ክህነት እና የአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ኃይል
የሰማይ አባት አላማ እንዲሳካ፣ የክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ኃይል ለእግዚአብሔር ልጆች መሰጠት አለበት። ክህነት እነዚህን እድሎች ያቀርባል።
አንድን መንኮራኩር ወደ መወንጨፊያው ቦታ ለመተኮስ እየታገዘ እንዳለ ከእኔ ጋር አብራቹ ሳሉ። አሁን መለኮሻውን በምናባችሁ ሳሉ። በቁጥጥር ስር ያለው ነዳጅ መንኮራኩሩን ወደ ህዋ እንዲመነጠቅ አስፈላጊ የሆነውን የማንሳፈፍ ጉልበት እየሰጠው ወደ ሞቀ አየር ይቀየራል። በመጨረሻም፣ በመንኮራኩሩ አናት ላይ የሚቀመጠውን ጭነት አስቡት። የጭነቱ ሙሉ ዋጋ የሚደርሰው መገኘት በሚገባበት ሲደርስ እና መስራት በሚገባበት ሲሰራ ብቻ ነው። ብዙ ገንዘብ የሚያስከፍለው የአለም አቀፍ ማስተላለፊያ ሳተላይት በማከማቻ ቦታ ውስጥ ሲቀመጥ ትንሽ ዋጋ ያለው እንደሆነ ለማወቅ የመንኮራከሩ ሳይንቲስት መሆን አያስፈልጋችሁም። የመንኮራኩሩ ተልዕኮ ጭነትን ማድረስ ብቻ ነው።
በዚህ ምሽት፣ የተሸከምነውን ክህነት ከመንኮራኩር እንዲሁም የአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ኃይል ያለውን የመጠቀም እድል መንኮራኩር ከሚያደርሰው ጭነት ጋር ላወዳድር እፈልጋለሁ።
በኃጢያት ክፍያ መሰዋትነቱ ምክንያት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር በሙሉ የማዳን ኃይልና ስልጣን አለው። የኃጢያት ክፍያውን ኃይል ግልጋሎት ለማግኘት በምድር ላይ ላሉ ሰዎች የኃይሉን የተወሰነ ክፍል እና ስልጣን ወክሎ ሰጥቷል። ይህ የተወከለው ኃይልና ስልጣን ክህነት ተብሎ ይጠራል። የክህነት ተሸካሚዎችን በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ስራ ውስጥ የእግዚአብሔርን ልጆች ደህንነት ለማምጣት እንዲያግዙ ያስችላል። ይህን የሚያደርገው ለእርሱ ልጆች የአዳኙን የኃጢያት ክፍያ በረከቶች የመቀበል እድልን ስለሚሰጥ ነው።
የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ኃይል አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ማንኛችንም ወደ ሰማይ አባታችን መኖሪያ ካለእርዳታ መመለስ ስለማንችል ነው። ሟች በሆነው ሕይውት ውስጥ፣ ስህተቶችን እንፈፅማለን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ህጎች እንጥሳለን። በኃጢያተኞች እንሆናለን እናም በእግዚአብሔር መገኛ ተመልሰን እንድንገባ አይፈቀድልንም። ከሰማይ አባታችን ጋር ለመታረቅ የአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ኃይል ያስፈልገናል። ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤን ለሁሉም እውን በማድረግ የአካላዊ ሞትን ቀንበር በጣጠሰው። በወንጌሉ ህግጋቶችና ሥነ-ስርዓቶች ላይ ታዛዥ በመሆን ለኃጢያት ይቅርታን ይሰጣል። በእርሱ አማካኝነት መዳን ተሰጥቷል። ከአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ኃይል የመጠቀም እድል የተፈጥሮ አስፈላጊ ጭነት ነው።
