2010–2019 (እ.አ.አ)
የተለየ፣ ግን አንድ
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


2:3

የተለየ፣ ግን አንድ

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ ብንለያይም፣ ጌታ አንድ እንድንሆን ይጠብቃል!

በሰኔ 1994 (እ.አ.አ)፣ የአገራችን የእግር ኳስ ቡድን በአለም ዋንጫ ድርድር ሲጫወቱ ለመመልከት ወደ ቤት በጉጉት መኪና እየነዳሁ እሄድ ነበር። ጉዞዬን ከጀመርኩ ወዲያውም፣ አካል ስንኩል የሆነ ሰው በብራዚል ባንዲራ ያሸበረቀ ጋሪው በመንገድ ዳርቻ ላይ እየፈጠነ ሲሄድ ከሩቅ አየሁት። እርሱም ጨዋታውን ለመመልከት እየሄደ እንደሆነም አወቅኩኝ።

የምንጓዝበት መንገድ ሲተላለፉ፣ እና አይኖቻችን ሲተያዩ፤ ለጥቂት ሰከንድም ከዚህ ሰው ጋር አንድነት ተሰማኝ። በተለያየ መንገድ ነው የምንጓዘው፣ አንተዋወቅም፣ እናም በግልጽም የተለያየ ህብረተሰባዊና የሰውነት ሁኔታ አለን፣ ነገር ግን ለእግር ኳስ ያለን አንድ አይነት ጥልቅ ስሜት እና ለአገራችን ያለን ፍቅር በዚያ ጊዜ አንድ እንደሆንን እንዲሰማን አደረገን፡ ከዚያ ጊዜ በኋላ ያን ሰው አይቼውም አላውቅም፣ ነገር ግን ዛሬ፣ በብዙ አመት በኋላ፣ እነዚያን አይኖች አሁንም ይታዩኛል እናም ያ ጠንካራ ግንኙነት ከዚያ ሰው ጋር ይሰማኛል። ሁሉም ካለፈ በኋላ እኛም ጨዋታውን አሸነፍን እናም የአለም ዋንጫ አሸናፊዎች ሆንን!

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ ብንለያይም፣ ጌታ አንድ እንድንሆን ይጠብቃል! በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ እንዳለው፣ “አንድ ሁኑ፤ እናም አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም።”1

እንደ ቡድን ለማምለክ ወደ ማምለኪያ ቤት ስንገባ፣ ልዩነታችንን፣ እንዲሁም ዘርን፣ የህብረተሰብ ሁኔታን፣ የፖለቲካ ልዩነትን፣ የትምህርት እና የስራ ውጤትን ወደኋላ እንተው፣ እናም በምትኩ በጋራ ባለን መንፈሳዊ አላማ ላይ እናተኩር። አብረን መዝሙር እንዘምራለን፣ በቅዱስ ቁርባንም ስለአንድ አይነት ቃል ኪዳን እናሰላስላለን፣ ከንግግር፣ ከትምህርት፣ እና ከጸሎት በኋላም በአንድነት “አሜን” እንላለን—ይህም በአንድነት የተካፈልነውን እንስማማለን ማለት ነው።

አብረን የምናደርጋቸው እነዚህ ነገሮ ች በተሰብሳቢዎች መካከል ጠንካራ አንድነት ስሜት ለመፍጠር ይረዳሉ።

ነገር ግን፣ አንድነታችንን የሚወስነው፣ የሚያጠናክረው፣ ወይም የሚያጠፋው ከቤተክርስቲያን አባላታችን በተለየንበት ጊዜ የምናደርገው ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው፣ ስለእርስ በራስ መነጋገራችን የማይቀር እና ልዩ ያልሆነ ነው።

ስለእርስ በራስ ምን ለማለት በምንመርጠው ላይ በመመካት፣ ቃላቶቻችን አልማ በሞርሞን ውሀ እንዳስተማረው፣ “ልባችንን በአንድነት ያስተሳስራሉ፣”2 ወይም በመካከላችን መገኝ የሚገባቸውን ፍቅር፣ ታማኝነት፣ እና መልካው ሀሳብ ይሸረሽራሉ።

“አዎን፣ እርሱ መልካም ኤጲስ ቆጶስ ነው፤ ኦ፣ ግን በወጣትነቱ ብታውቁት ኖሮ!” የሚሉት አስተያየቶች አንድነትን በቀስታ ያጠፋሉ።

ከዚህ የተሻለ ገንቢ አስተያየት የሚሆነው “እርሱ መልካም ኤጲስ ቆጶስ ነው፣ እናም በአመታት ውስጥ በበሳልነት እና በጥበብ አድጓል።”

በብዙ ጊዜ በሰዎች ላይ እንዲህ በማለት የማይጠፋ ምልክት እናደርጋለን “የሴቶች መራደጃ ማህበር ፕሬዘደንታችን መቀየር የማትችል ነች። መንቻካ ናት!” በአንጻራዊው፣ እንዲህ ለማለት እንችላለን፣ “የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንት በቅርቡ እምብዛም ብዙ አመቺ አይደለችም፤ ምናልባት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እያለፈች ይሆናል። እንርዳት እናም እንደግፋት!”

