ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
የካቲት 22–28 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18–19፥ “የነፍስ ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ [ነው]”


“የካቲት 22–28 (እ.አ.አ)። ትምህትና ቃል ኪዳኖች 18-19፥ ‘የነፍስ ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ [ነው]’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“የካቲት 22–28 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18-19፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
የማርቲን ሀሪስ እርሻ

ማርቲን ሀሪስ እርሻ በአል ራውንድስ

የካቲት 22–28 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18–19።

“የነፍስ ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ [ነው]”

በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ላይ የተሰጡት ራእዮች ከ200 አመት በፊት ለተለያዩ ያጋጠሙ ሁኔታዎች ምላሽ የተሰጡ ቢሆኑም በውስጣቸው የያዙት መርህ ግን ጊዜ የማይሽረው ነው። እነዚህን መርሆች በምታነቡበት ወቅት ልብ ለማለት ሞክሩ እናም እንዴት ለእናንተ እንደሚሰሩ አስቡበት።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ማርቲን እና ሉሲ ሃሪስ በፓልማይራ፣ ኒው ዮርክ ውስጥ ድንቅ የሆነ እርሻ ነበራቸው። ይህንን ለማካበት አመታት ፈጅቶባቸዋል፣ ቤተሰብ እንዲያሳድጉበት አስችሏቸዋል፣ እናም በማህበረሰቡ ጥሩ ቦታንም እንዲያገኙ አድርጓቸዋል። ነገር ግን በ1829 (እ.አ.አ) መፅሐፈ ሞርሞን ለመታተም የሚችለው ማርቲን መሬቱን በብድር አስይዞ ለማተሚያ ቤቱ ለመክፈል ከቻለ ብቻ መሆኑ ግልጽ ሆነ። ማርቲን የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክርነት ቢኖረውም ሉሲ ግን አልነበራትም። ማርቲን መሬቱን በብድር አስይዞ መፅሐፈ ሞርሞን እንደታሰበው በደንብ መሸጥ ሳይችል ቢቀር እርሻውን ሊያጣ ይችላል እናም ትዳሩንም አደጋ ላይ ይጥላል። በአንድ አጋጣሚ ወይንም በሌላ፣ እኛም ልክ እንደ ማርቲን ሁሉ እራሳችንን ከተመሳሳይ ጥያቄ ጋር ተጋፍጠን ልናገኘው እንችላለን፥ ለእኔ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምን ያህል ዋጋ አለው?። የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት ምን መስዋዕት ለማድረግ ፍቃደኛ ነኝ? “ከሁሉም ታላቅ ከሆነው” ከኢየሱስ ክርስቶስ በስተቀር ለእግዚአብሔር ልጆች ታላቁን መስዋዕትነት የከፈለ ማንም እንደሌለ ማስታወስ ይረዳናል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥18)።

ማርቲን እርሻውን በእዳ ለማስያዝ ወሰነ። የእርሱ መስዋዕትነት የመጀመሪያዎቹን 5000 የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂዎች ማተሚያ ዋጋ ከፈለ። አሁን ከ190 ሚሊዮን ቅጂዎች በላይ በኋላም፣ ሚልዮኖች የሆኑ በአለም ዙሪያ ያሉ ነፍሳት እየተባረኩ ናቸው።

ሰለመፅሐፈ ሞርሞን ህትመት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቅዱሳን፣ 1፥76–84ን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–16

እኛ ንስሃ ስንገባ ጌታ ይደሰታል።

ንስሃ ግቡ እና ንስሃ የሚሉት ቃላት ምን ያህል ጊዜ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18 እና 19 ላይ አገልግሎት ላይ እንደዋሉ ልብ በሉና በእያንዳንዱ በተጠቀሱበት ወቅት ከእነዚህ ቃላት ምን እንደምትማሩ አሰላስሉ። በተለይም ደግሞ ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 18፥10–16ን አስቡበት፤ እነዚህ ቃላት እንዴት አድርገው ስለ ንስሃ ያላችሁን አስተሳሰብ ይነኩታል—ስለራሳችሁ ንሰሃ መግባትና ሌሎችን ወደ ንስሃ መጥራት ስላለባችሁ ሃላፊነትስ?

በተጨማሪም አልማ 36፥18–21፤ ዳሊን ኤች. ኦክስ “ንስሃ፥ አስደሳቹ ምርጫ፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 121–24ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥34–36

በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የጌታን ድምጽ እሰማለሁ።

ሰው የጌታ ድምጽ እንዴት አይነት ነው ብሎ ቢጠይቃችሁ ምን ብላችሁ ትመልሳላችሁ? ስለዚህ ጥያቄ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥34–36ን እያነበባችሁ አስቡት። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን ስታነቡ ስለ ጌታ ድምጽ ምን ተማራችሁ? ድምጹን በበለጠ ጥራት ለመስማት ምን ማድረግ አለባችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥15–20

ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቃየው እኔ ንስሃ ገብቼ ወደእርሱ እንድመጣ ነው።

