ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 12–18 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37–40፥ “አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም”


“ሚያዝያ 12–18 (እ.አ.አ)። ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 37-40፥ ‘አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ሚያዝያ 12–18 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37–40፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ቅዱሳን ለመጓዝ ሲዘጋጁ

ቅዱሳን ወደከርትላንድ ሲጓዙ በሳም ላውሎር

ሚያዝያ 12–18 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37–40

“አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም”

የሚሰማንን ስሜት መዝግቦ መያዝ አንደኛው “ጥበብን አከማቹ” የሚለውን የእግዚአብሔርን ምክር መታዘዝ ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥30)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ለቀደሙት አባላት፣ ቤተክርስቲያን እሁድ ስብከት ከሚሰሙበት ስፍራ በላይ ነበር። ለጆሴፍ ስሚዝ በሰጣቸው ራእዮቹ ውስጥ ጌታ ቤተክርስቲያንን ምክንያት፣ መንግስት፣ ፅዮን፣ እናም ብዙውን ጊዜም ስራ በሚሉ ቃላት ይገልጻል። ይህም ብዙዎቹን ቀደምት አባላት ወደ ቤተክርስቲያን እንዲሳቡ ያደረጋቸው ሊሆን ይችላል። የቤተክርስቲያኗን በዳግም የተመለሰ አስተምህሮ ቢወዱትም፣ ብዙዎቹ በህይወታቸው የሚታትሩለትም ነገር ጭምር እንዲሆን ይፈልጉ ይሆናል። ይህም ቢሆን፣ ጌታ ቅዱሳን ወደ ኦሃዮ እንዲሰበሰቡ የሰጠው የ1830 (እ.አ.አ) ትዕዛዝ ለአናዳንዶቹ ቀላል አልነበረም። እንደ ፊቢ ካርተር አይነት ሰዎችም፣ ይህ ማለት የተደላደለ ቤትን ትቶ ወደማይታወቅ ጠረፍ መጓዝ ማለት ነበር (በዚህ ክፍል በስተመጨረሻ ያለውን “በዳግም የመመለስ ድምጾች” ይመልከቱ)። ዛሬ እኛ እነዚያ ቅዱሳን በእምነት አይናቸው ብቻ ሊያዩት የሚችሉትን በግልጽ ማየት እንችላለን፥ ጌታ ታላቅ በረከቶች በኦሃዮ አሰናድቶላቸው ነበር።

በኦሃዮ መሰባሰብ ማስፈለጉ ከቀረ ቆይቷል፣ ነገር ግን ዛሬም ቅዱሳን በተመሳሳይ አላማ፣ በተመሳሳይ ስራ “ፅዮንን ለማምጣት” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39፥13 ) በጋራ ህብረትን ይፈጥራሉ። ልክ እንደቀደምት ቅዱሳን፣ እኛም “ለአለም መጨነቅን” እንተዋለን (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 40፥2) ምክንያቱም “የማታውቀውን ታላቅ በረከት ትቀበላለህ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39፥10) የሚለውን የጌታን ቃል ኪዳን እናምናለንና።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥109–11ን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37፥1

ጆሴፍ ስሚዝ በ1830 (እ.አ.አ) ምን ነበር የሚተረጉመው?

በዚህ ጥቅስ ውስጥ ጌታ ያጠቁመው የነበረው የጆሴፍ ስሚዝን የመፅሐፍ ቅዱስን “ትርጉም” ተብሎ የሚጠራውን መንፈሳዊ ክለሳ ስራ ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ በክፍል 37 ተመዝቦ ያለውን ራእይ ሲቀበል፣ የተወሰኑትን የዘፍጥረትን ክፍሎች ጨርሶ ነበር እናም ስለሔኖክና ስለከተማው ፅዮን ገና መማሩ ነበር (ዘፍጥረት 5፥18–24ሙሴ 7 ይመልከቱ)። ጌታ ሔኖክን ያስተማራቸው መርሆዎች በክፍል 38 ውስጥ ከገለጻቸው ጋር ተመሳሳይ ናቸው።

የቤተክርስቲያን ታሪክ ርዕሶች፣ “የጆሴፍ ስሚዝ የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣” ChurchofJesusChrist.org/study/topics ይመልከቱ።

