2010–2019 (እ.አ.አ)
ታዕምራት ቆሟልን?
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


2:3

ታዕምራት ቆሟልን?

የእኛ ታላቁ አተኩሮት ለእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ ስላለ መንፈሳዊ በረከቶች መሆን አለበት።

ከአመት በፊት በተሰጠኝ ሀላፊነት ወደ ካሊፎርኒያ ስቴት ከካስማው ፕሬዘዳንት ጋር የክላርክ እና ሆሊ ፎልስ ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት ሄድን። በቅርቡ ታአምር እንዳጋጠማቸው ተነግሮኝ ነበር። ልክ ስንደርስ ክላርክ ተነስቶ ሰላም ለማለት ተቸገረ፤ የጀርባ እና የአንገት ብሬስ፣ የጉልበት ብሬስ እናም ክንዶቹም ላይ ብሬስ ነበረውና።

ከሁለት ወር በፊት ክላርክ፣ ልጁ ታይ እና ሌሎች 30 ወጣቶች እና መሪዎቻቸው ጋር 4,322 ሜትር ከፍታ ወዳለው ሻስታ ተራራን ጫፍ ለመውጣት በተዘጋጀው የካስማ ድርጊት ለመሳተፍ ሄደው ነበር፤ ይህም በካሊፎርኒያ ካሉት አንዱ ከፍተኛው ተራራ ነው። በአድካሚው የተራራ መውጣት ላየ በሁለተኛው ቀን፣ አብዛኛዎቹ ጫፉ ላይ ደረሱ—አስድሳች ስኬት ነበር ምክንያቱም የወራት ዝግጅት ወስዷልና።

በዚያ ቀን ጫፍ ከደረሱት ሰዎች መካከል ክላርክ አንዱ ነበር። በጫፍ አፋፍ ላይ ትንሽ ካረፈ በኃላ ተነስቶ መራመድ ጀመረ። ከዛም ከኮረብታማው ጫፍ አዳልጦት ወደ ኃላ 12 ሜትር ወደቀ ከዚያም ያለቁጥጥር በረዷማው አዳላጭ ላይ ሌላ 91 ሜትር ያለቁጥጥር ተንከባሎ ወደቀ። በሚገርም ሁኔታ ክላርክ ተረፈ ነገር ግን ክፉኛ ተጎድቶ መንቀሳቀስ አልቻለም።

ከላርክ በዚህ አሰቃቂ ጊዜ ያጋጠመው ታአምራት ገና ጅማሪው ነበር። ቀድመው የደረሱለት ተራራውን የወጡ ግሩፖች፣ የተራራ አዳኝ ቡድኖች እና የአደጋ ጊዜ የህክምና ባለሞያዎች ነበሩ። በአፋጣኝ እረዱት እናም እንዲሞቀው የሙቀት ልብስ አለበሱት። እነዚህ ቡድኖችም አዲስ መሳሪያ ላይ ሙከራ እያደረጉ ነበር የሞባይል ስልኮች ወደ ማይደርስበት አካባቢ የእርዳታ ጥሪ ላኩ። ትንሽዬ ሄሊኮፕተር ወደ ተራራው በፍጥነት አንድ ሰአት ከሚርቅ ቦታ ወደ ሻስታ ተራራ ጫፍ ተላከ። የሄሊኮፍተሩን አቅም በሚገፋ ከፍታ ላይ እና በክፉኛ የንፋስ ሁኔታ ውስጥ ከሁለት አደገኛ እና ያልተሳካ የማረፍ ሙከራ በኋላ አብራሪው ለሶስተኛ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሙከራ አደረግ። በተለያዩ አንግሎች ሄሊኮፕተሩ ሲመጣ ንፋሱ ተቀየረ እና ቡድኑ በፍጥነት እና እያመመው ይዘውት ክላርክን ከፓይለቱ መቀመጫ ጀርባ ትንሽ ቦታ ላይ እስኪያስቀምጡት ድርስ ሄሊኮፕተሩ አርፈ።

