ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
መጋቢት 1–7 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20–22፥ “የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መነሳት”


“መጋቢት 1–7 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20–22፥ ‘የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መነሳት’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 1–7 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20–22፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

የፒተር ዊትመር ቤት

የፒተር ዊትመር ቤት በአል ራውንድስ

መጋቢት 1–7 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20–22

“የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መነሳት”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20–22ን ስታነቡ ከመንፈስ ቅዱስ ለሚመጣ ምሪት ዝግጁ ሁኑ። በኋላ እንደማጣቀሻ እንድትጠቀሙባቸው መዝግባችሁ ያዟቸው።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን የመተርጎም ስራ በዚያን ሰአት ተጠናቆ ነበር። ነገር ግን ዳግም የመመለሱ ስራ ገና መጀመሩ ነበር። ከቀደሙት ራእዮች እንደምንረዳው አስተምህሮንና የክህነት ስልጣንን በዳግም ከመመለስ በተጨማሪ ተቋሙን የእርሱን ቤተክርስቲያን በዳግም ለመመለስ እንደሚፈልግ ግልጽ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥5318፥5ን ይመልከቱ)። እናም በሚያዝያ 6 ቀን 1830 (እ.አ.አ)፣ ከ40 በላይ የሚሆኑ አማኞች በፋየት፣ ኒው ዮርክ በዊትመር ቤተሰብ የእንጨት ቤት ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሲመሰረት ምስክር ለመሆን ተሰብስበው ነበር።

አሁንም፣ አንዳንድ ሰዎችም የተደራጀ ቤተክርስትያን ለምን አስፈላጊ ነው? ብለው ያስባሉ። መልሱ በከፊልም ቢሆን ከ1830 (እ.አ.አ) የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ስብሰባ ጋር በማያያዝ በተሰጠው ራእይ ውስጥ ይገኛል። እዚህ ውስጥም እውነተኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በኋለኛዎቹ ቀናት “ተስማሚ በሚሆን ሁኔታ ተደራጅታ [የተመሰረተች” ባትሆን ሊፈጸሙ ስለማይችሉ በረከቶች ተገልጸዋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥1)።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥84–86፣ እና “[Build Up My Church] ቤተክርስቲያኔን ገንቡ፣” ራዕይ በአገባብ፣ 29–32ን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥1–36

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በእውነተኛ አስተምህሮ ላይ ነው።

ክፍል 20 የሚተዋወቀው “ስለቤተክርስቲያን አደረጃጀት እና አስተዳደር … የተሰጠ ራዕይ” ተብሎ ነው (የክፍል መግቢያ)። ነገር ግን ይህ ራእይ የቤተክርስቲያን ህግጋቶችን፣ የክህነት ክፍሎችን፣ እና የስርአቶችን አፈጻጸም ሂደት ከመግለጹ በፊት መሰረታዊ የሆኑ አስተምህሮዎችን በማስተማር ይጀምራል። የመጀመሪያዎቹን 36 ቁጥሮች ስታነቡ፣ ይህ ለምን ሆነ ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። እናንተም ያገኛችሁትን የወንጌል እውነታ ዝርዝር ማዘጋጀት ትችላላችሁ። እነሆ አንዳንድ ምሳሌዎች፥

ቤተክርስቲያኗ በመቋቋም ላይ ሳለች እነዚህ እውነቶች ላይ አጽኖት መስጠት ለምን ጠቀሜታ አለው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37፣ 75–79

የተቀደሱ ስርአቶች በዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያን አስፈላጊ ክፍሎች ናቸው።

ቤተክርስቲያኗ በተቋቋመች ወቅት ጌታ ቅዱሳኑን፣ ጥምቀትና ቅዱስ ቁርባንን ጨምሮ፣ ስለቅዱስ ስርአቶች አስተማረ። “የጥምቀትን ስርአት በተመለከተ” ከቁጥር 37 መመሪያዎችን ስታነቡ፣ ስለራሳችሁ ጥምቀት አስቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ላይ የተገለጹት ስሜቶች ተሰምተዋችሁ ነበርን? አሁንስ ስሜቶቹ አሏችሁን? “[ኢየሱስ ክርስቶስን] እስከመጨረሻ ድረስ ለማገልገል ፈቃድ” ያላችሁን ለመቀጠል ምን ማድረግ እንደምትችሉ አሰላስሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥75–79 ውስጥ ስለ ቅዱስ ቁርባን ስታነቡ የተቀደሱትን ጸሎቶች ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማ እንዳለ ሰው ሆናችሁ ለማንበብ ሞክሩ። ስለ ቅዱስ ቁርባን ምን አይነት ማስተዋልን ትቀበላላችሁ? ስለራሳችሁስ? እነዚህ ማስተዋሎች በዚህ ሳምንት ቅዱስ ቁርባንን ለመውሰድ ራሳችሁን የምታዘጋጁበት መንገድ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ይኖራቸዋል?

