2010–2019 (እ.አ.አ)
እርሱን እናምነዋለንን? ከባድ መልካል ነው
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


2:3

እርሱን እናምነዋለንን? ከባድ መልካል ነው

ጉዳዩ ምንም ይሁን ምን፣ ከባድ ነገር በእምነት ወደ ፊት ለሚጓዙ እና ጌታንና ዕቅዱን ለሚያምኑ ሰዎች ጥሩ ሊሆን ይችላል።

ከመጀመሬ በፊት፣ በቅርብ በደረሱት የአውሎ ንፋስ እና የምድር መንቀጥቀጥ መዓት የተነካነውን በመወከል፣ እርዳታ እና ተስፋ ለሰጡን ለሚረዱት እጆች እና ለእነርሱ መሪዎችከልቤ የተሰማ ምስጋናንን አቀርባለሁ።

በጥቅምት 2006 (እ.አ.አ) የመጀመሪያ የአጠቃላይ ጉባኤ ንግግሬን አቀረብኩ። የአለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አስፈላጊ መልእክት “ጌታ ያምነናል” የሚል ማረጋገጫ እንደሚኖረው ተሰማኝ።

በእውነቱ በብዙ ዓይነት መልኩ ያምነናል። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ሙሉነት በዚህ ዘመን ውስጥ ሰጥቶናል። ለዓላማው ጥቅም ቁልፎች ጋር በክህነት ስልጣኑ አምኖናል። በዛ ኃይል መባረክ፣ ማገልገል፣ ሥነ-ስርዓቶችን መቀበል፣ እናም ቃል-ኪዳኖችን መግባት እንችላለን። በተመለሰው ቤተክርስቲያኑ እና በቅዱስ ቤተ-መቅደሱ ያምነናል። አገልጋዬቹን በምድር የታሰረው በሰማይ እንዲታሰር በህትመት ኃይል ያምናቸዋል። እንዲሁም ለእርሱ ልጆች ወላጆች፣ አስተማሪዎች እና ተንከባካቢዎች እንድንሆን ያምነናል።

ከእነዚህ ዓይነት የብዙ ዓመታት የአጠቃላይ ባለስልጣን በብዙ የዓለም ክፍሎች አገልግሎት በኋላ፣ በበለጠ እርግጠኝነት ያምነናል ብዬ አውጃለሁ።

አሁን ለዚህ ጉባኤ ጥያቄው “እኛ እናምነዋለንን?” ሚል ነው።

እርሱን እናምነዋለንን?

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ሁልጊዜ እንድናስታውስ እንደሚያደርጉን “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤

“በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።”

በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን” (ምሳሌ 3፥5–7)።

ትዕዛዛቱን ለእኛ ጥቅም ነው ብለን እናምናለንን? የእርሱ መሪዎች ምንም ፍፁም ባይሆኑም በመልካም እንደሚመሩን እንምናለንን? ቃል-ኪዳኖቹ እውን እንደሆኑ እናምናለንን? የሰማይ አባታችንና ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያውቁንና ሊረዱን እንደሚፈልጉ እናምናለንን? ምንም እንኳ በፈተና፣ በችግር እና በከባድ ጊዜዎች ውስጥ እናምናለንን?

ወደ ኋላ በመመልከት ወጣትም ሆኜ፣ በሚስዮን ላይ፣ አዲስ ስራ በመጀመር፣ ጥሪዬን ለማጉላት በመጣር ውስጥ፣ ትልቅ ቤተሰብን በማፍራት ውስጥ፣ ወይም እራስን ለመቻል ጥረት ሳደርግ በጣም ጥሩ የሚባሉትን ትምህርቶች በከባድ ጊዜዎች ውስጥ ተምሬአለሁ። ከባድ መልካም እንደሆነ ይህም ግልፅ ይመስላል።

