የጌታ ድምፅ
በዚህ ጉባኤ ውስጥ የጌታን ድምፅ እንደሰማን እመሰክርለሁ። ለእያንዳንዳችን ፈተናው እንዴት ምላሽ እምደምንሰጥ ነው።
መጀመሪያ፣ ለትንሽ ልጆች ደግ ቃል። አዎን፣ ይህም የመጨረሻው ስብሰባ ነው፣ እና እኔም የመጨረሻው ተናጋሪ ነኝ።
በቅርቡ፣ የፕሮቮ የከታ ማዕከል ቤተ-መቅደስን ስጎበኝ፣ የመጀመሪያ ዕይታ፣ ከሩቅ የሚል ስዕልን አደነቅኩኝ። ስዕሉ አብና ወልድ ወጣት ጆሴፍ ስሚዝን ሲጎበኙ የነበረውን የሰማይ ብርሃንና ኃይልን ያሳያል።
በመመለሱ ጊዜ ከነበረው ቅዱስ ከሆነው ክስተት ጋር ሳላወዳድር፣ የእግዚአብሔርን ብርሃንና ኃይል የሚያንፀባርቅ ተመሳሳይ ምስልን በዚህ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ሲወርድ እንዲሁም ያ ኃይልና ብርሀን በመላው ዓለም ሲንቀሳቀስ መገመት እችላለሁ።
ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ፣ የዚህን ቅዱስ ስራ ጉዳይ እንደሚመራ፣ እናም አጠቃላይ ጉባኤም እርሱ ለቤተክርስቲያኑ እና ለእኛም በግል መመሪያ የሚሰጥበት በጣም አስፈላጊ ጊዜ እንደሆነ ምስክርነቴን እሰጣችኋለሁ።
ከከፍተኛ መማር
ቤተክስቲያኗ በተቋቋመችበት ቀን፣ ጌታ ጆሴፍ ስሚዝን ነብይ፣ ገላጭ እና የጌታ የኢየሱ ክስቶስ ሐዋርያ አድርጎ መረጠው1 እናም ለቤተክርስቲያኑ እንዲህ ሲል ተናገረ፥
“ቃሉን ከራሴ አንደበት እንደወጣ አድርጋችሁ በሁሉም ትዕግስትና እምነት ተቀበሉ።
“ይህንን በማድረጋችሁ የሱኦል ደጃፍ አይከፈትባችሁም … እና ጌታ እግዚአብሔር የጨለማን ኃይሎች ያጠፋል እናም ሰማያት ለእናንተ መልካም እንዲንቀጠቀጡ ያደርጋል።”2
ከዛም በኋላ፣ የቀዳሚ አመራርና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ምልዓተ-ጉባኤ ተሾሙ እና እንደ ነብያት፣ ገላጮች እና ባለራዕዮች በሁሉም አባላት ተቀቡ።3
አሁን፣ ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን አመራር ስር ስንሰበሰብ፣ “የጌታ ፈቃድ፣… የጌታ አስተሳሰብ፣ … የጌታ ድምፅ እና ለደህንነት የእግዚአብሔር ኃይል”4 ለመስማት በጉጉት እንጠብቃለን። እንዲህ በሚለው ቃል-ኪዳኑ እናምናለን፥ “በራሴ ድምፅም ሆነ ወይም በራሪያዬ ድምፅ፣ አንድ ነው።”5
በዘመናዊ ዓለማችን ብጥብጥና ግራ መጋባት፣ በቀዳሚ አመራርና በአስራሁለቱ ሐዋርያት ምልዓተ-ጉባኤ ቃሎች ላይ ያለን እምነት መንፈሳዊ ዕድገታችንና ለጥንካሬአችን በጣም ጠቃሚ ነው።6
ለዚህ አስደናቂ ጉባኤ አብረን መጥተናል። ከ93 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በ200 ሃገራት ውስጥ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኋለኛ ቀን ቅዱሳኖችና የሌላ እምነት ተከታዮች፣ እነዚህን ስብሰባዎች ይከታተላሉ ወይም መልዕክቱን ያነባሉ።
