ሶስት እህቶች
ለራሳችን ደቀመዛሙርትነት ሀላፊነት አለን፣ እናም ይህም ሌሎች እኛን በሚይዙበት መንገድ ላይ ትንሽ ወይም ምንም ግንኙነት የለውም።
ውድ እህቶች፣ ውድ ጓደኞች፣ አጠቃላይ ጉባኤን በአለም አቀፍ የእህቶች ስብሰባ መጀመር ትርጉም ያለው እና አስደናቂ ነው። ይህን አስቡበት፥ የሁሉም እድሜ፣ አጋጣሚዎች፣ ዜጋዎች፣ እና ቋንቋዎች እህቶች ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው እምነት እና ፍቅር አንድ ሲሆኑ።
በቅርብ ከውድ ነቢያችን፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን ጋር ስንገናኝ፣ ጌታን ምን ያህል እንደሚወዱ ገልጸውልናል። እናም ፕሬዘደንት ሞንሰን ለፍቅራችሁ፣ ለጸሎታችሁ፣ እና ለጌታ ላላችሁ አምልኮ ስጋና እንዳላቸውም አውቃለሁ።
ከብዙ አመታት በፊት በሪቅ ሀገር የሶስት እህቶች ቤተሰብ ይኖሩ ነበር፡
የመጀመሪያዋ እህት ያዘነች ነበረች። ከአፍንጫዋ እስከ አገጯ ድረስ እናም ከቆዳዋ እስከ እግር ጣቶ ድረስ ምንም መልካም አይመስላትም ነበር። ስትናገርም፣ ቃላቶቿ አንዳንዴ አስቸጋሪ ሆነው ይወጣሉ፣ እናም ሰዎችም ይስቁ ነበር። አንድ ሰው ሲወቅሳት ወይም እርሷን ለአንድ ነገር ለመጋበዝ “ሲረሱ”፣ ታፍራለች፣ ዞር ብላም ትሄዳለች፣ እናም የሀዘን ትንፋሷን የምትተነፍስበት የሚስጥር ቦታ ታገኛለች እናም ለምን ህይወት ተስፋ የሌለው እና ደስታ የለሽ እንደሆነም ታስባለች።
ሁለተኛዋ እህትም የተናደደች ነበረች። ራሷን በጣም ጎበዝ እንደሆነች ትመለከታለች፣ ነገር ግን በትምህርት ቤት ውስጥ ከእርሷ በላይ ከፍተኛ ደረጃ የሚያገኝ አለ። ራሷን እንደምታስቅ፣ ቆንጆ፣ ፋሽን ያላት፣ እና አስደናቂ ነኝ ብላ ታስባለች። ነገር ግን ሁልጊዜም ከእርሷ የሚሻል የምታስቅ፣ ቆንጆ፣ ፋሽን ያላት፣ ወይም አስደናቂ የሆነች ሌላ ያለች ይመስላል።
በማኝኛውም ነገር መጀመሪያ አልነበረችም፣ እናም ይህን ለምፅናት አልቻለችም። ህይወት እንደዚህ መሆን አልነበረበትም!
