“የካቲት 8–14 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 12–13፤ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥66–75፥ ‘አገልጋይ ባልንጀሮቼ … ለእናንተ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“የካቲት 8–14 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 12–13፤ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥66–75፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)
የካቲት 8–14 (እ.አ.አ)
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች12–13፤ ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥66–75
“አገልጋይ ባልንጀሮቼ … ለእናንተ”
ጆሴፍ ስሚዝና ኦሊቨር ካውድሪ ከቅዱሳት መጻህፍት ስለተማሩት እውነቶች ሲጸልዩ ተጨማሪ እውቀትን ተቀበሉ (ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥68ን ይመልከቱ)። ምሳሌያቸውን እንዴት ለመከተል ትችላላችሁ?
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
በዓለም ዙሪያ ያሉ አብዛኞቹ ሰዎች ሃርመኒ፣ ፔንሲልቫንያ ስለሚባል ቦታ ሰምተው አያውቁም ይሆናል። ነገር ግን ጌታ በአብዛኛው በመንግሥቱ ውስጥ ለሚፈጸሙ ጉልህ ክስተቶች በብዙዎች ዘንድ የማይታወቁ ስፍራዎችን ይመርጣል። በግንቦት 15፣ 1829 (እ.አ.አ) በሃርመኒ አቅራቢያ ባለ ደን ስፍራ ላይ መጥምቁ ዮሃንስ ከሞት ትንሳኤን እንዳገኘ ሰው ለጆሴፍ ስሚዝና ለኦሊቨር ካውድሪ ተገለጠላቸው። እጁን ባናታቸው ላይ በመጫን “አገልጋይ ባልንጀሮቼ” ብሎ ከጠራቸው በኋላ የአሮናዊ ክህነት ስልጣንን አሸከማቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥1)።
ኢየሱስ ክርስቶስን ባጠመቀውና መንገዱን በጠረገለት በመጥምቁ ዮሃንስ (ማቲዎስ 3፥1–6, 13–17ን ይመልከቱ) እንደ አጋልጋይ ባልንጀራ መቆጠር በትህትና ዝቅ የሚያደርግና ምናልባትም ለእነዚህ ገና በሃያዎቹ የእድሜ ክልል ላሉ ሁለት ወጣቶች ካቅማቸው በላይ ሳይሆን አይቀርም። በወቅቱ ልክ እንደ ሃርመኒ ጆሴፍ እና ኦሊቨርም በተነጻጻሪው ማንም አያውቃቸውም ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር ስራ ውስጥ ማገልገል ሁሌም ቢሆን እንዴት እንደምናገለግል እንጂ ማን እንደሚያስተውለን አይደለም። ምንም እንኳን አስተዋጿችሁ አንዳንድ ጊዜ ትንሽ ወይንም የማይታይ ቢመስልም፣ እናንተም በታላቁ የጌታ ስራ አገልጋይ ባልደረባ ናችሁ።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ጌታ የፅዮንን መመስረት እንዳግዝ ይሻል።
ጆሴፍ ናይት ቀዳማዊና ባለቤቱ ፖሊ ጆሴፍ ስሚዝን የተዋወቁት የ20 አመት ልጅ ሳለ በኮልስቪል፣ ኒው ዮርክ ባለው እርሻቸው ላይ ሲሰራ ነው። ጆሴፍ ናይትም እርሱን ከነበሩት ሰራተኞች ሁሉ ምርጡ ነው በማለት ገልጿል። ስለወርቅ ሰሌዳዎች የጆሴፍ ስሚዝን ምስክርነት አመነ እናም ጆሴፍ ስሚዝ በሃርመኒ፣ ፔንስሊቫኒያ ውስጥ መፅሐፈ ሞርሞንን እየተረጎመ ሳለ ለመጎብኘት ሚስቱን ፖሊን ይዞ ሄደ። እርሷም ወዲያውኑ አመነች። በተቀረው ዘመናቸው ሁሉ ጆሴፍ እና ፖሊ በዳግም ለተመለሰው ወንጌል ታማኝ ሆነው ቀጠሉ። ከ60 በላይ የሚሆኑ የናይት ቤተሰቦች አባላት ሆነው ቤተክርስቲያኗንም በኒው ዮርክ፣ በኦሃዮ፣ በሚዙሪ፣ በናቩ፣ እናም በስተመጨረሻም በሶልት ሌክ ሲቲ ላይ በመመስረት ረዱ።
ጆሴፍ ናይት በጌታ ስራ ላይ እንዴት ማገዝ እንዳለበት ለማወቅ ፈለገ። የጌታ መልስ (አሁን ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 12) አናንተንም ጨምሮ “ይህንን ስራ ለመፈጸምና ለመመስረት ለሚሹ ሁሉ” የሚሆን ነው (ቁጥር 7)። “የፅዮንን እንቅስቃሴ ለመፈጸም እና ለመመስረት” ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው? (ቁጥር 6)። በቁጥሮች 7–9 ውስጥ ያሉት መርሆዎችና ባህሪዎች ይህንን እንድታደርጉ እንዴት ይረዷችኋል?
