“ጥር 18–24 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3–5፥ ‘ስራዬ ወደፊት ይቀጥላል፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ጥር 18–24 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3-5፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)
ጥር 18–24 (እ.አ.አ)
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3–5
“ስራዬ ወደፊት ይቀጥላል”
ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠኑ ስለምትማሩትና ስለሚሰማችሁ ነገሮች ጻፉ። ይህም የተሰማችሁን ስሜት እንድታስታውሱና ከሌሎችም ጋር እንድትካፈሏቸው ይረዳችኋል።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ጆሴፍ ስሚዝ የጌታ ነቢይ በነበረበት በመጀመሪያዎቹ ጥቂት አመታት እንዲሰራው ስለተጠራበት “ድንቅ ስራ” ሁሉንም ነገር ገና አያውቅም ነበር። ነገር ግን አንድ የመጀመሪያ ተሞክሮው ያስተማረው ነገር ቢኖር በእግዚአብሔር ስራ ብቁ ሆኖ ለመገኘት አይኖቹ በእውነታ “ወደ እግዚአብሔር ክብር” ብቻ መሆን እንዳለባቸው ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4፥1፣ 5)። ለምሳሌ ጌታ፣ ጌታ ከእርሱ ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ምክር ቢሰጠው እንኳን የጌታን ምክር መከተል ነበረበት። ምንም እንኳን “ብዙ ራዕይ ቢቀበል፣ እናም ብዙ ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት ሀይል ቢኖረውም፣” የራሱ ፈቃድ በራሱ እይታ ከእግዚአብሔር ፍላጎት ይበልጥ አስፈላጊ ከሆነበት እርሱ “ውድቀት” ይሆንበታል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥4)። ነገር ግን ጆሴፍ ልክ የእግዚአብሔርን ስራ እንደመስራት አስፈላጊ የሆነ ሌላ ነገርን ተማረ፥ “እግዚአብሔር መሃሪ ነው፣” እናም ጆሴፍ ከልቡ ንስሃ ከገባ እርሱ “[አሁንም የተመረጠ]” ነበር (ቀጥር 10)። ከዛም በበለጠ የእግዚአብሔር ስራ የማዳን ስራ ነውና። እናም ያም ስራ “ሊከሸፍ … አይችልም”(ቀጥር 1)።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ሰዎችን ከመፍራት ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን አለብኝ።
በጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያዎቹ የአገልግሎቱ ጊዜያት ጥሩ የሆኑ ጓደኞችን ማግኘት በጣም ከባድ ነበር—በተለይም እንደ ማርቲን ሃሪስ አይነት የተከበረ፣ የበለጸገ፣ ጠቃሚ የሆኑ እርዳታዎችን ሊለግስ የሚችል አይነት ጓደኛ። ምንም እንኳን ከመሰሎቹ የነበረውን ከበሬታን ቢያጣም እና የገንዘብ መስዋዕትነት ቢያስከፍለውም ማርቲን በፍላጎቱ ጆሴፍን ረዳው።
ስለዚህ ማርቲን የመጀመሪያዎቹን የመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም ክፍሎች የመፅሐፈ ሞርሞንን እውነተኛነት ለምትጠራጠረው ባለቤቱ ለማሳየት ጆሴፍን ሲጠይቀው ለምን እሺ ለማለት ፍላጎት እንዳሳደረ ለማየት በጣም ቀላል ነው። ምንም እንኳን ጌታ ቢከለክልም፣ ስለዚህ ጥያቄ ጆሴፍ ጌታን በመጠየቅ ቀጠለ፣ በስተመጨረሻም ጆሴፍ ለሶስተኛ ጊዜ ከጠየቀ በኋላ ጌታም እሺ አለ። በሚያሳዝን ሁኔታም፣ ጽሁፎቹ በማርቲን ይዞታ እያሉ ጠፉ፣ በዚህም የተነሳ ጌታ ጆሴፍንና ማርቲንን በሃይለኛ ሁኔታ ገሰጻቸው (ቅዱሳን፣ 1፥51–53ን ይመልከቱ)።
እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥1–15ን ስታነቡ፣ የሌሎች ሰዎች አስተያየት ምናልባት እንዴት ተጽዕኖ እየፈጠረባችሁ እንደሆነ አሰላስሉ። ጆሴፍ ስሚዝን ከመገሰጽም በተጨማሪ ጌታ የምህረት ቃላትን እንደተናገረውም ልታስተውሉ ትችላላችሁ። ጌታ ጆሴፍን ካረመበት እና ካበረታታበት መንገድ ምን ትማራላችሁ? ሌሎችን ሰዎች ከእግዚአብሔር አስበልጦ የመፍራት ፈተና ሲገጥማችሁ የሚረዳችሁን ምን ምክር አገኛችሁ?
