የተመረጡት መጽሀፍትን ፈልጉ
ከምርጥ መፅሀፎች ስናጠና፣ የመንፈስ ስራችንን ለማኘክ ከሚፈልጉ መንጋጋዎች ራሳችሁን ለመጠበቅ ትችላላችሁ።
በአንድ ጠዋት፣ የታረበ እና በደንብራሱን የሚደብቅ አባጨጓሬ በሚያምር በፅጌረዳ አትክልት ላይ አየሁት። የአትክልቱ አንዳንድ ቅጠሎች በሚመስሉበትም፣ በተራ ለሚመለእተው ሰውም ይህ ለስላሳ ቅጠሎችን በጣም እንዳኘካቸው ግልጥ ነው። በምሳሌ፣ የተደበቁ ብዙ አባጨጓሬዎች አይነት የሆኑ ሰዎች እንደሚገኙ አስባለሁ።፤ እነርሱም በአለም በሙሉ ይገኛሉ፣ እናም አንዳንዶች በደንብ ስለሚደበቁ በህይወታችን ውስጥ እንዲገቡ እንፈቅዳለን፣ እናም ከማወቃችን በፊት፣ መንፈሳዊ ስራችንን እና የቤተሰብ አባሎቻችንን እና ጓደኞቻችንን በልተዋቸዋል።
ስለሀይማኖታችን ስህተተኛ መረጃዎች በብዛት በሚገኙበት ዘመን ነው የምንኖረው። በእነዚህ ጊዜዎች፣ መንፈሳዊ ስራችንን አለመጠበቅና ዝልቅ አለማድረግ በክርስቶስ ያለንን እምነት እና በዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያኑ ያለንን እምነት ለማጥፋት በሚፈልጉት ይታኘካሉ። በመፅሐፈ ሞርሞን ጊዜዎች፣ የሚያምኑትን ሰዎች እምነት ለማጥፋት የፈለገው ዚዝሮም ነበር።
የእርሱ ስራዎች እና ቃላት “የጠላት ወጥመድ ነው፣ ይህም ለእርሱ [እንዲገዙ] ለማድረግ ለምርኮ ባለው ስልጣኑ መሰረት፣ በሰንሰለቱም [ይከባቸው] ዘንድ፣ በዘለአለማዊ ጥፋት ሰንሰለት [ይመታቸው] ዘንድ፣ ይህን ህዝብ ለመያዝ ያጠመደው ” (አልማ 12:6) ነበሩ። እንደዚህ አይነት ማጥመጃዎች አሁንም ይገኛሉ፣ እናም በመንፈስ ተከታታይ ካልሆንን እና በቤዛችን ፅኑ መሰረት ካልመሰረትን (ሔለማን 5:12 ተመልከቱ)፣ በሰይጣንሰንሰለት ለመታሰር እና በቀስታ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ወደተነገረበት የተከለከለው መንገድ ስንመራራሳችንን እናገኛለን (1 ኔፊ 8:28 ተመልከቱ)።
ሐዋሪያው ጳውሎስ በቀኑ ለእኛ ጠቃሚ የሚሆን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፥ “ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።” (የሐዋሪያት ስራ 20፥29–30)።
የእርሱ እና የነቢያችን እናም የሐዋሪያት ማስጠነቀቂያ እኛ ራሳችንን በመንፈስ ከሚያታልሉ ቃላት ለማጠናከር እንችል ዘንድ የምንችለውን ያህል ማድረግ እንዳለብን እንድናስታውስ ያደርግል። የቤተክርስቲያኗን ዎርዶች እና ካስማዎች ስጎበኝ፣ ቅዱሳን በአዳኝና በአገልጋዮቹ ትምምህርቶች ትክክል እና ታማኝ በሆነ ሲመልሱ በማየው፣ በምሰማው፣ እና በሚሰማኝ ከፍ ከፍ እላለሁ።
