አሰፈላጊ እውነት—የእኛ መተግበር አስፍላጊንት
የመጀመሪያው ራእይ እና ጆሴፍ ስሚዝ ለዚህ ህይወት እና ለዘለአለም ከፍተኛነታችን ደስታ በጣም አስፈላጊ የሆነን ተጨማሪ እውነትን እና እውቀትን አምጥተውልናል።
የሰባት አምት ሳለሁ “እኔ እና አንቺ ሞተን ወደ ሰማይ ቤት ስንሄድ አንቺ የእኔ እናት ትሆኛለሽ?” ስል ጠየኳት። እንደዚ አይነት ጥያቄ አልጠበቀችም። ካላት እውቀት በተቻላት ስትመልስ፤ “የለም በሰማይ ወንድም እና እህት ነው የምንሆነው። እናትህ አልሆንም አለች።” ያንን አይነት ምላሽ አልንበረም የጠበኩት።
ከዚህ ልውውጥ ብኋላ በቤታችን ደጃፍ ሁለት ወጣት ወንዶች መጡ። በሆነ ታዐምር አባቴ እንዲገቡ ፈቀደላቸው። ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲይን ሚሲሆኒያውያን ነን አሉ።
ብለን እንድንጠራቸው እንድተማርነው፤ እነዚህ ሽማግሌዎች ቤተሰባችንን ማስተማር ጀመሩ። ሁሌም ሲምጡ የነበረን የደስታ እና የፈንጠዝያ ስሜት በደንብ ትዝ ይለኛል። ወደ ጫካ አንድ ወጣት ወንድ ልጅ የትኛው ቤተክርስቲያን ትክክል እንደሆነ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ እንደሄደና የእግዚአብሔርን እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳየ ነገሩን።1 ሽማግሌዎቹም የእራዩን ምሳሌ ምስል አሳዩን፤ ልክ እንዳየሁትም ጆሴፍ ስሚዝ በእውነት እግዚአብሔር አብ እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳየ አወኩ። ሚሺነሪዎቹም በዚህ እራእይ ምክንያት እውነተኛው የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ዳግም አለ አሉ።2
ሚሺነሪዎቹም የእግዚአብሔርን ለደስታ እቅድን አስተማሩን እናም የቤተሰባችንን የእምነት ጥያቄን መለሰልን። በእውነትም ከዚህ አለም በኋላ ቤተሰብ እንደ አባት እንደ እናት እንደ ወንድ ልጆች እና ሴት ልጆች አንድ ላይ እንደሚሆኑ አስተማሩን።
ቤተሰባችን ተጠመቀ። የድሮን ልምድ የመቀየር፣ ባህልን የመቀየር እና ተሳታፊ የቤተክርስትያን አባል የምሆኑ መንግድ አባጣ ጎርባጣ ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር ምህረት እና ፍቅር እንዲሁም በብዙ አመራሮች እና በአባላት አማካኝነት የመጀመሪያውን አስቸጋሪ አመት አልፍነው።
ሚሊዮኖች ቤተክርስቲያኑን የተቀላቀሉ እናም እየተቀየሩ ያሉ በሳምንት እየትጠመቁ ያሉ ስለ መጀመሪያው ራእይ ምስክርነትን አግኝትዋል። ቀለል ያለውን የኢየሱስ ክርስቶስን እውነታን ለመኖር ስንጥር ይሄንን እውነታ መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዳችን ይድጋግምልናል።
የመጀመሪያው እራእይ እና ጆሴፍ ስሚዝ ለዚህ ህይውት ደስታ እና በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖረን እድገት በጣም አስፈላጊ የሆነን ተጨማሪ እውነትን እና እውቀትን አምጥተውልናል። ወጣት ልጁ ተንበርክኮ ከልቡ በፀለየው ፀሎት ምክንያት ያገኘነውን እና መተግበር ያለብንን ሶስት እውንታዎች እገልጻልሁ።
እግዚአብሔር እኛን ለመምራት ነብያትን ይጠራል
ከመጀመሪያው ራእይ እና ከጆሴፍ ስሚዝ የምንማረው ጠቃሚ እውነት እግዚአብሔር ነብያትን፣3 ባለራእዮችን እና ገላጮችን እኛን ለማስተማር፣ ለማስጠንቀቅ እና ለመምራት እንደሚጠራ ነው።4 እነዚህ ሰዎች በጌታ ስም ለማድረግ እና ለመናገር ስልጣን ያላቸው5 በምድር ላይ የእግዜብሔር አፍ ናቸው።6 ሙሉ በሙሉ ምክራቸውን በመከተል በዚህ ምድር ጉዧችን ላይ እንጠበቃለን እንዲሁም ምርጥ በርከቶችን እንቀበላለን።
በብሪንግህም ያንግ ዩኒቨርስቲ ሳለሁ እንደ ወጣት፣ ያላገባ እና ከሚሽን እንደተመለሰ በቴምፕል ስክዌር የክህነት ጠቅላላ ጉባኤ በተብረናክል ተካፈልኩ። በጊዜው የቤተክርስቲያኗ ፕሬዝዳንት የነበሩት እዝራ ታፍት ቤንሰን ሁሉንም ተመላሽ ሚሽነሪ ትዳር ላይ እንዲያተኩሩ እና በህይወታችው ውስጥ ቅድሚያ እንዲሰጡ አሳሰቡ።7 ከዚያም በኋላ ለንሰሀ እንደተጠራሁ እናም የነብዩ ምክር ተግባር ማድረግ እንዳለብኝ ተገነዘብኩ።
