲያን በእነዚህ በኋለኛው ቀናት ለማቋቋም የሚረዱ መሰረታዊ የሆኑ እውነታዎችን እንማራለን፥ “ብትጠይቁ … በራዕይ ላይ ራዕይን፣ በእውቀት ላይ እውቀትን ትቀበላላችሁ” (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥61) ።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥114–19 ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41

“ህጌን ተቀብሎ የሚያደርገው፣ እርሱ ደቀ–መዝሙሬ ነው።”

በ1831 (እ.አ.አ) መጀመሪያ አካባቢ፣ ቅዱሳን በኦሃዮ እግዚአብሔር እገልጻለው ብሎ ቃል የገባላቸውን ህግ ለመቀበል በስፍራው ሆነው በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ነበሩ (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 38፥32 ይመልከቱ)። ነገር ግን ጌታ በመጀመሪያ ደቀመዛሙርቱ ህግጋቱን ለመቀበል እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው አስተማረ። በቁጥሮች 1–5 ውስጥ ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ህግጋት ለመቀበል ሊረዱ ይችሉ የነበሩ ምን መርሆዎች ታገኛላችሁ? እነዚህ መርሆዎች እናንተ ከእርሱ መመሪያዎችን እንድትቀበሉ እንዴት ሊረዷችሁ ይችላሉ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42

የእግዚአብሄር ህግጋት ቤተክርስቲያኑን ያስተዳድራሉ እናም የእኛንም ህይወት ለማስተዳደርም ይችላሉ።

ቅዱሳን በትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥1–72 ውስጥ የሚገኘውን ራእይ ነቢዩ ከተቀበላቸው በጣም ጠቃሚ ራእዮች እንደ አንዱ አድርገው ይመለከቱታል። በሁለት የኦሃዮ ጋዜጣዎችም ላይ በመታተሙ፣ በቅድሚያ ከታተሙት ራዕዮች ውስጥ አንዱ ነበር፣ እና ይህም “ህግ” ተብሎ ይታወቅም ነበር። በዚህ ክፍል ያሉት ብዙዎቹ መርሆች ከዚህ ቀደምም በጌታ ተገልጸው ነበር። ምንም እንኳን ይህ ክፍል ጌታ ቅዱሳን እንዲታዘዙለት የሚፈልጋቸው ተዕዛዛትን ሁሉ የያዘ ባይሆንም፣ ለምን እነዚህን መርሆዎች ለአዲሱና በዳግም ለተመለሰው ቤተክርስቲያን መድገም እንዳስፈለገው ማሰላሰሉ አስፈላጊ ነዉ።

ክፍል 42ን በትንሹ ክፍሎች ከፋፍላችሁ ከዚህ በታች እንደተዘረዘረው አድርጎ በማንበብና መርሆዎቹን መለየት ሊረዳችሁ ይችላል። ይህንን ስታደርጉ ቤተክርስቲያኑን የሚያስተዳድረው ህግ የእናንተንም ህይወት እንዴት ሊያስተዳድር እንደሚችል አስቡበት።

ቁጥሮች 4–9፣ 11–17፣ 56–58 

ቁጥሮች 18–29 

ቁጥሮች 30–31 

ቁጥሮች 40–42 

ቁጥሮች 43–52 

በተጨማሪም 3 ኔፊ 15፥9ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥30–42

ቅዱሳን እንዴት አድርገው “[ንብረታቸው በማካፈል]” ድሆችን ረድተው ነበር?

ክፍል 42 ውስጥ ከተገለጸው ህግ ጠቃሚው ክፍል ቢኖር የቅድስና ህግ እና መጋቢነት በመባል የሚታወቁት ናቸው። ይህ ህግ ቅዱሳኑን እንደቀደምት የክርስቶስ ተከታዮች፣ “ማንም ድሃ ሳይኖር” (ሙሴ 7፥18)፣ “ሁሉም ነገር በጋራ” ሊኖራቸው እንደሚችል አስተማራቸው (የሐዋርያት ስራ 2፥444 ኔፊ 1፥3)። ቅዱሳን ንብረታቸውን ለጌታ በኤጲስ ቆጶሱ አማካይነት በመስጠት አካፈሉ (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥30–31 ይመልከቱ)። ኤጲስ ቆጶሱም የሚያስፈልጋቸውን ይመልስላቸው ነበር (ቁጥር 32 ይመልከቱ)—ብዙውን ጊዜ ያካፈሉትንና አብላጫውን ተደርጎም። አባላት የተረፋቸውን ሁሉ ለድሆች ይለግሱ ነበር (ቁጥር 33–34 ይመልከቱ)። ይህ ህግ ለቅዱሳን፣ በተለይ ደግሞ ሁሉንም ነገር ጥለው ወደ ኦሃዮ ለመጡት ትልቅ በረከት ነበር። ብዙዎቹ ቅዱሳን በስጦታቸው ለጋሾች ነበሩ።