ወንድሞችና እህቶች፣ ማንንም ሰው ያለቀለት መጥፎ ውጤት ነው ብለን መግለፅ የለብንም፣ በተጨማሪም በቤተክርስቲያን ክብ ውስጥ ያሉትን! ግን፣ ስለጓደኞቻችን የምንለው ቃላቶቻችን በኢየሱስ ክርስቶስና በኃጢያት ክፍያው ያለንን እምነት የሚያንጸባርቁ እና፣ በእርሱ እና በእርሱ በኩልም ሁልጊዜም ለተሻለ መቀየር እንችላለን።

አንዳንዶች በጣም ትንች በሆኑ ነገሮች ይሰለቻሉ እና ከቤተክርስቲያኗ መሪዎችና አባላት ጋር ይለያያሉ።

በ1831 (እ.አ.አ) የቤተክርስቲያኗ አባል የሆነው ሳይሞንድስ ራይደር የሚባለውም ሰው የዚህ ምሳሌ ነበር። ስለእርሱ በሚመለከት ያለውን ራዕይ ከተመለከተ በኋላ፣ ስሙ በትክክል እንዳልተጻፈ በእንግሊዘኛ Rideri ሳይሆን በy ስለተጻፈ ተናዶ ነበር። ለዚህ ድርጊት የነበረው መልስ ነቢዩን ለመጠራጠሩ እና በመጨረዛም ለጆሴፍ መሳደድና ከቤተክርስቲያኑ ወደ መውደቁ ረድተው ነበር።3

ሁላችንም አንዳንዴ በሀይማኖት መሪዎቻችን እንገሰጽ ይሆናል፣ ይህም ከእነርሱ ጋር እንዴት አንድ እንደምንሆን ይፈትነናል።

11 አመቴ ነበር፣ ግን ከ44 አመት በፊት፣ ቤተሰቤ ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄዱበት ቦታ ታላቅ ሁኔታ የሚጠገንበትን ጊዜ አስታውስ ነበር። ያን ስራ ከመጀመሩ በፊት፣ በዚህ አባላት እንዴት በጥረት እንደሚሳተፉ ለመወያየት የአካባቢው እና የክልል መሪዎች ስብሰባ ነበር። ቤተክርስቲያኗን ከዚህ በፊት ይመራ የነበረው አባቴም ይህ ስራ በባለሙያዎች እንጂ ሰርተው በማያውቁት እንዳይሰራ ጠንካራ ሀሳቡን ገለጸ።

የእርሱ አስተያየት ተቀባይነት ከማጣቱም በተጨማሪ፣ በዚህ ሁኔታ በሀይል እና በሰው ፊት ተገስጾ እንደነበረ ሰማን። አሁን ይህ ሰው ለቤተክርስቲያኗ ታማኝ የሆነ እና በሁለተኛው የአለም ጦርነት በአውሮፓ ለሚያምንበት የሚታገል እናም ለሚቃረንበት የተዋጋ ወታድር ነበር። ከዚህ ክስተት በኋላ የእርሱ ምላሽ ምን ይሆን ብሎ አንድ ሰው ሊያስብ ይችላል። በአስተያየቱ ይቀጥላል እና ውሳኔ የተደረገበትን ይቃወም ይሆን?

በዎርዳችን ውስጥ ከሚመሩት ጋር አንድ ለመሆን ባለመቻላቸው ምክንያት በወንጌል ደካማ የሆኑ እና በስብሰባ ተሳታፊነትን ያቆሙ ቤተሰቦችን አይተናል። ደግሞም ወላጆቻቸው በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ባሉት ላይ ስህተቶችን ሁልጊዜ የሚያገኙ ስለሆኑ፣የመጀመሪያ ክፍል ጓደኞቻችንን በወጣትነታቸው ታማኝ መሆናቸውን ሲያቆሙ ተመልክተናል።

አባቴ ግን ከቅዱሳን ጋር አንድ ሆኖ ለመቆየት ወሰነ። እናም ከትንሽ ቀናት በኋላ የዎርድ አባላት በስራው ለመርዳት ሲሰበሰቡ፣ ቤተሰባችን እንድንከተለው እና በማንኛውም መንገድ ለመርዳት ራሳችንን ለመገኘት እንድናስችል “ጋበዘን”።

ተናደድጄ ነበር። እኔም “አባዬ፣ አባላቱ እንዲያደርጉት የምትቃረን ከሆነ ለምን ነው በግንባቱ ለመርዳት የምንሄደው” ብዬ ለመጠየቅ ተሰማኝ። ነገር ግን በፊቱ ላይ የነበረው አስተያየት ይህን ከማድረግ አቆመኝ። ለዳግም መመረቁ ደህና ለመሆን ፈልጌ ነበር። ስለዚህ፣ ጸጥ ለማለት እና በመሄድ ለመርዳት ወሰንኩኝ!

አባዬ አዲስ ቤተክርስቲያኗ እስከሚያይ ድረስ አልኖረም፣ ይህ ስራ ከመፈጸሙ በፊት ሞቱልና። ነገር ግን ቤተሰብ፣ በእናቴ እየተመራን፣ እስከሚፈጸም የክፍላችንን አደረግን፣ እናም ያም ከእርሱ፣ ከአባላት፣ ከመሪዎች፣ እና በልዩም ከጌታ ጋር አንድ እንድንሆን አደረገ።

ከጌተሰማኔው ከነበረው ከሚያሰቃይ አጋጣሚ በፊት፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እና ለቅዱሳን ወደ አብ ሲጸልይ፣ እንዲህ አለ፣ “ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ።”4

ወንድሞችን እና እህቶች፣ አብረን ስንሰበሰብ፣ ነገር ግን ይበልጥ በተለያየንበት ጊዜ፣ ከቤተክርስቲያኗ አባላት እና መሪዎች ጋር አንድ ለመሆን ስንወስን፣ ከሰማይ አባታችን እና ከአዳኝ ጋር በፍጹም አንድነት እንደሚሰማን እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።