ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
መጋቢት 8–14። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23–26፥ “ቤተክርስቲያኗን [አጠናክሩ]”


“መጋቢት 8–14። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን 23–26፥ ‘ቤተክርስቲያኗን [አጠናክሩ]’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 8–14። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23-26፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ኤማ ስሚዝ

መጋቢት 8–14

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23–26

“ቤተክርስቲያኗን [አጠናክሩ]”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23–26ን ስታነቡ፣ ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጡትን ምሪቶች መዝግቡ። በእነዚህ ራዕዮች ላይ ያሉትን ምክሮች እንዴት አድርጋችሁ ነው የራሳችሁን ደቀመዝሙርነት እና ቤተክርስቲያኗን ለማጠንከር የምትጠቀሙበት?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ቤተክርስቲያን ከተቋቋመች በኋላ፣ ቅዱሳኑ አዳዲስ ፈተናዎች አጋጠሟቸው—ወንጌልን ለማስፋፋትና ከቤተክርስቲያን ጋር ህብረት የፈጠሩትን ለማጠንከር፣ ይህንንም የሚያደርጉት መሳደዱም እየጨመረ ሲመጣ ነበር። ኤማ ስሚዝ ተቃውሞውን በቀጥታ ሲፈጸም አይታለች። በሰኔ 1830 (እ.አ.አ)፣ ኤማ እና የናይት ቤተሰብ አባላት ለመጠመቅ ፈለጉ። ነገር ግን የቤተክርስቲያኗ ጠላቶች የተቀደሰ ተሞክሮ መሆን የነበረበትን ለማወክ ሞከሩ። በመጀመሪያ ለጥምቀት በቂ ጥልቀት ያለው ውሃ ማቆር እንዲችል ተብሎ የተገነባውን ግድብ አፈረሱ። ግድቡ ከታደሰ በኋላም እንኳ፣ አሳዳጆቹ የሚጠመቁት ላይ ማስፈራሪያዎችን ለመጮህ እና ለማፌዝ ተሰበሰቡ። ከዚያም ጆሴፍ አዲስ አባላቱን ማረጋገጫ ሊሰጥ ሲል፣ ስለመፅሐፈ ሞርሞን በማስተማር ህብረተሰቡን አበሳጭተሃል በሚል ምክንያት ለእስር ተዳረገ። በዳግም ለተመለሰችው የጌታ ቤተክርስቲያን ተስፋ የሌለው ጅማሮ ይመስል ነበር። ነገር ግን በእነዚህ ችግሮችና አመጾች መካከል፣ ጌታ “ለሁሉም የሆነውን [የእርሱን] ድምጽ” የሚወክሉትን ድንቅ የሆኑ መጽናኛዎችና ማበረታቻዎችን ሰጠ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥16)።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥89–9094–97ን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23–26

የጌታን ቤተክርስቲያን ለማጠናከር ለመርዳት እችላለሁ።

ዛሬ፣ በዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያን ከተቋቋመች ከ200 አመት አካባቢ በኋላም፣ “ቤተክርስቲያኗን [የማጠንከር]” አስፈላጊነቱ ቀጥሏል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23፥3–5)። እናም ይህ ስራ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ለኦሊቨር ካውድሪ ፣ ወይም አሁን ላሉት የቤተክርስቲያን መሪዎች ብቻ አይደለም—ለሁላችንም ጭምር ነው። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23–26ን በምታጠኑበት ጊዜ ሁሉ፣ ጌታ ለቀደምት የቤተክርስቲያን አባላት ቤተክርስቲያኗን እንዲያጠናክሩ እንዲረዳቸው የሰጠውን ምክር አሰላስሉ። በዚህ ጥረት ላይ እንድትሳተፉ ጌታ ከእናንተ ምን ይፈልጋል ብላችሁ ይሰማችኋል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24

አዳኝ “[ከስቃዬ] ከፍ” ሊያደርገኝ ይችላል።

አስጨናቂ በነበረ መሳደድ ውስጥ ቤተክርስቲያኗን መምራት ለጆሴፍ ስሚዝ ከባድ ሸክም የነበረ ሳይሆን አይቀርም። ጌታ ለርሱ የሰጠውን የማበረታቻ ቃላት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24 ውስጥ ተመልከቱ።