እንዳንዴ በሌሎች ላይ ትናደዳለች፣ እናም በአንድ ነገርም ይሁን በሌላ ለመናደድ ከአንድ ትንፋሽ የራቀች ይመስላል።
በእርግጥም፣ ይህ በምንም የምትወደድ ወይም ታዋቂ እንድትሆን እያደረጋት አልነበረም። አንዳንዴም፣ ጥርሷን ታፏጫለች፣ እጇን በጡጫ ትይዛለች፣ እናም “ህይወት ሚዛናዊ ያልሆነ ነው!” ብላ ታስባለች።
ከዚያም ሶስተኛዋ እህት ነበረች። እንዳዘነችው ወይም እንደተናደደችው እህት ሳትሆን፣ እርሷም ደስተኛ ነበረች። እና ይህም የነበረው እርሷ ከእህቶቿ በላይ ጎበዝ ወይም በተጨማሪ ቆንጆ ወይም ተጨማሪ ችሎታ ያላት ስለሆነች አይደለም። አይደለም፣ ሰዎች አንዳንዴ ከእርሷ ይሸሸጋሉ። እርሷ በምትለብሰው ወይም በምትለውም አንዳንዴ ይቀልዱባታል። እነርሱም አንዳንዴ ስለእርሷም ክፉ ነገሮች ይላሉ። ነገር ግን ማንኛውም እርሷን በብዛት እንዲሸብሯት አትፈቅድም።
ይህች እህት መዘመር ትወዳለች። የምትዘምርበት ድምጿ ጥሩ አይደለም፣ እና ሰዎችም ይስቁባታል፣ ነገር ግን ይህ እንድታቆም አያደርጋትም። “ሌሎች ሰዎች እና የእነርሱ አስተያየት መዝፈንን እንዳቆም እንዲያደርጉኝ አልፈቅድላቸውም!” ትላለች።
በመዝፈን መቀጠሏ የመጀመሪያ እህቷን እንድታዝን እና ሁለተኛ እህቷን እንድትናደድ አደረገ።
ብዙ አመታት ሲያልፉም፣ እና በመጨረሻም እያንዳንዷ እህት በምድር ያላት ጊዜ መጨረሻ ደረሰ።
በተደጋጋሚ በህይወት ተስፋ የሚቀረጥበት እጥረት እንደሌለ በማወቅ፣ የመጀመሪያዋ እህት አዛኝ በመሆን ሞተች።
በየቀኑ አዲስ አንድ ነገር የምትጠላውን ያገኘችው ሁለተኛዋም ተናድዳ ሞተች።
እናም ሶስተኛዋ እህት ህይወቷን በፊቷ ልበ ሙሉነትን በማሳየት ዘፈኗን በሀይሏ ሁሉ በመዝፈን እያሳለፈች፣ በደስታ ሞተች።
በእርግጥም፣ ህይወት እንደዚህ ቀላል አይደለም፣ እናም ሰዎች እንደ ታሪኩ ሶስቱ እህቶች አይነት በምንም አይነት አንድ መለኪያ ያላቸው አይደሉም። ነገር ግን እንደነዚህ አይነት በጣም የተለዩ ምሳሌዎችም ስለራሳችን አንዳንድ ነገሮች ሊያስተምሩን ይችላሉ። እናንተ እንደ እኛ አይነት ከሆናችሁ፣ የራሳችሁን ክፍል በአንድ፣ ሁለት፣ ወይም ምናልባትም በሶስቱ እህቶች ላይ ለማየት ትችሉ ይሆናል። በእያንዳንዱ ላይ የቅርብ ትኩረት እናድርግ።
የተጠቃችው
የመጀመሪያዋ እህት ራሷን እንደተጠቃች—ነገሮች እንደሚደረግባት ተመለከተች።1 አንድ ነገር ከሌላ በእርሷ ላይ ስለሚደርስባት እርሷን አሳዛኝ የሚያደርጋት ይመስል ነበር። በህይወት እንደዚህ አይነት አስተያየት እያላት፣ ሌሎች እርሷ እንዴት እንደሚሰማትና የእርሷ ጸባይ ምን እንደሆነ እንዲቆጣጠሩ አድርጋለች። ይህን ስናደርግ፣ በማንኛውም አስተያየት እንገፋፋለን—እናም በነዚህ ቀናት ሁሌ በሚገኘው በህብረተሰብ መተላለፊያ፣ እነዚህ አስተሳሰቦች በጣም ብዙ ናቸው።