በተጨማሪም ይመልከቱ፥ “The Contributions of Martin Harris [ማርቲን ሀርስ አስተዋጽዖ]፣” ራዕያት በአገባብ፣ 1–9፣ history.ChurchofJesusChrist.org።
ጌታ በሙሉ ልቤ እንዳገለግለው ጠይቆኛል።
ክፍል 4 ብዙውን ጊዜ በሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን ላይ ይተገበራል። ነገር ግን ልብ መባል ያለበት አስደናቂው ነግር ቢኖር፣ ይህ ራእይ በቅድሚያ ተሰጥቶ የነበረው ምንም እንኳን እንደ ሚስዮን ለማገልገል ባይጠራም “እግዚአብሔርን ለማግልግል ፈቃድ” ለነበረው ጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ ነበር (ቁጥር 3)።
አንደኛው ይህንን ክፍል ማንበብያ መንገድ ልክ ለአንድ የእግዚአብሔርን ስራ ለመስራት ለሚፈልግ ሰው የተሰጠ የስራ ዝርዝር አድርገን በማሰብ ነው። መስፈርቶቹ ምንድን ናቸው? እነዚህ መገለጫዎችና መስፈርቶች ለምን አስፈላጊ ሆኑ? ምናልባትም በጸሎት ይበልጥ “[ራሳችሁን] ለስራው ብቁ” (ቁጥር 5) የሚያደርጋችሁን ነገር ለመምረጥ ትችላላችሁ።
ስለ መፅሐፈ ሞርሞን የራሴን ምስክርነት ማግኘት እችላለሁ።
ፍርድ ቤት ቀርባችሁ ስለ መፅሐፈ ሞርሞን እውነተኛነት መስክሩ ብትባሉ፣ ምን አይነት ማስረጃዎችን ይዛችሁ ትቀርባላችሁ? ባሌቤቱ ሉሲ ጆሴፍ ስሚዝ ሰዎችን ከወርቃማ ሰሌዳዎች ላይ እየተረጎምኩ ነው ብሎ እያጭበረበረ ነው ብላ በከሰሰች ጊዜ ተመሳሳይ ጥያቄ በማርቲን ሀሪስ አዕምሮ ላይ ነበር (ቅዱሳን፣ 1፥56–58ን ይመልከቱ)። ስለዚህም ማርቲን የወርቅ ሰሌዳዎቹ እውነት ስለመሆናቸው የሚያሳይ ተጨማሪ መረጃ እንዲያቀርብ ጆሴፍን ጠየቀው። ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 5 ለማርቲን ጥያቄቆች መልስ ለመስጠት የተሰጠ ራእይ ነው።
ከዚህ ቀጥሎ ስላሉት ነገሮች ከትምህርትና ቃል ኪዳኖች 5 ምን ትማራላችሁ፥
-
ጌታ መንፈሳዊ ስለሆኑ እውነታዎች ማስረጃ ካልቀረበላቸው በስተቀር ስለማያምኑ ምን እንደሚሰማው (ቁጥሮች 5–8፤ በተጨማሪም ዮሐንስ 20፥24–29ን ይመልከቱ)።
-
በጌታ ስራ ላይ ምስክሮች ስላላቸው ድርሻ (ቁጥሮች 11–15፤ በተጨማሪም 2 ቆሮንቶስ 13፥1ን ይመልከቱ)።
-
ለራሳችን እንዴት አድርገን ስለመፅሐፈ ሞርሞን ምስክርነት ማግኘት እንደምንችል (ቁጥር 16፤ በተጨማሪም ሞሮኒ 10፥3–5ን ይመልከቱ)።
ይህ ትውልድ የእግዚአብሔርን ቃል በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ይቀበላል።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥1–10 በዚህ ዘመን ፍጻሜና በራሳችሁ ህይወት ላይ ስለጆሴፍ ስሚዝ አስፈላጊ ሚና ምን ያስተምራችኋል? በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት እንዴት አድርጋችሁ የእግዚአብሔርን ቃል እንደተቀበላችሁ አሰላስሉ። በእርሱ አማካኝነት ስለተመለሱት ወይንም ግልጽ ስለተደረጉት እውነታዎች ያላችሁን አመስጋኝነት በግል ማህደራችሁ አስፍሩ ወይንም ለሌሎች አጋሩ።
በተጨማሪም 2 ኔፊ 3፥6–24ን ይመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥1–4።የቤተሰቡን አንድ አባል “በጠመዝማዛ” መስመር ላይ ከዛ ደግሞ “በቀጥተኛ” መስመር ላይ እንዲራመድ ጠይቁ። “[የእግዚአብሔር] መንገዱ ቀጥተኛ” መሆኑን ማወቅ ለቤተሰባችን ምን ትርጉም አለው?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥7–10።ሌሎች ሰዎች እግዚአብሔርን እንዳንታዘዘው ሲገፋፉን፣ ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የትኞቹ እውነታዎች ታማኝነታችንን ይዘን እንድንቀጥል ይረዱናል? ምናልባትም የቤተሰቡ አባላት ምንም አንኳን እግዚአብሔርን እንዳይታዘዝ ጫና ቢደርስበትም እንኳን ጸንቶ ሲቆም የሚያሳይ ሁኔታን ፈጥረው ጭውውት ማቅረብ ይችላሉ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4።ቤተሰባችሁ በእግዚአብሔር እርሻ ላይ መስራት ምን ትርጉም እንዳለው በሚወያዩበት ጊዜ በአትክልት ስፍራ ላይ መስራት (ወይንም የሚሰሩ ማስመሰል) ይችላሉ። በአትክልት ስፍራ ለመስራት የሚያስፈልጉን መሳሪያዎች ምን ናቸው? እግዚአብሔር በክፍል 4 ውስጥ የእርሱን ስራ ለመስራት ያስችላሉ ተብለው የሚወሰዱ ምን መሳሪያዎችን ገልጿል? ቤተሰባችሁ እያንዳንዱ መሳሪያ የእግዚአብሔርን ስራ ለመስራት ለምን ጠቃሚ እንደሆነ ለመወያየት ይችላሉ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥7።የምናምናቸው ነገር ግን የማናያቸው እውነቶች ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ አንዳንድ ነገሮች ምን ናቸው? መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ለማወቅ ማስረጃ ለሚሻ ጓደኛችን እንዴት አይነት ምላሽ ለመስጠት እንችላለን?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ “ጀግና እሆናለሁ ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 162።