የጌታን እና የቤተሰባችሁን አመኔታ ማግኘት
“የሀቀኝነት ልብ” ያላቸው ሰዎች የሚታመኑ ሰዎች ናቸው - ምክንያቱም መታመን የሚገነባው በሀቀኝነት ላይ ነው።
ወንድሞች፣ ብቁ የክህነት ተሸካሚዎች እና ታላቅ ባሎች እና ኣባቶችን እንድንሆን ጌታ እንደሚያምነን ከማወቅ በላይ የምንቀበለው ሌላ ታላቅ ሙገሳ የለም።
አንድ ነገር እርግጥ ነው፤ የጌታን አመኔታ የማግኘት በረከት የሚመጣው በእኛ በኩል ባለ ታላቅ ጥረት ነው። መታመን ለእግዚአብሔር ትእዛዛት በመታዘዝ ላይ የተመሰረተ በረከት ነው። የጌታን አመኔታ ማግኘት የሚመጣው በጥምቀት ውሃ ውስጥ እና በቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ ለገባናቸው ቃልኪዳኖች ታማኝ ከመሆን ነው። ለጌታ ቃልኪዳናችንን ስንጠብቅ፣ ለኛ ያለው አመኔታ ይጨምራል።
የፃዲቅ ሰውን ባህሪይ ሲገልፁ “የሀቀኝነት ልብ” የሚለውን ሀረግ የሚጠቀሙ የጥንት እንዲሁም የአሁን ጊዜ ቅዱስ መፃህፍትን እወዳለሁ።1 ሀቀኝነት ወይም የሀቀኝነት መጉደል የአንድ ሰው ባህሪ ወሳኝ ክፍል ነው። “የሀቀኝነት ልብ” ያላቸው ሰዎች የሚታመኑ ሰዎች ናቸው - ምክንያቱም መታመን የሚገነባው በሀቀኝነት ላይ ነው።
የሀቀኝነት ሰው መሆን በቀላሉ ሰው ባለበት እና በግልም በሀሳብ እንዲሁም በተግባር በሁሉም የህይወታችሁ አቅጣጫዎች ንፁህ እና ቅዱስ መሆን ማለት ነው። በምናደርጋቸው እያንዳነዱ ውሳኔዎች፣ የእግዚአብሔርን አመኔታ ወይ የበለጠ እናሳድጋለን ወይም ደግሞ የእርሱን አመኔታውን እንቀንሳለን። ይሄ መርህ በይበልጥ ጎልቶ የሚገለጠው እንደ ባሎች እና አባቶች በተሰጡን መለኮታዊ ሀላፊነቶች ላይ ነው።
እደ ባሎች እና አባቶች፣ ከአሁን ጊዜ ነብያት፣ ትንቢተኞች፣ እና ገላጮች በ“ቤተሰብ፤ ለአለም አዋጅ” በሚለው መዝገብ መለኮታዊ ሀላፊነትን ተቀብለናል። ይህም መዝገብ (1) “አባቶች ቤተሰባቸውን በፍቅር እና በጻድቅነት ይመራሉ፣” (2) አባቶች “በህይወት አስፈላጊዎችን ለማስገኘት ሀላፊነት አለባቸው፣” እናም (3) አባቶች ቤተሰቦቻቸውን የመጠበቅ ሀላፊነት አለባቸው የሚሉትን ያስተምሩናል።2
እኛ የእግዚአብሔርን አመኔታ ለማግኘት፣ ለቤተሰቦቻችን የተሰጡንን እነዚህን ሶስት መለኮታዊ ሀላፊነቶች በጌታ መንገድ ማሟላት ይኖርብናል። በቤተሰብ አዋጅ ላይ ጨምሮ እንደተገለፀው፣ የጌታ መንገድ እነዚህን ሀላፊነቶች ከሚስታችን ጋር በጋራ “እንደ እኩል አጋሮች”3 በመሆን መወጣት ነው። ለእኔ፣ ከሚስታችን ጋር በአንድነት ካልሆነ በቀር እነዚህን ሶስት ሀላፊነቶች በተመለከተ ምንም አስፈላጊ ውሳኔን በመወሰን አለመጓዝ ማለት ነው።