የሰንበት መከተል የነቢያትን ግብዣ በመስማት አባላት በመንፈስ ራሳቸውን የሚያጠናክሩበት ምሳሌ ነው፡ ተጨማሪ መጠናከርም የሚታየው ቤተሰቦች ቅድመ አያቶቻቸውን በቤተመቅደስ ስርዓቶች በኩል በመሰብሰብ በሚደረጉት በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ እድገት ነው። ቅን የግል እና የቤተሰብ ጸሎታችን ዝልቅ ሲሆኑ፣ በየቀኑ ንስሀ ስንገባ፣ የመንፈስ ቅዱስ ጓደኝነትን ስንፈልግ፣ እና ስለአዳኛችን እና ስለጸባዩ ሰንማርና እንደእርሱ ለመሆን ስንጥር መንፈሳዊ ዝራችን ይዘልቃሉ (3 ኔፊ 27፥27 ተመልከቱ)።
አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የአለም ብርሀን ነው፣ እናም እርሱም እንድንከተለው ይጠራናል። በሁሉም ጊዜ እና በልዩም ጨለም ያለ እና ዝናባዊ ጭለማ ምሽት ሲኖሩ እና የመጠራጠር ንፋሶች እንደሚንከባለሉ ጭጋ በቀስታ ሲገቡ ወደ እርሱ መመልከት ይገባናል። “ከውሃው ወንዝ ባሻገር፣ ትልቅና ሰፊ ህንፃን [በቆመበት]” (1 ኔፊ 8:26) የሚያጠቁሙት ጣቶች ወደ እናንተ በሚያሳልቅ፣ በሚያሳድብ፣ እና በሚጠራ ሁኔታ የሚያጠቁሙ ቢመስሉም፣ በሚያታልል መንገድ ራሳችሁን ከእውነት እና ከበረከቱ ከሚያለያየው ወዲያው እንድትዞሩ እጠይቃችኋለሁ።
ነገር ግን፣ በዚህ ስድብ ነገሪች በሚናገሩበት፣ በሚጻፉበት፣ እና በሚታዩበት በዚህ ቀን ያ ብቻውን የሚበቃ አይደለም። ሽማግሌ ሮበርት ዲ. ሄልስ እንዳስተማሩን “‘በልባችሁ፣ በሀይላችሁ፣ በአዕምⶂችሁ፣ እና በጥንካሬአችሁ’ በሙሉ በመኖር—በወንጌል ለመኖር በሙሉ ካልወሰናችሁ፣ ጨለማውን ለመግፋት ብቁ መንፈሳዊ ብርሀን ለማግኘት አንችልም” (“Out of Darkness into His Marvelous Light,” Liahona, July 2002, 78)። በእርግጥም፣ የአለም ብርሀን የሆነው ክርስቶስን ለመከተል ያለን ፍላጎት (ዮሀንስ 8፥12 ተመልከቱ) በእርሱ ትምህርት መስራት ማለት ነው። በእግዚአብሔር ቃል ስንሰራ በመንፈስ እንጠናከራለን፣ እንሸሸጋለን፣ እናም እንጠበቃለን።
በህይወታችን ውስጥ ያለው ብርሀን ታላቅ ሲሆን፣ ጥላዎቹ ትንች ይሆናሉ። ነገር ግን፣ በብርሀን ብዛት ውስጥም ስለሀይማኖታችን ትክክል ያልሆኑትን የሚናገርትን ሰዎችና የሚሉት ያጋጥሙናል እናም እምነታችንን ይፈትናሉ። Tሐዋሪያው ያዕቆብ እንደጻፈው፣ “[የእምነታችን] መፈተን ትዕግሥትን [ያደርግልናል” (ያዕቆብ 1፥3)። በዚህ አስተያየት፣ ሽማግሌ ኒል ኤ. ማኽጽዊል እኝዻጽጠማሩጥ ”ትዕግስተኛ ደቀ መዛሙርት … ቤተክርስቲያኗ በተሳሳተ ሁኔታ ስትቀርብ በምንም አትደነገጡም ወይም አትወድቁም” (“Patience” [Brigham Young University devotional, ህዳር 27፣ 1979 (እ.አ.አ)]፣ speeches.byu.edu)።