ከዚያም ወደ አገሬ ብራዚል ሚስት ለማግኝት ለመሄድ ወሰንኩ። ለሁለት ወር ኢንተርንሺፕ ወደ ብራዚል ከመሄዴ በፊት፤ እናቴን እና ጥቂት ጓደኞቼን ስልክ ደውዬ አስር እያንዷንዷ ሚስት መሆን የሚችሉ ወጣት ሴቶች— ስም ዝርዝር አገኝሁ።
በብራዚል ሳለሁ ከብዙ ጸሎት እና ማሰላሰል በኋላ ከዝርዝር ውስጥ አንዷን ወጣት ሴት አግኝቼ አውቂያት ከአጨሗት በኋላ የምንጋባበትን ቀን ቆረጥን። ለፕሮቮ ዩታ ተማሪ ሪከርድ ሰባሪ አልነበረም ተዋውቆ መተጫጨት ነገር ግን በብራዚል ፈጣን ነብር።
ከጥቂት ወራት ብኃላ ኧሌንን አገባኋት። የህይወቴ ፍቅር እና ምርጥ በረከት ነች።
ሁሉም ሰው ተመሳሳይ የስም ዝርዝር ያዘጋጅ እያልኩ አይደልም፤ እያልኩ ያለሁት ግን ምናልባት ከማለት በላይ በህይወት ያሉ ነብዮቻችን ሲናገሩ መተግበር አለብን።
ዛሬ የእግዚአብሔር ነብይ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ነው። የእሱን ምክር ሙሉ በሙሉ በመከተል እንባረካለን።
የእግዚአብሔር እውነተኛ ተፈጥሮ እውቀት
በመጀመሪያው ራእይ እና ከጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ሌላኛው የምንማረው እውነት የእግዚአብሔር እውነተኛ ተፈጥሮ ነው። እውነተኛ የሆነውን አምላክ እንድናመልክ እግዚአብሔር እንደኛ የሚጨበጥ ስጋ እና አጥንት እንዳለው8 በማወቃችን እንዴት እንደተባረክን አስቡት። ልንረዳ የምንችለውን፣ እራሱን እና ልጁን ጥንትም ለነበሩ አሁንም ላሉ ነብያት የገለጠውን እና እውነት የሆነውን አምላክ ማምልክ እንችላለን።9 ጸለቶቻችንን የሚሰማ እና የሚመልስ አምላክ፣10 ከላይ ከሰማይ የሚመለከተን አምላክ፣11 ያለማቛረጥ ስለመንፈሳዊና ጊዚያዊ ደህንነታችን የሚጨነቅ፤ ሳንገደድ12 እሱን ለመከተል እና ትዕዛዛቱን ለመታዘዝ እራሳችን እንድንመርጥ ነፃ ምርጫን የሰጠን፤ አድገን እንደሱ እንድንሆን ችግሮችን እንድናይ የፈቀደ እና በረከት የሰጠን አምላክ ነው።
በዚህ አለም እና ለዘላለም እንድንደሰት እቅድን ያዝጋጀልን አፍቃሪ አምላክ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ መድሀኒታችን ነው።
ከመጀመሪያው ራእይ እና ከጆሴፍ ስሚዝ የእምነታችን የማእዘን ድንጋይ የሆነውን የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ እና የተቀደስውን ተልእኮው እውነተኛነት እውቀት ተቀብለናል።
ምክንያቱም ሞት ወደዚህ አለም መጥቷል፣ አሁን እንደምንኖርው ሁላችንም እንደምንሞት እርግጥ ነው። የሞት አንደኛው ተፅእኖ አካላችንን ማጣት ነው፤ መልሰን ለማግኝት ምንም ማድረግ አንችልም። በተጨማሪም በዚህ ምድራዊ ጉዛችን ላይ ሁላችንም ሀጥያት ስለምን ሰራ ወደ ሰማይ አባታችን ፊት መቼም መቅርብ አንችልም ነብር።
ከእግዚአብሔር ፊት መሆንን ማጣት ውጤቱ ምን እንደሚሆን እና መቼም አካላችንን አለማግኘትን ማሰብ ትችላላሁ?
ከሀጥይት እና ከሞት የሚያድነን አዳኝ እና ቤዛ ያስፈልግ ነብር። በእውነት ንሰሀ በመግባት እና ቅዱስ ቃልኪዳኖችን በመጠበቅ ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ በሰማይ አባታችን አዛዥነት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መጣ፣ ተሰቃየ፣ በመስቅል ላይ ሞት እናም እኛ ትንሳኤን እንድናደርግ ትንሳኤን አደረገ።
ያዕቆብ እንዳወጀው፣ “አቤቱ፣ ከዚህ ከሚያስቀይመው አስፈሪ እቅፉ፣ አዎን፣ እኔ የስጋ ሞት፣ እናም ደግሞ የመንፈስ ሞት ብዬ የምጠራው ያ አስፈሪ ሞትና ሲኦልን ሊያስመልጠን መንገዱን ያዘጋጀልን የአምላካችን ጥሩነት እንዴት ታላቅ ነው።”13
ቃል የተገባው መሲህ፣ ህግ ሰጪው፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ ጌታችን፣ አዳኛችን እናም ቤዛችን የሁላችንም ንጉሳችን ኢየሱስ ነው።
ታዛዥነታችንን ለእግዚአብሔር እና ለውዱ ልጁ በመስጠት እንዚህን አስፈላጊ እውነታዎች መተግበርንን ሁላችንንም እንቅጥልብት። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።