ከባድ መልካል ነው

ከባድ ጠንካራና ትሁት ያደርገናል እናም እራሳችንን እንድናሳይ እድል ይሰጠናል። የእኛ ውድ የቤተክርስቲያ መስራቾች እግዚአብሔርን በችግሮቻቸው ውስጥ ነው ያወቁት። ለምንድን ነው ኔፊንና ወንድሞቹን የነሃስ ሰሌዳውን ለማግኘት ሁለት ምዕራፎች የፈጀው የኢሽማኤልን ቤተሰብ በበረሃ እንዲቀላቀሏቸው ለመዘርዘር ግን ሶስተ ቁጥሮች ብቻ የፈጀው? (1 ኔፊ 347፥3–5 ተመልከቱ)። ጌታ ኔፊን ሰሌዳዎቹን በማግኘት ሂደት ውስጥ ለማጠንከር የፈለገ ይመስላል።

በሕይወታችን ውስጥ ከባድ ነገሮች ያለምንም ግርምታ መምጣት አለባቸው። ከጌታ ጋር ካደረግነው የቀድሞ ቃል-ኪዳኖች ውስጥ አንዱ የመስዋትነትን ህግ ለመኖር ነበር። መስዋትነት፣ በትርጉሙ፣ የሚያስፈልግን አንድን ነገር አሳልፎ መስጠትን ያጠቃልላል። ከልምድ ጋር ከሚከተለው በረከት በአንፃሩ የምንከፍለው ትንሽ እንደሆነ እንገነዘባለን። ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ አለ፣ “የሁሉንም ነገሮች መስዋትነት የማይጠይቅ ሐይማት ለሕይወትና ደህንነት የሚያስፈልገውን እምነት ለማፍራት በቂ ኃይል አይኖረውም።”1

የአመላክ አባሎች ለከባድ ነገሮች እንግዳ አይደሉም። አብ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለአስከፊው የኃጢያት ክፍያ ስቃይ በመስቀል ላይ ሞትንም ጨምሮ መስዋት አደረገ። ቅዱሳት መጻህፍት ኢየሱስ ክርስቶስ “ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ” (ዕብራውያን 5፥8) ይላሉ። የኃጢያት ክፍያን ስቃይ በፈቃደኝነት ተሰቃየበት፡ መንፈስ ቅዱስ አንድ አንድ ጊዜ ችላ ይባላል፣ በስህተት ይተረጎማል ወይም ይረሳል እንጂ ለማስታወስ፣ ለማስጠንቀቅና ለመምራት ታጋሽ መሆን አለበት።

የዕቅዱ አካል

ከባድ የወንጌሉ ክፍል ነው። ከዚህ ሕይወት ዓላማዎች አንዱ መፈተን ነው ( አብርሐም 3፥25 ተመልከቱ)። ጥቂቶች ከአልማ ሰዎች በበለጠ ካላግባብ ተሰቃይተዋል። ከኃጢያኑ ንጉስ ኖሃ ለላማንያኖች ባሪያ ለመሆን ብቻ ሸሹ። በእነዛ ፈተናዎች አማካኝነት ጌታ ሕዝቦቹን እንደሚገስፅና “ትዕግስታቸውንና እምነታቸውን” (ሞዛያ 23፥21) እንደሚፈትን አስተማራቸው።

በአሰቃቂው በሊብርቲ ወህኒ ቤት ውስጥ ጌታ ጆሴፍ ስሚዝን “በርታ”(ት. እና ቃ. 121፥8) አለው aእናም ከበረታ “ሁሉም ነገሮች ልምድ ይጡሃል እናም ለአንተ መልካም ይሆናሉ” (ት. እና ቃ. 122፥7) ብሎ ቃል ገባለት።

ፕሬዘደንት ሞንሰን እንዲህ ለምነዋል፣ “ከባዱን ትክክል በቀላሉ ስህተት ምትክ እንምረጥ”2 ስለቤተመቅደሳችን በሚመለከትም፣ እንዲህ አሉ “[የቤተመቅደስ] በረከቶችን ለመቀበል፣ ምንም መስዋዕት ታላቅ ነው፣ ምንም ዋጋ ከባድ አይደለም፣ ምንም ትግል አስቸጋሪ አይደለም።”3

በተፈጥሮ ዓለም ውስጥ፣ ከባድ የሕይወት ኡደት አካል ነው። ለዶሮ ጫጩት ከእንቁላሏ ውስጥ ፈልፍላ ለመውጣት ከባድ ነው። ነገር ግን፣ አንድ ሰው ቀላል ለማድረግ ሲጥር፣ ጫጩቷ ለመኖር ጥንካሬን ማዳበር አትችልም። በተመሳሳይ መልኩ፣ የቢራቢሮ ኮፈኑን የማምለጥ ትግል ለሚኖረው ሕይወት ጥንካሬ ይሰጠዋ።