ጸልየንና ተዘጋጅተን ነው የመጣነው። ለብዙዎቻችን፣ የሚጫኑ ጭንቀቶችና ውስጣዊ ጥያቄዎች አሉ። በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት ለማደስና ፈተናን ለመቋቋም እና መረበሽን ለማስወገድ አቅማችንን ለማጠንከር እንፈልጋን። ከላይ ከሰማይ ለመማር እንመጣለን።
የጌታ አስተሳሰብ እና ፍላጎት
በእያንዳንዱ ጉባኤ ለሚናገሩት ቀዳሚ አመራር እና አስራ ሁለቱ፣ መልእክታቸውን የማዘጋጀት ሀላፊነት በየጊዜው የሚመጣ ሸከም እና ቅዱስ እምነት ነው።
ከዓመታት በፊት፣ እንደ አጠቃላይ ባለስልጣን ከማገልገሌ በፊት፣ ሽማግሌ ዳለን ኤች ኦክስን ለእያንዳንዱ የካስማ ጉባኤ የተለያየ ንግግር ያዘጋጅ እንደሆነ ጠየቅኩት። እንደማያደርግ መለሰልኝ ነገር ግን እንዲህ አለ፤ “ነገር ግን የእኔ አጠቃላይ ጉባኤ ንግግርች ልዩ ናቸው። ጌታ እንድናገር የሚፈልገኝን ነገር ለመናገር ከ15 እስከ 15 ጊዜ ልፅፍ እችላለሁ።”7
ለአጠቃላይ ጉባኤ ንግግሮች መነሳሳት መቼና እንዴት ይመጣል?
ምንም ርዕስ ሳይመደብ፣ በእያንዳንዱ ጉባኤ ሰማይ በወብት የዘለአለም እውነት ርዕሶችን እና ዋና መልእክቶችን ሲያቀናብር እናያለን።
አንዱ ወንድሜ ለዚህ ጉባዬ የሚናገረው ዕርዕስ ወዲያውኑ ከባፈው ሚያዝያ ንግግሩ በኋል እንደተሰጠው ነገረኝ። ሌላም ሰው ከሶስት ሳምንት በፊት ወደ ጌታ እየጸለየና ምላሽ እየጠበቀ እንደነበር ገለፀልኝ። ሌላም፣ አንድን የሚነካ ንግግር ለማዘጋጀት ምን ያህል ጊዜ እንደፈጀ ሲጠየቅ “ሃያ አምስት ዓመት” ብሎ መለሰ።
አንድአንዴ ዋናው ሃሳብ በፍጥነት ሊመጣ ይችላል፣ ነገር ግን ይዘቱና ተጨማሪ ሃሳቦቹ እጅግ ብዙ መንፈሳዊ ከፍታዎችን መውጣት ይጠይቃሉ። ፆምና ጸሎት፣ ጥናትና እምነት፣ ሁሌም የሂደቱ አካል ናቸው። ጌታ ለቅዱሳኖቹ የሚሰጠውን ድምፅ የሚያሳንስ ሰው አይፈልግም።
ለአጠቃላይ ጉባኤ ንግግር ምሪት ሲመጣ፣ ብዙን ጊዜ ንግግሩ ከአዕምሮ ሃሳብ በጣም እርቆ ባለበት በማታ ወይም በጣም በጠዋት ነው የሚመጣው። በድንገት፣ ያልታሰበ ሃሳብ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የተለዩ ቃላቶችና ሃረጎች እንደ ንፁህ ራዕይ ይፈሳሉ።8
ስታደምጡ፣ የምትቀበሉት መልዕክት በጣም ቀጥተኛ ወይም ለእናንተ ተስተካክሎ የቀረበ ሊሆን ይችላል።