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን

ጆሴፍ ስሚዝ ከስድኒ ሪግደን ጋር በጋራ በመንፈሳዊ በሆነ የመፅጽሐፍ ቅዱስ ክለሳ ላይ ሰርቷል። ምስል በአኒ ሄንሪ ኔደር

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38

እግዚአብሔር ሊባርከን ያሰባስበናል።

ጌታ ወደ ኦሃዮ የመሰባሰቡን ትዕዛዝ እንዲህ በማለት ነበር የደመደመው፣ “እነሆ ጥበብ በዚህ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37፥4)። ነገር ግን ሁሉም አልነበሩም ይህንን ጥበብ በትክክለኛው መንገድ የተመለከቱት። በክፍል 38 ውስጥ ጌታ ጥበቡን በበለጠ ዝርዝር ገልጿል። ከቁጥሮች 11–33 ውስጥ ስለመሰባሰብ በረከቶች ምን ትማራላችሁ? የቤተክርስቲያን አባላት ከቦታ ወደቦታ በመዘዋወር እንዲሰባሰቡ አሁን አይታዘዙም፤ ዛሬ በምን አይነት መልኩ ነው የምንሰባሰበው? እንዴት ነው እነዚህ በረከቶች በእኛ ላይ ሊሰሩ የሚችሉት? (ራስል ኤም. ኔልሰን “የተበታተኑት እስራኤላውያን መሰባሰብ፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2006 (እ.አ.አ)፣ 79–81 ይመልከቱ)።

የተቀረውን የዚህን ክፍል ስታነቡ፣ ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተቀብለው ወደ ኦሃዮ እንዲሰባሰቡ ያስቻላቸውን እምነት እንዴት እንዳገኙ የሚገልጹትን ክፍሎች ተመልከቱ። በተጨማሪም ስለሰጣችሁ ትዕዛዛቶች እና ለመታዘዝ ስለሚያስፈልጋችሁ እምነት አስቡ። ተከታዮቹ ጥያቄዎች ጥናታችሁን ሊመሩላችሁ ይችላሉ፥

  • ቁጥሮች 1–4 ውስጥ በጌታና በትዕዛዛቱ ውስጥ ምን መተማመንን የሚሰጠንን ታገኛላችሁ?

  • እንዴት አድርጎ ነው ምንም እንኳን መስዋዕትነትን ቢጠይቁም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንድንታዘዝ ቁጥር 39 እንዴት ሊረዳን ይችላል?

ሌላ ምን ታገኛላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥11–13፣ 22–32፣ 41–42

ዝግጁ ከሆንኩ፣ ልፈራ አይገባም።

ቅዱሳን ብዙ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር፣ እናም ጌታ ገና ተጨማሪ እንደሚኖርም ያውቅ ነበር (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 38፥11–13፣ 28–29 ይመልከቱ)። እንዳይፈሩ ለማድረግ እንዲረዳቸው ድንቅ የሆኑ መርህን ገለጠ፥ “ከተዘጋጃችሁ ፍርሀት አይኖራችሁም” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥30)። ስለሚያጋጥሟችሁ ፈተናዎች ለማሰላሰል ጥቂት ደቂቃዎችን ውሰዱ። ከዛም ክፍል 38ን ስታነቡ፣ አንፈራ ዘንድ እራሳችንን ለፈተናዎች ለማዘጋጀት ስለሚያስችሉን መንገዶች ከመንፈስ የሚመጡ ማነሳሻዎችን አድምጡ።

በተጨማሪም ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ “አትሸበሩ፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 18–21 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39–40

