ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ጥር 25–31 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–9፥ “ይህ የራዕይ መንፈስ ነው”


“ጥር 25–31 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–9፥ ‘ይህ የራዕይ መንፈስ ነው’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ጥር 25–31 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–9፥ ‘ይህ የራዕይ መንፈስ ነው’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ጸሃፍ በወረቀት ላይ ሲጽፍ

ጥር 25–31 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–9

“ይህ የራዕይ መንፈስ ነው”

ጌታ እውነቶችን በአዕምሮአችንና በልባችን ይገልጽልናል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፥2–3ን ይመልከቱ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–9ን ስታነቡ የሚመጣላችሁን ግንዛቤዎች መዝግቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በ1828 (እ.አ.አ) ክረምት ወቅት ኦሊቨር ካውድሪ የተባለ አንድ ወጣት የትምህርት ቤት አስተማሪ በማንቸስተር ኒው ዮርክ የአስተማሪነት ስራን አገኘ፣ እናም ከሉሲ እና ጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ ጋር ይኖር ነበር። ኦሊቨር አሁን ሃርመኒ፣ ፔንስልቫኒያ እየኖረ ስላለው ልጃቸው ጆሴፍ ሰምቶ ነበር፣ እናም እራሱን እንደ እውነት ፈላጊ የሚመለከተው ኦሊቨር ስለእርሱ ተጨማሪ ለማወቅ ፈለገ። የስሚዝ ቤተሰቦችም ስለመላእክት ጉብኝቶች፣ ስለጥንታዊ ጽሁፎች፣ እናም ከእግዚአብሔር በመጣ ሃይል ስለመተርጎም ስጦታ ገልጸው ነገሩት። ኦሊቨርም በጣም ተደነቀ። እውነት ሊሆን ይችላልን? ሉሲና ጆሴፍ ቀዳማዊ ለሁሉም የሚሰራውን ምክር ለገሱት፥ ጌታን በጸሎት ይጠይቅ።

ኦሊቨርም እንዲያው አደረገ፣ እናም ለኦሊቨር አእምሮ ሰላምንና ማረጋገጫን በመስጠት ጌታም መለሰ። ራዕይ የግል ሊሆን እንደሚችል ኦሊቨር ተረዳ—ስለዚህም በይበልጥ በመጪው ወራት በስፋት ይማራል። ራዕይ ለነቢያት ብቻ ሳይሆን ለሚፈልጉትና ለሚሹት ሁሉ ነው። ኦሊቨር ሁሉንም ነገር ባያውቅም ግን ቀጣዩን እርምጃውን ለመውሰድ በቂ ነገር አውቋል። ጌታ በጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት በጣም ጠቃሚ ነገር እያደረገ ነበር፣ እና ኦሊቨርም የዚሁ አካል ለመሆን ፈለገ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–9 በስተኋላ ስላለው ታሪክ በይበልጥ ለመረዳት፣ ቅዱሳን፣ 1፥58–64፤ “Days of Harmony [የሃርመኒ ቀናት]” (ቪድዮ፣ ChurchofJesusChrist.orgን ይመልከቱ)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68–9

የሰማይ አባት እኔን በ“እውነት መንፈስ” ያናግረኛል።

በ1829 (እ.አ.አ) ጸደይ ኦሊቨር ካውድሪ ወደ ሃርመኒ ተጉዞ ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን በሚተረጉምበት ወቅት እንደጸሃፊ ለማገልገል በጎ ፈቃደኛ ሆነ። ኦሊቨር አሁን በራዕይ ስለሚመራው ትርጉም ሂደት ቅርብ የሆነ እይታ ነበረው። ተሞክሮው እጅጉን አስደነቀው፣ እናም እርሱም በመተርጎም ስጦታ ይባረክ እንደሆን ማሰብ ጀመረ። ጌታም እንዲተረጉም እድሉን ሰጠው፣ ነገር ግን ራዕይን መቀበል ለኦሊቨር አዲስ ነገር ስለነበር ሙከራው አልተሳካም። ብዙ መማር የሚቀረው ነገር ነበር፣ እናም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፣ እናም9 እንደ ጌታ ሊያስተምረው ፈቃደኛ እንደነበር ያሳያሉ።

