ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
የካቲት 15-21 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14–17፥ “ምስክር ሆነህ ትቆም ዘንድ”


“የካቲት 15-21 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14-17፥ ‘ምስክር ሆነህ ትቆም ዘንድ፣’” ኑ ተከተሉኝ—ለግለሰቦችና ለቤተሰቦች፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“የካቲት 15-21 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14-17፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ እና ሶስቱ ምስክሮች ለጸሎት ተንበርክከው

የካቲት 15–21 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14–17

“ምስክር ሆነህ ትቆም ዘንድ”

የጆሴፍ ስሚዝ የቤተሰብ አባላትና ጓደኞች ጌታ እነርሱ ምን እንዲያደርጉ እንደሚፈልግ በሚመለከት ራዕይን እንዲሻ አንዳንዴ ይጠይቁታል። እነዚህን ራዕዮች ስታነቡ፣ ጌታ ለእናንተ ምን አይነት መመሪያ እንዳለው አስተውሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ምንም እንኳን የትርጉም ስራው በደንብ እየሄደ የነበረ ቢሆንም፣ በግንቦት 1829 (እ.አ.አ) በሃርመኒ ውስጥ የነበረው ሁኔታ ለጆሴፍ፣ ኤማ፣ እና ኦሊቨር በጣሙን ከባድ ሆኖ ነበር። ከጎረቤቶቻቸው ጥላቻ እያደገ ሲሄድ ከኤማ ቤተሰብ በኩልም የነበረው ድጋፍ እየላላ ሄደ። ሃርመኒ ከዚህ በኋላ ደህንነት የሌለበት ቦታ እየሆነ ስለሚሰማቸው፣ ኦሊቨር በጆሴፍ ስራ ላይ ፍላጎትን አሳድሮ የነበረው ጓደኛውን ዴቪድ ዊትመር ለእርዳታ ጠየቀው። ዴቪድ ከወላጆቹና ከእህት ወንድሞቹ ጋር በ100 ማይል (161 ኪሎ ሜትር) ርቀት ባለው በፋይት ኒው ዮርክ ውስጥ ይኖር ነበር። ኦሊቨር ጋር ከአመት በፊት ተገናኝቶ ነበረ፣ እናም ኦሊቨርም ከነቢዩ ጋር በመስራት የነበረውን ተሞክሮ በተለያዩ ደብዳቤዎች ከዛን ጊዜ አንስቶ እየጻፈለት ነበር። ዴቪድም ሆነ ማንኛውም የቤተሰቡ አባላት ከጆሴፍ ጋር ተገናኝተውት አያውቁም ነበር። ነገር ግን ኦሊቨር እርሱና ጆሴፍ የመጽሐፈ ሞርሞንን ትርጉም መጨረስ ይችሉ ዘንድ በዊትመር ቤት ውስጥ ስለመኖር ሲጠይቅ፣ የዊትመር ቤተሰቦች ዝግጁ ሆነው በሮቻቸውን ክፍት አደረጉ። ጌታም ለዊትመር ቤተሰቦች ነቢዩን በቤታቸው ከማኖር በላይ ተጨማሪ አላማ ለእነርሱ ነበረው። ለእነርሱም በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14–17 ውስጥ የሚገኘው በቀጥታ የተሰጠ መመሪያ ነበረው፣ እናም እነርሱ ከጊዜ በኋላ ከቤተክርስቲያኗ መሰረታዊ ቤተሰቦች አንዱና እየተገለጠ ላለው የዳግም መመለስ ምስክሮችም ይሆኑ ነበር።

ስለዊትመር ቤተሰብ በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥68–71ን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክቶች

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14

በእግዚአብሔር “ታላቅ እና ድንቅ ስራ” ላይ ተሳታፊ መሆን እችላለሁ።

ጆሴፍን በተዋወቀበት ወቅት፣ ዴቪድ ዊትመር በቤተሰቡ እርሻ ላይ ታትሮ የሚሰራ ወጣት ነበር። ነገር ግን ምንም እንኳን በአንዳንድ መልኩ እንደ እርሻ አይነት ቢሆንም፣ ጌታ ለዴቪድ የተለየ ስራ ነበረው። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥1–4ን ስታነቡ፣ ጌታ ስራውን ዴቪድ ከሚያውቀው አይነት ስራ ጋር ሲያመሳስለው አስተውሉ። ስለጌታ ስራ ከንጽጽሩ ምን ትማራላችሁ?