በእነዚህ ምሳሌ፣ ከባድ የተለመደ ነገር እንደሆነ እያየን ነን! ሁላችንም ትግሎች አሉን። የሚለየው ለሚያጋጥሙን ከባድ ነገሮች ምላሻችን ነው።

በአንድ ወቅት የተወሰኑ የመጽሐፈ ሞርሞን ሰዎች “በታላቅ መሰደድ” እና “ከፍተኛ መከራ” (ሔለማን 3፥34) ተሰቃዩ። እንዴት ነው ምላሽ የሰጡት? “ዘወትር ፆሙ፣ እንዲሁም ፀለዩ፣ እናም ነፍሳቸውን በደስታና በመፅናናት እስከሚሞሉ ድረስም፣ አዎን፣ ልቦቻቸውን ለእግዚአብሔር በፍቃድ በመስጠት በሚመጣው ቅድስና ልቦቻቸው እንዲጸዱና እንዲቀደሱ እስከሚያደርጉ ድረስ በትህትና እየጠነከሩ፣ እናም በክርስቶስ እምነታቸውን እየጸኑ ሄዱ” (ሔለማን 3፥35)። ሌላ ምሳሌ ከዓመታት ጠርነት በኋላ ተከሰተ፤ “በኔፋውያ እናም በላማናውያን መካከል በነበረው ታላቅ ጦርነት እርዝማኔ እናም ጦርነቱ እጅግ ረጅም በመሆኑ ብዙዎች ጠጣሮች ሆኑ፣ … እናም ብዙዎች በስቃያቸው የተነሳ በእግዚአብሔር ፊት እራሳቸውን እስከሚያዋርዱ በታላቅ ትህትናም ዝቅ እስከሚሉ ለስላሶች ነበሩ” (አልማ 62፥41)።

እያንዳንዳችን ለከባድ የምንሰጠውን ምላሽ እንመርጣለን።

በቀላል ነገር ተጠንቀቁ

ከዚህ ጥሪ በፊት በሂውሰተን ክሳስ ውስጥ የገንዘብ ቤት አማካሪ ነበርኩኝ። ብዙ ስራዬ የራሳቸው ንግድ ካላቸው ከባለ ሚሊዮነሮች ጋር ነበር። ብዙዎቹ ከባዶ ተነስተው ነው ውጤታማ ንግዳቸውን ያቋቋሙት ማለት ይቻላል። ለእኔ አሳዛኙ ነገር ለልጆቻቸው ነገሮችን ቀላል ለማድረግ እንደፈለጉ ሲናገሩ መስማት ነበር። እነሱ እንደተሰቃዩት ልጆቻቸው እንዲሰቃዩ አልፈለጉም። በሌላ አነጋገር፣ እነሱን ውጤታማ እንዲሆኑ ያደረጋቸውን ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ ይከለክሏቸው ነበር።

በተቃራኒው፣ ስለተለየ መንገድ የወሰዱ ቤተሰብ እናውቃለን። አባቱ የስምንት ዓመት ልጅ ሲሆን በገንዘብ እራሱን መቻል እንዳለበት በነገረው በጄ. ሲ. ፔኔይ ልምድ ወላጆቹ መነሳሻ አግኝተዋል። ወደራሳቸው ቀየሩትና እያንዳንዳቸው ልጆች ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲመረቁ በገንዘብ እራሳቸውን መርዳት እንዳለባቸው እና ለወደፊት ት/ቤ (ማለትም ለኮሌጅ፣ ለሁለተኛ ድግሪ ወ.ዘ.ተ.) እና ለተለያዩ ወጨዎች በገንዘብ እራሳቸውን መርዳት አለባቸው (ት. እና ቃ. 83፥4 ተመልከቱ)። በደስታ ልጆቹ በጥበብ ምላሽ ሰጡ። ሁሉም የኮሌጅ ምሩቆች ናቸው እናም አብዛኛዎቹ የማስተርስ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ፣ እናም ሁሉም እራሳቸውን ቻሉ። ቀላል አልነበረም፣ ነገር ግን አደረጉት። ይህን ያደረጉት በከፍተኛ ስራ እና እምነት ነው።

