እጅግ ታላቅ እና የተከብሩ ቃል ኪዳኖች
የሰማይ አባታችን ታላቁ የደስታ እቅድ ትምህርቶችን፣ ስርአቶችን፣ ቃል ኪዳኖች፣እናም የመለኮቱ ባህሪይ ተካፋዮች እንድንህን እንዲያስችሉን የሆኑትን እጅግ ታላቅ እና የተከብሩ ቃልኪዳኖችን ያካትታሉ።
እያንዳንዳችን በየቀኑ ከምንጋፈጣቸው ፈተናዎች ከሆኑት ታላቅ ፈተናዎች መካከል በጣም አስፈላጊ የሆኑት ዘላለማዊ የሆኑ ነገሮችን እስክንረሳ ድረስ የዚህ አለም ጭንቀቶቸ ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን እንዳይቆጣጠሩ አለመፍቀድ ነው።1 ባለን ብዙ ሀላፊነቶች እና እቅዶች ምክንያት ጠቃሚ ከሆኑ መንፈሳዊ ቅድሚያዎች ከማስታወስ እና ከማተኮር በቀላሉ ልንወጣ እንችላለን። አንዳንዴ የት እንድምንሄድ እና ለምን እንደምንሮጥ እስከማናውቅ ድረስ በጣም በፍጥነት ለመሮጥ እንሞክራለን።
ለኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ለሆንነው ለእኛ ሃዋሪያው ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ አስታወሰን፣ “የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፣ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠንስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።
“ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች: በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ቃልኪዳኖችን ሰጠን።”2
መልእክቴ የሚያተኩረው፣ በዚህ የሟቸነት ጉዞችን ላይ ወዴት እና ለምን እንደምጓዝና እውንተኛ አስታዋሾች ተብለው በጴጥሮስ በተገለጹት እጅግ ታላቅ እና የተከብሩ ቃልኪዳኖች ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ ነው። እንዲሁም የሰንበትን ቀን፣ ቅዱስ ቤተመቅድስን፣ እናም እነኚህን ጠቃሚ መንፈሳዊ ተስፋዎችን ለማስታወስ ስለሚረዱን ቤቶቻቸን አወራለሁ።
እነኚህን ጠቃሚ እውነታዎቸ በአንድ ላይ ሆነን ስናገናዝብ መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዳችንን እንዲያስተምረን በቅንነት እጸልያለሁ።
የእኛ መለኮታዊ ማንነት
የሰማይ አባታችን ታላቁ የደስታ እቅድ ትምህርቶችን፣ ስርአቶችን፣ ቃል ኪዳኖች፣እናም የመለኮቱ ባህሪይ ተካፋዮች እንድንህን እንዲያስችሉን የሆኑትን እጅግ ታላቅ እና የተከብሩ ቃልኪዳኖችን ያካትታሉ። የእሱ እቅድ የእኛን ዘላለማዊ ማንነት እናም ለመማር፣ ለመለወጥ፣ ለማደግ፣ እና በስተመጨረሻም ከእሱ ጋር ለዘላለም ለመኖር መከተል ያለብንን መንገድ ይገልጹልናል።
“በቤተሰብ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” ላይ እንደተብራራው፥
“የሰው ልጆች በሙሉ --ወንድና ሴቶች --በእግዚአብሔር አምሳል ነው የተፈጠሩት። እያንዳንዱም በሰማይ ወላጆች የተወደዱ የመንፈስ ሴት እና ወንድ ልጆች ናቸው፣ እናም ይህ ስለሆነም፣ እያንዳንዱ መለኮታዊ ተፈጥሮ እና ፍጻሜም አላቸው። …
