ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
መጋቢት 22–28 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቦቹን ይሰበስባል”


“መጋቢት 22–28 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥ ‘ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቦቹን ይሰበስባል’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) 2020 (እ.አ.አ)

“መጋቢት 22–28 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ 2021 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ በተንበረከኩ ሰዎች ፊት ቆሞ

ጉልበት ሁሉ ይንበረከካል በጄ. ከርክ ሪቻርድስ

መጋቢት 22–28 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29

ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቦቹን ይሰበስባል

ቅዱሳት መጻህፍትን የምናጠናበት አንደኛው ምክንያት ትምህርቶችን፣ ወይም ለመዳናችን አስፈላጊ የሆኑ የወንጌል እውነቶችን ለመማር ነው። በዚህ ሳምንት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29ን ስታጠኑ፣ ለእናንተ ትርጉም ያላቸውን ትምህርታዊ ምክረ ሃሳቦች ፈልጉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ምንም እንኳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በ1830 (እ.አ.አ) የተቋቋመች ብትሆንም፣ ብዙ የወንጌል እውነቶች ወደፊት ገና ይገለጡ ነበር፣ እናም ብዙ ቀደምት አባላት ጥያቄዎች ነበሯቸው። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ስለእስራኤል መሰባሰብና ስለፅዮን መገንባት ትንቢቶችን አንብበው ነበር (3 ኔፊ 21ን ይመልከቱ)። ይህ እንዴት ሆነ? ሀይም ፔጅ ተቀበልኩ ያለውና የአባላቱን ጉጉት የጨመረው ራእይ ይህን ጉዳይ አንስቷል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28)። ሌሎችም ሰዎች ስለአዳም እና ሔዋን ውድቀት እና ስለ ዘለአለማዊ ሞት አሰቡ። ጌታ እነዚህን ጥያቄዎች በ1830 (እ.አ.አ) ተቀበላቸው፥ ለቅዱሳኑ እንዲህ አለ “እንደ ትእዛዜ በጸሎት አንድ ሆናችሁ በእምነት የምትጠይቁትን ማንኛውንም ነገር ትቀበላላችሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥6)። ዛሬም ጥያቄዎቻችንን ይቀበላል፤ እርሱ እኛ በጸሎት እስከምንጠይቀው ብቻ ነው የሚጠብቀው። በእርግጥም በአስተምህሮቱ ራእይ ሙሉ የሆነው ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29 እንደሚያሳየው፣ እርሱ አንዳንድ ጊዜ መልስ የሚሰጠው እኛ በመጀመሪያ ከጠየቅነው የበለጠ እውነትና እውቀትን በመጨመር ነው።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29

የሰማይ አባታችን ለእኛ ከፍ ማለት ፍጹም የሆነ እቅድን አዘጋጀ።

እግዚአብሔር ለልጆቹ ስላለው እቅድ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29 ብዙ እውቀቶችን ያስተምራል። ስታነቡም፣ ከእያንዳንዱ ከተከታዮቹ የእቅዱ አካሎች የምትማሩባቸው ስለሆኑት እውነታዎች ፈልጉ፥

ምን አዳዲስ ምክረ ሃሳቦችን አገኛችሁ? ስለእነዚህ እውነቶች ባታውቁ ኖሮ ህይወታችሁ በምን አይነት መልኩ የተለየ ሊሆን ይችላል?

ስለሰማይ አባት እቅድ ይበልጥ ለማጥናት “የደህንነት እቅድ” (ወንጌሌን ስበኩ፥ ለሚስዮናዊ አገልግሎት መመሪያ፣ የተከለሰ ቅጂ 2018 (እ.አ.አ)]፣ ChurchofJesusChrist.org/manual/missionary)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥1–8

ኢየሱስ ክርስቶስ ከዳግም ምፅዓቱ በፊት ህዝቦቹን ይሰበስባል።

ኢየሱስ ክርስቶስ የህዝቦቹን መሰባሰብ የገለጸው “ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምሰበስብ” ብሎ ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥2)። ይህ ምስል ጌታ ስለእናንተ ለማሰባሰብ ስላለው ፍላጎት ምን ያስተምራችኋል? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥1–8ን ስታነቡ፣ ለምን እንሰባሰባለን፣ ማን ያሰባስባል፣ እንዴት አድርገን “የተመረጡትን” (ቁጥር 7) በማሰባሰብ እንረዳለን ስለሚሉት የተገለጹትን ምክረ ሃሳቦች ፈልጉ።

በእኛ ዘመን ወደ ፅዮን መሰባሰብ ማለት በፅዮን ካስማ በአለም ዙሪያ ህብረት መፍጠር ማለት ነው። ከአዳኙ ዳግም ምፅዓት በፊት ለሚመጡት መከራዎች “እንዲዘጋጁ” እንደ ቅዱሳን መሰባሰባችን እንዴት ይረዳናል? (ቁጥር 8፣ በተጨማሪም ቁጥሮች 14–28 ን ይመልከቱ)።

በተጨማሪም እነዚህን ይመልከቱ፥ የእምነት አንቀጾች 1፥10፣ ራስል ኤም. ኔልሰን እና ዌንዲ ደብሊው. ኔልሰን “የእስራኤል ተስፋ” (አለም አቀፍ የወጣቶች ስብስብ፣ ሰኔ 3 ቀን 2018 (እ.አ.አ)፣ ChurchofJesusChrist.org)።

