“ታህሳስ 28፟–ጥር 3 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥ ‘አቤቱ እናንት … ሰዎች ሆይ አድምጡ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]
“ታህሳስ 28፟–ጥር 3 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ 2021 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 28፟–ጥር 3 (እ.አ.አ)
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1
“አቤቱ እናንት … ሰዎች ሆይ አድምጡ”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1ን ጌታ ለኋለኛው ቀን የራዕይ መፅሐፉ የግሉን ማስተዋወቅ እንዳደረገ አርጋችሁ አስቡት። ስለትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ምን እንድታውቁ ይሻል? ይሄንን ጥያቄ አሰላስሉ፣ እናም ክፍል 1ን ስታነቡ ወደእናንተ የሚመጡ ሃሳቦችን በመጻፍ ያዙ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
በህዳር 1831 (እ.አ.አ)፣ በዳግም የተመለሰችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአንድ አመት ተኩል ብቻ እድሜ ነበራት። ምንም እንኳን እያደገ የነበረ ቢሆንም፣ በብዛት ሰዎች በማይገኙበት ድንበር ውስጥ የሚገኙ ሰፋሪዎች ያሉበትና በሃያዎቹ አጋማሽ እድሜ ላይ ያለ ነቢይ የሚመራቸው ጥቂትና ድብቅ የሆኑ አማኞች ነበሩ። ነገር ግን እግዚአብሔር እነዚህን አማኞች አገልጋዮቹና መልእክክተኞቹ አድርጎ ቆጠራቸው፣ እናም እርሱ የሰጣቸው ራዕዮችም ታትመው ለአለም እንዲደርሱ ፈለገ።
ለጌታ ይህ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 1 ለተሰጡት በርካታ ራዕዮች መቅድም ሆኖለት ያገለግላል፣ እናም ምንም እንኳን የቤተክርስቲያኗ አባላት ቁጥር አናሳ ቢሆንም እግዚአብሔር አገልጋዮቹ እንዲያስተላልፉት የፈለገው መልእክት ግን ትንሽ እንዳልሆነ በግልፅ ያሳያል። ይህም ለሁሉም “የምድር ነዋሪዎች” እንዲማሩና ንስሃ እንዲገቡ እናም የእግዚአብሔርን “ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን” እንዲመሰርቱ የሚያስተምር የ“ማስጠንቀቂያ ድምጽ” ነው (ቁጥሮች 4፣ 8፣ 22)። ይህንን መልእክት የሚሸከሙት አገልጋዮች“ደካሞችና ተራ ሰዎች” ናቸው፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያኔም ሆነ አሁን ቤተክርስቲያኑን “ ከተደበቀችበት እና ከጭለማ” እንዲያወጡለት የሚፈልገው ትሁት አገልጋዮችን ነው። (ቁጥሮች 23፣ 30)።
ስለትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1 ታሪክ በተጨማሪ ለማወቅ ቅዱሳን፣ 1፥140–43ን ይመልከቱ።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ጌታ “እነዚህን ትእዛዛት [እንድመረምር]” ይጋብዘኛል።
መቅድም መጽሃፍን ያስተዋውቃል። የመጽሃፍን አላማና ገጽታዎች ይገልጻል እናም አንባቢውን ለንባብ ለማዘጋጀት ይረዳል። ክፍል 1ን፣ እንዲሁም የጌታን የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች “መቅድም” ስታነቡ (ቀጥር 6)፣ ጌታ ስለ ራዕዮቹ የሰጠውን አላማና ገጽታ ፈልጉ። ከክፍል 1 ውስጥ ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ጥናት የበለጠ ጥቅም እንድታገኙ የሚረዳችሁን ምን ትምህርት አገኛችሁ? ለምሳሌ በእነዚህ ራዕዮች ውስጥ “የጌታን ድምጽ መስማት” (ቁጥር 14) ወይንም “እነዚህን ትእዛዛት [መመርመር]” (ቁጥር 37) ምን ማለት እንደሆነ ማሰላሰል ትችላላችሁ።
በተጨማሪም የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መግቢያን ይመልከቱ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥1–6፣ 23–24፣ 37–39
እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ አማካኝነት ይናገራል፣ እንዲሁም ቃላቱ ይፈጸማሉ።
ክፍል 1 የሚጀምረውም ሆነ የሚፈጸመው እግዚአብሔር በተመረጡ አገልጋዮቹ እንደሚናገር በማወጅ ነው (ቁጥሮች 4–6፣ 23–24፣ 38 ይመልከቱ)። ስለጌታ እና ስለ ድምጹ ከዚህ ራዕይ ውስጥ የተማራችሁትን በዝርዝር ጻፉ። ስለ ጌታ አገልጋዮች ምን ተማራችሁ? የጌታን ድምጽ በአገልጋዮቹ ድምጽ የሰማችሁት መቼ ነው? (ቁጥር 38ን ይመልከቱ)።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥3፣ 24–28፣ 31–33
ትሁት ከሆንኩ፣ የእግዚአብሔር ተግሳጽ ወደንስሃ ይመራኛል።
ጌታ በቁጥር 3 እና ቁጥሮች 24–28 ውስጥ የህዝቦቹ ኃጢያቶችና ስህተቶች እንዲታወቁ ይሆናሉ እንዳለ አስተውሉ። በአንድ መልኩ ይህ ከባድና አሳዛኝ ተሞክሮ ሲሆን፣ በሌላ መልኩ አስተማሪ ነው። እነዚህ ሁኔታዎች ለምን የተለያዩ ሆኑ? ኃጢያታችሁንና ድክመታችሁን ስትገነዘቡ ምን አይነት ስሜት እንደሚኖራችሁ አስቡት። በቁጥሮች 24–28 ውስጥ በትክክለኛው መንገድ እንድትመልሱ የሚረዳችሁን ምን አይነት ጠቃሚ ነገር ታገኛላችሁ? ከቁጥር 31–33 በተጨማሪ፣ እነዚህ ጥቅሶች ጌታ ድክመቶቻችሁንና ኃጢያቶቻችሁን እንዴት እንደሚመለከት ምን ያስተምሯችኋል?