“በቅድመ ምድራዊ ህይወት ውስጥ፣ የመንፈስ ወንድ እና ሴት ልጆች እግዚአብሔርን እንደ ዘላለማዊ አባታቸው ያውቁትም ያመልኩትም ነበር፣ እናም ልጆቹ ስጋዊ አካልን አግኝተው ምድራዊ አጋጣሚዎችን በማግኘት ወደ ፍጹምነት ለመሻሻል እና በመጨረሻም እርሱ ወይም እርሷ እንደ መለኮታዊ እጣቸው ዘላለማዊ ህይወትን ወራሽ እንዲሆኑ የሚያደርገውን አላማውን ተቀብለው ነበር።”3
የእሱን እቅድ መርሆዎች እናም የውድ ልጁን ምሳሌ ከተከተሉ፣ ትእዛዛትን ከጠበቁ፣ እናም በእምነት እስከመጨረሻው ከጸኑ፣ ከዚያም የአዳኝ የማዳን ጸጋ፣ ከዚያም “ከእግዚያብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ የሆነው ስጦታ፣ የዘላለም ህይወት ይኖራቸዋል”4 ብሎ እግዚያብሔር ለልጆቹ ቃል ገባ። ዘላለማዊ ህይወት የእጅግ ታላቅ እና የተከብሩ ቃልኪዳኖች የመጨረሻ ደረጃ ነው።
መንፈሳዊ ዳግመ ውልደት
ወደ ክብር እና በጎነተ የጌታን ጥሪን በፍቃድኝነት በመቀበል እጅግ ታላቅ እና የከበረ ቃልኪዳኖችን የበለጠ ሙሉ ለሙሉ እንረዳለን እና መለኮታዊ ባህሪን መካፈል እንጀምራለን። በጴጥሮስ እንደተገለጸው፣ ይህ ጥሪ የሚሟላው በአለም ካለው ክፋት ለማምለጥ ስንጥር ነው።
በታዛዥነት በአዳኝ እምነት ወደፊት ስንጓዝ፣ ከዚያም በቤዛነቱ ምክንያት እናም በመንፈስ ቅዱስ ሀይል “ታላቅ ለውጥ ለእኛ፣ ወይንም በልባችነ ውሰጥ በመመስረቱ፣ ከእንግዲህ ሃጢያትን ለመፈጸም ምንም ፍላጎት የለንም፣ ነገር ግን ያለማቋረጥ መልካምን መስራት እንጂ።”5 እኛ “በድጋሚ ተወልደናል፣ አዎን ከእግዚያብሔር ተወልደናል፣ ከስጋና ከወደቅንበት ሁኔታ ወደ ጻድቁ መንገድ ወደ እግዚያብሔር ተፈውሰናል።”6 “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”7
እንደዚህ አይነቱ ሙሉ ለውጥ በተፈጥሮ በፍጥነት የሚከሰት አይደልም ወይም ሁሉም በአንዴ አይሆንም። ልክ አዳኝ እንዳለው፣ “በሙላቱ በጸጋ ላይ ጸጋንም ተቀብለናል።”8 “እነሆም ጌታ እግዚያብሔር እንዲህ ይላል፥ ለሰው ልጆች በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በስርአት ላይ ስርአት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ እሰታቸዋለሁ፣ ትምህርቴን የሚሰሙ የተባረኩ ናቸው፣ እናም ምክሬን የሚያዳምጡ ጥበብን ይማራሉና።”9
ቀጣይነት ባለው የመንፍሳዊ ዳግም መወለድ ሂደት ውስጥ የክህነት ስርአቶች እና ቅዱስ ቃልኪዳኖች ጠቃሚ ናቸው፤ እንዲሁም በእነርሱ እግዚያብሔር እጅግ ታላቅ እና የከበረ ቃልኪዳኖችን እንድንቀበል የመረጠበት መንገዶች ናቸው። በብቁነት እና ቀጣይነት ባለው ማስታውስ የተቀበሉ ስርአቶች የእግዚያብሔርን መልካምነት ሀይል በህይወታችን ውስጥ መፍሰስ የሚያስችሉትን ሰማያዊ መንገዶቸ ይከፍታሉ። በጽናት የተከበሩ እና ሁሌም የታወሱ ቃል ኪዳኖች አላማና በሟችነት እና በዘላለምነት ያሉ በረከቶችን ማረጋገጫ ያዘጋጃሉ።
ለምሳሌ፣ እንደ እምነታችን መጠን አምላክ ሶስተኛ አባል የሆነውን የመንፈስ ቅዱስን ቋሚ አጋርነት10 በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት አማካኝነት ሁሌም የሀጢያታቸንን ስርየት መቀበል እና ማቆየት እንደምንችል፣11 በዚህ ምድር ስላምን መቀበል እንደምንችል፣12 አዳኝ የሞት እስርን ብጥሷል እናም መቃብርን ድል አእንዳደረገ፣13 እናም ቤተሰብ ለጊዜው እና ለዘላለም አብረው እንደሚኖሩ እግዚያብሔር ቃል ገብቶልናል።