ዶሮ እና ጫጩቶቿ

ምን ያህል ጊዜ፣ በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥31–35

“ሁሉም ነገሮች ለእኔ መንፈሳዊ ናቸው”

በምን አይነት መልኩ ነው ሁሉም ትእዛዛት መንፈሳዊ የሆኑት? ሁሉም ትእዛዛት መንፈሳዊ መሆናቸውን ማወቁ ስለትእዛዛት አስፈላጊነት ምን ያስተምራችኋል? የተወሰኑ ትእዛዛትን ከዘረዘራችሁ በኋላ ከእያንዳንዱ ጋር ያለውን መንፈሳዊ መርሆች አስቡበት።

በእለት ተእለት ተግባራችሁ ጊዜያዊ እና የተለመዱ በሚመስሉት እንቅስቃሴዎቻችሁ ሁሉ መንፈሳዊ ትርጉምን ብትፈልጉ ምን ሊቀየር ይችላል?

በተጨማሪም ሮሜ 8፥61 ኔፊ 15፥30–32ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥36–50

ኢየሱስ ክርስቶስ ከውድቀት አድኖናል።

ይህ ራእይ የተጀመረው ጌታ ራሱን፣ እንደ ቤትዛችን፣ “[ለኃጢያቶቻችን] ክፍያ” (ቁጥር 1) እንደሆነ በማስተዋወቅ ነው ። ራእዩም ማብራራቱን በመቀጠል ለምን አዳኝ እንዳስፈለገን ይናገራል። ቁጥሮች 36–50ን በመጠቀም በአዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ቤዛነት እንደሚያስፈልገን እንዴት አድርገን ልናብራራ እንደምንችል አስቡበት። በብዙ የእምነት ባህሎች ውድቀት እንደ መጥፎ አጋጣሚ እንደሆነ ይታሰባል፤ እናንተ ከእነዚህ ጥቅሶች ስለውድቀት ጠቃሚ ውጤት የሚያስተምር ምን ታገኛላችሁ? (በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ15፥222 ኔፊ 2፥6–8፣ 15–29ሞዛያ 3፥1–19ሙሴ 5፥9–12ን ይመልከቱ።)

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29 ጋር በዚህ ክፍል መጨረሻ ላይ ያለውን ምስል በመጠቀም ቤተሰባችሁን ስለ ደህንነት እቅድ ማስተማር ትችላላችሁ። ለምሳሌ የቤተሰብ አባላት ስለእቅዱ የተመከሩትን ጥቅሶች የተለያዩ ክፍሎች በማንበብና ስለእነዚህም በመወያየት ሊማሩ ይችላሉ። ተጨማሪ እውነታዎችን ከወንጌል ርዕሶች (topics.ChurchofJesusChrist.org) ወይንም ከቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org) ማግኘት ይችላሉ። የተማራችሁትን በጽሁፍ አስፍሩ። ስለደህንነት እቅድ በማወቃችን አመስጋኝ የምንሆነው ለምንድን ነው? ስለእርሱ ማወቃችን የየእለት ኑሯችን ላይ ምን አስተዋጽዖ ይኖረዋል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥2፣ 7–8በአዳኝ መሰብሰብ ማለት ምን ማለት ነው? የተመረጡትን እንዲያሰባስብ እንዴት ልንረዳው እንችላለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥3–5“[ልባችንን እንድናነሳ እናም እንድንደሰት]” (ቁጥር 5) ከሚረዱን ከእነዚህ ጥቅሶች ስለአዳኝ ምን እንማራለን? “ደስታን ማግኘት እንችላለን” የሚለው ቪድዮ (ChurchofJesusChrist.org) የደህንነትን እቅድ በማወቃችሁ ለቤተሰባችሁ ስላመጣው ደስታ እንድትወያዩ ሊረዳችሁ ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥34–35እነዚህን ጥቅሶች ማንበብ ቤተሰባችሁ ልትከተሏቸው እየሞከራችሁ ስላሉችኋቸው ትእዛዛት ወይንም ነቢያዊ ምክር ጀርባ ስላለው መንፈሳዊ ምክንያት እንድትወያዩበት እድሉን ይፈጥራላችኋል። ለምሳሌ ጌታ ለምንድን ነው ቅዱሳት መጻህፍትን እንደ ቤተሰብ እንድናነብ የሚፈልገው? ትእዛዛትን በመጠበቅ ምን አይነት መንፈሳዊ ጠቀሜታዎችን አይተናል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “እስራኤል፣ እስራኤል እግዚአብሔር አየተጣራ ነው,” መዝሙር፣ ቁጥር 7።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ኢየሱስ ክርስቶስን መፈለግ። ቅዱሳት መጻህፍት የእግዚአብሔር ፍጥረቶች ሁሉ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚመሰክሩ ያስተምሩናል (ሙሴ 6፥62–63 ይመልከቱ)፣ ስለዚህም ቅዱሳት መጻህፍትን ስታነቡ እርሱን ፈልጉ። ስለእርሱ የሚያስተምሩ ጥቅሶችን ለመመዝገብ ወይም ለማቅለም ሞክሩ።