ውድ እህቶች፣ ደስታችሁን ለምን ስለእናንተ፣ ወይም ለደስታችሁ ምንም ለማያስቡት ለሌላ ሰው፣ ወይም ለአንዳንድ ቡድኖች በምርኮ ትሰጣላችሁ።
ሌሎች ሰዎች ስለእናንተ ስለሚሉት በማሰብ ላይ እራሳችሁን ካገኛችሁ፣ ይህን መዳኒት በሀሳብ ላቅርብላችሁ፥ ማን እንደሆናችሁ አስታውሱ። እናንተ በእግዚአብሔር መንግስት የልዑል ቤት አባል፣ በሁለንተና በሙሉ በሚነግሱ የሰማይ ወላጆች ሴት ልጆች እንደሆናችሁ አስታውሱ።
የእግዚአብሔር መንፈሳዊ ዘር ናችሁ። በመንፈሳዊ ፍጥረታችሁ የጀመሩ ልዩ ስጦታዎች አሏችሁ እናም እነዚህም የተገነቡት በረጅሙ ከምድር ህይወታችሁ በፊት ነበር። እናንተ የሰማይ አባት፣ የሰራዊት ጌታ፣ ጠፈርን የፈጠረው፣ የሚዞሩትን ከዋክብት በሁለንተና የዘረጋው፣ እናም ፕላኔቶችን በተመደቡባቸው በምህዋራቸው እንዲሆኑ ያስቀመጠ ምህረታዊው እና ዘለአለማዊው እግዚአብሔር ልጅ ናችሁ።
በእጆቹ ናችሁ።
በጣም መልካም በሆኑ እጆች።
በሚያፈቅሩ እጆች፡
በሚንከባከቡ እጆች።
እናም ማንም ምንም ቢል ይህን ሊቀይረው አይችልም። ቃላቶቻቸው እግዚአብሔር ስለእናንተ ካለው ጋር ሲመዛዘኑ ትርጉም የሌላቸው ናቸው።
እናንተ የእርሱ ውድ ልጅ ናችሁ።
ይወዳችኋል።
ስትደናቀፉም፣ ከእርሱም ስትዞሩ፣ እግዚአብሔር ይወዳችኋል። የመጥፋት፣ ወይም የመተው፣ ወይም የመረዳት ስሜት ሲኖራችሁ—አትፍሩ። መልካሙ እረኛ ያገኛችኋል። በትከሻው ላይ ያደርጋችኋል። ወደቤትም ተሸክሞ ይወስዳችኋል።2
ውድ እህቶቼ፣ እነዚህ መለኮታዊ እውነቶች በልባችሁ እንዲዘልቁ አድርጉ። እናም ሀዘነኛ ላለመሆን ብዙ ምክንያቶች እንዳላችሁ ታገኛላችሁ፣ እናንተ ዘለአለማዊ እጣ ፈንታ አላችሁና።
ውዱ አዳኝ እናንተ ያን እጣ ፈንታ እውነተኛ ለማድረግ ለመምረጥ እንድትችሉ ህይወቱን ለአለም አሳልፎ ሰጥቷል። ስሙን በራሳችሁ ላይ ወስዳችኋል፤ እናንተም ደቀመዛሙርቱ ናችሁ። በእርሱም ምክንያት፣ ራሳችሁን በዘለአለማዊ ክብር ልብስ ለማጎናጸፍ ትችላላችሁ።
የምትጠላው
ሁለተኛዋ እህት በአለም ላይ የተናደደች ነች። እንደምታዝነው እህትም፣ በህይወቷ የሚደርሱት ችግሮች በሙሉ በሌላ ሰው የተፈጠሩ እንደሆኑ ይሰማታል። ቤተሰቧን፣ ጓደኛዎቿን፣ አለቃዋንና የስራ ጓደኞቿን፣ ፖሊስን፣ ጎረቤቶችን፣ የቤተክርስቲያን መሪዎችን፣ የአሁን የፋሽን ሁኔታን፣ የጸሀይ ነጸብራቅን፣ እና መጥፍ እድልን ትወቅሳለች። በእነርሱም ትቆጣለች።