የሰማይ አባት አላማ እንዲሳካ፣ የክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ኃይል ለእግዚአብሔር ልጆች መሰጠት አለበት።1 ክህነት እነዚህን እድሎች ያቀርባል። መንኮራኩሩ ነው። ክህነት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በምድር ላይ ያሉ አስፈላጊ ሥነ-ስርዓቶች እና ቃል-ኪዳኖቸ ለሰዎች ግልጋሎት ላይ የሚቀርቡት በራሱ ስልጣን ብቻ ነውና። ክህነቱ ከአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ኃይል የመጠቀም እድልን መስጠንት ካልቻለ፣ አላማው ምን ይሆናል? ይህስ ትኩረትን የሚስብ ርችት ይሆናልን? እግዚአብሔር ክህነትን ከሰንበት ትምህርት ውስጥ ወይም አገልግሎት ከመስጠት እድል ባለፈ እንድንጠቀምበት ይፈልጋል። ጭነቱን ተሸክሞ እንዲያደርስ ይፈልጋል።
በመንኮራኩሮች ውስጥ ትንሽዬዋ ስህተት የተልዕኮን መበላሸት ያስከስታል። ተሰባሪ ግጣሞችና የመሳሪያዎች መበላት መንኮራኩሩን ከጥቅም ውጪ ያደርጉታል። ክህነትን ከተሰባሪ ግጣሞችና የመሳሪያ መበላት ምሳላዊ አነጋገር ለመጠበቅ፣ እግዚአብሔር ሹመቱን እና ጥቅሙን ይጠብቃል።2 የክህነት ሹመት ለሰው ልጅ የተሰጠ የአመራር መብቶች በሆነው በክህነት ቁልፎች ይጠበቃል።3 የክህነት ጥቅም እንደዚህም የክህነት ተሸካሚው በሚገባው ቃል-ኪዳኖች ይጠበቃል። በዚም ምክንያት የክህነት ጥቅም ኡ=የሚመራው በቁልፍ እና በቃል ኪዳንኖች ነው። የሰው የክህነት ሀላፊነት የሚሰጠው በግል ነው እናም ከእርሱ ተለይቶ አይገኝም።4 ክህነት ቅርጸ ቢስ የሆነ ራስን የሚገዛ ሀይል አይደለም።
ሁለቱም የአሮናዊና የመልከፀዴቅ ክህቶች በቃል-ኪዳን ነው የሚቀበሉት።5 እግዚአብሔር መርሆዎቹን ይወስናል ሰው ድግሞ ይቀበላል። በስፋት ለመናገር፣ የክህነት ተሸካሚዎች እግዚአብሔርን በስራው ለማገዝ ቃል-ኪዳን ይገባሉ። ከዚህ ዘመን ቀደም ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስ የክህነት ቃል-ኪዳን “በላያችሁ ላይ ለራሳችሁ ጥቅም እንደሚሰጥ፣ ለእናንተ ጥቅም ብቻም ሳይሆን ለመላው ዓለም ጥቅም እንደሚሰጥ … ምክንያቱም ወደ እኔ ስለማይመጡ” ብሎ አስረዳ።6
ይህ የሚያስተምረው የክህነት አላማ ሌሎች ሰዎችን የተመለሰውን ወንጌል እንዲቀበሉ በመርዳት ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጋበዝ ነው። ክህነት ያለን የሰማይ አባት ልጆችን ከኃጢያት ቀንበር እንዲላቀቁ እና እንደርሱ እንዲሆኑ ለመርዳት እንድንችል ነው። በክህነት አማካኝነት፣ የመለኮታዊ ኃይል የወንጌል ቃል-ኪዳኖችን በሚገቡና በሚጠብቁ እንዲሁም የተያያዘውን ሥነ-ስርዓቶች በሚቀበሉ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ይገለፃል።7 እያንዳንዳችን ወደ ክርስቶስ የምንመጣበት፣ የምንነጻበት፣ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር የምንታረቅበት መንገድ ይህ ነው። የክርስቶስ የኃጥያት ክፍያ ኃይል፣ ጭነቱን በሚያደርሰው በክህነት አማካኝነት ለሁሉም ይቀርባል።
ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባው ቃል-ኪዳኖች እውነተኛ እና ቅዱስ ናቸው። አንድ ሰው ለእሱ ዝግጁ መሆን፣ መማር፣ እንዲሁም እንደዚህ አይነቱን ቃል-ኪዳኖች ለማክበር በማሰብ መግባት አለበት። ቃል-ኪዳን ለራስ የተገባ መሃላ ይሆልና። የእንግሊዙ ፀሐፊ ሮበርት ቦልት ያለውን በሌላ አገላለፅ ለመናገር፣ አንድ ሰው ቃል-ኪዳን የሚገባው እራሱን ለቃል-ኪዳኑ በተለየ ሁኔታ ተገዝቶ እራሱን ለመስጠት ሲፈልግ ብቻ ነው። በቃል-ኪዳኑ እውነታ እና በራሱ ፅድቅ መካከል ማንነትን ይፈጥራል። አንድ ሰው ቃል-ኪዳን ሲገባ እራሱን በጎደጎደ እጅ ውስጥ እንዳለ ውኃ ይቆጥራል። ጣቶቹን ከከፈተ፣ እራሱን መልሶ ለማግኘት ተስፋ ማድረግ አይገባውም። ቃል-ኪዳን ሰባሪ እራሱን የሚሰጥበት ወይም ዋስትና የመስጠት እድሉ መልሶ አይኖርም።8
የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚ መጥፎ ነገሮችን ለማስወገድ፣ ሌሎችን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ ለመርዳት እና የመልከፀዴቅ ክህነትን ለመቀበል እንዲዘጋጁ ለመርዳት ቃል-ኪዳን ይገባል።9 በሚያስተምርበት ጊዜ፣ በሚያጠምቅበት ጊዜ፣ የቤተክርስቲያን አባሎችን በሚያጠነክርበት ጊዜ እና ሌሎችን ወንጌልን እንዲቀበሉ በሚጋብዝበት ጊዜ እነዚህ የተቀደሱ ኃፊነቶች ይሟላሉ። እነዚህ የእሱ “መንኮራኩር” ስራዎች ናቸው። በተዘዋዋሪም፣ እግዚአብሔር የተስፋን፣ የይቅር ባይነትን፣ የመላዕክት ግልጋሎትን እና የንስሃና የጥምቀት ወንጌል ቁልፎችን ቃል ይገባል።10
የመልከፀዴቅ ክህነት ተሸካሚ ከአሮናዊ ክህነት ጋር የሚያያዙ ኃላፊነቶችን ለማሟላት እና በመለክፀዴቅ ክህነት ውስጥ ጥሪውን ለማጉላት ቃል-ኪዳን ይገባል።11 ይህን የሚያደርገው ከቃል-ኪዳኑ ጋር በተያያዘ ትዕዛዛትን በመጠበቅ ነው። እነዚህ ትእዛዛቶች “ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጡትን እያንዳንዱን ቃሎች” መኖርን “ለዘላለማዊ ሕይወት ቃሎች ጥብቅ የሆነ መስማት”12 መስጠትን፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስና የሱን የኋላኛው ቀን ስራ መመስከርን፣13 በራሱ አለመኩራትንና የአዳኙ ጓደኛ መሆንን፣14 እናም ጓደኛ እንደሚያምነው ማመንን ያካትታሉ።15
በምላሹ፣ እግዚአብሔር የመልከፀዴቅ ክህነት ተሸካሚው የእግዚአብሔርን ሚስጥር የሚረዳበትን ቁልፎች እንደሚቀበል ቃል ይገባል። በእግዚአብሔር መገኛ መቆም ይችል ዘንድ ፍፁም ይሆናል። በደህንነት ስራ ውስጥ ኃፊነቱን ለመወጣት ብቁ ይሆናል። ኢየሱስ ክርስቶስ ከክህነት ተሸካሚው ፊት በመሄድ መንገዱን ያዘጋጃል እንዲሁም አብሮት ይሆናል። መንፈስ ቅዱስ በክህነት ተሸካሚው ልብ ውስጥ ይሆናል እንዲሁም መላዕክት ያግዙታል። ሰውነቱ ይጠነክራል እንዲሁም ይታደሳል። ለአብርሃም በረከቶች ከባለቤቱ ጋር ወራሽ ይሆናል እንዲሁም ለሰማይ አባት መንግስት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ጣምራ ወራሽ ይሆናል።16 እነዚህ “እጅግ ታላቅ እና ድንቅ በረከቶች” ናቸው።17 ከእነዚህ የበለጡ ቃል-ኪዳኖች አይታሰቡም።