የጌታን አመኔታ የማግኘት የመጀመሪያው ደረጃ የእኛን እምነት በእርሱ ላይ ማድረግ ነው። ነብዩ ኔፊ ይህን አይነቱን ቁርጠኝነት በፀሎቱ እንዲህ መስሎታል፥ “አቤቱ ጌታ፣ በአንተ ታምኛለሁ፣ እንዲሁም ለዘለአለም በአንተ እታመናለሁ። እምነቴን በስጋ ክንድ ላይ አላደርግም።”4 ኔፊ የጌታን ፍቃድ ለማድረግ ሙሉ ለሙሉ ቁርጠኛ ነበር። “ጌታ ያዘዘኝን ነገሮች አደርጋለሁ” ከማለቱ በተጨማሪም፣ ኔፊ የተሰጠውን ስራ ሲያሟላ አላመነታም ነበር፣ በዚህ አርፈተ ነገር ገልፆታል፥ “ጌታ ህያው እንደሆነ፣ እኛም እስካለን ድረስ ጌታ ያዘዘንን ሳናከናውን ወደአባታችን ወደ ምድረ በዳ አንመለስም።”5
ምክንያቱም ኔፊ ቅድምያ በእግዚአብሔር ላይ ስለታመነ፣ እግዚአብሔር በኔፊ ላይ ታላቅ አመኔታን አደረገ። ህይወቱን፣ የቤተሰቦቹን ህይወቶች፣ እናም የህዝቦቹን ህይወቶች በባረከ ታላቅ የመንፈስ ቅዱስ መትረፍረፍ ጌታ ባረከው። ኔፊ በፍቅር እና በቅድስና ሰለመራ እና ለቤተሰቡ እና ለህዝቦቹ ስላሟላ እና ጥበቃን ስላደረገ፣ እንዲህ ብሎ መዘገበ፣ “አስደሳች ህይወት ኖርን።”6
በዚህ እርስ ላይ የሴትን አመለካከት ለመወከል፣ ሁለት ያገቡ ሴት ልጆቼ እንዲያግዙኝ ጠየኳቸው። ትዳራቸው እና ቤተሰባቸው ላይ ባለው ተፅእኖ የመታመን አስፈላጊነትን እንዴት እንደሚመለከቱት አንድ ወይም ሁለት አርፍተ ነገሮችን እንዲየቀርቡ ጠየኳቸው። የላራ ሀሪሰን እና የክርስቲና ሀንሰን ሀሳቦች እነዚህ ናቸው።
በመጀመሪያ፣ ላራ፤ “ለእኔ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች አንዱ ባለቤቴ በቀን ድርጊቶቹ፣ ለእኔ አክብሮት እና ፍቅር እንዳለው የሚያሳዩ ምርጫዎችን እንደሚያደርግ ማወቅ ነው። በእዚህ መልኩ እርስ በእርሳችን መተማመን ስንችል፣ ሰላምን በቤታችን ያመጣል፣ በጋራ ቤተሰባችንን በማሳደግ መደሰት የምንችልበት ይሆናለ።”
አሁን የክርስቲና ሀሳቦች፤ “በአንድ ሰው ላይ መተማመን በአንደ ሰው ላይ እምነትን ከማድረግ ጋር ተመሳሳይ ነው። ያለዛ መተማመን እና እምነት፣ ፍራቻ እና ጥርጣሬ ይኖራል። ለእኔ፣ በባለቤቴ ላይ ሙሉ ለሙሉ መታመን በመቻሌ ከሚመጡት ታላቅ በረከቶች አንዱ ሰላም ነው--- አደርጋለው ያለውን ነገር እንደሚያደርግ ከማወቅ የሚመጣ የአእምሮ ሰላም። መታመን ሰላምን፣ ፍቅርን፣ እና ያ ፍቅር የሚያድግበትን አከባቢ ያመጣል።”
ላራ እና ክርስቲና ሌላኛዋ የጻፈችውን አላዩም። ሊያምኑት የሚችሉት ባለቤት ሲኖራቸው የሚመጣው ቀጥተኛ ውጤት የቤት ውስጥ ሰላም በረከት እንደሆነ በተናጠል ማሰባቸው ለእኔ አስደሳች ነው። በሴት ልጆቼ ምሳሌ እንደተገለፀው፣ ክርስቶስን ያማከለ ቤት በመገንባት ውስጥ የመታመን መርህ እጅግ በጣም አስፈላጊ ሚናን ይጫወታል።
እያደኩ ባለሁበት ወቅት አባቴ ክህነቱን በማክበር እና “በሀቀኛ ልቡ” የተነሳ የሙሉ ቤተሰቡን አመኔታ ባገኘበት ተመሳሳይ ክርስቶስን ያማከለ ባህል ውስጥ ለመሆን ችዬ ነበር።7 በሀቀኝነት ላይ የተገነባ የመታመን መርህ በቤተሰቡ ላይ የሚኖረውን የማያልቅ አውንታዊ ተፅእኖን የተረዳ እና የሚኖር አባትን የሚያሳይ ከወጣትነት ተሞክሮዬ ላካፍላችሁ።