የአለም ነገሮች በእግዚአብሔርን ቃላት ከመታዘዝ በጭራሽ ሊያደናቅፉኝ አይገባቸውም።

በክፍል መግቢያዎች ውስጥ ያሉትን የታሪኩን የኋሊት አመጣጥ ጨምሮ፣ ክፍሎች 3940 አንብቡ፣ እናም የጄምስ ኮቪል ተሞክሮ እናንተ ላይ እንዴት ሊሰራ እንደሚችል አስቡበት። ለምሳሌ “[ልባችሁ በእግዚአብሔር] ፊት መልካም” የነበረበትን ጊዜ አስቡት (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 40፥1)። በታማኝነታችሁ እንዴት ነበር የተባረካችሁት? እናም “በአለም መጨንቅ” የሚደርስባችሁን ነገሮች አስቡ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39፥940፥2)። በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ የበለጠ ያለማቋረጥ ታዛዥ እንድትሆኑ የሚያነሳሳችሁን ምን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ማቴዎስ 13፥3–23 ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37፥3ቤተሰባችሁ ቅዱሳን ወደ ኦሃዮ በተሰባሰቡ ጊዜ የከፈሉትን መስዋዕትነት እንዲረዱ ለማገዝ ከዚህ ክፍል ጋር አብሮ የሚሄደውን ካርታ አሳዩአቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥22.ኢየሱስ ክርስቶስን የቤተሰባችን “ህግ ሰጪ” እንዴት ማድረግ እንችላለን? የእርሱን ትዕዛዝ መከተል እንዴት ነው “ነጻ ህዝብ” የሚያደርገን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥24–27ልጆችን “አንድ ሁኑ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማስተማር የቤተሰባችሁን አባላት እንዲቆጥሩ እና እያንዳንዱ ሰው ምን ያህል ለቤተሰቡ ጠቃሚ እንደሆነ እንዲወያዩ አድርጉ። በጋራ አንድ ቤተሰብ እንደሆናችሁ በትኩረት ግለጹ። ልጆቻችሁን በትልቁ 1ን በፖስተር ላይ እንዲስሉና ዙሪያውን በእያንዳንዱ የቤተሰቡ አባላት ስም እና ምስል እንዲያሳምሩት ልትረዷቸው ትችላላችሁ። በፖስተሩም ላይ እንደቤተሰብ አንድ ለመሆን እንዲረዷችሁ የምትፈጽሟቸውን ነገሮች መጻፍ ትችላላችሁ። እንዲሁም ደግሞ “ፍቅር በልባችን” ትችላላችሁ (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪድዮ ለመመልከት ወይም ሙሴ 7፥18 ለማንበብ ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥29–30በግል ወይም በቤተሰብ ውስጥ በቅርብ ስላጋጠማችሁ ዝግጅት ስላስፈለጉት ተሞክሮ ተወያዩ። ዝግጅታችሁ ተሞክሯችሁ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ነበረው? ጌታ በምን ላይ እንድንዘጋጅ ይፈልጋል? ዝግጁ መሆናችን እንዳንፈራ እንዴት ይረዳናል? ዝግጁ ለመሆን ምን ማድረግ አለብን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 40“የአለም መጨነቅ” የሚለው ሃረግ (ቁጥር 2) ለእኛ ምን ትርጉም አለው? የእግዚአብሔርን ቃል “በደስታ” እንዳንቀበል የሚያደርጉን ከአለም የሚመጡ ጭንቀቶች አሉን? እንዴት እናሸንፋቸዋለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ኢየሱስ ሁሉንም ውደዱ ብሏል፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 61።

ምስል
በዳግም የመመለስ ድምጾች ምልክት

በዳግም የመመለስ ድምጾች

ወደኦሃዮ መሰባሰብ

ምስል
የከርትላንድ ህንጻዎች

የከርትላንድ መንደር በኦል ራውንድስ

ምስል
ፊቢ ካርተር ውድረፍ

በ1830 (እ.አ.አ) አመታት ወደኦሃዮ ከተሰባሰቡት ብዙ ቅዱሳን መሃከል ፊቢ ካርተር ነበረች። ምንም እንኳን ወላጆቿ በቤተክርስቲያኗ ባይቀላቀሉም፣ እርሷ ግን በደቡብ ምስራቅ አሜሪካ በሃያዎቹ የእድሜዋ አጋማሽ ላይ በቤተክርስቲያኗ ተቀላቀለች። በኋላም ወደ ኦሃዮ ሄዳ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ለመቀላቀል ስለወሰነችው ውሳኔ ጽፋለች፥

“ጓደኞቼ ልክ እንደእኔ በምወስደው እርምጃ ተደንቀው ነበር፣ ነገር ግን አንዳች ነገር ከውስጤ ገፋፋኝ። ቤቴን ትቼ ለመሄድ በመወሰኔ እናቴ ላይ የደረሰው ሃዘን ከምቋቋው በላይ ነበር፤ እናም በውስጤ በነበረው መንፈስ ሃይል ባይሆን ኖሮ በስተመጨረሻው እሸነፍ ነበር። እናቴ ወደልብ አልባው አለም ብቻዬን ስሄድ ከምትመለከት ይልቅ እዛው ስቀበር ብታይ እንደምትመርጥ ነገረችኝ።

“‘[ፊቢ]፣’ አለችኝ በሚያስገርም ሁኔታ፣ ‘ሞርሞንነት ሃሰት ሆኖ ካገኘሽው ወደእኔ ትመለሻለሽን?’