በተጨማሪም ምሳሌ 3፥11–12፤ ኤተር 12፥27፤ ሞሮኒ 6፥8ን ይመልከቱ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥12–30፣ 35–36
በኋለኛው ቀናት የሚያጋጥሙኝን መከራዎች መቋቋም እችል ዘንድ ጌታ ወንጌሉን በዳግም መልሷል።
ምንም እንኳን ክፍል 1 ወደፊት ስለሚመጡ አስከፊ ጊዜያት ቢያወሳም፣ በተጨማሪም አጽናኝ መልእክትንም በውስጡ ይዟል፣ “ስለዚህም እኔ ጌታ በምድር ሀነዎሪዎች ላይ የሚመጣውን መቅሰፍት በማወቄ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን ጠራሁት እናም ከሰማይም ተናገርኩት እንዲሁም ትእዛዛትን ሰጠሁት” (ቁጥር 17)።
ጌታ ስላስጠነቀቀባቸው አደጋዎች ልብ በሉ (ለምሳሌም ቁጥሮች 13–16፣ 35ን ይመልከቱ)። በራሳችሁም ህይወት ሆነ በዛሬው አለም ውስጥ ምን አይነት አደጋዎችን ታስተውላላችሁ? ቁጥሮች 17–30 ጌታ እነዚህን አደጋዎች አስቀድሞ በማወቅ በመዘጋጀት ለእናንተ ምን እንዳደረገ ይዘረዝራሉ። ያገኛችሁትን ነገሮች በዝርዝር ለመመዝገን አስቡ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥1–6፣ 37–39።ከጌታ ስለምንቀበላቸው ማስጠንቀቂያዎች ውይይት ለመጀመር፣ ልክ እንደ አንሸራታች ወለል፣ አደገኛ ማዕበል፣ ወይንም በፍጥነት እየመጣ እንዳለ መኪና አይነት ለማየት ስለማንችላቸው አደጋዎች ከሌሎች ስለምንቀበላቸው ማስጠንቀቂያዎች በመነጋገር ለመጀመር ትችላላችሁ። እነዚህ ምሳሌዎች ስለጌታ ማስጠንቀቂያዎች ምን ያስተምሩናል? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥1–6፣ 37–39 እንደሚገልጹት፣ ጌታ እንዴት ያስጠነቅቀናል? በቅርብ ጊዜያትስ ስለምን አስጠንቅቆናል? ምናልባትም በቅርብ ከተደረጉ አጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶች ክፍሎችን ለማንበብ እና የእግዚአብሔርን “ማስጠንቀቂያ ድምጽ” ምሳሌዎችን ለማግኘት ለመፈተሽ ትችላላችሁ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥16።“[የጌታን] ጽድቅ መመስረት” ማለት ምን ማለት ነው? እንደዚያ እያደረግን እንጂ፣ “በገዛ [በራሳችን] መንገድ” እየተጓዝን እንዳልሆንን እንዴት ለማረጋገጥ እንችላለን?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥30።ቤተክርስቲያኗ “እውነተኛ እና ህያው” ናት ብሎ ማለት ምን ማለት ነው? ቤተሰባችሁ ስለዚህ ጥያቄ እንዲያስቡ ለማድረግ እንዲያስችላችሁ ምናልባትም በህይወት ያሉ እና ህይወት የሌላቸውን ነገሮች ምስል ልታሳዩአቸው ትችላላችሁ። ደግሞም እንደቤተሰብ “[ቤተክርስቲያኗን] ከጭለማ እና ከተደበቀችበት [ለማውጣት]” ምን ማድረግ እንደምትችሉ ተወያዩበት።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥37።እንደቤተሰብ በዚህ አመት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን ውስጥ እንዴት አድርጋችሁ “[ትእዛዛትን እንደምትመረምሩ]” አቅዱ። የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትን እንዴት አድርጋችሁ የቤተሰባችሁ የህይወት አካል ታደርጋላችሁ? ምን አይነት የጥናት ሀሳቦች ከቅዱሳት መጻህፍት እንድትማሩ ይረዷችኋል? (በዚህ የጥናት ምንጭ መጀመሪያ ላይ ያለውን “Ideas to Improve Your Family Scripture Study [የቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትን ለማሻሻል የሚረዱ ሃሳቦች]” የሚለውን ይመልከቱ።)
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፥ “ነቢዩን ተከተሉ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 110–11፣ በተለይም የመጨረሻው ክፍል።