ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
የካቲት 1–7 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10–11፥ “ድል ታደርግ ዘንድ”


“የካቲት 1–7 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10-11፥ ‘ድል ታደርግ ዘንድ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦችና ለቤተሰቦች፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“የካቲት 1–7 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10-11፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

የመፅሐፈ ሞርሞን የእጅ ጽሁፍ

የመጀመሪያው የመፅሐፈ ሞርሞን የእጅ ጽሁፍ ግልባጭ

የካቲት 1–7 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10–11

“ድል ታደርግ ዘንድ”

ቅዱሳት መጻህፍትን በምናነብበት ጊዜ የሚሰሙንን ስሜቶች መመዝገብ ልክ ዘር እንደመዝራት ነው፤ የተሰሙን ትናንሽ ስሜቶች እንኳን ትርጉም ወዳለው የግለሰብ ራዕይ ሊያመሩ ይችላሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የመፅሐፈ ሞርሞን የትርጉም ስራ እያደገ ሲሄድ የሚጠበቅ ጥያቄ ተነሳ፥ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ የጠፉትን የትርጉም ገጾች በተመለከተ ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል? ምክንያታዊ የሆነው ነገር ወደኋላ ተመልሶ ያንን ክፍል እንደገና መተርጎም ነበር፣ ነገር ግን እነሱ ያላዩትን ጌታ ተመልክቶ ነበር፤ ክፉ ሰዎች በእነዚያ ገጾች ላይ ያሉትን ቃላት በመቀየር የጆሴፍን በፈጣሪ አነሳሽነት የተከናወነ ስራ ላይ ጥርጣሬ ለመዝራት ሲያሴሩ ነበር። እግዚአብሔር የሰይጣንን ጥረት ከንቱ ለማድረግ የጠፉትንም ለማካካስ እቅድ ነበረው። ይህ እቅድ ተግባራዊ የሆነው ከሺህ አመታት በፊት ኔፊ በተመሳሳይ ወቅት የተከናወነውን ታሪክ ሁለተኛ ቅጂ ማዘጋጀት እንዳለበት በተሰማው ወቅት ነው። በኋላም ሞርሞን እነዚህን ጽሁፎች በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ በጌታ ብቻ ለሚታወቀው “ለብልህ ዓላማ” እንዲያካትታቸው ተነሳሳ (የሞርሞን ቃላት 1፥3–7 ይመልከቱ)።

“ጥበቤ፣” አለ ጌታ ለጆሴፍ “ከአጋንንት ብልጠት የላቀ” ነው (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 10፥43)። ያም በተለይ በእኛ ጊዜ ጠላት እምነትን ለማዳከም የሚያደርገው ጥረት በተጠናከረበት ወቅት ይህንን መልዕክት መስማት ጥሩ ማረጋጊያ ይሆናል። ልክ እንደ ጆሴፍ እኛም እግዚአብሔር እንድንሰራው በጠራን ስራ “ታማኝ ሆነን ለመጨረስ” እንችላለን (ቁጥር 3)። ከዛም በእኛ ላይ “የሲዖል ደጆችም አይቋቋሙ” ዘንድ መንገድን እንዳዘጋጀ እንገነዘባለን (ቁጥር 69)።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥51–61ን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥1–33