እነዚህን ክፍሎች ስታነቡ፣ ጌታ ስለግል ራዕይ ምን እንዳስተማረው አስተውሉ። እናንተ ከነበራችሁ ተሞክሮ ወይንም እንዲኖራችሁ ከምትፈልጉት ተሞክሮ ጋር የእርሱ ቃላት እንዴት ይዛመዳሉ?

ለምሳሌ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥5–78፥19፥7–8 ጌታ የእርሱን ፍቃድ ከመግለጹ በፊት ከእናንተ ምን እንደሚሻ ምን ሃሳብ ያቀርባሉ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥14–17፣ 22–248፥2–39፥7–9 ውስጥ ስለተለያዩ ራዕይ ሊመጣባቸው ስለሚችሉ መንገዶች ምን ትማራላችሁ?

ከእነዚህ ክፍሎች ስለራዕይ ሌላ የምትማሩት ነገርስ አለን?

ስለ ራዕይ በተጨማሪ ለመማር የሚቀጥሉትን ይመልከቱ፥ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ራዕይ ለቤተክርስቲያን፣ ራዕይ ለህይወታችን፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 93–96፤ ጁሊ ቢ. ቤክ፣ “ደግሞም በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ግንቦት 2010 (እ.አ.አ)፣ 10–12። በክፍል 8 ውስጥ ስለተጠቀሱት የ“አሮን ስጦታዎች” ይበልጥ መረጃ ለማግኘት፣ “የኦሊቨር ካውድሪ ስጦታዎች፣” ራዕያት በአገባብ 15–19 ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥18–21፣ 29–37

በሃሳባችሁ ሁሉ ወደክርስቶስ ተመልከቱ።

ምንም እንኳን ጆሴፍ የጌታን ስራ ሲሰራ “አስቸጋሪ ሁኔታ”ን ቢያጋጥመውም (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥18)፣ እርሱና ኦሊቨር በመጪዎቹ ብዙ አመታት እነዚህ ሁኔታዎች እንዴት ይበልጥ አስቸጋሪ እንደሚሆኑ ምንም ግምቱ አልነበራቸውም። ነገር ግን ጌታ ይህን ያውቅ ነበር፣ እናም እርሱ በእናንተም ቀጣይ ህይወት ላይ ስለሚመጡት ፈተናዎችም ያውቃል። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥18–21፣ 29–37 ላይ ለጆሴፍ እና ኦሊቨር የሰጠው ምክር እናንተንም ሊረዳ ይችላል። ጆሴፍና ኦሊቨር እነዚህን ቃላት ከሰሙ በኋላ ምን ሊሰማቸው ይችላል? በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ በጌታ እንድትታመኑ የሚያደርጋችሁ ምን ነገር ታገኛላችሁ? በህይወታችሁ የበለጠ ወደጌታ እንዴት መመልከት ትችላላችሁ?

ምስል
ኦሊቨር ካውድሪ

ኦሊቨር ካውድሪ በልውስ ኤ. ራምዚ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–79፥3፣ 7–14

“ላደርግላችሁ እንደምትሹ እንዲሁ ይሆንላችኋል።”

ምን ያህል ጊዜ “መሻት” ወይንም “መፈለግ” የሚለው ቃል በክፍል 6 እና 7 እንደሚገኝ ልብ በሉ። እግዚአብሔር በመሻታችሁ ላይ ስለሚጥለዉ አስፈላጊነት ከእነዚህ ክፍሎች ምን ትማራላችሁ? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 7፥1 ውስጥ ያለውን “ምንን ትሻለህ” የሚለውን የጌታን ጥያቄ እራሳችሁን ጠይቁ።