ምንም እንኳን አሁን በተለየ መልኩ ብናደርገውም፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን አሁንም የማካፈልን ህግ ይኖሩበታል። ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥30–42ን ስታነቡ፣ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ነገር እንዴት አድርጋችሁ የእርሱን መንግስት ለመገንባት እና ለተቸገሩት እንዴት ለማካፈል እንደምትችሉ አሰላስሉ።

ሊንዳ ኬ. በርተንን “እኔ እንግዳ ሳለሁ፣” ኤንዛይን ወይንም ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 13–15፤ “ህግ ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 93–95፣ history.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ምስል
ክርስቶስ እና ሀብታሙ ወጣት ገዢ

ክርስቶስና ወጣቱ ወጣት ገዢ በሄንሪች ሆፍማን

ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥61፣ 65–6843፥1–16

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኑን ለመምራት ራእይን ይሰጣል።

ቤተክርስቲያኗ በራእይ እንደምትመራ ለማወቅ ከጓጓ አዲስ የቤተክርስቲያን አባል ጋር እያወራሁ ነዉ ብላችሁ አስቡ። ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 43፥1–16ን በመጠቀም ለእርሱ ወይም ለእርሷ ጌታ ቤተክርስቲያኑን በነቢያት አማካኝነት የሚመራበትን ንድፍ ማብራራት እንዴት ትችላላችሁ? ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥61, 65–68ን በመጠቀም የግል ራእይን ስለመቀበል ማስተማር የምትችሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም “ሁሉም ነገሮች በስርአት ይከናወኑ ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 50–53፣ history.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41፥1–5ከህብረተሰብ ህጎች ውስጥ እንደምሳሌ ሊጠቀሱ የሚችሉ አንዳንዶች ምን ናቸው፣ እናም እነዚህ ህጎች እኛን እንዴት ሊጠቅሙን ይችላሉ? የሰማያዊ አባታችን ህግጋት ወይም ትዕዛዛት እንዴት ይባርኩናል? የቤተሰብ አባላት የእግዚአብሔርን ህግጋት ሲታዘዙባቸው የሚያሳይ የራሳቸውን ምስልን መሳል ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥45፣ 88ቤተሰባችሁ “እርስ በርስ ተዋደው እንዲኖሩ” ምን ሊረዳቸው ይችላል? (በተጨማሪም ሞዛያ 4፥14–15 ይመልከቱ)። አንዳችሁ ስለሌላችሁ መልካም የሆኑ ነገሮችን ለማለት ወይም ለመጻፍ አስቡ ወይንም በቤተሰብ ውስጥ ስላለ ፍቅር የሚያወሱ እንደ “ፍቅር በቤት” ያሉ መዝሙሮችን ዘምሩ (መዝሙር ቁጥር 294)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥61.ወይንም ይሄንን ጥቅስ እንቆቅልሽ መገጣጠም በመጫወት ላይ ሳላችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። እንቆቅልሹን እግዚአብሔርር ሚስጥራቱን እንዴት “በራእይ ላይ ራእይ በእውቀት ላይ እውቀት አድርጎ” እንደሚገልጽ ለማስተማር ለመጠቀም ትችላላችሁ። የቤተሰብ አባላትም እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ እውቀተን ጥቂት በጥቂቱ እንደገለጸላቸው ማካፈል ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 43፥25ምናልባትም ቤተሰባችሁ ቁጥር 25 ላይ ውይይት የሚያደርጉበትን ለማስተዋወቅ የነጎድጓድን ድምጽ የሚፈጥር ነገር መጠቀም ትችላላችሁ። የጌታ ድምጽ እንዴት “የነጎድጓድ ድምጽ” ይሆናል? ጌታ ወደ ንስሃ ሊጠራን የሚችልበትን መንገድ የሚያሳዩትን ጥቅሶች በጋራ ፈልጉ። ለጌታ ድምጽ በይበልጥ ምላሽን መስጠት እንዴት ትችላላችሁ?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ወንጌልን መኖር እሻለሁ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 148፤ “Ideas to Improve Your Family Scripture Study [የቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትን ለማሻሻል የሚረዱ ሃሳቦች]ን ይመልከቱ።”

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ፍቅር የተሞላበት አካባቢን አሳድጉ የቤተሰብ አባላት እርስ በርስ ያላቸው ስሜትና አንዳቸው ሌላኛውን የሚመለከቱበት መንገድ በቤት ውስጥ ያለውን መንፈስ ይወስነዋል። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ተወዳጅ፣ ክብር ያለበት ቤት እንዲፈጠር የበኩሉን አስተዋጾዖ እንዲያበረክትና ሁሉም ልምዱን እንዲያካፍል፣ ጥያቄን እንዲያነሳና ምስክርነትን መስጠት የሚያስችል እንዲሆን የበኩላቸውን እንዲያረጉ እርዷቸው። (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኝ መንገድ ማስተማር] 15ን ይመልከቱ።)

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ ሲሰብክ

ጆሴፍ ስሚዝ በናቩ ሲሰብክ፣ በሳም ሎውሎር

አትም