ከብዙ ዓመታት በፊት በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ በመናገር፣ ሚስዮን ለማገልገል ዝግጁ መሆን አለመሆኔን ሳሰላስል ወደ አዕምሮዬ ስለገባው አንድ ሃረግ ታሪክ ተናገርኩኝ። ሃረጉ “ሁሉንም አታውቅም፣ ነገር ግን በቂ ነገር ላውቃለህ!” ይላል።9 አንድ ወጣት ሴት በዛ ቀን በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ ተቀምጣ ስለተቀበለች የጋብቻ ጥያቄ ላይ እየጸለየች እንደነበር እና በተመሳሳይ ጊዜ ወጣቱን ልጁ ምያ ያህል እንደምታውቀው እያሰላሰለች ነበር። “ሁሉንም አታውቅም፣ ነገር ግን በቂ ነገር ላውቃለህ” የመሚለውን ቃላት ስናገር፣ መንፈስ ለእርሷ ልጁን በሚገባ እንደምታውቀው መሰከረላት። ለብዙ ዓመታት በደስታ ተጋብተው ይገኛሉ።
መንፈሳችሁን ስታዘጋጁ እና የጌታን ቃል እንሰማለን ብላችሁ በተስፋ ስትመጡ፣ ለእናንተ ተስተካክለው የቀረቡ ሃሳቦችና ስሜቶች ወደ አዕምሮአችሁ ውስጥ እንደሚመጡ ቃል እገባላችኋለሁ። እነዛን ነገሮች በዚህ ጉባኤ ተሰምቷችኋል ወይም በሚመጡት ሳምንታት ውስጥ መልዕክቶቹን በምታጠኑ ሰዓት ይሰማችኋል።
ለአሁን እና ለሚመጡት ወራት
ፕሬዘዳንት ሞንሰን እንዲህ ገለፁ፤
“የጉባኤ መልእክቶችን ለማንበብ ጊዜን ውሰዱ።”10
“[እነዚህንም] አሰላስሉ። … እነዚህን የተነሳሱ ትምህርቶች በጥልቅ ሳነብ የበለጠ ከእነሱ እንደማገኝ አውቃለሁ።”11
የአጠቃላይ ስብሰባ ትምህርቶች በሚከተሉት ወራቶች ውስጥ እንድናስብባቸው ጌታ በፊታችን የሚያስቀምጥልን ናቸው።
ያ እረኛ “ከበጎቹ ፊት ይሄዳል እናም በጎቹ ይከተሉታል፤ ድምፁን ስለሚያውቁ።”12
ብዙውን ጊዜ፣ ድምፆቹ በሕይወታችን ውስጥ የሆነ ነገር እንድንቀይር ይመሩናል። ንስሃ እንድንገባ ይጋብዘናል። እንድንከተለው ይጋብዘናል።
ከዚህ ጉባኤ እነዚህን ዓረፍተ-ነገሮች አስብ፥
በዚህ ጠዋት ፕሬዝዳንት ሄነሪ ቢ. አይሪንግ እንዳሉት፥ እግዚአብሔር አብ እንደሚኖር እና ወደ እርሱ ቤት እንድንመጣ እንደሚፈልግ ምስክርነቴን እሰጣለሁ። ይህ እነተኛው የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው። ያውቃችኋል፣ ይወዳችኋል፣ እንዲሁም ይጠብቃችኋል።13
ፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ ትላንትና እንዳሉት፥ “ወደ እግዚአብሔር በሚመራው አስደናቂ መንገድ ለመጓዝ ስንጀምር ወይም ስንቀጥል፣ህይወታችን የተሻለ ይሆናል … እና ጌታም በሚያስደንቅ ሁኔታ በአካባቢያችንን ለመባረክ እና ዘለአለማዊ እቅዱን ለማከናወን ይጠቀመናል።”14
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በትላንትና ከሰዓት በኋላ እንዳሉት፥ “ሁልቀን እራሳችሁን በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ ስትከቱ፣ ከቀኑ ክፋት እንዲሁም ከራቁት ምስል ተምች እና አዕምሮ ከሚያደነዝዙ ነገሮችም ጨምሮ እንደምትጠበቁ ቃል እገባለሁ።”15