የኦሊቨር ካውድሪ ቅዱስ የሆነ፣ ልክ እንደ ጆሴፍ ስሚዝ የመተርጎም ፍላጎቱ አልተሳካም ነበር። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 9፥3፣ 7–14ን ስታነቡ፣ የተቀደሱ ፍላጎቶቻችሁ ሳይሟሉ ሲቀሩ ሊረዳችሁ የሚችል ምን ሃሳብን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥8፤ ዳለን ኤች. ኦክስ “እሹኤንዛይን ወይም ሊያሆና ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 42–45ን ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥7፣ 13ቤተሰባችሁ እውነተኛ “ሃብት” ከዘለአለማዊ ህይወት እንደሚገኝ እንዲረዱ እንዴት ለማድረግ ትችላላችሁ? (ቁጥር 7)። የቤተሰብ አባሎቻችሁን የውሸት ገንዘብ እንዲሰሩ፣ እናም እላዩ ላይ በመጻፍ ወይም በመሳል ወንጌሉ በዳግም በመመለሱ ቤተሰባችሁ ከተቀበሏቸው ብዙ በረከቶች አንዳንዶችን እንዲጽፉ ጋብዟቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥15፣ 22–238፥2–39፥7–9እግዚአብሔር ልጆቹን ሲያናግር የሚገልጹትን ጥቅሶች በማንበብም፣ እናንተ እርሱ እንዴት እንዳናገራችሁ ለመግለጽ መልካም አጋጣሚ ሊሆንላችሁ ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥33–37የቤተሰብ አባላት ፍራቻ ቢኖርባቸውም እንኳን “መልካም ማድረግ” የሚችሉበትን መንገዶች ማካፈል ይችላሉ። የሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ የሆነውን “አትሸበሩ” (ኤንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2018 (እ.አ.አ), 18–21) የሚል መልእክትን ሁሉ ወይም ጥቂት ክፍል መመልከት ደግሞም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። “ባሰባችሁት ነገር ሁሉ ወደ [ክርስቶስ] ተመልከቱ” ማለት ምን ማለት ነው? (ቁጥር 36)። ጥርጣሬና ፍራቻን ለማሸነፍ ሲኖርባቸው ወደ ጌታ የተመለሱ አንዳንድ የሌሎች ሰዎች ምሳሌዎች ምንድን ናቸው? (ለምሳሌ አስቴር 4አልማ 26፥23–31ን ይመልከቱ)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፥10በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁ እምነት አንዴት አድርጎ እናንተንና ቤተሰባችሁን እንዳጠናከራችሁ ለማካፈል ይህ መልካም አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። ለምንድን ነው በ“እምነት መጠየቅ” ጠቃሚ ሊሆን የሚችለው? በእምነት መልስን ወይንም እርዳታን በመሻት ምን አይነት በረከትን አግኝታችኋል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ትክክለኛውን ለማድረግ ጣሩ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 158።

ምስል
በዳግም የመመለስ ድምጾች ምልክት

በዳግም የመመለስ ድምጾች

የመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም

በሚያዝያ 1829 (እ.አ.አ) በክፍሎች 6–9 ያሉት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች በተረከበበት ወር ውስጥ፣ የጆሴፍ ስሚዝ ዋናው ስራው መፅሐፈ ሞርሞንን መተርጎም ነበር። ከዚያ በኋላ እንዴት ይህን መዝገብ እንደተረጎመ ሲጠየቅ፣ ጆሴፍ “ለአለም እያንዳንዱን ዝርዝር መንገር አስፈላጊ አይደለም”1 አለ። ብዙውን ጊዜ ቀለል ባለ መልኩ የተተረጎመው “ በእግዚአብሔር ስጦታና ሃይል ነው” ይል ነበር።2