በቀላሉ መረዳት እንደሚቻለው፣ የሰማይ አባት ለልጆቹ ያቀረበው እጅግ ታላቅ እና የከበሩ ቃልኪዳኖች በሙሉ መቆጠር አይችሉም ወይም በተሟላ መልኩ ሊገልጽ አይቻሉም። ይህ ቢሆንም አሁን ለእናንተ ያቀረብኩላችሁ ከፊል ቃል የተገቡ የበረከቶች ዝርዝር እያንዳንዳችንን በሙሉ “መገርም ሊያቆሙን፣”14 እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም “ወደታች ወድቀን እና አባትን እንድናመልክ”15 ሊያደርገን ይገባል።
ቃል ኪዳኖችን ማስታወስ
ፕሬዝዳንት ሎሬንዞ ስኖው እንዲህ አስጠነቀቁት “ታላቁን የህዎት አላማ፣ የሰማይ አባት ሟችነትን አንድንለብስ ወደዚ የላከበተን ምክንያት አንዲሁም የተጠራነበተን ቅዱሱን ጥሪ የመርሳት ታላቅ ችሎታ አለን። ሰለዚህ ጊዜአዊ ከሆኑ ነገሮች በላይ ከፍ በሎ ከመገኘት ይልቅ … ፣ ጊዜአዊ ነገሮችን አንድናሸነፍ ከሚያስችለን፣ አግዚአብሔር ለአቋቋመው መለኮታዊ እርዳታ እራሳችንን ባለማዘጋጀት ብዙውን ጊዜ ወደአለማዊ ነገር ዝቅ አንድንል እንፈቅዳለን።”16
የሠንበት ቀንና ቅዱስ ቤተመቅደስ ከዓለምና ከዓለም ርካሽ ነገሮች በላይ ከፍ ለማለት አንድያገዙን በእግዚአብሔር የተቋቋሙ ሁለቱ የመለኮታዊ እርዳታ ምንጮች ናቸው። ሲጀመር፣ ሰንበትን የመቀደስና ቤተመቅደስ የመግባት ዋነኛ አላማዎች የሚዛመዱ ግን የተለያዩ አንደሆኑ አናሰብ ይሆናል። በእኔ አምነት ግን አነዛ ሁለት አላማዎች አንድ ናቸው አናም በየቤታችን አንዲሁም በግል እኛን በመንፈስ ለማጠንከር አብረው ይሰራሉ።
ሰንበት
እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ከፈጠረ በኋላ በሰባተኛው ቀን አረፈ አናም እሱን ለማሰብ ይረዳ ዘንድ በየሳምንቱ አንድ ቀን የረፍት ቀን አንዲሆን አዘዘ።17 ሰንበት የእግዚአብሔር ሰዓት ነው፣ የተቀደሰ ሰዓት፣ የእሱን ታላቅና ወድ የሆኑ ቃል ክዳኖችን የምናስታውስበት፣ የምንቀበልበትናም እርሱን የምናመልክበት አንዲሆን ተብሎ የተለየ ሰዓት ነው።
በዚህ ዘመን ጌታ መመሪያ ሰጥቷል፥
“ከአለም ነገሮች ራስህን ንጹህ እና ነውር የሌለበት ለማድረግ ወደ ጸሎት ቤት ሂድ፣ እናም በቅዱስ ቀኔም ቅዱስ ስርዓቶችህን አቅርብ፤
“በእውነት ከስራህ እንድታርፍ እናም ለልዑልም አምልኮህን እንድትሰጥ ይህ ቀን ተሰጥቶሀልና።”18
ሰለዚህ፣ በሰንበት ቀንቃልኪዳን ስለመግባት፣ ሰለማስታወስና ስለማደስ በመማር እናም በስርአቶች ላይ በመሳተፍ በልጁ በክርስቶስ ስም የሰማይ አባትን አናመልካለን። በእሱ ቅዱስ ቀን፣ ሀሳቦቻችን፣ ድርጊቶቻን፣ እናም ባህሪያችን ለእሱ ያለንን ፍቅር የሚያሳዩ ለእግዚያብሔር የምንሰጠው ምልክቶች ናቸው።19
ተጨማሪው የሰንበት አላማ ራያችንን ከዓለማዊ ነገሮች ላይ አንስተን ወደ ዘላለማዊ በረከቶች ማድረግ ነው። ዚህ በተቀደሰ ሰዓት፣ በሥራ ከተወጠረው ህይወታችን መደበኛ ተግባራት ስንርቅ፣ ወድና ታላቅ የሆኑትን ቃል ኪዳኖቹን በመቀበልና በማስታወስ በ“ወደ እግዚአብሔር መመልከትና መኖር”20 እንችላለን እና በዚህም የመለኮታዊ ተፈጥሮን ተካፋይ እንሆናለን።
