ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
መጋቢት 29፟–ሚያዝያ 4 (እ.አ.አ)። ፋሲካ፥ “እኔ ህያውም ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ”


“መጋቢት 29፟–ሚያዝያ 4 (እ.አ.አ)። ፋሲካ፥ ‘እኔ ህያውም ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 29፟–ሚያዝያ 4 (እ.አ.አ)። ፋሲካ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ክርስተስ ሃውልት

መጋቢት 29፟–ሚያዝያ 4 (እ.አ.አ)

ፋሲካ

“እኔ ህያውም ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ”

በፋሲካ ሰንበት የአዳኝን ትንሳኤ ለማክበር ስትዘጋጁ፣ ዘመናዊ ራእዮች እንዴት አድርገው ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር አንድያ ልጅ እና የአለም ሁሉ ቤዛ እንደሆነ ያምታውቁበትን እምነት ጥልቅ እንዳደረጉላችሁ አሰላስሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ሚያዝያ 3 ቀን 1836 (እ.አ.አ) የፋሲካ ሰንበት ነበር። ቅዱስ ቁርባንን አዲስ በተመረቀው በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ለቅዱሳን ካሳለፉ በኋላ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ ከመጋረጃው በስተጀርባ ጸጥ ያለ ስፍራን መርጠው ለጸሎት ተንበረከኩ። በኋላም በሁሉም ስፍራ ክርስቲያኖች የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤ እያሰቡ ባለበት በዚህ በተቀደሰ ቀን፣ ከሞት የተነሳው አዳኝ እራሱ በቤተመቅደሱ ተገልጾ “እኔ ህያውም ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ” ሲል አወጀ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥4)።

ኢየሱስ ክርስቶስ “ህያው ነው” ማለት ምን ማለት ነው? ከመቃብር በሶስተኛው ቀን ተነስቶ በገሊላ ለነበሩት ደቀመዝሙሮቹ ተገለጸ ማለት ብቻ አይደለም። አሁንም በህይወት ይኖራል ማለት ነው። ዛሬም በነቢያት በኩል ይናገራል። ዛሬም እርሱ ቤተክርቲያኑን ይመራል። የታመሙ ነፍሳትን ያድናል እናም የተሰበሩ ልቦችን ይጠግናል። እኛም የጆሴፍ ስሚዝን ጠንካራ ምስክርነት በማስተጋባት፥ “ስለእርሱ ከተሰጡት ብዙ ምስክሮች በኋላ፣ ይህም በመጨረሻ ስለእርሱ የምንሰጠው ምስክርነት፥ እርሱ ህያው መሆኑን ነው!” ማለት እንችላለን።” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥22)። በእነዚህ ራዕያት ውስጥ የእርሱን ድምጽ መስማት እንችላለን። የእርሱን እጆች በህይወታችን ልናይ እንችላለን። እያንዳንዳችንም “‘አዳኜ ህያው እንደሆነ አውቃለው!’ የሚለው ይህ አረፍተ ነገር የሚሰጠው ደስታ” ሊሰማን ይችላል። (መዝሙር ቁጥር 136)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥538፥762፥176፥11–14፣ 20–24110፥1–10

ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው ነው።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተነሳውን አዳኝ ብዙ ጊዜ አይቶታል እናም ሁለቱ አጋጣሚዎች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ተመዝግበው ይገኛሉ። ክፍል 76፥11–14፣ 20–24110፥1–10ን ስታነቡ፣ ስለጆሴፍ ስሚዝ ምስክርነት ምን ያስደንቃችኋል? ምስክርነቱ ለእናንተ ጠቀሜታው ምንድን ነው?

በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ በሙሉ አዳኝ ስለራሱ ተልዕኮና መለኮታዊነቱ ምስክርነትን ሰጥቷል። ስለህያው ክርስቶስ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥538፥762፥1 ውስጥ ካሉት ከራሱ ቃላት ምን ትማራላችሁ? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን ስታጠኑ እንደዚህ አይነት አዋጆችን መመዝገብን አስቡበት።

በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥17ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥26–2742፥45–4663፥4988፥14–17፣ 27–3193፥33–34

በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነትም በትንሳኤ እነሳለሁ።

ጆሴፍ ስሚዝ የሚወዱትን ሰው በማጣት የሚመጣውን ሃዘን ያውቃል። ሁለቱ ወንድሞቹ አልቪን እና ዶን ካርሎስ ገና ወጣቶች ሳሉ ነበር የሞቱት። ጆሴፍ እና ኤማ እያንዳንዳቸው ከሁለት አመት በታች የሆኑ ስድስት ልጆች ቀብረዋል። ነገር ግን በተቀበለው ራእይ አማካኝነት፣ ጆሴፍ ስለሞትና ስለእግዚአብሔር ዘለአለማዊ እቅድ ዘለአለማዊ የሆነ አስተሳሰብን አገኘ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥26–2742፥45–4663፥4988፥14–17፣ 27–3193፥33–34 ውስጥ የተጠቀሱትን እውነታዎች አስቡባቸው። ስለሞት ያላችሁን አስተሳሰብ ይህ ራእይ እንዴት ይቀይረዋል? አኗኗራችሁስ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ አለው?

በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 15፤ ኤም. ራስል ባላርድ “የሙታን ድነት ራእይ፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 71–74፤ Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [የቤተክርስቲያን ፕሬዚደንቶች ትምህርቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ] [2007 (እ.አ.አ)]፣ 174–76 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–1319፥16–1945፥3–576፥69–70

ኢየሱስ ክርስቶስ “ፍጹም የኃጢያት ክፍያን” አከናውኗል።

በፋሲካ ወቅት አንደኛው በአዳኝ ላይ ማትኮሪያ መንገድ ቢኖር በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ስለመስዋዕትነቱ የሚያስተምሩ ክፍሎችን ማጥናት ነው። አንዳንዶቹ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–1319፥16–1945፥3–576፥69–70 ውስጥ ይገኛሉ። ምናልባትም በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለአዳኝ የኃጢያት ክፍያ የምታገኟቸውን እውነታዎች መዘርዘር ትችላላችሁ። ጥናታችሁን ጥልቅ ለማድረግ፣ በየኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ” በሚለው ርዕስ ስር ተጨማሪ የቅዱሳት መጻህፍት ማጣቀሻዎችን በመፈልግ በዝርዝራችሁ ለመጨመር ትችላላችሁ (የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ scriptures.ChurchofJesusChrist.org)።

ጥናታችሁን ሊመሩላችሁ የሚችሉ ጥያቄዎችም እነሆ፥

  • ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሰቃየት ለምን መረጠ?

  • የእርሱን መስዋዕትነት በረከት ለመቀበል ምን ማድረግ አለብኝ?

  • የእርሱ የኃጢያት ክፍያ በህይወቴ ላይ ተጽዕኖ እንዳለው እንዴት ማወቅ እችላለሁ?

ምስል
ኢየሱስ ሲጸልይ

የጸሎት ጌታ በዮንግሳንግ ኪም

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

አጠቃላይ ጉባኤ።አጠቃላይ ጉባኤ በዚህ አመት በፋሲካ ሰንበት ስለሚውል፣ የጉባኤው ንግግሮች (መዝሙሮቹን ጨምሮ) ቤተሰባችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን ምስክርነት እንዴት በጥልቅ ሊያጠነክሩ እንደሚችሉ ልታስቡበት ትችላላችሁ። ለምሳሌ ህጻናት ልጆቻችሁ ስለኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክት ሲሰሙ ወይም መዝሙር ሲሰሙ የእርሱን ምስል መሳል ወይም የእርሱን ምስል ከፍ አድርገው መያዝ ይችላሉ። ሌሎች የቤተሰብ አባላት ደግሞ የሰሙትን እውነት በዝርዝር መጻፍ ይችላሉ። ከዛም በኋላ የቤተሰብ አባላት የሳሉትን ወይንም የጻፉትን የራሳቸውን ምስክርነት ማካፈል ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥14–17138፥17, 50ቤተሰባችሁ በቁስ የተደገፈ ወይም በማሰብ ላይ የተመሰረተ መሞት እና ከሞት መነሳት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚያሳይ ትምህርታዊ ሀሳቦችን በማሰብ ሊደሰቱ ይችላሉ—አንደ ጓንት እና እጅ አይነት ሰውነት እና ነፍስ ሲለያዩ እና ተመልሰው ሲዋሃዱ የሚያሳዩ ምሳሌዎችንም። ጌታ ለእኛ ስላደረገው ነገር ያለንን ምስጋና እነዚህ ጥቅሶች በምን መልኩ ያጠናክሩታል?

“ህያው ክርስቶስ፥ የሐዋሪያት ምስክር።”ስለዘመናዊ ነብያት የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነቶች ውይይትን ለማነሳሳት እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል “ህያው ክርስቶስ፥ የሐሃዋርያት ምስክርነትን” (ኤንዛይንወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ በፊት ለፊት ገጽ ውስጠኛው ሽፋን) እንዲያነቡ እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተማሩትን እንዲያካፍሉለመመደብ ትችላላችሁ። የሚከተለውን ቪድዮ ማሳየት ትችላላችሁ፥ “Apostle Testimony Montage” (ChurchofJesusChrist.org)። እኛን የሚያነሳሳ ምን እውነታ እናገኛለን?

“አዳኜ ህያው እንደሆነ አውቃለሁ።”ቤተሰባችሁ ህያው ክርስቶስ እኛን ዛሬ የሚባርክበትን ብዙ መንገዶች እንዲረዱ በጋራ “አዳኜ ህያው እንደሆነ አውቃለሁ” የሚለውን መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ (መዝሙር ቁጥር 136) እናም በዚህ መዝሙር ላይ የተጠቀሱትን እውነቶች ከእሚቀጥሉት ጥቅሶች ጋር አገናኙ፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥3445፥3–584፥7798፥18138፥23። ቤተሰባችሁ ለመዝሙሩ አዳኛቸው ህያው እንደሆነ የሚገልጹ ተጨማሪ ግጥሞችን መጻፍ ሊያስደስታቸው ይችላል።

ለፋሲካ ቪድዮዎችና ለሌሊች ማጣቀሻዎች በሚቀጥለው ይመለከቱ፥ Easter.ComeUntoChrist.org

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ኢየሱስ ተነስቷል፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 70።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

በየእለቱ ነገሮች ትምህርቶችን ማግኘት። የቤተሰባችሁ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ወደ ወንጌል ጠቃሚ ውይይት እንዴት ሊመራ እንደሚችል አስቡበት (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 4)። ለምሳሌ፣ ዝናብ እግዚአብሄር እንዴት አድርጎ ልጆቹን በበረከት እንደሚያጥለቀልቃቸው ለመወያየት መልካም አጋጣሚ ሊሆን ይችላል።

ምስል
ኢየሱስ ለጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ ሲገለጽ

ኢየሱስ ክርስቶስ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ ሲገለጽ በዋልተር ሬን

አትም