ስለተአምራዊ የትርጉም ሂደቱ ብዙ አናውቅም፣ ነገር ግን ጆሴፍ ስሚዝ እግዚአብሔር ባዘጋጀለት መሳሪያዎች፣ እንዲሁም ሁለት አንጸባራቂ በሆኑ ዩሪም እና ቱሚም በሚባሉ ድንጋዮችና ሌላ ተጨማሪ ገላጭ ተብሎ በሚጠራ ድንጋይ የሚረዳ፣ ገላጭ እንደነበር እናውቃለን።3

የአይን ምስክሮች የተናገሯቸው ተከታዮቹ ስለትርጉም ሂደቱ የጆሴፍን ምስክርነት ይደግፋሉ።

ምስል
የወርቅ ሰሌዳዎቹን የያዙት የሃይረም ስሚዝ የእንጨት ሳጥን

እንደሚታመነው የሃይረም ስሚዝ የነበረው ይህ ሳጥን በጊዜያዊነት የወርቅ ሰሌዳዎችን ለመሸሸግ አገልግሏል።

ኤማ ስሚዝ

ምስል
ኤማ ስሚዝ

“ባለቤቴ መፅሐፈ ሞርሞንን በሚተረጉምበት ወቅት፣ እርሱ እያንዳንዱን አረፍተነገር በማንበብ ቃል በቃል ሲናገርና አንዳንድ ማለት የሚያስቸግሩት ስሞች ሲኖሩም ወይም ረጅም ቃላት ሲሆኑ ፊደል እየቆጠረ በሚያነብበት ጊዜ፣ እኔ የተወሰነውን ክፍል እጽፍ ነበር፤ እኔ በምጽፍበት ወቅት የፅህፈት ስህተት ሳደርግ፣ ምንም እንኳን ምን እንደጻፍኩ ለማየት በምንም ባይቻለውም አቁሞ ስህተቴን ያርም ነበር። ሳራ የሚለውን ቃል እንኳን በመጀመሪያ ማለት አይችልም ነበርና ቃል በቃል ይዘረዝረው ነበር፣ እና እኔም እንዴት እንደሚባል እልለት ነበር።”4

“ሰሌዳዎቹ ብዙውን ጊዜ ምንም መደበቅ ሳያስፈልጋቸው ጠረጴዛ ላይ እኔ በሰጠሁት በትንሽ የጠረጴዛ ላይነን ጨርቅ ተሸፍነው ይቀመጡ ነበር። በአንድ ወቅት ሰሌዳዎቹን በጠረጴዛ ላይ ሳሉ መስመራቸውን እና ቅርጻቸውን በመመልከት ዳሰስኳቸው። ልክ እንደ ወረቀት ጠንካራ ይመስል ነበር፣ እናም ልክ አንዳንዴ ሰዎች ከጠርዝ ጠርዝ መጽሃፍ በእጅ ሲገልጡ እንደሚሰማው አይነት ድምጽ በጣት ከጠርዙ ሲገለጥ እንደ ብረት አይነት ድምፅ ይፈጥራል።

“የእኔ እምነት መፅሐፈ ሞርሞን እውነተኛ መለኮታዊ መሆኑን ነው—ስለዚህ ምንም አይነት ቅንጣት ጥርጣሬ የለብኝም። የዚህን ጽሁፍ ሃሳቦች አንድ ሰው የተነሳሳ ካልሆነ በስተቀር በራሱ ሃሳቦቹን አመንጭቶ እንደማይናገር በማወቄ ለእኔ በቂ ማሳመኛ ነው፤ እኔ እንደጸሃፊው ሆኜ ሳገለግል [ጆሴፍ] ለረጅም ሰአታት የምጽፈውን በቃሉ ይደረድራል፤ እናም ከምግብ በኋላ ወይም በሌሎች ጉዳዮች ከመቋረጥ በኋላ ስንመለስ፣ ምንም ጹሁፉን ማየት ሳያስፈልገዉና ቅድም ያቆመበት ክፍል ሳይነበብለት ወዲያው ካቆመበት ይቀጥላል። ይህን ማድረግ ለእርሱ ዘወትር የተለመደ ነገር ነበር። ምናልባትም ለተማረም ሰው ይህንን ማድረግ ቀላል ላይሆን ይችላል፤ እናም እንዳልተማረ ሰው ይሄንን ማድረጉ በፍጹም የማይቻል ነበር።”5