ቅዱሱ ቤተመቅደስ
ብቁ የሆኑ ቅዱሳን ለራሳቸውና ለሙታን የተቀደሰ የወንጌል ስነስራትና ስርዓቶች የሚያደርጉበት ቅዱስ ቦታ በተመቅደስን አንዲገነቡ ሁልጊዜ ጌታ ሕዝቡን አዟል። ቤተመቅደሶች ከሁሉም የማምለኪያ ቦታዎች የተቀደሱ ናቸው። ቤተመቅደስ የጌታ ቤት፣ የእሱን ወድና ታላቅ ቃልኪዳኞች የምንቀበልበትና የምናስታውስበት አንዲሁም እግዚአብሔርን ለማምለክ ተብሎ የተለየ የተቀደሰ ስፍራ ነው።
በዚህ ዘመን ጌታ መመሪያ እንደሰጠው፣ “ራሳችሁን አደራጁ፤ አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ አዘጋጁ፤ ቤትን፣ እንዲሁም የጸሎትን ቤት፣ የጾምን ቤት፣ የእምነትን ቤት፣ የእውቀትን ቤት፣ የክብርን ቤት፣ የስርዓትን ቤት፣ የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ፤”21 ዋናው የቤተመቅደስ አምልኮ ትኩረት ቃልኪዳኞችን ስለመቀበልና ማስታወስ መማርና በስርዓቶች ላይ ማሳተፍ ነው። በቤተመቅደስ ውስጥ አስተሳሰባችን፣ ድርጊታችን እንዲሁም አለባበሳችን ከሌላ ከምናዘወትራቸው ቦታዎች ይለያል።
ዋነኛው የቤተመቅደስ አላማ ራእያችንን ከዓለማዊ ነገሮች ላይ አንስተን ወደ ዘላለማዊ በረከቶች ማድረግ ነው። ከለመድነው አለማዊ ሁኔታ ለአጭር ሰዓት ስንወገድ፣ ውድና ታላቅ የሆኑትን ቃልኪዳኖቹን በመቀበልና በማስታወስ “ወደ እግዚአብሔር በመመልከትና በመኖር”22 የመለኮታዊ ተፈጥሮን ተካፋይ አንሆናለን።
ሰንበት ቀን እና ቤተመቅደስ እግዚአብሔርን ለማምለክ እና የእርሱን ታላቅና ውድ ቃል ኪዳኖች ለመቀበል እና ለማስታወስ በልዩ የተመደቡ ቅዱስ ሰዓት እና ቅዱስ ቦታ እንደሆኑ እናስታውስ። በእግዚአብሔር እንደተቋቋሙ፣ ዋናው የእነዚህ መለኮታዊ የእርዳታ ምንጮች አላማ አንድ ነው። ያም፣ ትኩረታችን ኃይል በተሞላና በተደጋገመ መልኩ በሰማይ አባት፣ በአንድያ ልጁ፣ በመንፈስ ቅዱስና በተመለሰው የአዳኝ ወንጌል ሰርአቶችና ቃልኪዳኞች ጋራ በተያያዙት ቃልኪዳኞች ላይ እንድናደርግ ነው።
ቤቶቻችን
ቤት ቤተሰቦዎች እጅግ በተዋጣለት መንገድ የእግዚአብሔርን ታላቅና ውድ ቃልኪዳኞች የሚያስታውሱበት የተሻለ የጊዜና ስፍራ ጥምር መሆን አለበት። የሰንበት ጉባዬዎችን ለመካፈል አንዲሁም በተቀደሰው የቤተመቅደስ ስፍራ ለመግባት ቤታችንን ጥላን መሄዳችን አስፈላጊ ነው ግን በቂ አይደለም። ከነዚያ ከተቀደሱ ስራዎች ያገኘነውን መንፈስና ጥንካሬ ወደቤታችን ይዘን ስንመለስ ብቻ የምድራዊ ህይወታችን አላማ ላይ ትኩረት ማድረጋችንን የምንቀትለው አናም በዚህ ዓለም ውስጥ ያለን ርካሽ ነገር ምናሸንፈው። የሰንበትና የቤተመቅደስ ተሞከሮዎቻችን፣ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ቃልኪዳኞች ላይ “ፍፁም በሆነ የተስፋ ብረሃን፣”23 እና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ቀጣይነት በነበረው ጥልቅ ውይይት መንፈስ ቅዱስ በተገኘበት አና የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በነበረበት የተማርናቸውን ትምህርቶች በግል አና በቤተሰብ አና በቤቶቻችን ቀጣይነት ባለው መንገድ አንደናስታውስ የሚሞሉን መንፈሳዊ መንገዶች መሆን አለባቸው።