በጣም ወጣት ሳለሁ፣ አባቴ ማሽን በማምረት ላይ ያተኮረ ድርጅትን አቋቋመ። ይሄ ንግድ በመላው አለም ያሉ የማሽን ምርት ሂደቶችን በምህንድስና መስራት፣ ማምረት፣ እና መጫን ነበር።
በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ሳለሁ፣ አባቴ እንዴት ስራ እንደሚሰራ እንድማር ፈለገ። ንግዱን ከታች እስከላይ እንድማርም ፈለገ። የመጀመሪያው ስራዬ በተጨማሪም ሜዳውን መንከባከብ እና ሰዎች የማያዩአቸውን ቦታዎች በወቀለም መቀባት ነበር።
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ስገባ፣ በማምረቻ ወለል ላይ እንድሰራ እድገት አገኘሁ። ንድፎችን ማንበብ እና ከባድ የብረት ምርት ማሽኖች ላይ መስራትን መማር ጀመርኩ። ከሁለተኛ ደረጃ ምርቃቴ በኋላ፣ ዩኒቨርስቲ ገባሁ እና ከዛ ወደ ሚስኦን መስክ ገባሁ። ከሚስኦኔ ወደቤት ስመለስ፣ ቀጥታ ወደስራ ተመለስኩ። ለቀጣዩ አመት ትምህርት ወጪ ገንዘብ ማግኘት ነበረብኝ።
ከሚስኦን ከመመለሴ ብዙም ሳይቆይ አንድ ቀን፣ በማምረቻው እየሰራሁ ሳለሁ ነበር ኣባቴ ወደ ቢሮው የጠራኝ እና ከእርሱ ጋር ለንግድ ጉዞ ወደ ሎሳንጀለስ ለመሄድ እንደምፈልግ ጠየቀኝ። ለንግድ ጉዞ አብሬው እንድሄድ አባቴ ሲጋብዘኝ ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። በህዝብ ፊት ድርጅቱን በመወከል እንድረዳ እያደረገኝ ነበር።
ወደ ጉዞው ከመሄዳችን በፊት፣ ደንበኛው ሊሆን ሰለሚችል ድርጅት አንዳንድ መረጃዎችን በመስጠት አዘጋጀኝ። መጀመሪያ፣ ይሄ ደንበኛ የብዙ ሀገራት ማህበር ያለው ነው። ሁለተኛ፣ የምርት ሂደታቸውን በመላው አለም በአዲስ የቴክኖሎጂ ማሽኖች እያዋቃሩ ነበር። ሶስተኛ፣ የእኛ ድርጅት ከዚህ በፊት በምህንድስና ወይም በቴክኖሎጂ በፍፁም አቅርቦት አላደረገም። እና በመጨረሻም፣ ዋና የማህበሩ መኮንን ነበር በአዲስ የስራ እቅድ ላይ ያለንን የዋጋ ተመን ለመወያየት ይህን ስብሰባ የጠራው። ይሄ ስብሰባ አዲስ እና ምናልባትም አስፈላጊ እድልን ለድርጅታችን የሚወክል ነበር።
በሎሳንጀለስ ከደረስን በኋላ፣ እኔ እና አባቴ ለስብሰባው ወደ ስራ አስፈፃሚው ሆቴል ሄድን። የቀዳሚ የስራ ሂደቱ የስራ እቅዱ የምህንድስና መዋቅርን መወያየት እና መመርመር ነበር። ቀጣዩ ውይይት የአዘገጃጀት ሂደትን፣ የክምችት እና አጉዞ የማድረሻ ቀናትን የሚመለከት ነበር። የመጨረሻው የውይይት ነጥብ ያተኮረው ዋጋ፣ የስምምነተ ነጥቦች፣ እና ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ነበር። እዚህ ጋር ነበር ነገሮች ሳቢ የሆኑት።