ሽማግሌ ዳለን ኤች. ኦክስ ትላንትና እንዳሉት፥ “የቤተሰብ አዋጅ የዘላለም እውነት ዓረፍተ-ነገር፣ የዘለአለም ህይወትን ለሚፈልጉት ልጆቹ ጌታ ያለው ፈቃድ እንደሆነ እመሰክራለሁ።”16
እናም ሽማግሌ ኤም. ራስል ባለርድ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እንዳሉት፥ “የእግዚአብሔር ልጆች በርኅራኄ መቀበል አለብን እና የዘረኝነት፣ የጾታ እና ብሔራዊ ስሜት ጭፍን ጥላቻን ማስወገድ ይኖርብናል።”17
ጥቂት ደቂቃ ስላለን፣ ስለሽማግሌ ሮበርት ዲ. ሔልስ ትንሽ አስተሳሰቤን ለመግለፅ እፈልጋለሁ። ሽማግሌ ሔልስ፣ ሼናቸው የሚፈቅድ ከሆነ በእሁድ ጠዋት ስብሰባ አጭር ንግግር እንዲያደርጉ ቀዳሚ አመራር ነግረዋቸው ነበር። ጤንነታቸው ይህን የማይፈቅድ ቢሆንም፣ ባለፈው ሳምን የፈጸሙት እና ከእኔ ጋር የተካፈሉት መልእክት አዘጋጅተው ነበር። ከሶስ ሰዓት በፊት ከህይወት በማለፋቸው፣ ከንግግራቸው ሶስት መስመሮችን ለመካገል እፈልጋለሁ።
ሽማግሌ ሔልስ እንዳሉት፥ “እምነት እንዲኖረን ስንመርጥ፣ በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም እንዘጋጃለን። … ከአዳኙ ስቅለት በኋላ፣ በሟች ሕይወት ውስጥ በእርሱ ምስክርነት ላይ ታማኝ ለሆኑት ብቻ መልሶ ታየ።’ [ት. እና ቃ. 138፥12።] … የነብያትን ምስክርነቶችን የተቃወሙት ሰዎች [የአዳኙን] ገፅታ አያዩም።’ [ት. እና ቃ. 138፥21።] … እምነታችን በጌታ መገኛ ስር እንድንሆን ያዘጋጀናል።”
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ከዚህ ጠዋት ስብሰባ በኋላ ከህንጻው በፍጥነት በመሄድ፣ ምሳ ሳይበሉ፣ ቶሎ ለሽማግሌ ሔልስ መኝታ አጠገብ በመገኘት፣ የእርሳቸው ቡድን ፕሬዘደንት የሆኑት ከሜሪ ሔልስ ጋር እርሳቸው ከስጋዊ ህይወት በእርፍት ሲያልፉ ለመገነት በመቻላቸው እንዴት ጌታ ደግ ነበር።
ለጌታ ድምፅ መልስ መስጠት
በዚህ ጉባኤ ውስጥ የጌታን ድምፅ እንደሰማን እመሰክርለሁ።
የጌታ አገልጋይ ቃላት የአለምን አስተሳሰብ፣ እናም፣ አንዳንዴ፣ የራሳችንን አስተሳሰብ ተቃርኖ ሲሄድ መደንገጥ አያስፈልገንም። ይህም ሁልጊዜ እንደዚህ ነበር። ከወንድሞቼ ጋር በቤተመቅደስ ውስት ተንበርክኬአለሁ። ስለነፍሳቸው መልካምነት እመሰክራለሁ። የእነርሱ ታላቅ ፍላጎት ጌታን ለማስደሰት እና የእግዚአብሔር ልጆች ወደ እርሱ ፊት እንዲመለሱ ነው።
የሰባ፣ የኤጲስ ቆጶስ፣ የሴት መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ አመራር፣ የወጣት ሴቶች፣ የመጀመሪያ ክፍል፣ እና የሌሎች መረዳጃ መሪዎች ልክ እንደ ቆንጆዎቹ መዝሙሮችና የለሰለሱ ጸሌቶች ታላቅ መነሳሻዎችን ለዚህ ጉባኤ ጨምረዋል።
በአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶች ውስጥ እናንተ ልታገኟቸው የምትችሉት የሰማይ መመሪያዎች ሀብት አሉ። የእያንዳንዳችን ፈተና እንዴት ለምንሰማው፣ ለምናነበው፣ እና ለሚሰማን እንዴት እንደምንመልስ ነው።
ከፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ህይወት የመጣ ለነቢያዊ ቃላት መመለስ አጋጣሚን ላካፍላችሁ፥
በ1979 (እ.አ.አ)፣ እንደ አጠቃላይ ባለስልጣን ከመጠራታቸው ከአምስት አመት በፊት፣ ወንድም ኔልሰን ልክ ከአጠቃላይ ጉባኤ በፊት የሆነ ስብሰባብ ተካፈሉ። “ፕሬዘዳንት ሰፔንሰር ደንሊው ኪምባል የታደሙትን ሰዎች ወንጌልን ወደ መላው ዓለም በማንሰራፋት ላይ እርምጃቸውን እንዲያስረዝሙ ጠየቁ። ፕሬዝደንት ኪምባል ከጠቀሷቸው ሃገራት መካከል ቻይና ነበረች፣ እንዲህም አሉ ለቻይናዎች አገልግሎት መስጠት አለብን። ቋንቋቸውን መማር አለብን። ልጸልይላቸውና ልንረዳቸው ይገባናል።’”18
በ54 ዓመታቸው፣ ወንድም ኔልሰን በስብሰባው ወቅት ማንደሪን ቋንቋን ማጥናት እንዳለባቸው ተሰማቸው። ምንም እንኳን በጣም ስራ የበዛባቸው የልብ ቀዶ ጥገና ባለሞያ ቢሆኑም የአሰጠኒ የአገልግሎቶችን ቦታን አገኙ።
ጥናታቸውን ከመጀመራቸው ብዙም ሳይርቁ፣ ዶ/ር ኔልሰን ስብሰባ ውስጥ ተካፈሉ፣ እናም ሳያውቁት እራሳቸውን ከታዋቂ የቻይና የቀዶ ጥገና ባለሞያ ከዶ/ር ዉ ዪንግካይ አጠገብ አገኙት። … ምክንያም ወንድም ኔልሰን ማንደሪን ቋንቋን አጥንተው ስለነበር ከዶ/ር ዉ ጋር ንግግር ጀመሩ።”19
የደ/ር ኔልሰን ነብይን የመከተል ፍላጎት ዶ/ር ዉ ሶልት ሌክ ከተማን እንዲጎበኙ እና ደ/ር ኔልሰን ወደ ቻይና ንግግር ለመስጠትና ለቀዶ ጥገና እንዲጓዙ ዳረገ።
ለቻይና ሰዎች ያላቸው ፍቅር እና እነሱ ለእሳቸው ያላቸው ፍቅርና አክብሮት ጨመረ።
በየካቲት 1985 (እ.አ.አ)፣ ወበ አስራሁለቱ ሐዋርያት ምልዓተ-ጉባኤ ከመጠራታቸው ከአስር ወራት በኋላ፣ ሽማግሌ ኔልሰን ድንገተኛ የስልክ ጥሪ ከቻይና ዶ/ር ኔልሰን ወደ ቤጂንግ ወጥተው በቻይና ታዋቂ የኦፔራ አቀንቃኝ እየደከመ ያለ ልብ ላይ ቀዶ ጥገና እንዲሰሩ ተለመኑ። በፕሬዳንትጎርደን ቢ. ሂንክሊ አበራታችነት ሽማግሌ ኔልሰን ወደ ቻይና ተመለሱ። የመጨረሻውን ቀዶ ጥገና ያደረጉት ቻይና የህዝብ ሪፐብሊክ ውስጥ ነበር።
ከሁለት ዓመታት በፊት፣ በጥቅምት 2015 (እ.አ.አ) ፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “የቻይና የድሮ ጓደኛ” ተብለው በድጋሜ በክብር ታወጁ።