ሰይጣን የእግዚአብሔርን ስራ ለማጥፋት ይሻል።

ሰይጣን መኖሩንም እንድንረሳ ይፈልጋል—ወይንም ትጽዕኖ ሊያሳድርብን እየጣረ እንደሆነ እንዳንገነዘብ ይፈልጋል (2 ኔፊ 28፥22–23 ይመልከቱ)። ነገር ግን በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10 ውስጥ ባሉት የጌታ ቃላት እንደተገለጹት፣ ሰይጣን በተደጋጋሚ ንቁ ሆኖ የእግዚአብሔርን ስራ በመቃወም ላይ ነው። እናንተ ቁጥሮች 1–33ን ስታነቡ፣ ሰይጣን በጆሴፍ ስሚዝ ጊዜ እንዴት አድርጎ የእግዚአብሔርን ስራ ለማጥፋት እንደጣረ ተመልከቱ (በተጨማሪም ቁጥሮች 62–63 ይመልከቱ)። ሰይጣን ዛሬም እየሰራ ካለበት መንገድ ጋር ምን ተመሳሳይነትን ትገነዘባላችሁ? ሰይጣን በምን አይነት መንገድ እየፈተናችሁ እንደሆነ ለማየት ጌታ እንዲረዳችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ። በክፍል 10 ውስጥ የሰይጣንን ጥረት የምትቋቋሙበትን ምን አይነት እርዳታ ታገኛላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥34–52

የጌታ “ጥበብ ከአጋንንት ብልጠት የላቀ” ነው።

ከ2,400 አመታት በላይ በፊት ጌታ ለጠፉት የመፅሐፈ ሞርሞን ገጾች ማካካሻ አዘጋጅቶ ነበር (1 ኔፊ 9ን ይመልከቱ)። ስለጌታ ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች10፥34–52 ውስጥ ምን ትማራላችሁ? ስለጌታ ጥበብና ቅድመ አዋቂነት በህይወታችሁ ውስጥ ምን አይነት ማረጋገጫዎችን አይታችኋል?

እግዚአብሔር የጠፉትን ጽሁፎች ለመተካት ያዘጋጃቸው ጽሁፎች በ1ኛ ኔፊ እስከ ኦምኒ ውስጥ ይገኛሉ። እነዚህ ታሪኮች እና በእነዚህ ጽሁፎች ውስጥ ያሉ ትምህርቶች ለእናንተ እንዴት “በወንጌሌ ላይ ታላቅ መረዳትን” ሰጥተዋችኋል? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥45)።

ሞርሞን የወርቅ ሰሌዳዎችን አሳጥሮ ሲፅፍ

ሞርሞን ሰሌዳዎቹን አሳጥሮ ሲጽፍ በቶም ሎቬል

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11

እግዚአብሔርን ብጠይቅ አቀበላለሁ።

ብዙዎቹ የጆሴፍ ስሚዝ የቤተሰብ አባላትና ጓደኞች ስለእነርሱ የጌታ ፍቃድ ምን እንደሆነ እንዲጠይቅላቸው ጠይቀውታል። ጆሴፍ ያንን ለማድረግ ደስተኛ ነበር፣ ነገር ግን ጌታም የግላቸውን ራዕይ ለመስጠት ፈቃደኛ ነበር። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11 ጆሴፍ ለወንድሙ ሃይረም በተቀበለው ራእይ ውስጥ ጌታ እንዲህ ይላል “ከመንፈሴ … እሰጥሃለሁ፤ እናም ከዚያም … ከእኔም የምትሻቸውን ማንኛውንም ነገሮች ሁሉ … ታውቃለህ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥13–14)።

ጌታ ሲናገር ቃሉ “መልካም ፈቃድ ላላቸው፣ እናም በማጭዳቸው ለመሰብሰብ ለሚያጭዱ ሁሉ” ነው ብሏል (ቁጥር 27)። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11 ውስጥ ጌታ ስለግል ራእይ ምን ሊነግራችሁ እየሞከረ ነው? በእርሱ ስራ ላይ ስለመሳተፍስ? ለእናንተ ሌላ ምን መልዕክቶች አለው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥15–26