አዳኝ ከስቃያችሁ እንዴት አድርጎ ከፍ ሊያደርጋችሁ እንደሚችል ተከታዮቹ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች ምን ሀሳብ ያቀርባሉ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥1–3 

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥8 

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥7–8 

ኢሳይያስ 40፥28–31 

ሞዛያ 24፥14–15 

ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ከስቃያችሁ ከፍ አድርጎ አውጥቷችኋል? በአስቸጋሪ ጊዜያት ሁሉ የእርሱን እርዳታ መሻታችሁን ለመቀጠል ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን ሲፈውስ

እርሱ ብዙ የተለያዩ ህመሞችን ፈወሰ በጄ. ከርክ ሪቻርድሰን

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25

ኤማ ስሚዝ “የተመረጠች ሴት” ነች።

ኤማ ሄል ጆሴፍ ስሚዝን ስታገባ፣ መስዋዕትነትን እንደምትከፍል ታውቅ ነበር ማለት ይቻላል። ከአባቷ ፍላጎት በተቃራኒ እየሄደች እንዲሁም በንጽጽር የተደላደለ ኑሮዋን ችግር በተጋለጠበት እየለወጠች ነበር። ጌታ ከእርሷ ዳግም በተመለሰው ስራው ምን እንደሚጠብቅ ሳታስብ አትቀርም። ጌታ የሰጠውን ምላሽ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25 ላይ ፈልጉ። የጌታን ቃል በቁጥር 16 ላይ ልብ በሉ—በዚህ ክፍል ውስጥ የርሱ “[ለእናንተ የሆነ] ድምጽ” እንደሆነ እንዲሰማችሁ የሚያደርግ ምን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም “የተመረጠች ሴት” (ቪዲዮ፣ ChurchofJesusChrist.org )፤ “አንቺ የተመረጥሽ ሴት ነሽ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 33–39፤ ጆይ ዲ. ጆንስ፣ “በልዩ ልዑል የሆነ ጥሪ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 15–18 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 26፥2

የጋራ ስምምነት ምን ማለት ነው?

አባላት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ጥሪ ወይም የክህነት ሹመት ሲሰጣችው፣ እነሱን እንደምንደግፍ ለማመልከት እጃችንን የማንሳት እድል አለን። ህዝባዊ ድጋፍና ስምምነትን የማሳየት መርህ የጋራ ስምምነት ይባላል። ፕሬዚደንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ እንዳስተማሩት፣ “እጅን አንስቶ የመደገፉ ሂደት መንፈሳዊ የሆነ እጅን ከማንሳት ባህል የበለጠ ነው። የተመረጡትን ከፍ ለማድረግ፣ ለመደገፍ፣ ለመርዳት ቃል መግባት ማለት ነው” (“ይህ ስራ ስለሰዎች የሚጨነቅ ነው፣” ኤንዛይን፣ ግንቦት 1995 (እ.አ.አ)፣ 51)።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና የቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23፥6ጌታ ለምንድን ነው “[በእኛ] ቤተሰብ መካከል፣ እናም [በእኛ] ባልንጀሮች መካከል፣ እናም በሁሉም ስፍራዎች” እንድንጸልይ የሚፈልገው? “ፍቅር በዚህ ይነገራል” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 190)—ወይንም ሌላ ስለጸሎት የሚያወራ መዝሙር—ስለ ጸሎት ሃይል ምን ሊያስተምረን ይችላል?