እንዴት አድርጋችሁ “[ማጨድ] እናም [መሰብሰብ]” ትችላላችሁ? (ቁጥር 4)። በብዙ የዚህ ክፍል ውስጥ “ፅዮንን ወደፊት ለማምጣትና ለመመስረት [ለሚፈልጉ]” የተሰጠውን ቃል ኪዳን አስተውሉ (ቁጥር 6)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥2

የእግዚአብሔር ቃል “ፈጣን እና ሀያል” ነው።

ጌታ ቃሉን “ሁለት አንደበት ካለው ሰይፍ” ጋር ያነጻጽረዋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥2)። ይህ ንጽጽር ስለ እግዚአብሔር ቃል ምን ይጠቁማችኋል? ለምሳሌ፣ ቃሉ እንዴት ፈጣን፣ ሀያል፣ እና የተሳለ ነው? የእግዚአብሔር ቃል ሃይል እንዴት ተሰምቷችሁ ታውቃላችሁ?

እግዚአብሔር ቃሉን የሚገልጽበትን ሊሎች መንገዶች አስተውሉ። ለምሳሌ፣ ከሚቀጥሉት አንቀጾች ውስጥ ካሉት ንጽጽሮች ስለእግዚአብሔር ቃል ምን ትማራላችሁ?

መዝሙር 119፥105 

ኢሳያስ 55፥10–11 

ማቴዎስ 4፥4 

1 ኔፊ 15፥23–24 

አልማ 32፥28 

ምስል
ሰይፍ በቅዱሳትን መጻህፍት ውስጥ

ጌታ ቃሉን ከሰይፍ ጋር አነጻጸረ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥7

ዘላለማዊ ህይወት “ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነ” ነው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥7ን ስታነቡ፣ ዘለአለማዊ ህይወት “ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነው” ለምን እንደሆነ አሰላስሉ። ይህ የፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን አስተያየት ሊረዳችሁም ይችላል፥ “በእግዚአብሔር ታላቅ የደስታ እቅድ ስር ቤተሰቦች በቤተመቅደስ ውስጥ ሊጣመሩና በእርሱ ቅዱስ ስፍራው ተመልሰው ለዘለአለም ለመኖር ይዘጋጃሉ። ይህም ዘለአለማዊ ህይወት ነው!” (“ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2012 (እ.አ.አ)፣ 77)።

ቁጥር 7 ላይ የጎንዮሽ ማጣቀሻን በመጨመር ስለ ዘለአለማዊ ህይወት ይበልጥ እንድትረዱ እንዲረዳችሁ አስቡበት (“ዘላለማዊ ህይወት” በአርዕስቶች መመሪያ ወይንም የቅዱሳት መጻህፍት መምሪያ ውስጥ፣ scriptures.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ)። ዘለአለማዊ ህይወትን እንድትመኙ የሚያነሳሳችሁ ምን ትምህርት አገኛችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15–16

ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ማምጣት ታላቅ ዋጋ አለው።

ጆን እና ፒተር ዊትመር በህይወታቸው “በጣም ትልቅ ዋጋ” ሊኖረው የሚችለው ምን እንደሆነ ሁለቱም ማወቅ ፈለጉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15፥416፥4)። እናንተስ ስለዚህ ጉዳይ አስባችሁ ታውቃላችሁን? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15–16ን ስታነቡ፣ ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ማምጣት ትልቅ ዋጋ ያለው ለምን እንደሆነ አሰላስሉ። ነፍሳትን እንዴት ወደ ክርስቶስ ትጋብዛላችሁ?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–16ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 17

ጌታ ቃሉ እንዲፈጸም ምስክሮችን ይጠቀማል።

ምስክር ምንድን ነው? ጌታ በስራው ምስክሮችን ለምን ይጠቀማል? (2 ቆሮንጦስ 13፥1ን ይመልከቱ)። የእግዚአብሔርን ቃል ለሶስቱ ምስክሮች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 17 ላይ ስታነቡ እነዚህን ጥያቄዎች አሰላስሉ። ደግሞም “የሶስቱ ምስክሮች ምስክርነትን” ከመፅሐፈ ሞርሞን ላይ መከለሱ ጠቃሚ ይሆናል። ምስክሮች እንዴት አድርገው ነዉ የእግዚአብሔርን “የጽድቅ አላማ” ለማምጣት የሚረዱት? (ቁጥር 4)።