በተጨማሪም “The Knight and Whitmer Families [የናይት እና ዊትመር ቤተሰቦች]፣” ራዕያት በአገባብ፣ 20–24 ይመልከቱ።
የአሮናዊ ክህነት መጥምቁ ዮሐንስ ነበር የተመለሰው።
በአንድ አረፍተ ነገር መጥምቁ ዮሐንስ ስለአሮናዊ ክህነት ብዙ እውነታዎችን ገለጸል። ከዚህ ክፍል የተማራችሁትን ነገር ሁሉ ለመዘርዘር አስቡ (የክፍል መግቢያውንም በመጨመር)። የምታገኟቸውን አንዳንድ ሃረጎችን ማጥናት ጠቃሚ ሆኖ ልታገኙት ትችላላችሁ። ለማስጀመሪያ ያህል የሚሆኑ ጥቂት ሃሳቦች እነሆ፥
-
“የመላእክት … አገልግሎት ቁልፎች”፥ 2 ኔፊ 32፥2–3፤ ሞሮኒ 7፥29–32፤ ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “የመላእክት አገልግሎት፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 29–31፤ የቅዱሳት መጻህፍ መመሪያ፣ “መላእክት፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org
-
“የንስሃ ወንጌል … ቁልፎች”፥ 3 ኔፊ 27፥16–22፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥26–27፤ ዴል ጂ. ረንላንድ “ክህነት እና የአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ሀይል፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 64–67
-
“የሌዊ ወንድ ልጆች”፥ ዘኁልቁ 3፥5–13፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥31–34፤ የቅዱሳት መጻህፍ መመሪያ “አሮናዊ ከህነት፣” “ሌዊ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org
በአሮናዊ የክህነት ስርዓቶች ምን በረከቶችን ተቀብላችኋል?
ስርአቶች የእግዚአብሔርን ሃይል እንዳገኝ መንገድ ይሰጡኛል።
በቀድሞ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ አመራር ውስጥ አማካሪ የነበሩት እህት ካሮል ኤም. ስቲቨንስ እንዲህ እንዳስተማሩት፥ “የክህነት ስርአቶች እና ቃል ኪዳኖች በአዳኝ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት እውን የሆኑትን ከእግዚአብሔር ቃል የተገቡልንን ሙሉ በረከቶች እንድናገኝ መንገድ ይሰጡናል። የእግዚአብሔርን ወንድ እና ሴት ልጆች በሃይል፣ በእግዚአብሔር ሃይል፣ ያሳጥቃሉ እናም ዘለአለማዊ ህይወትን ለመውረስም እድልን ያመቻቻሉ” (“ምን እንዳለን እናውቃለንን?” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 12)።
የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥66–75 እና በተጨማሪም በቁጥር 71 መጨረሻ አካባቢ ያለውን ማስታወሻ ስታነቡ፣ ጆሴፍና ኦሊቨር ስለጥምቀት ለመጠየቅ ምን እንዳነሳሳቸው ልብ በሉ፣ እናም በክህነት ስርአቶች በመሳተፍ ወደ እነርሱ የመጡትን በረከቶች አስተውሉ። ስርአቶችን ስትቀበሉ የጻፋችሁት የግል ማህደር ካላችሁ ማንበብ ወይም ስለሂደቱ የነበራችሁን ትውስታ መመዝገብን አስቡበት። በክህነት ስልጣን ስርዓቶች በኩል ምን በረከቶችን ተቀብላችኋል?
በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥20–22፤ ቅዱሳን፣ 1፥65–68ን ይመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 12፥8።የጌታን ስራ ስንሰራ በእነዚህ ጥቅሶች ላይ የተዘረዘሩት መገለጫዎች ለምን አስፈላጊዎች ናቸው?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13።ቤተሰባችሁ ስለአሮናዊ የክህነት ስልጣን በዳግም መመለስ ያላቸውን እምነት ምን ሊገነባው ይችላል? “Restoration of the Aaronic Priesthood [የአሮናዊ ክህነት በዳግም መመለስ]” የሚለው ቪድዮ (ChurchofJesusChrist.org) ወይም ይህንን ትምህርት የሚደግፈው የጥበብ ስራ ቤተሰቦቻችሁን ስለ አሮናዊ ክህነት በዳግም መመለስ በአእምሮአችሁ እንድትስሉ ይረዷችኋል። ከጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥68–74 ውስጥ በሚያነቡት በመነሳት ስለሁኔታው ሰዕል ለመሳል የሚፈልጉ ይመስላችኋል? በህይወታቸው ውስጥ ክህነት ስላለው ሃይልም ምስክርነታቸውን ማካፈል ይችላሉ።
በተጨማሪም “Priesthood Restoration Site [ክህነት በዳግም የተመለሰበት ስፍራ]” የሚለውን በhistory.ChurchofJesusChrist.org ላይ ይመልከቱ።
-
ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥68።ለጥያቄያችን መልስ ለማግኘት የጆሴፍ ስሚዝን እና የኦሊቨር ካውድሪን ምሳሌ እንዴት መከተል እንችላለን? ምናልባትም በጋራ ስታነቡ፣ በንባብ መሃል በማቋረጥ ስለሚነበበው ጥያቄ እንዳለ መጠየቅን እንደ ባህል ልታደርጉት ትችላላችሁ።
-
የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥71፣ ማስታወሻ።ከኦሊቨር ካውድሪ ቃላት የቤተሰብ አባሎቻችሁን ያስደነቀው ምንድን ነው? የቤተሰባችሁ “መቼም የማይረሱ ቀናት” የትኞቹ ናቸው?
-
የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥73–74።በጆሴፍ እና ኦሊቨር ላይ መንፈስ ቅዱስ ምን አይነት ተጽዕኖ ነበረው? መንፈሱ በቤተሰባችሁ ቅዱሳት መጻህፍትን እንድትረዱና በጌታ እንድትደሰቱ ያደረጋችሁ መቼ ነበር?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ “ክህነት በዳግም ተመልሷል፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 89።