ስለቤተክርስቲያናችን ታሪክ እና እምነት ጥያቄዎች ይኖራሉ። መልስን ለማግኘት ወዴት መዞራችን ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ብዙ መረጃ ከሌለው እና ቅር ከተሰኘው አስተያየትን እና ሀሳብን መፈተሽ ምንም ሊገኝበት አይችልም። ምርጥ የሆነው ምክር የተሰጠው በሐዋሪያው ያዕቆብ ነው፥ “ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው እግዚአብሔርን ይለምን” (ያዕቆብ 1፥5)።
እግዚአብሔርን ከመጠየቅ አስቀድሞ የሚመጣው በጥንቃቄ ማጥናት ነው፣ ምክንያቱም “ከተመረጡት መጽሀፍትም የጥበብን ቃላት ፈልጉ፤ እውቀትን፣ እንዲሁም በጥናትና ደግሞም በእምነት፣ እሹ” (ት. እና ቃ. 88፥118) በሚለው ቅዱስ መጻህፍት አደራ ስር ነን። በሰማይ-በተነሳሱ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች እና በሚታወቁ፣ አደገኛ ባልሆኑ፣ እና ለመመካት በሚቻልባቸው የቤተክርስቲያኗ ታሪክና ትምህርት አስተማሪውች የተጻፉ እንደዚህ አይነት መፅሀፎች በብዛት ይገኛሉ። ይህም ከተባለ በኋላ፣ በይፉ ቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ከሚገኙ ከተገለጹ የእግዚአብሔር ቃላት በላይ የሚበልጥ ምንም የለም። በመንፈሳዊ አስተያየት ሰፊ ከሆኑት ከእነዚያ ቀጭን ገጾች፣ በመንፈስ ቅዱስ በኩል እውነትን እንማራለን እናም በዚያም በብርሀን እናድጋለን።
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን “በየቀኑ መፅሐፈ ሞርሞንን በጸሎት እንድናጠና እና እንድናሰላስል” (“The Power of the Book of Mormon,” Liahona, May 2017, 87) ለምነውናል።
ከብዙ አመት በፊት፣ እንደ ፊጂ ሱቫ ሚስዮን ፕሬዘደንት እያገለገልኩኝ እያለሁ፣ አንዳንድ ሚስዮኖች የመፅሐፈ ሞርሞን የሚቀይር ሀይልን የሚገልጹ የሚያጠናክርላቸው አጋጣሚዎች አግኝተዋል። በአንድ በሞቀና ርጥበት ያዘለ አየር በሚገኝበት ቀን፣ ሁለት ሽማግሌዎች በላባሳ መኖሪያ ስፍራ ውስጥ ወደሚገኘው ትንሽ ቤት ደረሱ።
ሲያንኳኩ በሩን ያረጀ ሰው ከፈተ እና ስለመፅሐፈ ሞርሞን እውነትነት ሲመሰክሩ አዳመጣቸው። መፅሀፉን ሰጡት እና እንደ እነርሱ ይህ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ለማመው እንዲያነብና እንዲጸልይ ጠየቁት። መልሱም አጭር ነበር፥ “ነገ ወደ አሳ ማጥመድ እመለሳለሁ። በባህር ላይ ሳለሁ አነበዋለሁ፣ እናም ስመለስ እንደገና ልትጎበኙን ትችላላችሁ።”
