2010–2019 (እ.አ.አ)
ጌታ፣ አይኖቼ ይከፈቱ ዘንድ ታደርጋለህን
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


2:3

ጌታ፣ አይኖቼ ይከፈቱ ዘንድ ታደርጋለህን

ሌሎችን በኣዳኛችን አይኖች ማየት አለብን።

ላየን ኪንግ የተባለው የቅንብር ፊልም ስለአፈሪካ ሳራማ አካባቢ የሚያሳይ ፊልም ነው። የአንበሳ ንጉስ ልጁን በማዳን ሲሞት፣ ወጣቱ አንበሳ ልዑል በሳራማ አካባቢው ውስጥ የነበረውን ስምምንት በሚመጠብጥ በክፉ መሪ ተሰድዶ ነበር። የአንበሳው ልዑል በአስተማሪው እርዳታ መንግስቱን እንደገና ለማግኘት ችሏል። በሳራማ አካባቢው ውስጥ በሚገኘው የህይወት ክብ ውስጥ ስለስምምነት አስፈላጊነት ተምሯል። የንጉስነት ሀላፊነቱን በመውሰድ፣ ትንሹ አንበሳ “ከሚያታየው ባሻገር እንዲመለከት”1 ምክርን ተቀበለ።

አባታችን ያለውን ሁሉ ተረካቢ ለመሆን ለመማር፣ ወንጌል ከምናየው ባሻገረ እንድንመለከት ይመክሩናል። ከምናየው ባሻገር ለመመልከት፣ ሌሎችን በኣዳኛችን አይኖች ማየት አለብን። የወንጌሉ መረብ ሁሉንም አይነት ሰዎች በማካተት እረጅም ነው። በዓለማችን፣ በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች እንዲሁም በቤተሰባችን ውስጥ ያሉ ሰዎችን ምራጫዎችና የአስተሳብ መንስኤዎች ሙሉ በሙሉ መረዳት አንችልም ምክንያቱም የማንነታቸውን መግለጫ ሙሉ ምስል ስለሌለን። ቀላል ከሆነ አስተሳሰብ እና እውነታ ላይ ያልተመረኮዘ አመለካከት ባሻገር መመልከት አለብን እንዲሁም የራሳችንን የጠበበ ማጉሊያ መነፅር ልምድ ማስፋት አለብን።

እንደ ሚስዮን ፕሬዘዳንት ሆኜ ሳገለግል፣ ከማየው ነገር ባሻገር ለማየት አይኖቼን ከፍቼ ነበር። አንድ ወጣት ሚስዮን በአይኖቹ ላይ ፍርሃት ተሞልቶ መጣ። በቃለ መጠይቅ ጊዜ ስንገናኝ፣ ወደ ቤት መሄድ እፈልጋለሁ በማለት በማዘን ተናገረ። እሺ፣ ይህን ማስተካከል እንችላለን በማለት ለራሴ አሰብኩኝ። ለሳምንት ጠንክሮ እንዲሰራና ስለዚህ ጉዳይ ከፀለየ በኋላ እንዲደውልኝ መከርኩት። ከሳምንት በኋላ፣ ልክ በሰዓቱ ደወለ። አሁንም ወደ ቤት መሄድ ፈለገ። እንደገና እንዲጸልይ፣ ጠንክሮ እንዲሰራ እና ከሳምንት በኋላ ስልክ እንዲደውልልኝ መከርኩት። በቀጣዩ ቃለ መጥይቃችን ጊዜ ነገሮች አልተቀየሩም ነበር። ወደ ቤት መሄዱ ላይ አተኮረ።

ይህ እንዲሆን አልፈቅድም ነበር። ስለጥሪው ቅድስና እርሱን ማስተማር ጀመርኩኝ። ራሱንም “እንዲረሳ እና ወደ ስራ እንዲሄድ”2 አበረታታሁት። ነገር ግን ምንም አስተያየት ባቀርብለትም፣ አዕምሮውን አልቀየረም። በመጨረሻ የምስሉ ሙሉ ገፅታ እንደሌለኝ ተገለጠልኝ። ከዛ በኋላ ነው ይህን ጥያቄ ለመጠየቅ የተገፋፋሁት፤ “ሚስዮን ሆይ፣ ምንድን ነው የከበደህ?” ያለው ልቤን ነካው። “ፕሬዘዳንት ማንበብ አልችልም።”