ራሷን እንደ ክፉ ሰው አታስብም። በሚቃረን ሁኔታም፣ ለራሷ መብት እንደምትቆም ይሰማታል። ሁሉም ሰው ራስ ወዳድ በመሆን፣ በቅናት፣ እና በጥላቻ የሚነሳሱ ናቸው ብላ ታምናለች። እርሷ በሌላ አስተሳሰብ ግን በመልካም ሀሳብ—በፍትህ፣ በፅኑ አቋም፣ እና በፍቅር የምትነሳሳ ነች።
በሚያሳዝን ሁኔታ ግን፣ የምትናደደው እህት አስተሳሰብ ልዩ አይደለም። በሚወዳደሩ ቡድኖች ላይ በተደረገው በቅርብ ጥናት ይህም ተገኝቶ ነበር። በዚህ ጥናት ክፍል ውስጥ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ፈታሾቹ ፍልስጢማውያንንና እስራኤላውያንን እናም በዩናይትድ ስቴትስም ሪፐብሊካን እና ዴሞክራትን የቃል ጥያቄዎች አቀረቡላቸው። “እያንዳንዱም የራሳቸው ቡድን [ከሌላኛው በላይ በጥላቻ ሳይሆን በፍቅር የተነሳሱ የሆኑ እንደሚሰማቸው፣ ነገር ግን የሚወዳደሩት ቡድኖች ለምን እንደሚጣሉ ሲጠየቁ፣ [እነርሱም] ጥላቻ [ሌላኛውን] ቡድን እንደሚያነሳሳ እንዳመለከቱ”3 አግኝተዋል።
በሌላም አባባል፣ እያንዳንዱ ቡድን ራሳቸውን “እንደ ጥሩም ሰዎች”—ትክክለኛ፣ ደግ፣ እና እውነተኛ እንደሆኑ ያስባሉ። በሚነጻጸር ሁኔታም፣ የሚወዳደሯቸውን “እንደ መጥፎ ሰዎች”—መረጃ እንደሌላቸው፣ ውሸታም፣ እንዲሁም ክፉ እንደሆኑ ነው የሚያዩአቸው።
በተወለድኩበት አመት፣ አለም የሚያሳቅቅ ሀዘን በፈጠረ መጥፎ ጦርነት ተጥለቅልቃ ነበር። ይህም ጦርነት የተጀመረው በሀገሬ ሰዎች ነበር—አንዳንድ ቡድኖችን እንደ ክፉ በጠቆሙ እና ሌሎች እነርሱን እንዲጠሉ ባበረታቱ ሰዎች ነበር።
የማይወዷቸውን ዝም አስደረጉ። እነርሱን እንዲያፍሩ እና እንደ እርኩስ እንዲመለከቷቸው አደረጉ። እነዚህን ከራሳቸው በታች—እንዲሁም ሰው እንዳልሆኑ አይነት ተመለከቷቸው። አንድ ቡድን ሰዎችን ዝቅ የምታደርጉ ከሆናችሁ፣ በእነርሱ ላይ የምትሉትን እና በረብሻ የምታደርጉባቸውን ትክክል ነው ብላችሁ ታስባላችሁ።
በ20 መቶ አመት ውስጥ በጀርመን ውስጥ የደረሰውን ሳስብ እንዳንቀጠቅጥ ያደርገኛል።
ሰው ከእኛ ጋር ሲቃረን ወይም የማይግባባ ሲሆን፣ ከእነርሱ አንድ ትክክል ያልሆነ ነገር አለ ብለን ለማሰብ እንፈተናለን። እናም ከዚያ በቃላታቸው ወይም በስራቸው ላይ የክፉ መነሳሻ ለመያዝም ብዙ እርምጃ አይወስድም።
በእርግጥም፣ ትክክል ለሆነው ሁልጊዜም መቆም አለብን፣ እናም ድምጻችንን ለዚህ ምክንያት ከፍ ማድረግ የሚያስፈልገን ጊዜዎችም አሉ። ይህም ቢሆን፣ ይህን በበልባችን ውስጥ ንዴት ወይም ጥላቻ እያለ ስናደርግ—ሌሎችን ለመጉዳት፣ ለማሳፈር፣ ወይም ዝም ለማስደረግ ስንቆጣ—ይህን የምናደርገው በጻድቅነት እንደማይሆን ነው።
አዳኝ ምን አስተምሯል?
“እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ፣
“ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሟችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ።”4
ይህም የአዳኝ መንገድ ነው። ይህም የበዛ ንዴትን፣ ጥላቻን፣ መለያየትን፣ እና ጥብ በአለም ውስጥ የፈጠረውን ገደብ የምንሰብርበት የመጀመሪያ ደረጃ ነው።
“አዎን፣ ጠላቶቼን ለመውደድ ፈቃደኛ ነኝ—እነርሱ እንደዚህ ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆኑ” ትሉ ይሆናል።
ነገር ግን ያም ችግር ያለበት አይደለም፣ ነውን? ለራሳችን ደቀመዛሙርትነት ሀላፊነት አለን፣ እናም ይህም ሌሎች እኛን በሚይዙበት መንገድ ላይ ትንሽ ወይም ምንም ግንኙነት የለውም። እነርሱ የሚረዱን እና ልጋስ እንዲሆኑ ተስፋ አለን፣ ነገር ግን ለእነርሱ ያለን ፍቅር እነርሱ ለእኛ ካለው ስሜት ጋር የተገናኘ አይደለም።
ምናልባት ጠላቶቻችንን ለማፍቀር ያለን ጥረት ልባቸውን ያሰላስላል እናም ጥሩ ተፅዕኖ ያደርግላቸዋል። ምናልባት አይሆንም። ነገር ግን ያም ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል የምንወስንበትን አይቀይርም።
ስለዚህ፣ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት፣ ጠላቶቻችንን እናፈቅራለን።
ንዴትን ወይም ጥላቻን እናሸንፋለን።
ልባችንን ለእግዚአብሔር ልጆች ባለን ፍቅር እንሞላለን።
ሌሎችን ለመባረክ እና ለማገልገል እንደርሳለን—እነርሱ “[የሚጠሉን]፣ እና [የሚያሳድዱን]” ቢሆኑም።5
እውነተኛዋ ደቀ መዛሙርት
ሶስተኛዋ እህት እውነተኛዋ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርትን የምትወክል ነች። በጣም ከባድ የሆነውም አድርጋለች—በምትሳለቅበት እና ችግር ጊዜ እግዚአብሔርን አምናለች። በንቀት እና ተጠራጣሪነት ብትከበብም፣ እምነትና ተስፋን ጠበቀች። የእርሷ ጉዳይ ደስታ ያለው ሳይሆን፣ ግን እርሷ ደስተኛ ስለነበረች፣ በደስታ ኖረች።
ማንኛችንም ያለመቃረን በህይወት ጉዞ አንጓዝም። ብዙ ሀይሎች ሊስቡን እየሞከሩ፣ አስተያየታችንን ለታማኞች ቃል በተገቡት ግርማዊ ደስታዎች ላይ በማትኮር እንዴት ለመቆየት እንችላለን?
የዚህ መስል የሚገኘው ነቢይ ከብዙ ሺህ አመቶች በፊት ባለመው ህልም ውስጥ እንደሚገኝ አምናለሁ። የነቢዩ ስም ሌሂ ነው፣ እናም ህልሙ በውዱ እና በሚያስደንቀው በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የተመዘገበ ነው።
በህልሙ ውስጥ፣ ሌሂ ትልቅ ሜዳ አየ፣ እናም በዚህም ውስጥ ለመግለጽ ከባድ የሆነ ውብ የሚያስደንቅ ዛፍ ነበር። ደግሞም ወደ ዛፉ ብዙ የሰዎች ቡድን ሲሄዱ ተመለከተ። የዚህን ግርማዊ ፍሬ ለመቅመስ ፈልገዋል። ታላቅ ደስታ እና የሚቆይ ሰላም እንደሚሰጣቸው ተሰምቷቸውና አምነው ነበር።
ወደ ዛፉ የሚመራ ጠባብ መንገድ ነበር፣ እናም በመንገዱ ዳርቻም በመንገዳቸው እንዲቆዩ የሚረዳ የብረት በትር ነበር። ነገር ግን በዚያ ደግሞም መንገዱን እና ዛፉን የሚሰውር የጭለማ ጭጋግ ነበር። እና ምናልባት ከዚህም በላይ አደገኛ የሚሆኑ ታላቅ የሳቅ ድምጽ እና መሳለቂያዎች በቅርብ ከሚገኙ ትልቅ እና ሰፊ ግንቦች ይመጡ ነበር። በሚያስደነግጥ ሁኔታም፣ ማፌዣው ወደ ዛፉ የደረሱትን እና አስደናቂ ፍሬውን የቀመሱ አንዳንድ ሰዎች እፍረት ሊሰማቸው ጀመር እና ጠፍተው ሄዱ።።6