መልከፀዴቅ ክህነትን ለሚቀበል ለእያንዳንዱ ሰው፣ እግዚአብሔር የቃል-ኪዳኑን በረከቶች በመሃላ ያረጋግጣል።18 ይህ መሃላ ለመልከፀዴቅ ብቻ ነው የሚመለከተው19 እናም የክህነት ተሸካሚው ሳይሆን እግዚአብሔር ነው መሃላውን የሚምለው።20 ምክንያቱም፣ ይህ የተለየ ሁኔታ የእርሱን መለኮታዊ ኃይልና ስልጣንን ያካትታል። የበረከቶቹን መምጣትና አለመታጠፍ ለማረጋገጥ እግዚአብሔር በሚችለው ሁኔታ በጣም ኃያል የሆነውን ቋንቋ በመጠቀም መሃላን ይገባል።
አስከፊ የሆኑ ውጤቶች የክህነት ቃል-ኪዳንን በመስበር እንዲሁም ከእነሱ በመዞር ይመጣሉ።21 በክህነት ጥሪ ውስጥ መዝናናት ወይም ፍላጎት ያለማሳየት ልክ በመንኮራኩር ክፍሎች ውስጥ የመሳሪያ መበላትን ማስተዋወቅ እንደማለት ነው። የክህነት ቃል-ኪዳኑን አደጋ ላይ ይጥላል ምክንያቱም ወደ ተልዕኮ አለመሳካት ሊመራ ይችላል። ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት አለመታዘዝ ቃል-ኪዳኑን ይሰብረዋል። ለተደጋጋሚም ሆነ ለጊዜአዊ ቃል-ኪዳን ሰባሪ ቃል የተገቡት በረከቶች ይወሰዳሉ።
በክህነት መንኮራኩር እና በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ኃይል በመጠቀም እድል መካከል ያለውን የጭነት ግንኙነት ከብዙ አመት በፊት በበለጠ ሁኔታ በሙሉ ለመረዳት ችያለው። በአንድ የሳምንት መጨረሻ ላይ ሁለት የቤት ስራዎች ተሰጥተዉኝ ነበር። አንደኛው በአንድ ሃገር ውስጥ ካስማን መፍጠር ነበር፣ ሌላኛው ደግሞ አንድ ወጣት ልጅን ቃለ መጠይቅ ማድረግ እንዲሁም ሁሉም ነገር መስመሩን ከያዘ ክህነቱን እና የቤተ-መቅደስ በረከቶቹን መልሶ መስጠት ነበር። ይህ የ30 ዓመት ወጣት ቤተክርስቲያኗ ልጅነቱ በማብቂያው ጊዜ ነበር የተቀላቀለው። የተከበረ ሚስዮን አገልግሎት ሰጠ። ነገር ግን፣ ወደ ቤት ሲመለስ መንገዱን ሳተ እና በቤተክርስቲያው ውስጥ አባልነቱን አጣ። ከተወሰኑ አመታት በኋላ፣ “ወደራሱ ተመለሰ፣”22 እና በወዳጅ የክህነት ተሸካሚ መሪዎች እና በደግ አባሎች እርዳታ ንስሃ ገባ እናም በጥምቀት ቤተክርስቲያኑን መልሶ ተቀላቀለ።
ከዛ፣ የክህነት እና የቤተመቅደስ በረከቶቹ እንዲመለሱለት አመለከተ። በመሰብሰቢያ ቦታ ለቅዳሜ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዝን። ከእርሱ በፊት ለነበረው ቀጠሮ ቀድሜ ስመጣ እሱ እዛ ነበር። ክህነትን መልሶ ለማግኘት መጠበቅ አቅቶት በጣም ጓግቶ ነበር።
በቃለ መጠይቁ ወቅት፣ ደብዳቤውን በማሳየት ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን ማመልከቻውን እንዳነበቡት እና ቃለ መጠይቁን እንደፈቀዱ ገለፅኩለት። ይህ ቻይ ወጣት እንባውን አነባ። ከዛ የቃለ መጠይቃችን ቀን በሕይወቱ ውስጥ ምንም ዓይነት ትርጉም እንደማይኖረው ነገርኩት። ተገረመ። በረከቶቹን ከመለስኩለት በኋላ የአባልነት መዝገቡ፣ የቀድሞ ጥምቀቱን፣ ማረጋገጫውን፣ የክህነት ሹመቱን፣ እና ቡራኬ የተቀበለበትን ቀናት እንደሚያሳይ ነገርኩት። እንደገና ትን አለው።