ክላርክ በጉዳት ማእከል ውስጥ ሲመረመር ውጤቱ በብዙ ቦታዎች ላይ፣ በአንገቱ፣ በጀርባው፣ በጎን አጥንቱ ላይ ስብራቶች እንዳለ ውጤቱ አሳየ፤ ሳምባውም የመቆረጥ እና ሌሎች መቆራረጥ እና በመቧጨር የተጎዳ ሰውነትን። በዛ እለት እንዳጋጣሚ ታዋቂ የነርቭ ቀዶ ጠጋኝ በስራ ላይ ነበር በዚህም ሆስፒታል በአመት ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው የሚገኘው። በኋላም ይሔን ያህል የጀርባ አጥንት ላይ ጉዳት ደርሶበት የተቋቋመ እና ካሮቲድ አርትሪስ ላይ ጉዳት ደርሶበት የኖረ ሰው እንዳላየ ተናገረ። ከላርክ በህይወት ለመኖር ብቻ ሳይ ሆን ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ይሰራል ተብሎ አልተጠበቀም ነበር። በአምላክ እንደማያምን በመግለጽ የክላርክ ነገር ከተማረው ሳይንሳዊ የነርቭ ጉዳቶች ጋር ተቃራኒ እንድሆነና እንደ ታእምር እንደሚገለጽ ቀዶ ጥገና አድራጊው ገለጽ።

ክላርክ እና ሆሊ ይህን አስደንጋጭ ነገር መንገራቸውን ሲጨርሱ፣ ማውራትን ከባድ ሆኖ አገኘሁት። በሚታወቀው ታእምር ምክንያት አልነበረም ነገር ግን በሀያሉ ነበር። ሆሊ እና ቤተሰቦቻቸው ዙሪያ የተቀመጡት አምስት የሚያምሩ ልጆቻችው በዛ እለት በተከሰተው ነገር ውጤቱ ምንም አይነት ቢሆንም እንኳን ያን ያህል እምነት ስላላቸው መቀበል እንደሚችሉ እና በመንፈሳዊ አሁንም ይበለጸጉ እንደነበር ጥልቅ ስሜት እና መንፈሳዊ ምስክርነት ነበረኝ። ክላርክ እና ሆሊ እንዲሁም ሁለቱ ትልቅ ልጆቻቸው ታይ እና ፖርተር በዚህ ስብሰባ ማእከል ዛሬ ከእኛ ጋር ይገኛሉ።

የነ ፏልስ ቤተሰብን ገጠመኝ ሳሰላስል የሌሎች የብዙኋኑ ሁኔታ አሰብኩ። ልክ በሌለው እምነት የተሞሉ፣ በክህነት በረከት እየተቀበሉ ያሉ፣ ያለማቋረጥ የተጸለየላቸው፣ ቃልኪዳን ጠባቂዎች እና በተስፋ የተሞሉ የኋለኛው ቀን ቀዱሳን ታመራታቸው መቼም የማይመጣስ? ምናልባት እነሱ ታእምራትን በሚረዱበት በኩል እንኳ። ምናልባትም ሌሎች ታአምራትን በሚቀበሉበት መንገድ በሚመስል እንኳ።

እነዛዝ ለአመታት ምናልባትም ለአስር አመታት ከውስጥ በመነጨ ስቃይ አካላዊ፣ አእምሮዊ ስሜታዊ ስቃይ የሚሰቃዩትስ? በጣም በወጣትነት የሞቱስ?

አሁን ከሁለት ወራት በፊት፤ የቤተመቅደስ መግቢያ የያዙ ሁለት ጥንዶች ከሶስት የሙሉ ጊዜ ሚሲሆናውያን ልጆቻቸው ጋር እና በመሀከላቸው ሌሎች አምስት ልጆቻቸው ጋር ሆነው በትንሽዬ አውሮፒላን ለአጭር በረራ ተሳፍረው በረሩ። ከመብረራቸው በፊት ለደህንነት እንደፀለዩ እና አውሮፒላናቸውም ከባድ መካኒካል ችግር ሲፈጠር ከመከስከሱ በፊት እንደፀለዩ እርግጠኛ ነኝ። ማንም አልተረፈም። እነሱስ?

ጥሩ ሰዎች እና የነሱ ወዳጆች ሞርሞን እንዲህ የጠየቀውን ጥያቄ፥ “ታዕምራት ቆሟልን”1 ለመጠየቅ ምክንያት አላቸውን?