እኔ “[የእግዚአብሔርን ቃል] ለማግኘት” ስሻ፣ የእርሱን መንፈስና ሃይል እቀበላለሁ።

መፅሐፈ ሞርሞን ከመተርጎሙ በፊት አስቀድሞ እንኳን ሃይረም ስሚዝ ወንጌልን ለመስበክ ጉጉት ነበረው። ስለፍላጎቱ በሚመለከት የጌታን ምላሽ ስታነቡ ለእናንተ “ [የእግዚአብሔርን ቃል] ማግኘት” ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስቡበት (ቁጥር 21)። የእግዚአብሔርን ቃል መቀበል እንዴት አድርጎ በቤተክርስቲያን አገልግሎታችሁ ላይ ሊረዳችሁ ይችላል? የእግዚአብሔርን ሃይል ወደ ህይወታችሁ እንዴት አድርጎ ሊያመጣ ይችላል?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥5ስለጸሎት ሃይል ከእነዚህ ጥቅሶች ምን እንማራለን? እንዴት አድርገን ነው “ሁልጊዜም የምንጸልየው”? (ለአንዳንድ ሃሳቦች፣ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “ሁል ጊዜ ጸልዩ፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 41–44 ይመልከቱ።)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥38–46የቤተሰባችሁ አባላት ለጠፉት የመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉሞች እንዴት ጌታ ማካካሻ እንዳደረገ ለመወያየት፣ ምናልባት በቅርብ ጊዜ ስለጠፋባቸው ነገር እንዲያወሩ ማድረግ ትችላላችሁ። መጥፋቱን ሲገነዘቡ ምን ተሰማቸው? በተገኘ ጊዜ ምን ተሰማቸው? ምንም እንኳን የጠፉት የመፅሐፈ ሞርሞን ገጾች ባይገኙም፣ እንደ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥38–46 አገላለጽ ጌታ እንዴት አድርጎ ነው ያካካሰው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥55–70የቤተሰብ አባላት “እኔ … ነኝ” እና “እኔ አደርጋለሁ” የሚሉ ሃረጋትን ሲያገኙ እንዲያቀልሟቸው ጋብዟቸው። “እኔ … ነኝ” ከሚለው ሃረግ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ማንነትና ምን አይነት እንደሆነ ምን እንማራለን? “እኔ አደርጋለሁ” ከሚለው ሃረግ ስለሚያደርገው ነገር ምን እንማራለን? የቤተሰቡን አባላት እነዚህ እውነታዎች እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንደሚያጠነክርላቸው እንዲያካፍሉ አበረታቷቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥12–14እነዚህን ጥቅሶች ማንበብ የቤተሰባችሁን አባላት መንፈስ ሲያነጋግራቸው መገንዘብ የሚችሉበትን መንገድ እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል። የእጅ ባትሪን በመሬት ላይ በማብራት አንዱን የቤተሰብ አባል ወደሚበራው ስፍራ እንዲቀርብ መጠየቅ ትችላላችሁ። ይህ በምን አይነት መልኩ ነው የመንፈስ ቅዱስን ምሪት እንደመከተል ሊሆን የሚችለው? የትኛውን የግል ተሞክሯችሁን ማካፈል ትችላላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥15–30ጌታ ለሃይረም ስሚዝ ወንጌልን ለማካፈል ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ አለበት ብሎ የነገረውን ለመዘርዘር አስቡበት። እንደ ቤተሰብ ምን ለመስራት ይገባናል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “መርምሩ፣ አሰላስሉ፣ እናም ጸልዩየልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 109፤ “[Ideas to Improve Your Family Scripture Study] የቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትን ለማሻሻል የሚረዱ ሃሳቦችን ይመልከቱ።”

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ቅዱሳት መጻህፍትን ከሕይወታችሁ ጋር አመሳስሉ. የቅዱሳት መጻህፍትን ክፍል ካነበባችሁ በኋላ፣ የቤተሰብ አባላት መልዕክቱ በህይወታቸው እንዴት ሊሰራ እንደሚችል እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው። ለምሳሌ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥12–13 ውስጥ እንደተገለጸው መንፈስ እንዴት ተጽዕኖ እንዳሳደረባቸው ማካፈል ይችላሉ።

ጆሴፍ እና ሃይረም ስሚዝ

ጆሴፍ እና ሃይረም ስሚዝ በኬን ኮርቤት