“እኔም መለስኳት፣ ‘አዎ እማዬ፣ እመለሳለሁ።’ … መልሴ ፍርሃቷን ቢያበርደውም መለያየታችን ግን ብዙ ሃዘንን አስከተለ። መሄጃዬ ሲደርስ ለመሰናበት ዝግጁ ነኝ ብዬ እራሴን አላመንኩትም፤ እናም ስንብቴን በጽሁፍ አስፍሬ ለሁለቱም በጠረጴዛዬ ላይ አስቀምጬላቸው በደረጃው እሮጬ ወጣሁና ጋሪውን ተሳፈርኩኝ። ያኔም የልጅነት ተወዳጅ ቤቴን ትቼ ከእግዚአብሔር ቅዱሳን ጋር ህይወቴን ለማቀላቀል ሄድኩ።”1

ከስንብት ደብዳቤዎቿ ባንዱ ፊቢ እንዲህ ብላ ጻፈች፥

“ውድ ወላጆቼ፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ ባላውቅም አሁን ግን የወላጆቼን ጣራ ትቼ ለጊዜው ልሄድ ነው—ነገር ግን ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ላገኘሁት ደግነት ያለአመስጋኝ ስሜቶች አይደለም —ነገር ግን አመላክ ይህን ከሌላ ጊዜ በላይ አሁን ይህን ያዝዛል። ሁሉንም ነገር ለአምላክ ፍቃድ አሳልፈን እንስጥ እና ከሁሉም ነገር በላይ እግዚአብሔርን በጣም ከወደድነው ይህም ለእኛ መልካም እንደሚሆን በማመን፣ እስካሁን በአንድ ላይ ደስ በሚል ሁኔታ እንድንኖር ስለተፈቀደልን አመስጋኝ እንሁን። ከልብ የሆነውን የሁሉንም ፍጡሩን ጸሎት ወደሚሰማው እና ለእኛ መልካም የሆነውን ወደሚሰጠን ወደ ብቸኛው እግዚአብሔር መጸለየይ እንደምንችል እናስተውል። …

“እማዬ፣ የእኔ ወደ ምዕራብ መሄድ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ አምናለሁ እናም ፍቃዱ ይህ እንደሆነ ለረጅም ጊዜ አምኜበታለሁ። አሁን መንገዱ ተከፍቷል …፤ ይህን ያደረገ ለሁሉም በቂ የሆነው የጌታ መንፈስ እንደሆነ አምናለሁ። አቤቱ፣ እባካችሁ ስለልጃችሁ አትጨነቁ፤ እኔን ጌታ ያጽናናኛልና። ጌታ እንደሚንከባከበኝ አምናለሁ እናም መልካም የሆነውን ይሰጠኛል። … የምሄደውም ጌታዬ ስለ ጠራኝ ነው—ሀላፊነቴንም ግልጽ አድርጓል።” 2

ማስታወሻዎች

  1. ኤድዋርድ ደብሊው. ቱሊጅ The Women of Mormondom [የሞርሞንነት ሴቶች] 1877 (እ.አ.አ)፣ 412።

  2. የፊቢ ካርተር ደብዳቤ ለወላጆቿ፣ ቀን የለውም፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጽሃፍት፣ ሶልት ሌክ ሲቲ፤ አጻጻፉ ዘመናዊ ተደርጓል። ፊቢ በ1834 (እ.አ.አ) በቤተክርስቲያኗ ተቀላቀለች፣ በ1835 (እ.አ.አ) ወደ ኦሃዮ ተጓዘች፣ እናም ዊልፎርድ ውድሩፍን በ1837 (እ.አ.አ) አገባች።

አትም