ለእሱ በጣም ጠቃሚ ይሆናል ብዬ የገመትኩት ጥበበኛ ምክር ለፍላጎቱ ምንም ጠቀሜታ አልነበረውም። ይፈልግ የነበረው ከዛ የበለጠ ነገር እኔ ከመጥፎ ከሆነው ግምገማ ባሻገር መመልከትን እና በዚህ ሚስዮን አዕምሮ ውስጥ ያለውን ነገር እንድረዳ ለመንፈስ ቅዱስ መፍቅድ ነበር። በትክክል እንዳየውና ተስፋ ለማድረግ ምክንያት እንድሰጠው ነበር የሚፈልገኝ። በተቃራኒው፣ እንደ ታላቅ የማፍረሻ ኳስ ተገበርኩኝ። ይህ ተዋጊ ሚስዮን ማንበብን በእርግጥ ማንበብን ብ ተማረ እናም የኢየሱስ ክርስቶስ ንፁህ ደቀ መዝሙር ሆነ። እንደዚህ ለሚለው ለጌታ ቃሎች ዓይኖቼን ከፈተው፤ “ሰው ፊትን ያያል፣ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” (1 ሳሙአል 16፥7)።

የጌታ መንፈስ እይታችንን ሲያስፋፋ ምን አይነት በረከት ነው። ከእንቅልፉ ሲነሳ የሶሪያ ወታደሮች ከተማውን በፈረስና በሰረገላ የከበቡትን ነብይ ኤልሳዕምን ታስታውሳላችሁን? አገልጋዩ ፈርተው ኤልሳዕምን ከእደዚህ አይት ቁጥር ጋር ምን እንደሚያደርጉ ጠየቁት። ኤልሳዕም በማይረሳ ቃሎቹ እንዳይጨነቅ ነገረው፤ “ከእኛ ጋር ያሉት ከእነሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ” (2 ነገሥት 6፥16)። አገልጋዩ ነብዩ ስለምን እንደሚያወራ ሊገባው አልቻለም። ማየት ከሚችለው ባሻገር መመልከት አልቻለም ነበር። ይሁን እንጂ፣ ኤልሳዕም የመላዕክት እልፍ ወታደሮችን ለነብዩ ህዝብ ለመዋጋት ዝግጁ ሆነው አየ። ስለዚህ፣ ኤልሳዕም የወጣቱን አይኖች እንዲከፍት ወደ ጌታ ፀለየ፤ “አየም፣ እነሆም በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተው ነበር”(2 ነገሥት 6፥17)።

ኤልሳዕ እና የሰማይ ሰራዊት

በተደጋጋሚ ከምናየው ልዩነት እራሳችንን ከሌሎች እናገላለን። ልክ እንደኛ ከሚያስቡ፣ ከሚያወሩ፣ ከሚለብሱና ከሚተገብሩ ሰዎች ዙሪያ ጥሩ ምቾት ይሰማናል እና ከሌላ ሁኔታዎች ወይም ቦታዎች ከሚመጡ ሰዎች ዙሪያ ስንሆን ደግሞ ምቾት አይሰማንም። በእውን ግን፣ ሁላችንም ከተለያዩ ሃገሮች አይደለም የመጣነውን እናም የተለያየ ቋንቋ አይደለም የምንናገረውን? ዓለምን ውስን ከሆነው የገዛ የሕይወት ተሞኩሯችን አይደለምን የምናየው? ገሚሶቹ እንደ ነብዩ ኤልሳዕ በመንፈሳዊ አይናቸው ያያሉ እንዲሁም ይናገራሉ፣ ገሚሶቹ ደግሞ እኔ ያልተማረውን ሚስዮኔን እንዳየሁት ቀጥተኛ በሆነ እይታ ይመለከታሉ እንዲሁም ይናገራሉ።

በውድድር፣ ምንክት በመስጠት፣ እና ነቀፎታ ላይ እየተመገበ ባለ ዓለም ውስጥ ነው የምንሞረው። በህብረተሰብ መተላለፊያ እይታ ከመመልከት በምትኩ፣ መለኮታዊ ባህሪያት የኔ ብለን ለመውሰድ ወደራሳችን ውስጥ መመልከት ይኖርብናል። እነዚህ መለኮታዊ ባህሪዎች እና ምኞቶች በፒንትረስት ወይም በኢንስታግራም ድረ ገፆች ላይ በመለጠፍ አይመጡም።