ይሄ የማህበር መኮንኑ የእኛ የዋጋ ተመን በስራ እቅዱ ላይ ከተጫረቱት ዝቅተኛ እንደሆነ አብራራልን። ከዛ እርሱ፣ በመጓጓት፣ የቀጣዩን ዝቅተኛ ተጫራች ዋጋ ነገረን። ከዛም እቅዳችንን መልሰን ወስደን ዳግም ለማስገባት ፍቃደኛ እንደምንሆን ጠየቀን። አዲሱ ዋጋችን ከቀጣዩ ከፍተኛ ዋጋ ጨረታ በትንሽ እንዲያንስ ተናገረ። እና አዲስ የተጨመረውን ገንዘብ እኩል ለእኩል እደምንካፈል አብራራ። ሁሉም እንደሚጠቀም በመናገር ምክንያት አቀረበ። የእኛ ድርጅት ይጠቀማል ምክንያቱም መጀመሪያ ካቀረብነው የጨረታ ዋጋ የበለጠ ገንዘብ እናገኛለን። የእርሱ ድርጅት ይጠቀማል ምክንያቱም ስራው የሚያደርጉት ከዝቅተኛው ተጫራች ጋር ነው። እና፣ በእርግጥም፣ እርሱ ይተቀማል ምክንያቱም ይሄን ታላቅ ስምምነት ስላቀናበረ የድርሻውን ይወስዳል።
ከዛ እርሱ የጠየቀውን ገንዘብ የምንልክበትን የፖስታ ሳጥን ቁጥር ሰጠን። ከዚህ ሁሉ በኋላ፣ ወደ አባቴ ተመለከተና ጠየቀ፣ “ስለዚህ፣ ስምምነት አለን?” ለእኔ መደነቅ፣ አባቴ ተነሳ፣ እጁን ጨበጠው፣ እና መልሰን እንደምናናግረው ነገረው።
ከስብሰባው ከሄድን በኋላ፣ በኪራይ መኪና ውስጥ ገባን፣ እና ኣባቴ ወደ እኔ ዞረ እና ጠየቀ፣ “እንግዲ፣ ምን እናድርግ ብለህ ታስባለህ?”
ይህን መቀበል እንዳለብን እንደማላስብ መልሼ ነገርኩት።
ከዛ አባቴ ጠየቀ፣ “ሁሉም ሰራተኞቻችን መልካም የስራ ሂደትን እንዲጠብቁ ለማድረግ ሀላፊነት እንዳለብን አታስብም?”
በጥያቄው ላይ እያሰላሰልኩ ሳለሁ እና መመለስ ከመቻሌ በፊት፣ የእራሱን ጥያቄ እራሱ መለሰ። እንዲህ አለ፣ “ስማ፣ ሪክ፣ አንዴ ሙስና ከተቀበልክ ወይም ሀቀኝነትህን ካጋለጥቅ በኋላ፣ ዳግም ማግኘቱ በጣም ከባድ ነው። መቼም አታድርገው፣ አንዴም እንኳን ቢሆን።”
ይሄን ተሞክሮ ማካፈሌ አባቴ ከእርሱ ጋር በነበረኝ በዚያ የመጀመሪያ የስራ ጉዞ ላይ ያስተማረኝን መቼም አልረሳሁትም ማለት ነው። ይሄን ተሞክሮ የማካፍለው እንደ ኣባቶች ያለንን የማያልቅ ተፅእኖ ለማብራራት ነው። በነበረው የልብ ሀቀኝነት አማካኝነት በአባቴ ላይ የነበረኝን አመኔታ መገመት ትችላላችሁ። ይሄንኑ መርህ በግል ህይወቱም ከእናቴ፣ ከልጆቹ፣ እና ከሚገናኛቸው ሰዎች ሁሉ ጋር ይኖረዋል።
ወንድሞች፣ ኔፊ በምሳሌ እንዳስቀመጠው፣ ሁላችንም እምነታችንን በጌታ ላይ እንድናደርግ፣ እና ከዛም ከልብ ሀቀኝነታችን የተነሳ የጌታን አመኔታ እንዲሁም የሚስቶቻችንን እና የልጆቻችንን አመኔታ እንድናገኝ በዚህ ምሽት ፀሎቴ ነው። ይሄ በሀቀኝነት ላይ የተገነባውን አመኔታ መርህ ስንረዳ እና ስንተገብር፣ ለቃልኪዳኖቻችን እውነተኞች እንሆናለን። በቤተሰባችን ላይ በፍቅር እና በቅድስና በመመራት፣ ለህይወት የሚስፈልጉትን በማሟላት፣ እና ቤተሰቦቻችንን ከአለም ክፋቶች በመጠበቁም ስኬታማ እንሆናለን። እነኚህን እውነቶች በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለሁ፣ አሜን።