ምናልባት እነርሱ አንዴ ዛፉ በእውነትም ወብታማ ነው ብለው ያስቡበት የነበረውን ተጠራጠሩ። ምናልባት ያጋጠማቸውን ነገሮች እውነትነት መጠየቅ ጀመሩ።
ምናልባት ከዛፉ ከዞሩ፣ ህይወት ይቀልላል ብለው አስበው ይሆናል። ምናልባት በምንም አይሳለቁባቸውም ወይም አይስቁባቸውም ይሆናል።
እና በእርግጥም፣ የሚያሾፉባቸው ሰዎች ደስተኛ እና መልካም ጊዜ የሚያሳልፉ ይመስሉ ነበር። ስለዚህ፣ ምናልባት ዛፉን ትተው ከሄዱ በታላቅና ሰፉ ግንቦች ተሰብሳቢዎቹ ውስጥ ተቀባይነት እንደሚያገኙ እና ለፍርዳቸው፣ ለእውቀታቸው፣ እና ለዘመናዊነታቸው ይጨመጨብላቸው ይሆናል።
በመንገዱ ቆዩ
ውድ እህቶች፣ የብረት በትሩን በመያዝ ለመቆየት እና ወደ ደህንነት በፍጹም ውሳኔ ለመራመድ አስቸጋሪ እንደሆነ የምታገኙ ከሆናችሁ፤ በራስ የተማመኑ በሚመስሉት የሌሎች ሳቅ እና መሳለቅ እንድትነቃነቁ የሚያደርጋችሁ ከሆነ፤ መልስ ባልተሰጠው ጥያቄ ወይም ገና ባልተረዳችሁን ትምህርት የምትጨነቁ ከሆናችሁ፤ ተስፋ በመቁረጥ የምታዝኑ ከሆናችሁ፣ የሌሂን ህልም እንድታስታውሱ አበረታታችኋለሁ።
በመንገዱ ቆዩ!
የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የብረት በትር በምንም አትልቀቁ!
እናም በእግዚአብሔር ፍቅር የምትካፈሉትን እንድታፍሩበት ማንም ቢሞክር፣ እነዚህን አታድምጡ።
እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆናችሁ በምንም አትርሱ፤ የበረከቶች ሀብት በጎተራዎች ዋጥ አሉ፤ የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ ከተማራችሁ፣ ከእርሱ ጋር በዳግም ትኖራላችሁ!7
የአለም ምስጋና እና ተቀባይነት ቃል ኪዳኖች የማይታመን፣ እውነት ያልሆነ እና እርካታ የሌላቸው ናቸው። የእግዚአብሔር ቃል ኪዳኖች በአሁንም ይሁን በዘላለም እርግጠኛ፣ እውነት፣ እና በደስታ የሚሞሉ ናቸው።
ሀይማኖት እና እምነትን ከከፍተኛ እይታ እንድታስቡበት እጋብዛችኋለሁ። በታላቁና ሰፊ ግንብ ውስጥ የሚቀርበውስጦታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ፍሬ ጋር የሚመዛዘን አይደለም።
በእርግጥም፣ “ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።”8
ለራሴ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ የደቀ መዛሙርት መንገድ የደስታ መንገድ እንደሆነ ተምሬአለሁ። ይህም የደህንነት እና የሰላም መንገድ ነው። ይህም የእውነት መንገድ ነው።
በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እና ሀይል፣ ይህን ለራሳችሁ ለመማር እንደምትችሉ እመሰክራለሁ።
እስከዚያ ድረስ, መንገዱ ለእእናንተ አስቸጋሪ ከሆነ፣ በቤተክርስቲያኗ አስደናቂ ድርጅቶች ውስጥ መሳደጃ እና ጥንካሬ እንደምታገኙ ተስፋ አለኝ። እንዲሁም በመጀመሪያ ክፍል፣ በወጣት ሴቶች፣ እና በሴቶች መረዳጃ ማህበር ውስጥ። በመንገዱ ላይ ልበ ሙሉነታችሁን እና ወደፊት ለምትጓዙበት እምነት የምታሳድሱበት አቅጣጫዎች ናቸው። እነዚህም በዚያ መገኘት እንደሚገባችሁ ስሜት ለማግኘት የምትችሉባቸው እና ከእህቶቻችሁና ከሌሎች ደቀ መዛሙርቶች መበረታታትን የምትቀበሉባቸው የደህንነት ቤት ናቸው።