ሌሎችን ለመቀበልና ለመውደድ ሃሳባቸውን መቀበል አለብን ማለት አይደለም። ግልፅ በሆነ ሁኔታ፣ እውነት የእኛን ከፍተኛ ታማኝነት ይሻል ምንም እንኳን ለደግነት መሰናክል መሆን ባይኖርበትም እንኳን። በእውነት ሌሎችን መውደድ ሙሉ በሙሉ ልንረዳው በማንችለው የሌሎችን ሰዎች የሕይወት ልምዶችንና ገደቦችን ለመቀበል መሞከርን ይጠይቃል። ማየት ከምንችለው ባሻገር መመልከት በአዳኙ ላይ ማተኮርን ይጠይቃል።

በሁሉም መንገድ የሚጓዝ መኪና

በግንቦት 28፣ 2016 (እ.አ.አ) የ16 ዓመቱ ባዩ ሪቺ እና ጓደኛው ኦስተን በቤተሰብ ማሳ ውስጥ በኮሎራዶ ነበሩ። ባዩ እና ኦስተን በታላቅ ደስታ የቀናቸውን ጉዞ ለመጀመር ተሸከርካሪ ላይ ወጡ። አሳዛኝ ክስተት ሲያጋጥማቸው ብዙም አልራቁም ነበር። ባዩ ይነዳ የነበረው ተሸከርካሪ ባዩን ከ180 ኪሎ ግራም በሚበልጥ በሞቀ ብረትና ሞተር ክብደት ስር በመትከል በድንገት ተገለበጠ። የቦው ጓደኛ እሱ ጋር ሲደርስ፣ ቦውን ለሕይወቱ ሲጣጣር ተመለከተው። በሚችልው ጉለበት፣ ተሸከርካሪውን ከጓደኛው ላይ ለማንሳት ሞከረ። ምንም ሊንፏቀቅ አልቻለም። ለቦው በመፀለይ በቅስበት ለእርዳታ ሮጠ። ለአደጋ እርዳታ የሚሰጡ ሰዎች በመጨረሻም መጡ፣ ነገር ግን ከትንሽ ሰዓቶች በኋላ ቦው ሞተ። ከዚህች ሟች ህይወት ተለቀቀ።

ልባቸው የተሰበረው ቤተሰቦቹ ደረሱ። ከባዩ ውድ ጓደኛ እና ቤተሰብ አባላት ጋር በትንሽዬዋ ሆስፒታል ውስጥ ቆሙው ሳለ፣ አንድ ፖሊስ ወደ ክፍሉ በመግባት የባዩን ተንቀሳቃሽ ስልክ ለእናቱ ሰጣት። ስልኩን ስትቀበል፣ የቀጠሮ ማስታውሻ ደውል ስልኩ ላይ ጮኸ። ስልኩን ከፍታ የባዩን የቀን ተቀን የቀጠሮ ማስታወሻ ደውሉን አየችው። ጨዋታ ወዳጁ፣ እጅግ ጉዞ የሚወደው ወጣት ልጇ በየቀኑ ለማንበብ እቅድ የያዘውን ጮክ ብላ አነበበች፤ “ኢየሱስ ክርስቶስን በዛሬ ሕይወትህ መካከል ውስጥ ለማስቀመጥ አስታውስ።”

የባዩ በአደኙ ላይ ያለው ትኩረት እሱን በማጣት የደረሰባቸውን የወዳጆቹን ሃዘን አልቀነሰውም። ነገር ግን፣ ይህም ነገር ለባዩ ሕይወትና የሕይወት ምርጫ ከፍተኛ ተስፋንና ትርጉምን ሰጠው። ለቤተሰቦቹና ጓደኞቹ በልጅነቱ ከመሞቱ ሃዘን ባሻገር ወደ አስደሳቹ የቀጣጥ ሕይወት እውነት እንዲመለከቱ ፈቀደላቸው። በልጃቸው ዓይኖች አማካኝነት በጣም ያከበረውን ነገር በማየታቸው ለባዩ ወላጆች ምን አይነት የርህራሄ ምህረት ነበር።