በተጨማሪም 2 ኔፊ 32፥8–93 ኔፊ 18፥18–23 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥8“[በስቃይ] ታጋሽ ሁን” ስለሚለው መወያየት ቤተሰባችሁን ሊጠቅም ይችላልን? ህጻናት ልጆች ካሏችሁ፣ ፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ “በታጋሽነት ቀጥሉ” በሚል ንግግር የገለጹትን ሙከራ እንደ አዲስ መለማመዱ አስደሳች ሊሆን ይችላል (ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ግንቦት 2010 (እ.አ.አ)፣ 56፤ በተጨማሪም ቪድዮዎችን በChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥8 ስለታጋሽነት ምን ያስተምሩናል? ጌታ በስቃያችን ታጋሽ እንድንሆን እንዴት ይረዳናል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥11–12ምናልባትም የእያንዳንዱን የቤተሰብ አባል ተወዳጅ መዝሙርን በመዘመር ለምን የእርሱ ወይም የእርሷ “ከልብ የሆነ ዝማሬ” እንደሆነ መነጋገር ትችላላችሁ። እንዴት ነው እነዚህ መዝሙሮች “ለ[እግዚአብሄር እንደ] ጸሎት” የሚሆኑት?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 26፥2“የጋራ ስምምነት” የሚለውን ርዕስ የቅዱስ መጻህፍት መመሪያ ውስጥ መመልከቱ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል (scriptures.ChurchofJesusChrist.org)። ለመሪዎቻችን እንዴት አድርገን ነው ድጋፋችንን የምናሳየው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ድምጻችሁን ከፍ አድርጉ እናም ዘምሩ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 252፤ (“የቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትን ለማሻሻል የሚረዱ ሃሳቦች” ይመልከቱ)።

ምስል
በዳግም የመመለስ ድምጾች ምልክት

በዳግም የመመለስ ድምጾች

ኤማ ሄል ስሚዝ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25 ተመዝግቦ የሚገኘው ጌታ ለኤማ ስሚዝ የሰጠው ቃል ስለእርሷ ያለውን ስሜትና ለስራው ልታደርገው ስለምትችለው አስተዋጽኦ ይገልጻል። ነገር ግን ኤማ ምን አይነት ሰው ነበረች? ሰለስብዕናዋ፣ ስለግንኙነቶቿ፣ ስለጥንካሬዋ ምን እናውቃለን? ስለዚህች “የተመረጠች ሴት” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥3) የምናውቅበት አንደኛው መንገድ በግል የሚያውቋትን ሰዎች ቃላት በማንበብ ነው።

ምስል
ኤማ ስሚዝ

ኤማ ስሚዝ በሊ ግሪን ሪቻርድስ

ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ የእርሷ ባለቤት

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ

“በዛ ምሽት፥የእኔን ኤማን፣ እርሷ የእኔ ሚስት የሆነችውን፣ እንዲሁም የልጅነት ሚስቴ፣ የልቤን ምርጫ፣ በእጄ ስውሰድ በማይነገር ደስታ፣ ውስጤን ተጉዞ በሞላው ደስታ ተጥለቅልቄ ነበር። እንድናልፍ የተጠራንባቸውን ብዙ ትእይንቶችን ዞር ብዪ ሳስብ ብዙዎቹ በአእምሮዬ በተደጋጋሚ ንዝረት ይፈጥራሉ። ድካማችን፣ ልፋታችን፣ ሃዘናችን፣ ስቃያችን፣ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ የተቀበልነው መጽናኛ መንገዳችን የተደላደለ እና መጨረሻችንን ያማረ አድርጎታል። አቤቱ! ለጊዜው አእምሮዬን የተለያዩ ሃሳቦች ሞሉት፣ አሁንም እዚህ አለች፣ በሰባተኛውም ችግር ውስጥ፣ ሳትበገር፣ ጠንክራ፣ ሳትወላውል፣ ሳትለወጥ፣ ተወዳጇ ኤማ።”1

ሉሲ ማክ ስሚዝ፣ የባሏ እናት

ምስል
ሉሲ ማክ ስሚዝ

“ያኔ እርሷ ወጣት ነበረች፣ እናም በተፈጥሮዋ ጉጉ ስትሆን፣ ልቧ በሙሉ በጌታ ስራ ላይ ነበር፣ እንዲሁም ስለ ቤተክርስቲያን ስለ እውነት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ፍላጎት አልነበራትም። እጇ ለይ የገባውን ሁሉ በጥንካሬ ነበር የምትሰራው እናም ስግብግ የሆነውን ‘ከሌላው ሰው በበለጠ እጠቀማለው ወይ?’ የሚለውን ጥያቄ አትጠይቅም። የራሷን ጉዳዮች እንዳሉ በመተው ሽማግሌዎች ለመስበክ ሲላኩ ለጉዟቸው የሚያሰፈልጓቸውን ልብሶች በማልበስ ለማገዝ እርሷ ቀድማ በጎፈቃደኝነቷን ትገልጻለች።”2