ከዛ ትላንትና፣ የዛሬው የ93 ዓመቱ ፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ስለ ፕርዘዳንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን “እያንዳንዳችን [ባለፈው የሚያዝያ ጉባኤ] በእየቀኑ መጽሐፈ ሞርመንን በጸሎት እንድናጠና እና እንድናሰላስል” የሰጡንን ልመና ሲናገሩ ሰማን።
ልክ እንደ ስራ የበዛበት የልብ ቀዶ ጥገና ባለሞያ የማንደሪን አስተማሪን እንደቀጠሩት፣ ካለፈው የሚያዝያ ጉባኤ በኋላ ፕሬዘዳንት ኔልሰን ቶሎ ወደ ሕይወታቸው በመተርጎም የፕሬዘዳንት ሞንሰንን ምክር ወሰዱ። ከማንብም ብቻ በዘለለ፣ “መጽሐፈ ሞርሞን ምን እንደሆነ፣ ምን እንደሚያረጋግጥ፣ ምን እንደሚከራከር፣ ምን እንደሚያሟላ፣ ምን እንደሚያብራራ እና ምን እንደሚገልፅ ዝርዝሮችን ፃፉ።”20
ከዚያም፣ በሚገርም ሁኔታም፣ በዚህ ጠዋት፣ እንደ ሁለተኛ ምስክር፣ ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ ደግመውም በዚህ ጠዋት ለፕሬዘደንት ሞንሰን ግሰጻ መልሳቸውን ተናግረዋል። እነዚህን ቃላቶች ታስታውሳላችሁን? “እንደ ብዙዎቻችሁ፣ የነብዩን ቃላት ጌታ ለእኔ እንደተናገረው ድምፅ ነው የሰማሁት። እናም እንደ ብዙዎቻችሁ፣ እነዛን ቃላት ለመታዘዝ ወሰንኩኝ።”21
ይህንን በራሳችን ሕይወት ውስጥ እንደ ምሳሌ እንያቸው።
ቃል ኪዳን እና በረከት
ነገር ግን፣ በዚህ አጠቃላይ ጉባኤ ትምህርቶች ውስጥ የጌታን ድምጽ ስትሰሙ ከዛ በእነዛ መነሳሻዎች ላይ ስትተገብሩ፣ የሰማይ እጅ በእናንተ ላይ ሆኖ እንደሚሰማችሁ እና ሕወታችሁና በዙሪያችሁ ያሉት ሰዎች ሕይወት እንደሚባረክ ቃል እገባላችኋሁ።22
በዚህ ጉባኤ፣ ስለውድ ነቢያችን እናስባለን። እንወዶታለን፣ፕሬዘዳንት ሞንሰን። ከዚህ መስበኪያ ባቀረቡት ቃላት እፈጽማለሁ፥ እርሳቸው ዛሬ ከእኛ ጋር ለመገኘት ቢችሉ ለእያንዳንዳችን ሊሰጡን የሚፈልጉት በረከት እንዳለ አምናለሁ። እንዲህ አሉ፥ “ይህን ጉባኤ ለቀን በምንወጣበት ወቅት፣ የሰማይን በረከት በእያንዳንዳችሁ ላይ እጸልያለሁ። … የሰማይ አባታችን እናንተንና ቤተሰባችሁን እንዲባርካችሁ እጸልያለሁ። የዚህ ጉባኤ መልዕክቶችና መንፈሶች በምታደርጉት ነገሮች ላይ፣ በቤታችሁ ውስጥ፣ በስራችሁ ውስጥ፣ በስብሰባችሁ ውስጥ እና በሁሉም በመምጣታችሁና በመሄዳችሁ ውስጥ መገለጫን ያግኝ።”
እንዲህ ብለው ደመደሙ፤ “እወዳችኋለሁ። እጸልይላችኋሁ። እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ቃል የገባው ሰላም አሁንና ሁሌም ከእናንተ ጋር ይሁን።”23
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።