የሰንበት ቀንና ቤተመቅደስ በቤታችን ውስጥ “እጀግ በጣም ጥሩ የሆነ መንገድ”24 እንድናበጅ ሊያግዙን ይችላሉ አኛ “በክርስቶስ ያሉትን ነገሮች ሁሉ፣ በሰማይና በምድር ያሉትን፣ በሱ ውስጥ ያሉትን ጭምር በአንድ ስንሰበስብ”25 በእሱ ቅዱስ ስፍራ በተማርናቸው ትመህርቶች ላይ ተመስርተን በእሱ ቅዱስ ሰዓት በቤታችን ውስጥ የምንሰራው ስራ ለመለኮታዊ ተፈጥሮ ተካፋይ አንድንሆን አስፈላጊ ነው።
ቃል ኪዳን እና ምስክርነት
መደበኛ በሆነ የለት ተለት የምድራዊ ነገሮች በቀላሉ ልንሸነፍ እንችላለን። መተኛት፣ መብላት፣ መልበስ፣ መስራት፣ መጫወት፣ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ አናም ብዙ ዘልማዳው የሆኑ ድርጊቶች አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው። ነገር ግን በመጨረሻ የምንደርስበት ደረጃ የእውቀታችን አና ከሰማይ አባት፣ ከልጁና ከመንፈስ ቅዱስ ለመማር ያለን ፍቃደኝነት ውጤት ነው። በህይወት ዘመናችን የመናደርጋቸው ነገሮች ብቻ ውጤት አይደለንም።
ወንጌል በመደጋገም ከምንሰራቸው የተለያዩ ስራዎች ዝርዝር በላይ አጅግ ይለያል፤ እንዲያውም “ያማረ”26 የእውነት ሸማ ነው፣ እናም በልክ የተሰራ አና አንድላይ የተሸመ፣ አንደሰማይ አባት እና አንደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆን አንዲሁም የመለኮታዊ ተፈጥሮ ተካፋይ መሆን እንድንችል ሊረዳን የተቀመረ ነው። ይህ ዋናው መንፈሳዊ እውነታ በአለም ሀሳብ፣ ጭንቀት እና ነገሮችን ቀለል በማድረግ ሲሸፈን፣ በእውነት፣ ከምልክቱ ባሻገር27 እየተመለከትን ታውረና።
ብልህ ስንሆን እና መንፈስ ቅዱስን መሪያችን እንዲሆን ስንጋብዝ፣28 እውነተኛ የሆነውን እንድሚያስተምረን ቃል እገባለሁ። የዘላለም መድረሻችን ለሟሟላት ስንጥር እና የመለኮታዊው ባህሪይ ተካፋዮች ስንሆን፣ ‘‘ስለ ክርስቶስ ይመሰክርልናል፣[እናም] በሰማያዊ ምልከታ አእምሮአችንን ያበራልናል”29።
ከስርአቶቻችን እና ከቃልኪዳኖቻችን ጋር የተያያዙት እጅግ ታላቅ እና የተከበሩ ቃልኪዳኖች እውነት እንደሆኑ እመሰክራለሁ። ጌታ እንደዚህ አውጇል፥
‘‘ወይም፣ በሌላ አባባል፣ ለደህንነታችሁ ይሆንላችሁ ዘንድ፣ በፊቴ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።
እኔ ጌታ የምለውን ስታደርጉ በቃሌ እታሰራለሁ፤ ነገር ግን የምለውን ባታደርጉ፣ የተስፋ ቃል የላችሁም።”30
የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር ሕያው አንደሆነና የደህንነት ፀሐፊ አንደሆነ እመሰክራለው። ኢየሱስ ክርስቶስ አንድያ ልጁ፣ አዳኛችንና መድኃኒታችን ነው። ሕያው ነው። ህያው ነው። የአባታችን አቅድና ቃልኪዳን፣ ያዳኛችን ቤዛነት አና የመንፈስ ቅዱስ አጋርነት በዚህ ዓለም ሰላም በሚቀጥለው ዓለም ዘላለማዊ ሕይወት እንድናገኝ አንደሚያስችለን አመሰክራለው።31 ስለነዚህ ነገሮች ቅዱስ በሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለው አሜን።