ከትምህርት እና ቃኪዳኖች እንዲያነብ ጠየኩት፤
“እንሆ እርሱ ለሀጢያቶቹ ንሰሀ የገባ ይቅር ተብሏል እና እኔ ጌታ ዳግም አላስታውሳቸውም።
“በዚህ ሰው ንሰሀ መግባቱን ታውቃላችሁ እነሆ ይናዘዛቸዋል እናም ይተውታልም።”23
ለሶስተኛ ጊዜ እንባ አይኖቹን ሞሉት። ከዚያም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ በመልከፀዴቅ ክህነት እና በቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንት ፈቃድ እጆቼን በራሱ ላይ በመጫን የክህነት እና የቤተ-መቅደስ በረከቶቹን መለስኩለት።
በላያችን ላይ የመጣው ደስታ እጅግ ትልቅ ነበር። የእግዚአብሔርን ክህነት መልሶ እንዲሸከምና እዲለማመድ ስልጣን እንደተሰጠው አወቀ። የቤተ-መቅደስ በረከቶቹ ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ እንደዋሉ አወቀ። በአረማመዱ መተማመን ታየበት እንዲሁም ብርሃናማ ሆነ። በእሱ ኮራሁበት እንዲሁም የሰማይ አባትም በእሱ እንደኮራ ተሰማኝ።
ከዛ በኋላ፣ ካስማው ተቋቋመ። ስብሰባው ከልብ በተሞሉ፣ አማኝ ቅዱሳኖች በሆኑ ሰዎች ታደመ እንዲሁም መልካም የካስማ ፕሬዘደንት አመራሮች ተሸሙ። ይሁን እንጂ፣ ለእኔ፣ ታሪካዊ ከሆነው ሀገሩ ውስጥ ይህን የመጀመሪያ ካስማ ማቋቋም ክስተት ይህንን ወጣት በረከቱን መልሼ በመስጠቴ ባገኘሁት ደስታ ተውጦ ነበር።
ካስማን የማቋቋም አላማ ወይም የእግዚአብሔርን ክህነት በማንኛውም መንገድ መጠቀም የሰማይ አባትንና ኢየሱስ ክርስቶስን ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔርን ልጆች የመዳንና የመፈወስ እድል በመስጠት በስራቸው ውስጥ ማገዝ እንደሆነ መገንዘብ ችያለሁ። ልከ እንደ መንኮራኩሩ አላማው ጭነትን ማድረስ እንደሆነው ሁሉ፣ ክህነት የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ያደርሳል፣ ሁሉንም ቃል-ኪዳኖች እንዲገቡና ተጓዳኝ የሆኑትን በረከቶች እንዲቀበሉ ያስችላል። “የክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ”24 ደም የመንፈስ ቅዱስን የሚያጠራ ተፅዕኖ ስንለማመድ እና እግዚአብሔር ቃል የገባውን በረከቶች ስንቀበል፣ በሕይወታችን ውስጥ መተግበር ይችላል።
የወንጌልን ህግጋቶችንና ሥነ-ስርዓቶችን ከመታዘዝ በተጨማሪም፣ የክህነት ቃል-ኪዳኖችን እንድትገቡ እና እንድትጠብቁ እጋብዛችኋለሁ። የእግዚአብሔርን መሃላና ቃል-ኪዳን ተቀበሉ። የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን ለመርዳት በክህነት ውስጥ ሃላፊነታችሁን አጉሉ። የአዳኙን የኃጢያት ክፍያ ኃይል ለሌላ ሰው ለማድረስ ለመርዳት ክህነትን ተጠቀሙበት። ይህን ስታደርጉ፣ ከፍተኛ በረከቶች ወደ እናንተ እና ወደ ቤተሰባችሁ ይመጣሉ። ኣዳኙ ሕያው እንደሆነ እና ቤተክረስቲያኑን እንደሚመራ እመሰክራለሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።