ምስል
ኤማ ስሚዝ በትርጉሙ ስታግዝ

የኤማ እና የጆሴፍ ስሚዝ ምስል በሚካኤል ቲ. ማልም

ኦሊቨር ካውድሪ

ምስል
ኦሊቨር ካውድሪ

“በራሴ እስክርቢቶ ሙሉውን መፅሐፈ ሞርሞን (ከጥቂት ገጾች በስተቀር)፣ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ሃይል በዩሪምና ቱሚም፣ ወይም በመጽሃፉ እንደሚገለጹት፣ በቅዱስ ተርጓሚዎች፣ በመታገዝ ከነቢዩ አፍ እንደወረደ ጽፌአለሁ። የተተረጎሙበትን ወርቃማ ሰሌዳዎችንም በራሴ አይን አይቼና በእጆቼ ዳስሻለሁ። መተርጎሚያዎቹንም በእጄ ይዣለሁ።”6

ማስታወሻዎች

  1. ቃለ-ጉባኤ፣ 25–26 ጥቅምት 1831 (እ.አ.አ)፣” ቃለ ጉባኤ መጽሃፍ 2፣ 13፣ josephsmithpapers.org

  2. በ“ቤተክርስቲያን ታሪክ” ውስጥ Times and Seasons [ጊዜና ወቅቶች] መጋቢት 1፣ 1842 (እ.አ.አ)፣ 707፤ እንዲሁም Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [የቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንቶች አስተምህሮ፥ ጆሴፍ ስሚዝ] 2007 (እ.አ.አ)፣ 441ን ተመልከቱ።

  3. ለተጨማሪ መረጃ፣ “Book of Mormon Translation [መፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም]፣” የወንጌል አርስቶች፣ topics.ChurchofJesusChrist.org፤ ሪችርድ ኢ. ተርሊ ዳግማዊ፣ ሮቢን ኤስ. ጄንሰን፣ እና ማርክ አሽኸርስት-መጊ፣ “Joseph the Seer [ጆሴፍ ገላጩ]፣” ኤንዛይን ጥቅምት 2015 (እ.አ.አ)፣ 48–55 ይመልከቱ።

  4. በኤድመንድ ሲ. ብሪግስ “A Visit to Nauvoo in 1856 [ጉብኝት በናቩ በ1856 (እ.አ.አ)]” Journal of History [የታሪክ ማህደር]፣ ቅጂ 9፣ ቁጥር 4 ጥቅምት 1916 (እ.አ.አ)፣ 454፤ በ ራስል ኤም. ኔልሰን የተጠቀሰ “A Treasured Testament [የተከበረ ምስክርነት]፣” ኤንዛይን ሐምሌ 1993 (እ.አ.አ)፣ 62።

  5. በ“Last Testimony of Sister Emma [መጨረሻ የእህት ኤማ ምስክርነት]” Saints’ Herald [የቅድስት ሄራልድ]፣ ጥቅምት 1፣ 1879 (እ.አ.አ)፣ 290፤ አጻጻፉ ዘመናዊ ተደርጓል።

  6. በReuben Miller journal [ሪዩበን ሚለር የግል ማህደር] ውስጥ፣ ጥቅምት 21 1848 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተ-መጽሃፍት፣ ሶልት ሌክ ሲቲ፤ ስርአተ ሆሄና አወቃቀሩ ዘመናዊ ተደርጓል።

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ ወርቃማዎቹን ሰሌዳዎች ሲተረጉሙ።

ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ ወርቃማዎቹን ሰሌዳዎች በመተርጎም ሂደት ብዙ ተምረዋል።

አትም