ሄዶ ሳለ፣ የሚያገለግሉበት ቦታ ተቀየረ፣ እናም ከትንሽ ሳምንት በኋላ፣ አዲስ ሽማግሌዎች አሳ አጥማጁን ለመጎብኘት ተመለሱ። በዚህ ጊዜ መፅሐፈ ሞርሞንን በሙሉ አንብቦ፣ ስለእውነትነቱ መረጋገጫ ተቀብሎ፣ እና ተጨማሪ ለማወቅ ጉጉት ነበር።
ይህም ሰው ከብዙ አመት በፊት በመፅሐፈ ሞርሞን እያንዳንዱ ገፅ ውስጥ የሚገኙትን ድርጊቶችና ለቀናችን የተጠበቀውን እና ከረጅም ጊዜ ያስተማሩትን ትምህርቶች እውነትነትን በመንፈስ ቅዱስ ተቀብሎ ነበር። ያ በረከት ለእያንዳንዳችን የሚገኝ ነው።
ቤትም ቤተሰቦች ለማጥናት እና ከቅዱሳት መጻህፍ፣ ከህያው ነቢያት አስፈላጊ አስተያየትን ለመካፈል እና ከLDS.org የቤተክርስቲያን ነገሮችን ለማግኘት የሚችሉበት መልካም ቦታ ነው። በዚያም ስለመጀመሪያው ራዕይ አይነት የወንጌል ርዕስ ብዙ መረጃዎች ታገኛላችሁ። ከምርጥ መፅሀፎች ስናጠና፣ የመንፈስ ስራችንን ለማኘክ ከሚፈልጉ መንጋጋዎች ራሳችሁን ለመጠበቅ ትችላላችሁ።
በጸሎታችን፣ በጥናታችን፣ እና በምናሰላስላቸው፣ ምልስ ያላገኘንባቸው ጥያቄዎች ሊቀርም ይሆናሉ፣ ነገር ግን ያም በውስጣችን የሚንለበለብውን የእምነት ነበልባል ማጥፋት አይገባንም። እንደዚህ አይነት ጥያቄዎች እምነታችንን ለመገንባት የሚጋብዙ ናቸው እና የሚያልፍን የሚያታልል ጥርጥር የሚያነዱ መሆን አይገባቸውም። ለእያንዳንዱ ጥያቄ እርግጠና መልስ አለማግኘት፣ የሀይማኖት አስፈላጊ ነገር ነው፣ ምክንያቱም ይህ የእምነት አንድ አላማ ነው። ስለዚህም፣ ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ “መፍትሄው ወዲያው ግልጽ ያልሆኑ እነዚያ ጊዜዎችና ጉዳዮች ሲመጡ፣ የምታውቁትን አጥብቃችሁ ያዙ እና ተጨማሪ እውቀት እስከሚመጣ ድረስ በጥንካሬ ቁሙ” (“Lord, I Believe፣” Liahona፣ May 2013)።
በአካባቢያችን መንፈሳዊ ስራቸውን በመመገብ በጥንካሬ የቆሙት ብዙዎች ሲደሰቱ እናያለን። እምነታቸው እና ታዛዥነታቸው በአዳኛቸው ተስፋ ሊሰጣቸው ብቁ ነው፣ እናም ከዚያም ታላቅ ደስታ ይመነጫል። ሁሉንም ነገሮች እናውቃለን አይሉም፣ ነገር ግን ተጨማሪ ለማወቅ ሲፈልጉም ሰላም ለማግኘት እና በትእግስት ለመኖር ብቁ የሆነ ዋጋ ከፍለዋል። በመስመር ላይ መስመር፣ በክርስቶስ ያላቸው እምነት ተረጋግጧል፣ እናም እንደ ቅዱሳን ዜጋዎች በጥንካሬ ይቆማሉ።
አሁንም ቢሆን በምንም ጊዜ የተደበቁ አባጨጓሬ መንጋጋዎች ቦታ እንዳያገኙ እያንዳንዳችን “fበክርስቶስ ባለን ፅኑ እምነት፣ እስከመጨረሻም” (አልማ 27፥27) እንቆይ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።