ሜሪ ዊትመርም የወርቃማ ሰሌዳዎቹን ምስክርነት እንደተቀበለች ታውቃላችሁን? መልአኩ ሞሮኒ ጆሴፍ፣ ኤማ፣ እና ኦሊቨር በቤቷ በኖሩበት ጊዜ ለከፈለችው መስዋዕትነት እውቅና ለመስጠት ለእርሷ እነዚህን አሳያት (ቅዱሳን፣ 1፥70–71ን ይመልከቱ)። ምስክርነትን ስለመቀበል ከእርሷ ተሞክሮ ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ቅዱሳን፣1፥73–75፤ ዮሊሰስ ሶሬስ፣ “የመፅሐፈ ሞርሞን መምጣት፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 32–35 ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና የቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥1–4በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ከእርሻ ጋር የተያያዙ ቃላትን ቤተሰባችሁ እንዲፈልጉ ጋብዟቸው። ጌታ ስራውን ከአዝመራ ጋር ለምንያነጻጽር ይሆናል? በእርሱ ስራ ለማገዝ ምን ማድረግ እንችላለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥2“ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ጠቃሚ ሃሳቦች” ውስጥ የሚገኘው የዚህ ጥቅስ መሳተፊያ ስለእግዚአብሔር ቃል የሚገልጹ አንቀጾችን ይዘረዝራል። ምናልባትም የቤተሰብ አባላት ሊያነቧቸውና ምን እንደተማሩ ሊያካፍሉ ይችላሉ። እነዚህ ጥቅሶች እንዴት አድርገው ነው የእግዚአብሔር ቃል “ለማድመጥ” እንድንችል የሚረዱን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15፥616፥6እነዚህ ጥቅሶች በቤተሰባችሁ ውስጥ በጣም ትልቅ ዋጋ ስላላቸው ነገሮች ውይይት እንድታደርጉ ሊያነሳሱ ይችላሉ (በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10 ን ይመልከቱ)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 17ቤተሰባችሁ ሶስቱ ምስክሮች ያዩአቸውን እያንዳንዱን እቃዎች በመሳል ሊደሰት ይችላል(ቁጥር 1ን ይመልከቱ)። ክፍል 17ን ስታነቡ፣ የመፅሐፈ ሞርሞንን ጠቀሜታ የሚያስተምሩ ቃላትን ፈልጉ። የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮች እንዴት መሆን እንችላለን? ቤተሰባችሁ “አንድ ቀን ለዘለአለማዊነት” የሚለውን ቪድዮ መመልከት ይችላል (ChurchofJesusChrist.org)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከሩ መዝሙሮች፥ “አንተ ወደ ፈለግከው እሄዳለሁ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 270።

ምስል
በዳግም የመመለስ ድምጾች ምልክት

በዳግም የመመለስ ድምጾች

ሉሲ ማክ ስሚዝ እና ሶስቱ እና ስምንቱ ምስክሮች

መልዐኩ ሞሮኒ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ለኦሊቨር ካውድሪ፣ ለዴቪድ ዊትመር፣ እና ለማርቲን ሃሪስ በፌየት፣ ኒው ዮርክ አቅራቢያ ባለው ጫካ ውስጥ ወርቃማዎቹን ሰሌዳዎች አሳያቸው። የጆሴፍ ወላጆች በዛ ወቅት ከዊትመር ቤተሰብ ዘንድ እንግድነት ላይ ነበሩ። ሉሲ ማክ ስሚዝ፣ የጆሴፍ እናት፣ ይህ ተአምራዊ ተሞክሮ በምስክሮቹ ላይ የነበረውን ተጽዕኖ እንዲህ ገልጸዋል፥