የኔ የተገደብ እውቀት አንዳንዴ ለምን መለኮታዊ እርዳታ እንደሚመጣ ላንዳንዶች ደሞ ለምን እንደማይመጣ ማብራራት አልችልም። ምናልባት ታእምራትን ምን እንደሚከስታቸው ለመረዳት እንቸገር ይሆናል።

አብዛኛውን ጊዜ ታአምራትን በህክምናው ሳይንስ መብራራሪያ ሳይኖረው ሙሉ ለሙሉ መፈውስ ወይም ግልፅ የሆነ ትልቅ አደጋን እንድናስውግድ የሚነግር ድምፅ ብለን ነው የምንገልፀው። ሆኖም ግን፤ ታዕምርን “ሟቾች መራዳት በማይችሉት ሁኔታ በመለኮታዊ ሀይል ጠቃሚ ክስተት”2 ብለን መተርጎም በተፈጥሮ ዘላለማዊ ስለሆኑ ነገሮችን ሰፋ ያለ እይታ ይኖረናል። ይህ ትርጉምም እምነት በታአምራት ውስጥ ያለውን አስተዋፀኦ እንድናሰላስል ያደርገናል።

ሞሮኒ “ማንም ከእምነቱ በፊት በማንኛውም ሰአት ታአምራትን አላደረገም”3 ሲል አስተምሯል። አሞን “ሰው በእምነት አማካኝነት ታአምር እንዲያድርግ እግዚአብሔር መንገድ አዘጋጅቷል”4 ሲል አውጇል። ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ … በእኔ ስም ለሚያምኑ በሙሉ … ታአምራትን አሳያቸዋለሁ”5 ሲል ገልጿል።

ንጉስ ናቡከደነጽር “ካልሰገዳችሁ ወደ እሳት ነበልባሉ ትጣላላችሁ” ብሎ ሼድራቅ፣ ሚሳቅ እንዲሁም አብደናጎን ላቆመው የወርቅ ምስሉ እንዲያምልኩ አስገድዳቸው። ከዛም “ከእኔ እጅ የሚያድናችሁ ያአምላክ ማነው?”6 ሲል አሾፈባቸው።

እንዚህ ሙሉ ለሙሉ የተሰጡ ሶስት ደቀ መዝምሮች፥ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል። “ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።”7

እግዚአብሔር እንደሚያድናቸው ሙሉ እምነትን ይዘው ነበር ካልሆነም ደግሞ በእቅዱ ፍፁም እምነት ነበራቸው።

በተመሳሳይ ኢልደር ዴቪድ ኤ. ቤድናር የክህነት ስልጣን ፀሎት እንዲደረግለት የጠየቀውን ወጣት ወንድ ልጅ “የሰማይ አባት ፍቃድ ሆኖ በሞት ተቀይረህ ወደ መንፈስ አለም ሄደህ አገልግሎትህን ብትቀጥል ለእሱ ፍቃድ ለመሰጠት እና ላለመፈወስ እምነት አለህ?”8 ብሎ ጠየቀው። እኛስ ለዘላለም እንፈወስ ዘንድ ከምድራዊ ስቃያችን ”ላለመፈወስ” እምነት አለን?

ልናስብበት የሚገባ አሳሳቢ ጥያቄ “እምነታችንን የት ነው የምናደርገው?” የሚለው ነው። እምነታችን በቀላሉ ከህመም እና ከስቃይ መገላገል ላይ ነው ወይስ በእግዚአብሔር አብ እና በእቅዱ እቅዱ ላይ እንዲሁም በእየሱስ ክርስቶስ እና በሀጥያት ክፍያው ላይ ማእከል ያደረገ ነው? እምነት በአብ እና በወልድ ላይ ሲሆን ለዘላለማዊነት ስንዘጋጅ የነሱ ፍቃድ ምን እንደሆነ እንረዳ ያደርገናል።

ዛሬ ስለ ታአምራት እመሰክራለሁ። የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ታአምር ነው።9 በእሱ አምሳል መልክ አካል ማግኘት ታአምር ነው።10የአዳኝ ስጦታ ታአምር ነው።11 የኢየሱስ ክርስቶስ የሀጥያት ክፍያ ታአምር ነው።12 ለዘላለማዊ ህይወት ያማግኝት ችሎታ ታአምር ነው።13

መፀለይ እና ለአካላዊ ጥበቃ እና በሟች ህይወታችን ውስጥ ለፈውስ ስንሰራ ታላቁ አተኩሮታችን መንፈሳዊ ለሆነው ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ያለ ታአምር ላይ ነው መሆን ያለበት። ብሔራችነ፣ ዜግነታችን ምንም ቢሆን ምንም ብናጠፋና ንሰሀ ብንገባ ምንም እንኳ ቢደረግብን ሁላችንም እነዚህን ታአምራት ለማግኝት እኩል ነን። እኛ የምንኖር ታአምር ነን፣ ሌሎች በረከቶችም ወደፊት አሉ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።