በመጀመሪያ ክፍል የምትማሩት ነገሮች በወጣት ሴቶች ውስጥ ለምትማሩት ተጨማሪ እውነቶች ያዘጋጃችኋል። በወጣት ሴቶች ክፍሎች ውስጥ የምትራመዱባቸው የደቀ መዛሙርትነት መንገድ ወደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር ጓደኝነት እና እህትነት ይመራሉ። በመንገዱ እያንዳንዱ እርምጃ፣ ለሌሎች ያላችሁን ፍቅር በእምነት፣ በርህራሄ ስራ፣ በልግስና፣ እና በአገልግሎትየማሳየት ተጨማሪ እድሎች ይሰጣችኋል።
የደቀመዛሙርትነት መንገድን መምረጥ ሊነገር ወደማይቻል ደስታ እና ወደ መለኮታዊ ፍጥረታችሁ መሟላት ይመራል።
ይህም ቀላል አይደለም። ከሁሉም በላይ መልካም የሆነ ያላችሁን ሁሉ፣ እንዲሁም እውቀታችሁን፣ ፈጣሪነታችሁን፣ እምነታችሁን፣ ታማኝነታችሁን፣ ጥንካሬአችሁን፣ ልበ ውሳኔአችሁን፣ እና ፍቅራችሁን ያስፈልግባችኋል። ነገር ግን አንድ ቀን ወደ ጥረቶቻችሁ ዞር ብላችሁ ታስቡበታላችሁ፣ እናም ጠንካራ ሆናችሁ በመቅረታችሁ፣ በማመናችሁ፣ ከመንገዱ ባለመውጣታችሁ ምን ያህል ምስጋና ይኖራችኋልና።
ወደፊት ግፉ
ስለህይወት እናንተ ለመቆጣጠር የማትችሏቸው ብዙ ነገሮች ይኖሩ ይሆናል። ነገር ግን በመጨረሻም፣ የምትደርሱበትን እና በመንገዳችሁ የሚያጋጥሟችሁን ብዙ ነገሮች ለመምረጥ ሀይል ይኖራችኋል። ችሎታችሁ ሳይሆን ግን ምርጫዎቻችሁ ናቸው በህይወታችሁ ልዩነት የሚያመጡት።9
ሁኔታዎቻችሁ እንድታዝኑ እንዲያደርጋችሁ ለመፍቀድ አትችሉም።
ሁኔታዎቻችሁ እንድትናደዱ እንዲያደርጋችሁ ለመፍቀድ አትችሉም።
የእግዚአብሔር ሴት ልጅ በመሆናችሁ ለመደሰት ትችላላችሁ። በእግዚአብሔር ጸጋ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ውስጥ ደስታን ለማግኘት ትችላላችሁ።
ደስተኛ ለመሆን ትችላላችሁ።
ልባችሁን ለእግዚአብሔር መጠን እና ገደብ ለሌለው መልካምነት በምስጋና እንድትሞሉ እገፋፋችኋለሁ። ውድ እህቶቼ፣ ይህን ማድረግ ትችላላችሁ! በነፍሴ ፍቅር በሙሉ ወደ ህይወት ዛፍ ወደፊት ለመግፋት እንድትመርጡ እጸልያለሁ። ድምጻችሁን ከፍ ለማድረግ እና ህይወታችሁን በድንቅ የምስጋና መዝሙር፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እና ቤተክርስቲያኑ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለአለም በሚያመጡት ድንቆች ለመደሰት እንድትመርጡ እጸልያለሁ።
የደቀ መዛሙርትነት እውነተኛ መዝሙር ደስ የማይል ወይም ለአንዳንድ ትንሽ ከፍ ያለ ይሆናል። ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሪ እንደዚህም ነበር።
ነገር ግን ለሰማይ አባታችን፣ እናም እርሱል ለሚያፈቅሩና ለሚያከብሩም፣ ይህም በጣም ውድ እና ውበታዊ መዝሙር ነው—ለእግዚአብሔር እና ለስዎች ግሩም እና የሚያነጻ የሚያድን ፍቅርና አገልግሎት መዝሙር ነው።10
በመንገዱ እንድትቆዩ እና በግርማዊው የደቀ መዛሙርትነት መንገድ ላይ በየቀኑ በደስታ በመራመድ እንደ እግዚአብሔር ሴት ልጅ ለማደግ ጥንካሬ እና ብርታት ታገኙ ዘንድ በረከቴን እንደ ጌታ ሐዋሪያ እሰጣችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።