በእርሱ ላይ እምነት ለመጣል ማመን

“እናምነዋለንን?” የሚለው ጥያቄ “እርሱን ለማመን እምነቱ አለን?” በሚለው ተሻሽሎ መቅረብ ይችል ይሆናል።”

አስራትን በተመለከተ 100 ከመቶ በራሳችን ከምናገኘው ዓመታዊ ጭማሬ ይልቅ ከተሰጠን 90 ከመቶ እና ከጌታ እርዳታ ጋር የተሻለ እንደሚሆን የእርሱን ቃል-ኪዳኖቹን ለማመን እምነቱ አለ?

በመከራችን ወቅት እንደሚጎበኘን (ሞዛያ 24፥14 ተመልከቱ)፣ ከእኛ ጋር ከሚጣሉት ጋር እንደሚጣላ፣ (ኢሳይያስ 49፥252 ኔፊ 6፤17 ተመልከቱ)፣ መከራችንን ለራሳችን ጥቅም እንደሚቀባው በቂ እምነት አለን? (2 ኔፊ 2፥2 ተመልከቱ)።

በምድራዊም ሆነ በመንፈሳዊ እንዲባርከን ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ በቂ የሆነውን እምነት እንለማመዳለንን? ወደ መገኛው ይቀበለን ዘንድ እስከመጨረሻ ድረስ በእምነት እንቀጥላለንን? ሞዛያ 2፥41 ተመልከቱ።

ወንድሞችና እህቶች፣ እርሱን ለማመን እምነቱ ሊኖረን ይችላል! ለእኛ መልካሙን ነገር ይፈልጋል (ሙሴ 1፥39)። ፀሎታችንን ይመልሳል (ት. እና ቃ. 112፥10)። ቃል-ኪዳኑን ይጠብቃል (ት. እና ቃ. 1፥38)። እነዛን ቃል-ኪዳኖች የመጠበቅ ኃይል አለው (አልማ 37፥16)። ሁሉንም ነገር ያውቃል። በተለይም ደግሞ፣ የቱ መልካም እንደሆነ ያውቃል። (ኢሳይያስ 55፥8–9 ተመልከቱ)።

አደገኛ ዓለም

ዛሬ አለማችን አስቸጋሪ ናት። ብዙ መጥፎ ነገሮች፣ በእያንዳንዱ ሃገር ሙስና፣ ሽብር ደህና ቦታዎችም ደርሷላ፣ የኢኮኖሚ መውደቅ፣ ስራ አጥነት፣ ነሽታ፣ የተፈጥሮ አረጋ፣ ሃገራዊ ጦርነት፣ አምባ ገነን መሪዎች ወዘተ አሉን። ምን ማድረግ አለብን? መሸሽ ወይም መዋጋት ነው ያለብን? የትኛው ትክክል ነው? ሁሉቱም ምርጫዎች አደጋኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ለጆርጅ ዋሺንግተን እና ለወታደሮቹ መዋጋት አደገኛ ነበር፣ እንዲሁም ለመስራች ዘሮቻችንም መሸሽ አደገኛ ነበር። ለኔልሰን ማንዴላ ለነፃነት መታገል አደገኛ ነበር። ክፋት እንዲሰፍን መልካም ሰዎች ምንም እንዳያደርጉ አስፈላጊ ነው ተብሎ ነበር።4

አትፍሩ!

በምናደርገው ማንኛውም ነገር፣ በፍርሃት መንፈስ መወሰን ወይም መተግበር የለብንም። በእውነት “እግዚአብሔር የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም (2 ጢማቴዎስ 1፥7)። (“አትፍሩ” የሚለው ሀሳብ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ በሙሉ ትኩረት እንደተሰጠው ተረድታችኋልን?” ጌታ ተስፋ መቁረጥና ፍርሃት የጠላት መሳሪያ እንደሆኑ አስተምሮኛል። ለከባድ ጊዜያት የጌታ መልስ በእምነት ወደፊት መጓዝ ነው።

ከማድ ምንድን ነው?