እንደ ቤተክርስቲያን አባልነታችን፣ ሟች በሆነው አይኖቻችን ብቻ ከደህንነት ርቀን ስንመለከት የሚያስጠነቅቀን ግላዊ መንፈሳዊ የማንቂያ ደውል ተሰጥቶና። ቅዱስ ቁርባን በተደጋጋሚ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እንድናተኩር የሚረዳን፣ ሁሌም እናስታውሰው ዘንድ የሚረዳን እና የእርሱ መንፈስ ሁሌም ከእኛ ጋር ይሆን ዘንድ የሚረዳን ሳምንታዊ አስታዋሻችን ነው (ት. እና ቃ. 20፥77 ተመልከቱ)። ግን አንዳንዴ እነዚህን የማስታውስ ወይም የአደጋ ስሜቶች ችላ እንላቸዋለን። በሕይወታችን መካካል ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን ስናስቀምጥ፣ ለብቻችን መገንዘብ እንችል ዘንድ ዓይኖቻችን እንዲከፈቱ ያደርጋል።

በአንድ አማኝ እህት ስለማንቂያ ደውል ይህን የሚያስገርም ደብዳቤ ተቀበልኩኝ። እንዴት እንደሚሰማት ለማስረዳት በስልኳ ውስጥ ባሏ በማድረግና በመናገር ያናደዳትን ነገርች ዝርዝር እደፃፈች ነገረችኝ። ሰዓቱ ሲደርስ የፃፈችውን ነገር አሰባስባ ይቀይረዋል ብላ በማሰብ እንደምታካፍለው ገመተች። ይሁን እንጂ፣ አንድ እሁድ ቅዱስ ቁርባን በምትካፈልበት ጊዜና ትኩረቷን በአዳኙ የኋጢያት ክፍያ ላይ ስታደርግ ስለባሏ የእሷን መጥፎ ስሜት መዝግቦ መያዙ መንፈስ ቅዱስን ከእሷ እንደሚያሸሽና እሱን እንደማይቀይረው ተገነዘበች።

መንፈሳዊ ማንቂያ ደውል በልቧ ውስጥ እንዲህ በማለት ጮኸ፤ “ተዪው፣ ሁሉንም ተዪው። እነዛን ማስታወሻዎች ደልቻቸው። አይጠቅሙሽም።” ከዛም እንደዚህ ብላ ፃፈች እኔም አነበዋለው፤ “ሁሉንም የፃፍኳቸውን በጋራ ለመምረጥ ጊዜ ወሰደብኝ እንዲሁም ማጥፊያውን ለመጫን የበለጠ ጊዜ ወሰደብኝ። ነገር ግን ያንን ሳደርግ፣ እነዛ መጥፎ ስሜቶች በሙሉ በአየር ላይ ጠፉ። ልቤ ለባለቤቴ እና ለጌታዬ በፍቅር ተሞላች።” እንደ ወደ ዳማስኮ በሚመራው መንገድ ላይ እንደነበረው ሳኦል ዕይታዋ ተቀየረ። የማዛባት ሚዛኖቿ ከዓኖቿ ወደቁ።

አዳኛችን በተደጋጋሚ በመንፈስና በስጋ የታወሩ ዓይኖችን ይከፍታል። ለመለኮታዊ እውነታ በቀጥታም ሆነ በምሳላዊ አነጋገር ዓይኖቻችንን መክፈት ከዓለማዊ አጭር ዕይታ እንድንፈወስ ያዘጋጀናል። የጉዞ ማስተካከያ ምልክቶችን ለሚሰጡ መንፈስዊ የማንቂያ ደውሎች ትኩረት ስንሰጥ፣ መንፈሱ ከእኛ ጋር እንዲሆን የቅዱስ ቁርባኑን ቃል-ኪዳንን እንቀበላለን። ይህ ለጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ በከርትላንድ ቤተ-መቅደስ ውስጥ የዓለማዊ ጉድለቶች “መጋረጃ” ከአዕምሯቸውና ከመረዳት ዓይናቸው እንደሚነሳ ቃል በገባው በኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ እውነታዎች ሲገለፁ ተከሰተ።(ት. እና ቃ. 110፥1)።

በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በመንፈስ በቀጥታ ከምናየው ባሻገር ማየት እንደምንችል እመሰክራለሁ። እርሱን ስናስታውስ እና መንፈሱ ከእኛ ጋር ሲሆን፣ የመረጃ አይኖቻችን ይከፈታሉ። ከዛም፣ በእያንዳንዳችን ውስጥ ያለው መለኮታዊነት ታላቅ እውነታ ከዚህ በበለጠ በልቦቻችን ላይ ይቀመጣሉ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. From The Lion King 1½ (2004); outside North America, known as The Lion King 3: Hakuna Matata.

  2. Teachings of Presidents of the Church: Gordon B. Hinckley (2016), 201.