ምስል
ሉሲ ማክ ስሚዝ

“በሶስት እና አራት ሰአት መሃከል ነበር። ወ/ሮ ዊትመር እና አቶ ስሚዝ እና እኔ በአንዱ መኝታ ቤት ተቀምጠን ነበር። ከአልጋው ጎን ተቀምጬ ነበር። ጆሴፍ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ እራሱን አጠገቤ አልጋው ላይ ወረወረ። ‘አባዬ! እማዬ!’ አለ። ‘ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ አታውቁም። ጌታ ከእኔ ሌላ ሰሌዳዎቹን ለሶስት ሰዎች አሳየ፣ መልአክንም ተመለከቱ እናም ስለተናገርኩት ነገር እውነትነት መመስከር አለባቸው። ሰዎችን ለማጭበርበር እንደማልንቀሳቀስ እነርሱ ለራሳቸው አውቀዋል። እናም ልቋቋመው ከምችለው በላይ በጣም ከባድ ሸክም እንደተገላገልኩኝ ለራሴ እየተሰማኝ ይገኛል። ነገር ግን እነሱም የተወሰነውን ይሸከማሉ፣ እናም በዚህ አለም ላይ ብቻዬን አለመሆኔን ማወቄ ነፍሴን ያስደስታታል።’ ከዛም ማርቲን ሃሪስ ወደ ውስጥ ገባ። በደስታ ብዛት የተዋጠ ይመስላል። እርሱም ስላየውና ስለሰማው መሰከረ፣ ሌሎቹም ኦሊቨርና ዴቪድም እንዲሁ አደረጉ። ምስክርነታቸው በመፅሐፈ ሞርሞን ላይ እንዳለው በይዘቱ አንድ ነበር። …

“ማርቲን ሃሪስ በተለይ ለስሜቱ በቃላት ዘርዝሮ መጨረስ ሁላ የተሳነው ይመስላል። እንዲህም አለ ‘አሁን ስለጽሁፎቹ የሰማሁትን ሁሉ በእርግጠኝነት እውነት እንደሆነ የመሰከረልኝን ከሰማይ የመጣ መልአክ አይቻለሁ፣ እንዲሁም በአይኔ አይቼዋለሁ። እናም ነሃሶቹን አይቻለሁ እናም በእጄም ዳስሻቸዋለሁ እናም ስለዚሁ ለአለም ሁሉ መመስከር እችላለሁ። ነገር ግን ለራሴ ቃላት የማይገልጹት፣ ምንም አይነት ንግግር የማያብራራው ምስክርነትን አግኝቻለሁ፣ እናም እግዚአብሔርን እራሱን ዝቅ አድርጎ እኔ ለዚያውም እኔን ለሰው ልጆች ታላቅ ስራውና እቅዱ ምስክር ስላደረገኝ ከልቤ በትህትና እባርከዋለሁ።’ ኦሊቨርና ዴቪድም እርሱን ተቀላቅለው መለኮታዊ ምስጋናን ለእግዚአብሔር ስለደግነቱና ምህረቱ አደረጉ። ወደ ቤታችን ወደ [ፓልማይራ፣ ኒው ዮርክ] በሚቀጥለው ቀን ደስተኛ ቡድን ሆነን ተመለስን።” 1

ምስል
ሶስቱ ምስክሮች

የኦሊቨር ካውድሪ፣ ዴቪድ ዊትመር፣ እና ማርቲን ሃሪስ ምስሎች በሉውስ ኤ. ራምዚ

ሉሲ ማክ ስሚዝ ስምንቱ ምስክሮችም ከተሞክሯቸው ሲመለሱ በስፍራው ነበሩ፥

“እነዚህ ምስክሮች ወደቤት ከተመለሱ በኋላ፣ መልአኩ በድጋሚ ለጆሴፍ ተገለጠ፣ በዚህ ወቅትም ጆሴፍ ሰሌዳዎቹን በእጁ አስረከበው። በዛን ምሽት ስብሰባን አደረግን፣ በዚሁም ሁሉም ምስክሮች ምስክርነታቸውን ከላይ በተገለጸው መልኩ ሰጡ፤ መላ ቤተሰባችን፣ እንዲሁም ምንም እንኳን 14 አመቱ ቢሆንም ዶን ካርሎስ [ስሚዝ] እንኳን ሳይቀር ስለኋለኛው ቀን የዘመን ፍጻሜ፣ ይህም በሙላት እንደመጣ፣ ምስክርነት ሰጡ።”2

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ ለስምንቱ ምስክሮች ሰሌዳዎችን ሲያሳይ

የጆሴፍ ስሚዝና የስምንቱ ምስክሮች ቅርጽ በጌሪ ኧርነስት ስሚዝ

ምስል
መልአኩ ሞሮኒ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ኦሊቨር ካውድሪ፣ እና ዴቪድ ዊትመር የወርቅ ሰሌዳዎችን ሲያሳይ

መልአኩ ሞሮኒ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ኦሊቨር ካውድሪ፣ እና ዴቪድ ዊትመር የወርቅ ሰሌዳዎቹን ሲያሳይ በጌሪ ቢ. ስሚዝ

አትም