እያንዳንዳችን ከባድ ምን እንደሆነ የተለየ ሃሳብ ሊኖረን ይችላል። አንዳንዶች ገንዘብ ሲያጥራቸው አስራት መክፈልን እንደ ከባድ ነገር ያዩት ይሆናል። መሪዎች እንድ እንድ ጊዜ ደሃዎች አስራት መክፈል እንዳለባቸው መገመቱን እንደ ከባድ ነገር ያዩታል። ለአንዳንዶቻችን በእምነት ወደ ፊት ተጉዞ ማግባትና ቤተሰብ መመስረት ከባድ ሊሆን ይችላል። አንዳንዶች “ጌታ በሰጣቸው ነገሮች ፀብን መፍጠሩን” እንደ ከባድ ነገር ያዩታል (አልማ 29፥3)። ባለን ጥሪ እርካታ ለማግኘት ከባድ ይሆናል (አልማ 29፥6 ተመልከቱ)። የቤተክርስቲያን ፀባይ ማረሚያ ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ለተወሰኑት የትክክለኛ ንስሃ መጀመሪያ ምልክት ይሆና።

ጉዳዩ ምንም ይሁን ምን፣ ከባድ ነገር በእምነት ወደ ፊት ለሚጓዙ እና ጌታንና ዕቅዱን ለሚያምኑ ሰዎች ጥሩ ሊሆን ይችላል።

የእኔ ምስክር

ወንድሞቼና እህቶቼ፣ አነዚህ ከኋላዬ የተቀመጡት መሪዎች በእግዚአብሔር እንደተጠሩ እመሰክራለሁ። ፍላጎታቸው ጌታን በደንብ ማገልገልና ወንጌልን በልቦቻችን ውስጥ እንድንመሰርት ለመርዳት ነው። እነርሱን እወዳቸዋለሁ እናም እደግፋቸዋለሁ።

አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ። አብንና እኛን በመውደዱ የተነሳ “በህመሙ ምክንያት ተንቀጥቅጦ እና በእያንዳንዱ የሰውነት ቀዳዳ እስኪደማ ድረስ አካላዊና መንፈሳዊ ስቃይን” (ት. እና ቃ. 19፥18) በማየት አዳኛችንና ቤዛችን መሆን ስለቻለ እገረማለሁ። Yይሁን እንጂ፣ ይህን አሰቃቂ ነገር በመጋፈጥ “የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ” (Luke 22:42) ብሎ ለአብ አረጋገጠ። እንዲህ በሚለው በመላዕኩ ቃሎች እደሰታለሁ። “ተነስቷልና በዚህ የለም” (Matthew 28:6)።

የእርሱ ምሳሌ እውነትም “መንገድም፣ እውነትም እና ሕይወትም” (ዮህንስ 14:6) ነው። ያንን ምሳሌ በመከተል ብቻ ነው “በዚህ ዓለም ሰላምን እና ዘላለማዊ ሕይወትን በሚቀጥለው ዓለም” (ት. እና ቃ. 59፥23) ማግኘት የምንችለው። የእርሱን ምሳሌ ስከተል እና ትምህርቱን ስጠቀምባቸው፣ የእርሱ “በጣት ታላቅ እና ውድ ቃል ኪዳኖቹ” (2 ጴጥሮስ 1፥4) እውነት እንደሆኑ ለራሴ ተማርኩኝ።

የእኔ ታላቅ ምኞት እንደ እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ከሞረሞን ጋር መቆም (3 ኔፊ 5፥13) ና አንድ ቀን ከራሱ ከንፈር “መልካም አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ” (ማቴዎስ 25፥21) የሚለውን መስማት ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Lectures on Faith (1985), 69.

  2. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “ምርጫዎች፣”Liahona፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 86።

  3. ቶማስ ኤስ ሞንሰን፣ “ቤተመቅደስ—ለአለም ምልክት፣”Liahona፣  ግንቦት 2011 (እ.አ.አ.)፣ 92።

  4. See John Stuart Mill, Inaugural Address: Delivered to the University of St. Andrews, Feb. 1, 1867 (1867), 36.