ዲያቆን ቅዱስ ቁርባንን ሲያሳልፍ

ቅዱስ ቁርባን የተቀደሰ ስርአት ነው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥38–60

የክህነት አገልግሎቶች የቤተክርስቲያን አባላትን እና ቤተሰባቸውን ይባርካሉ።

ሰው የክህነት ተሸካሚዎች ስራ ምንድነው ብሎ ቢጠይቃችሁ ምን ብላችሁ ትመልሳላችሁ? የተለያዩ የክህነት ክፍሎች ስላላቸው ሀላፊነቶች የሚዘረዝረውን ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥38–60 አንብቡ። ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለክህነት ስራዎች እና አዳኙ ስራውን ስለሚሰራበት መንገድ ያላችሁን አስተሳሰብ የሚቀይር ምን ነገር አለ? በእነዚህ ጥቅሶች ላይ በተገለጹት ስራዎች እንዴት ተባርካችኋል?

ሴቶች እንዴት አድርገው የክህነት ስልጣንን በቤተክርስቲያን ስራ ላይ እንደሚለማመዱ ለማወቅ የዳለን ኤች. ኦክስን “የክህነት ሃይል እና ቁልፎች፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 49–52ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ህያው በሆነ ነቢይ ይመራል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፥4–9 ውስጥ ስለጌታ ነቢያት ቃል ምን ትማራላችሁ? የጌታን ቃል በነቢያት ለሚቀበሉ ቃል የተዘረዘሩትን ኪዳኖች በቁጥር 6 ላይ አስተውሉ። እነዚህ ቃል ኪዳኖች ለእናንተ ምን ምርጉም አላቸው?

ህያው የሆነውን የነቢይ ቃላት “ቃሉን ልክ [ከእግዚአብሔር] አንደበት እንደወጣ” አድርጋችሁ እንዴት ልትቀበሉ ትችላላችሁ (ቁጥር 5)? አሁን ያሉት ነቢይ በቁጥር 6 ላይ ወደተገቡት የበረከት ቃል ኪዳኖች እንድንመራ ምን አይነት ምክር ይለግሱናል?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20.ሰው ቤተክርስቲያን ለምን ያስፈልጋል ብሎ ቢጠይቀን ምን እንመልሳለን? ምን አይነት ምላሾችን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20 ውስጥ እናገኛለን? በተጨማሪም ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን “ለምን ቤተክርስቲያን፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 108–11 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥69“በጌታ ፊት በቅድስና [መሄድ]” ማለት ምን ማለት ነው? ለቤተሰብ አባላት በቅድስና ለመሄድ የሚረዷቸውን ነገሮች ወይም ያንን ከማድረግ ሊያስተጓጉሏቸው የሚችሉ ነገሮችን በወረቀት ላይ መሳል ወይም መጻፍ ሊያስደስታቸው ይችላል። ወረቀታቸውንን በመጠቀም መንገዶችን ለመሳል፣ እናም ወደክርስቶስ ሊወስዷቸው የሚችሉትን የመንገድ ምስሎች ላይ ብቻ በመርገጥ ጉዟቸውን ማድረግ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37፣ 71–74በቤተሰባችሁ ውስጥ ገና ያልተጠመቀ ሰው ካለ፣ እነዚህ ጥቅሶች ለጥምቀት እንዴት መዘጋጀት እእንደምንችል (ቁጥር 37 ይመልከቱ) እናም እንዴት ጥምቀት እንደሚከናወን (ቁጥሮች 71–74 ይመልከቱ) ውይይት ለማድረግ ይረዳሉ። የቤተሰብ አባላት የጥምቀታቸው እለት ፎቶን ወይም ተሞክሮን ማካፈል ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥75–79ቤተሰባችሁ እነዚህን ጥቅሶች ትርጉም ያለው፣ ውዳሴያዊ የቅዱስ ቁርባን ተሞክሮ ለመዘጋጀት እንዴት ሊጠቀምባቸው ይችላል? እነዚህ ጥቅሶች በቅዱስ ቁርባን ወቅት ልታሰላስሉባቸው ስለምትችሏቸው ነገሮች ሀሳብ ሊሰጡ ይችላሉ፣ እናም የቤተሰብ አባላት እነዚህን መፈለግ ወይም የእነዚህን ነገሮች ምስል መሳል ይችላሉ። እንዳስፈላጊነቱም፣ እናንተ እነዚያን ምስሎች ወደሚቀጥለው የቅዱስ ቁርባን ስብሰባችሁ ይዛችሁ በመሄድ በቅዱስ ቁርባን ወቅት ስለምን ማሰብ እንዳለባችሁ እንዲያስታውሷችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፥4–7የቤተሰብ አባሎቻችሁን በቁጥሮች 4–5 ውስጥ የጌታን ነቢያት ስለመከተል የሚያስተምሩ ቃላትና ሃረጎችን እንዲፈልጉ መጋበዝ ትችላላችሁ። የነቢያትን ቃላት በትእግስት መቀበል ማለት ምን ማለት ነው? በእምነትስ? በቁጥር 6 ውስጥ ያሉትን የቃል ኪዳን በረከቶች መቼ ተቀብለናቸዋል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 77።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የአዳኝን ህይወት ተከተሉ። “የጌታ ሌሎችን የማስተማርና ከፍ የማድረግ ሀይል የመጣው በሚኖርበት ህይወት ምክንያት እና ከእርሱ ማንነት ነው። በታታሪነት እንደ ክርስቶስ ለመኖር ስንጥር፣ በበለጠ ልክ እንደርሱ ለማስተማር እንችላለን” (በአዳኝ መንገድ ማስተማር፣ 13)።

ኦሊቨር ካውድሪ ጆሴፍ ስሚዝን ሲሾመው

ኦሊቨር ካውድሪ ጆሴፍ ስሚዝን ሾመው በዋልተር ሬን