አዲስ ኪዳን አዳኝ በጌተሰማኔ የነበረውን ስቃይ የገለጸው ይህን በተመለከቱት ሰዎች እይታ አንጻር ነው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥15–20 ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ ቃላት ስለ ስቃዩ ተናግሯል። ይህን የተቀደሰ የግል ታሪክን ስታነቡ፣ ጌታ ስለስቃዩ ሲገልጽ የተጠቀማቸውን ቃላትና ሃረጎች ለማግኘት ሞክሩ። እያንዳንዱ ቃልና ሃረግ ምን እንደሚያስተምራችሁ አስቡበት። ጌታ ለመሰቃየት ለምን ፈቃደኛ ነበር? ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ለእናንተ ብሎ መስዋዕት ስለማድረጉ የሚሰማችሁን ስሜት መዝግቡ።

ዮሀንስ 15፥13ሞዛያ 3፥7አልማ 7፥11–12ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–13ን ይመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ህጻን ልጅን ታቅፎ

የነፍስ ዋጋ በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥26–27፣ 34–41

የእግዚአብሔር በረከቶች ከምድር ሁሉ ሃብት ይልቃሉ።

መፅሐፈ ሞርሞን በፓልማይራ ብዙም አልተሸጠም፣ በዚህም የተነሳ ማርቲን ሃሪስ ብዙውን የእርሻውን ክፍል ሸጦ እዳውን መክፈል ነበረበት (“The Contributions of Martin Harris [የማርቲን ሃሪስ አስተዋጽዖ]፣” ራዕያት በአገባብ፣ 7–8)ን ይመልከቱ። እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ ስለመስዋዕት እና እናንተ በዚህም አማካኝነት እየተቀበላችሁ ስላላችሁት በረከትም አሰላስሉ። በተጨማሪም ጌታ ምንን መስዋዕት እንድታደርጉ እንደጠየቃችሁም ማሰብ ትችላላችሁ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በ“ደስታ” እና በ“ሃሴት” መስዋዕትን እንድትከፍሉ የሚያበረታታችሁን ምን ታገኛላችሁ? (በተጨማሪም ቁጥ ሮች 15–20)ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥23

ሰላም የሚመጣው ስለኢየሱስ ክርስቶስ በመማርና እርሱን በመከተል ነው።

“ስለ እኔ ተማሩ” የሚለውን የአዳኙን ግብዣ አስቡበት። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19 ውስጥ ምን ትማራላችሁ? ይህ የአዳኙ እውነታ እንዴት አድርጎ ሰላምን ማግኘት እንድትችሉ እንደረዳችሁ ሃሳባችሁን መዝግቡና አሰላስሉት። “[በመንፈሱ] በትህትና ተጓዝ” የሚለው ለእናንተ ምን ትርጉም አለው?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥1–5ምናልባትም የቤተሰብ አባላት “በብዙ አጋጣሚዎች” (ቁጥር 2) መንፈስ ለኦሊቨር ካውድሪ ቅዱሳት መጻህፍት እውነት እንደሆኑ ልክ እንደገለጸለት አይነት ለእነርሱም እንደገለጸላቸው ለማካፈል ይችላሉ። ቤተሰባችሁ እንዴት በቅዱሳት መጻህፍት “በተጻፉት ላይ [መደገፍ]“ (ቁጥር 3) ይችላሉ? የቤተሰባችሁን መሰረት በወንጌል “አለት” ላይ እንዴት መገንባት ትችላላችሁ (ቁጥር 4)?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–1319፥16–19እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–13ን አንብበው የራሱን ወይንም የራሷን ስም “ነፍስ”፣ “ነፍሳት”፣ እና “ሰዎች” በሚለው ተክተው ማንበብ ይችላሉ። ከዛም እነዚህ ጥቅሶች እንዴት በአብና ልጁ ዘንድ ያለንን ዋጋ እንድንገነዘብ እንደሚረዱን መወያየት ትችላላችሁ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥16–19)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥21–25የቤተሰባችሁ አባላት ስሞች የተለየ ትርጉም አላቸውን? ስሞች ለምን ጠቃሚ እንደሆኑና በላያችን ላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም መውሰድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ልትነጋገሩበት ትችላላችሁ (ሞዛያ 5፥7 ይመልከቱ)። ይህም የቤተሰብ አባላት በሚጠመቁበት ወቅት የክርስቶስን ስም በላያቸው ለመውሰድ የሚያዘጋጁበት መልካም አጋጣሚ ሊሆን ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥15–20ቤተሰባችሁ ከእነዚህ ጥቅሶች ጋር የተሻለ ተሞክሮ እንዲኖረው ለማስቻል እንዲረዳ፣ ምናልባት የኢየሱስ ክርስቶስን ምስል (ከዚህ ክፍል ጋር አብሮ የመጣውን) በማሳየት ልታነቡ ትችላላችሁ። ከዚያም የቤተሰብ አባላት ስለአዳኙ የተሰማቸውን ስሜት ማካፈል ይችላሉ። ስለአዳኙ የሚያወሳ ተወዳጅ መዝሙርም መንፈስን ሊጋብዝ ይችላል።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “እኔ በመደነቅ ቆሜያለሁ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 193።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ጥያቄዎችን ጠይቁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ጥያቄዎች ወደ ራእይ እንደሚመሩ ማረጋገጫ ነው። ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠኑ የሚከሰቱባችሁን ጥያቄዎች መዝግባችሁ ያዙ። ከዚያዛም አሰላስሉ እናም መልስ ለማግኘት ጸልዩ።

ምስል
ክርስቶስ በጌተሰማኔ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ

ክርስቶስ በጌተሰማኔ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በሀርማን ክሌመንትዝ

አትም