“በህይወቴ እንደሷ ያለ ምንም አይነት መልክ ያለውን ችግር እና መከራ፣ ሁሌም እንደምታደርገው፣ ከወር ወር ከአመት አመት በማይናወጥ ጽናት፣ ቅንአትና፣ ታጋሽነት የምትጸና ሴት አይቼ አላውቅም፤ ለመጽናት ምን ማድረግ እንደነበረባት፣ በማይረጋገጥ ባህር ውስጥ ተወርውራ እንደነበር አውቃለሁ፤ ማንኛዋንም ሴት ማንበርከክ የሚችል የችግር ባህር ውስጥ እሰምትሰምጥ ድረስ የመሰደድን ማእበል ተግታለች፣ የሰውን እና የሰይጣንን ቁጣ ተቋቁማለች።”3

ጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ፣ የባሏ አባት

የኤማ የፓትሪያሪክ በረከት በወቅቱ የቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ሆነው ሲያገለግሉ በነበሩት በጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ የተሰጠ፥

“ኤማ፣ ምራቴ፣ በታማኝነትሽና እውነትሽ በጌታ የተበረክሽ ነሽ፥ ከባለቤትሽ ጋር ትባረኪያለሽ፣ በእርሱ ላይ በሚመጣ ክብርም ትደሰቻለሽ፥ የአጋርሽን መውደም በሚፈልጉ ሰዎች ክፋት የተነሳ ነፍስሽ ታውካለች፣ ለእርሱ ደህንነትም ነፍስሽ በሙሉ በጸሎት ተስባለች፥ ተደሰቺ ጌታሽ እግዚአብሔር ልመናሽን ሰምቶሻልና።

“ስለ አባትሽ ቤት ልበ ደንዳናነት በጣም አዝነሻል፣ ደህንነነታቸውንም ናፍቀሻል። ጌታ እንባሽን ያከብራል፣ በፍርዱም የተወሰኑትን ስህተታቸውን እንዲገነዘቡና ለሃጥያታቸው ንስሃን እንዲገቡ ያደርጋል፤ ነገር ግን የሚድኑት በመከራ ነው። ብዙ ዘመናትን ታያለሽ፤ አዎን፣ እስከምትረኪ ድረስ ጌታ ያኖርሻል፣ አዳኝሽንም ታያለሽና። በጌታ ስራም ልብሽ ደስ ይለዋል፣ እናም ማንም ደስታሽንም ካንቺ ሊወስድ አይችልም።

“ከልጄ ጋር የኔፋውያንን መዝገብ መልአኩ ሲሰጠው አብረሽ እንድትሄጂ ስላደረገ ሁልጊዜም የጌታን ታላቅ ምህረት ታስታውሺዋለሽ። ጌታ ሶስት ልጆችሽን ስለወሰደ ብዙ ሃዘን ገጥሞሻል፥ በዚህም አንቺ አትወቀሽም፣ የእኔ ልጅ ስም ይባረክ ዘንድ ቤተሰብን ለማሳደግ ያለሽን ንጹህ ፍላጎት ያውቃል። እናም እነሆ፣ አሁን እንዲህ እልሻለሁ፣ ጌታም እንዲህ ይላል፣ ብታምኚ በዚህ ነገር ትባረኪያለሽ እናም ለነፍስሽ ሃሴትና ለባልንጀሮችሽ ደስታ ይሆን ዘንድ ሌሎችንም ልጆች ትወልጃለሽ።

“በማስተዋል ትባረኪያለሽ፣ እናም የጾታ አጋሮችሽን ለማስተማር ሃይል ይኖርሻል። ቤተሰብሽን ጽድቅን አስተምሪ፣ እናም ትንንሾችሽን የህይወትን መንገድ፣ እናም ቅዱስ መላዕክት ይጠብቁሻል፥ እናም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥም ትድኛለሽ፤ ይህም ይሁን። አሜን።”4

ምስል
ኤማ ስሚዝ ከልጆቿ ጋር

ኤማ ስሚዝ ከልጆቿ ጋር። የመሳቅ ጊዜ በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

ምስል
የኤማ ስሚዝ ስትፅፍ

የኤማ መዝሙሮች፣ በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

አትም